1 month ago
ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን ለመተካት ሳውዲ አረብያ እጩ አቀረበች!
#ethiopia | ሳኡዲ አረቢያ ዶክተር ሃናን ባልኺን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሆነው እንዲወዳደሩ ዕጩ አድርጋ ማቅረቧን አስታወቀች።
ዶ/ር ሃናን ባልኺ ከ2024 ጀምሮ የዓለም ጤና ድርጅት ቀጠናዊ ዳይሬክተር በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩ ሲሆን ለቦታው በመመረጥ የመጀመሪያዋ ሴት ነበሩ።
የዓለም ጤና ድርጅት አዲሱን የዕጩዎች አሰራር መመሪያ ተከትሎ፣ ዶ/ር ሃናን ለዋና ዳይሬክተርነት የምርጫ ቅስቀሳቸውን በነጻነት እና በተዘጋጀ መልኩ ለማካሄድ ከተመደቡበት ቀጠናዊ ኃላፊነት ጊዜያዊ ፈቃድ መውሰዳቸው ታውቋል።
ዶ/ር ባልኺ በህጻናት እና በተላላፊ በሽታዎች ዘርፍ ሰፊ ልምድ ያላቸው ሲሆን፣ ቀደም ሲል በዓለም ጤና ድርጅት ዋና መስሪያ ቤት በረዳት ዋና ዳይሬክተርነትም ሰርተዋል።
ዶ/ር ሃናን ባልኺ ከተመረጡ የአሁኑን ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖምን በመተካት ድርጅቱን የሚመሩ ይሆናል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #saudiarabia #nominates #drhananbalkhy #worldhealthorganization #drtewodrosadhanom

Comments