10 days ago
የዓለም ቱሪዝም ቀን ትኩረቱን ቴክኖሎጂ ላይ አድርጎ በአለም አቀፍ ደረጃ እየተከበረ ይገኛል።
#ethiopia | የ2026 የዓለም ቱሪዝም ቀን ቱሪዝምን በዲጂታል ለውጥና በሰው ሰራሽ አስተውሎት አቅም ለማሳደግ በሚያተኩር መሪ ሃሳብ ለ47ኛ ጊዜ በመካከለኛው አሜሪካ በምትገኘው ኤል ሳልቫዶር ዋና አከባበሩን እያካሄደ ነው።
ኤል ሳልቫዶር የዓለም ቱሪዝም ቀንን ዋና አከባበር ስታስተናግድ ይህ ለሀገሪቱ የመጀመሪያ ጊዜ ሲሆን፣ የዘንድሮው አከባበር የሚያተኩረው ቱሪዝም በዲጂታል ለውጥና በሰው ሰራሽ አስተውሎት እየተቀየረ በመምጣቱ ላይ ነው።
የዘንድሮው የዓለም ቱሪዝም ቀን “ዲጂታል አጀንዳና ሰው ሰራሽ አስተውሎት – ለቱሪዝም አዲስ ቅኝት” በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ሲሆን፣ ቴክኖሎጂና ሰው ሰራሽ አስተውሎት የቱሪስቶችን የጉዞ ልምድ ከማሻሻል ጀምሮ የቱሪዝም መዳረሻዎችን አስተዳደር፣ ግብይትና የመረጃ አገልግሎት እስከማሻሻል ድረስ ያላቸውን ሚና ለማጉላት ያለመ ነው።
የዓለም ቱሪዝም ቀን በየዓመቱ መስከረም 17 የሚከበር ሲሆን፣ የቀኑ መነሻ እ.ኤ.አ. በ1970 የዓለም የቱሪዝም ድርጅት ሕገ ደንብ የጸደቀበትን ቀን ለማስታወስ ነው። በይፋ መከበር የጀመረው እ.ኤ.አ. በ1980 ሲሆን፣ የ2026 አከባበር 47ኛው ዓለም አቀፍ አከባበር ነው።
በኢትዮጵያ የዘንድሮው የዓለም ቱሪዝም ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ39ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው። የቱሪዝም ሚኒስቴር እንዳስታወቀው፣ የዘንድሮው መሪ ሃሳብ በኢትዮጵያም የቱሪዝም ዘርፉ ከዲጂታል ቴክኖሎጂና ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር በማቀናጀት አዳዲስ የቱሪዝም ልምዶችንና የመዳረሻ ማስተዋወቂያ ዘዴዎችን ለመፍጠር ያለውን እድል ያጎላል።
ኢትዮጵያ ከዲጂታል ለውጡ በተጨማሪ በተፈጥሮ፣ በታሪክና በባህል ያላትን የቱሪዝም አቅም ወደ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለመቀየር የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ሥራዎችን እያከናወነች መሆኗን የቱሪዝም ሚኒስቴር ያስረዳል። በተለይም በገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ መርሐ ግብሮች የተገነቡ መዳረሻዎች የኢኮ-ቱሪዝምን አቅም ለማሳደግ እየተሠሩ ካሉ ሥራዎች መካከል ይጠቀሳሉ።
የቱሪዝም ሚኒስቴር በቅርቡ እንዳስታወቀውም፣ የቱሪዝም ዘርፉ በኢትዮጵያ ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያስገኘ መሆኑ ተገልጿል። ይህም ዘርፉ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና የሀገሪቱን ተፈጥሯዊና ባህላዊ ሀብቶች ለዓለም ማስተዋወቅ ያለውን አስተዋጽኦ ያሳያል።
በዚህ ዓመት የዓለም ቱሪዝም ቀን ትኩረቱን በቴክኖሎጂ ላይ ቢያደርግም፣ ዋናው ጉዳይ ቴክኖሎጂ ሰዎችንና ማኅበረሰቦችን እንዲጠቅም ማድረግ መሆኑ ተጠቁሟል። ስለሆነም ዲጂታል ለውጥና ሰው ሰራሽ አስተውሎት የጉዞን ሂደት በማቀላጠፍ ብቻ ሳይወሰኑ፣ የአካባቢ ማኅበረሰቦችን፣ ባህልንና ተፈጥሮን በማክበር ዘላቂ የቱሪዝም ልማትን ማጠናከር እንደሚገባ ትኩረት ተሰጥቶታል።
ጌትነት ተመስገን
#ethiopia #worldtourismday #worldtourismday2026 #tourism #sustainabletourism #digitaltourism #artificialintelligence #aitourism

Comments