6 months ago
መሬማ ያ የመኒያ
*********
ታሪክን የኋሊት ስንበረብር ወደ ኢትዮጵያ የገናነት ዘመን ይወስደናል - የአክሱም ዘመነ መንግስት። ኢትዮጵያዊያን ነገስታት ባብል መንደብ (Bab El Mendeb chokepoint) ይቆጣጠሩ ደቡብ ዓረብያ ድረስም ያስተዳድሩ ነበር። ሀገረ ናግራን ብዙ የክርስትና ታሪክ የነበረባት የአክሱም ግዛት አካል ነበረች። የአይሁድ ነገስታት በክርስቲያኖች ላይ ያደርሱ የነበረውን ጭቆና እና ግድያ ለማስቆም የአክሱም ነገስታት ህዝባቸውን ለመታደግ ሰፊ ውጊያ እና ወታደራዊ እንቅስቃሴ ያደርጉ ነበር። ከፋርስ (Persia) እና ሃድራሙት ኃይሎች ጋር በተደረጉ ጦርነቶች ሳቢያ የአክሱም ተፅዕኖ በዓረቢያ ላይ ቀነሰ። ከእስልምና መምጣት በኋላ ደግሞ የአክሱም ተፅዕኖና ገናነት በቀይ ባህርና አከባቢው ቀጠና መሸርሸር ዠመረ። የኢኮኖሚ ድቀትንም አስከተለ። በመጨረሻም የአክሱም መንግስት በዮዲት አመጽ ሙሉ ለሙሉ ወደቀ።
ነገረ-መሬማ
ከየመን አጠቃላይ ህዝብ 10% ያህሉ ቀለማቸው ምስራቅ አፍሪካዊ ነው። በዚህም ምክንያት ሰብአዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ተገፎ ከሰው በታች የሆነ ህይወት ለአያሌ ዘመናት በመግፋት ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ዜጎች ከቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል በጦርነቱ ሳቢያ ተቆርጠው የቀሩ ሊሆኑ ይሆናል። ቴዎድሮስ ካሳሁን Teddy Afro ለመግለጽ የፈለገውም እነዚህን ጭቁኖች ሊሆን ይችላል - በኔ አረዳድ። ለዛም ነው "ሊብናን ቤሩት ካታር ባህሬን ሳውዲ ዱባይ
እንደሚያዝነው ልቤ እህት ወንድሜን ሳይ" ብሎ የጠይሟን የመኒ ስቃይ ከእህት ወንድሞቹ ስቃይ እኩል ህመም እንደሆነበት የገለጸው።
መሬማ በሰንዓ ከባድ ህይወትን የምትገፋ ክቡር የሰው ልጅ ናት። በሀገሯ ዜጎች የሰውነት ክብር የተነፈጋት ሴት። የመኒዎች ለተራበ አጉራሽ ለታረዘ አልባሽነታቸው በስፋት ሲወራ ብንሰማም ቅሉ፤ በቀለም ለተለዩት የመኒዎች ግን በተቃራኒው እንደሆኑ መሬማ ማሳያ ነች። እኛኑ ኢትዮጵያውያንን የሚመስሉት "እንደ አፋር አፍሌታ" ፊታቸው የጠየመው ምስኪን ህዝቦችን ግን ኑሯቸውን አስከፊ አድርገውባቸዋል። ብቸኛው የገቢ ምንጫቸውም ከተማውን የደረቅ ቆሻሻ ማስወገድ እና ሌሎች ለመስራት የሚጸየፉት መሰል ስራዎችን ነው።
"ጠጋ ብለሽ አውጊኝ እስኪ ያለሽበት ሁኔታውን
እያየሽው በትካዜ የምትጠርጊው ጎዳናውን
አጎንብሰሽ ስትቆዝሚ ተደግፈሽ መጥረጊያውን
አሳዘንሽኝ እኔማ
ስንት አለ ሆድሽ መሬማ" መሬማ እነርሱን ጠይም የመኒዎችን የምትወክል ናት። አምሳያዎቻችን በመልክ እንጂ በቋንቋችን ብንጠራቸው አይሰሙንም። በዘመን ብዛት ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ትስስራችን ደብዝዟል። ለዚህም ነው ቴዲ
"ባያት አምሳያዬን ብጠራት አትሰማ
መሬማ
....
ኑሮሽ ኑሮሽ እንዴት ነው
በሰነዓ ከተማ
ያ መሬማ" ያለው።
የመኒያ ምድር ላይ የፍትህ ጀምበር ስትወጣ እንደሰው እንደዜጋ ክብርን ትጎናፀፊያለሽ ፥ ያ መሬማ።
Via Habtu A nigus
"ሙሀማሺን" (ትርጉሙም "የተገለሉ" ማለት ነው) በየመን የሚኖሩ ቁጥራቸው እስከ 3.5 ሚሊዮን የሚደርስ ጥቁር አናሳ ማህበረሰቦች ናቸው።
እነዚህ ወገኖች ለዘመናት በዘለቀ የዘር መድልዎ በከፋ ድህነት እና በማህበራዊ መገለል ውስጥ ይገኛሉ።
ስለ አመጣጣቸው የተለያዩ መላምቶች ቢኖሩም አብዛኛው የታሪክ ድርሳናት እንደሚጠቁሙት ከ6ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በየመን የነበሩ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወይም ከምስራቅ አፍሪካ (ሱዳን እና ኢትዮጵያ) የፈለሱ ባሮች ዝርያዎች ናቸው ተብሎ ይታመናል።
ይህ የታሪክ ትስስር ቢኖራቸውም፣
በየመን የማህበራዊ ደረጃ ዝቅተኛው እርከን ላይ ተቀምጠው እንደ "የማይነኩ" (untouchables) ተቆጥረው ይኖራሉ።
ሙሀማሺኖች እምነታቸው እስልምና ቢሆንም እና አረብኛ ቋንቋን የሚናገሩ ቢሆንም ከዋናው የየመን ማህበረሰብ ጋር እንዳይቀላቀሉ ተደርገዋል ይህም አብዛኛውን ጊዜ በዝቅተኛ ስራዎች (ለምሳሌ በፅዳት) ላይ ብቻ እንዲሰማሩ ይገደዳሉ የተሻለ የስራ ዕድልና ትምህርት አይፈቀድላቸውም።
ንጹህ ውሃ የጤና አገልግሎት እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት እጅግ ይቸገራሉ።
አብዛኞቹ እንደ ሰነዓ ባሉ ትልልቅ ከተሞች ዳርቻ በሚገኙ የድህነት መንደሮች (Slums) ውስጥ ተፋፍገው ይኖራሉ።
በየመን ለዓመታት የቀጠለው የእርስ በእርስ ጦርነትና ሰብአዊ ቀውስ የሙሀማሺኖችን ሁኔታ ይበልጥ አባብሶታል በጦርነቱ ምክንያት ለከፋ ረሃብና ለልመና የተጋለጡ ሲሆን እርዳታ በሚከፋፈልበት ወቅትም በመገለላቸው ምክንያት የመጨረሻ ተጠቃሚ ወይም ተጠቃሚ የማይሆኑበት ሁኔታ በስፋት ይታያል።
*ምንጭ፦ ቶምሰን ሮይተርስ ፋውንዴሽን ኒውስ (Thomson Reuters Foundation News)*

11 months ago
መልህቁን የሚደግፉ ሌሎች ህልዩቶች
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ)
#ethiopia | የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር ጥያቄን ለመደገፍ ከዓለም አቀፍ ግንኙነት(IR)ህልዮት አንፃር ከዚህ በፊት አጭር ሀሳብ ማቅረቤ ይታወሳል።ሀሳቡን ይበልጥ ለማዳበር እና በተለይም በርዕሰ ጉዳዩ ላይ ምንም ግንዛቤ ሌላቸው ሰዎች ይረዳ ዘንድ ሌሎች ንድፈ-ሐቦች ምን ይላሉ የሚለውን ለመመልከት የተለያዩ የጥናት እና ምርምር ወረቀቶችን እና (Article Review) ለማድረግ ሞክሪያለሁ፤እንዲሁም የሁለተኛ ዲግሪዩን አለምአቀፍ ግንኙነት እና ዲፕሎማሲ እንደ አጠና ሰው በተጨማሪም የተለያዩ ከፍተኛ ሥልጠናዎችን፤አለምአቀፍ ጉዳዬችን እንደ ሚከታተል ባለሙያ በድጋሚ ሌሎች መልህቁን ሊደጋፉ የሚችሉ ህልዩቶችን ተመልክቻለሁ ።
እንደ አንድ ዜጋ የሀገር እና የብሔራዊ ጥቅም (National Interest )ጉዳይ ሲነሳ በምንም ሁኔታ እና አስተሳሰብ ወደ ጎን የሚተው ነገር እንዳልሆነ አምናለሁ።ይህ አጀንዳ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) አማካኝነት በመንግስት ደረጃ መነሳቱ በዘላቂነት አጥተነው(በሆነ ዘመን) የነበረውን እድል እና ባለቤትነት በትውልድ ቅብብሎሽ መሳካቱ እንደማይቀር በማመን(በኢትዮጵያ ልጆች፥ለታላቁ ህዳሴ ግድብን በተባበረ ክንድ ገንብተን እንደጨረስነው ሁሉ)ይህም የዚህ ዘመን ትውልድ አሻራ የሚጠይቅ እንደመሆኑ ታሪክ ስንመረምር ደግሞ የጥንት ስልጣኔዎች ከአክሱም(አዱሊስ)ጀምሮ የኢትዮጵያ መርከቦች በቀይ ባህርና ወደብ ናኝተውበታል።እኛ የጥንት ህዝቦች እና የአባቶቻችን ልጆች ነን ለዚህም እንደ ሀገር ልጅነት በጋራ እና በትብብር በመቆም መስራት ይጠበቅብናል።
በዛሬው አጭር ሀሳቤ የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች በማቅረብ ይበልጥ መረዳትን ለማሳደግ እና በተለይ በአንዳንድ የመረጃ ምንጮች የሚተላለፉ ጥሬ መረጃዎች በእውቀት እና በግንዛቤ ላይ ያልተመሰረቱ እና የተሳሳቱ መሆኑን ባደረኩት ቅኝት ለመረዳት ችያለሁ።
ዛሬ የምንመለከተው የጂኦ-ፖለቲካዊ እና የጂኦ-ኢኮኖሚያዊ ህልዮቶች መሰረት በማድረግ እነዚህ ንድፈ-ሐሳቦች መልካምድራዊ አቀማመጥ እና የኢኮኖሚ ጥቅሞች በዓለም አቀፍ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸውን ሚና መሰረት በማድረግ እንፈትሻለን:-( ሌሎች በመስኩ የምርምር ስራ የሰራችሁ ሊቃውንት ሀሳባችሁን ወደ መድረክ በልዩ ልዩ አማራጮች በማቅረብ ለሀገር እና ለብሔራዊ ጥቅም የሚደረጉ ጥረቶችን በእውቀትና ሳይንስ ተኮር በሆኑ አስረጂዎች በማቅረብ ለሀገር እና ለህዝብ ያላችሁን አጋርነት አሳዩ)። (የተረዳነውን እናስረዳ)
🔴.የባህር ኃይል ፅንሰ-ሀሳብ (Sea Power Theory/ Mahanian Thought):-ይህ ንድፈ-ሀሳብ የሚያጠነጥነው የሀገር ልማትናብልጽግ እንዲሁም ኃይል የሚወሰነው በባህር ላይ ባለ ቁጥጥር እና አጠቃቀም ላይ ነው ብሎ ያምናል።የባህር መንገድን መቆጣጠር እና ነፃ የባህር ላይ ንግድ ማካሄድ ለብሔራዊ ደህንነት እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ወሳኝ መሆኑን ያስረዳል።ይህ ንድፈ ሀሳብ ለጥያቄው በተለያ መንገድ ድጋፍ ይሰጣል።ኢትዮጵያ ለንግድ እና ለሌሎች አገልግሎቶች ቀይ ባህርን መድረስ፣መጋራት መፈለጓ፣የባህር በር እንደ "ህልውና ጉዳይ"(Existential Matter) መታየቱ፣ይህ ንድፈ-ሐሳብ እንደሚደግፈው፣አንድ ሀገር ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ ለመፍጠር ተሰሚነትን ለማሳደግ የባህር ላይ አቅም (Sea Power) ማጎልበት አስፈላጊ መሆኑን ያሳያል።
🔴.የሪምላንድ ፅንሰ-ሀሳብ (Rimland Theory - Spykman):-የዚህ ህልዮት ዋና ሀሳብ በአህጉር ዳርቻ የባህር ጠረፎችን(ሪምላንድን) የሚቆጣጠር ሀይል የአለምን እጣ ፈንታ ይወስናል የሚል እምነት አለው።የባህር ዳርቻ አካባቢዎች በየብስ እና በባህር ኃይሎች መካከል ድልድይ በመሆናቸው ስልታዊ ጠቀሜታ አላቸው የሚል እይታ አለው።አስረጅ ሲያቀርብ ቀይ ባህር ከአፍሪካ ቀንድ፣ከመካከለኛው ምስራቅ እና ከእስያ ጋር የሚያገናኝ "ወሳኝ የንግድ እና የጂኦ-ፖለቲካዊ መስመር"(Chokepoint)በመሆኑ፣በዚያ አካባቢ ተሳትፎና እንቅስቃሴ ማድረጉ የኢትዮጵያን አካባቢያዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሚና ለማሳደግ ስልታዊ ጠቀሜታ አለው።
🔴.ጂኦ-ኢኮኖሚክስ(Geo-economics):-የዚህ ንድፈ ሀሳብ መነሻ የሀገሮች ተሰሚነት፣ስልጣንና ግንኙነት በዋነኛነት የሚወሰነው በኢኮኖሚ አቅማቸው እና ንግድን በሚጠቀሙበት መንገድ ነው።የንግድ መስመሮችን እና የገበያ ተደራሽነትን መቆጣጠር ከወታደራዊ ኃይል የበለጠ ተፅዕኖ መፍጠር ይችላል ይላል።ለኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር አቅርቦት ጥያቄን ሲያስረዳ ቀይ ባህር በዓለም አቀፍ ንግድ ውስጥ ያለው ወሳኝ ሚና (As the gateway to the Suez Canal and Bab el-Mandab)፣ለኢትዮጵያ ነፃ የባህር በር ማግኘቷ የንግድ ወጪን ለመቀነስ፣ወደ ውጭ መላክን ለማሳደግ እና በሌሎች ሀገሮች ላይ ያለውን ጥገኝነት ለመቀነስ ወሳኝ ነው።
🔴.ዓለም አቀፍ የህግ እና ትብብር ንድፈ-ሐሳቦች:-እነዚህ ንድፈ-ሐሳቦች ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት ትብብር እና የህግ ማዕቀፎችን አስፈላጊነት ያመለክታሉ።የዓለም አቀፍ ሊብራሊዝም እና ተቋማዊነት (International Liberalism and Institutionalism)ሀገሮች በጋራ ጥቅሞቻቸው ላይ በመመርኮዝ በትብብር (Cooperation) እና በዓለም አቀፍ ተቋማት (እንደ የተባበሩት መንግስታት የባህር ህግ ኮንቬንሽን-UNCLOS) አማካኝነት ግጭቶችን በመፍታት የጋራ ተጠቃሚነትን ማስፈን ይችላሉ የሚል እይታ አለው ።
🔴.የተባበሩት መንግስታት የባህር ህግ ስምምነት (UNCLOS) እና የባህር-በር የሌላቸው ሀገራት መብቶች:-የዚህ ህልዮት ዋና ሀሳብ (በህጉ ላይ የተመሠረተ አቀራረብ) ይህ ኮንቬንሽን (A landlocked Country) የተዘጉ ወይም ወደብ አልባ ሀገራት ወደ ባህር የመድረስ መብት (Right of Access to and from the Sea) እና በጎረቤት ሀገራት በኩል በነጻ የመጓጓዝ መብት (Freedom of Transit) እንዳላቸው በግልጽ ይደነግጋል (አንቀጽ 125-127)። ይህ መርህ ታዲያ የኢትዮጵያን ወደብ የመጠቀም ፍላጎት "በዓለም አቀፍ ህግ የተደገፈ" መሆኑን ያረጋግጣል።
✍️እንደ መውጫ ⁉️:-
የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ "የባህር ኃይል እና የጂኦ-ኢኮኖሚክስ" ንድፈ-ሐሳቦች በሚደግፉት መሠረት ለብሔራዊ ጥቅም እና ህልውና ወሳኝ ነው።በተመሳሳይ ጊዜ፣ "የሊብራሊዝም እና ዓለም አቀፍ የህግ ማዕቀፎች" (እንደ UNCLOS) ይህንን ጥያቄ በሰላማዊ እና በትብብር መንገድ ለመፍታት መነሻ መሆን እንደሚችሉ ያመለክታሉ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia
ለበለጠ ወዳጅነት የፃሃፊውን የኤክስ(X) እና የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ :-
🔗የኤክስ(X)ገፅ:-tps://x.com/HDebasu?t=WkEcsELrZrHGV1UGX3oSMg&s=09
🔗የፌስቡክ:-https://www.facebook.com/s...

Comments