1 month ago
“ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ” - የዓለም አቀፍ ሽልማቶቿ ምስጢር
*******************
አዲስ አበባ ያሸነፈቻቸው ዓለም አቀፍ ሽልማቶች ዋነኛ ምስጢር የገነባቻቸው መሠረተ ልማቶችና ውጤታማ ሥራዎቿ ብቻ ሳይሆኑ፣ መዲናዋን “ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ” ለማድረግ የሁለንተናዊ ብልፅግና ጉዟችን ማዕከል በሆነው ሰብዓዊ ልማት እና ትውልድን ማነጽ ላይ ባመጣችው ስር ነቀል ለውጥ ጭምር ነው።
ከንቲባ አዳነች አቤቤ “የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም”ን በብቃት በመምራታቸው በዓለም አቀፉ “አክት ፎር ኧርሊ ይርስ” (Act for Early Years) ኢኒሼቲቭ “የቅድመ ልጅነት ዕድገት ሻምፒዮን” ተብለው ተሸልመዋል።
ይህ ትልቅ እውቅና ከተማዋን ለህፃናት የምትመች ከተማ እና ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ የአፍሪካ መዲና ለማድረግ የሰነቀችውን ራዕይ የሚያንፀባርቅ፣ እንዲሁም ለትውልድ ግንባታ የሚደረገው ኢንቨስትመንት ያመጣውን ለውጥ በጉልህ የሚያሳይ ነው።
የዚህ ስኬት እና የከተማዋ አስደናቂ ዕድገት መገለጫ የሆነው ከቁጥር በላይ ማሳያ፣ የመጫወቻ ስፍራዎች እና የሕፃናት ማቆያዎች መስፋፋት ነው።
ከ20 ብቻ የመጫወቻ ስፍራዎች የተነሳው የከተማዋ አስተዳደር፣ በሦስት ዓመታት ውስጥ ብቻ ቁጥሩን ከጥራት ጋር 5 ሺህ 500 ማድረስ ችሏል።
በሌላ በኩል 5 ሺህ 3 የሚሆኑ የልጆችን የዕድገት ደረጃና ሥርዓት ታሳቢ ያደረጉ የመጫወቻ ቦታዎችም ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
በተጨማሪም የሕዝብ የሕፃናት ማቆያዎች ከ11 ብቻ ተነስተው በአሁኑ ወቅት 1 ሺህ 100 ደርሰዋል።
ይህ በተለያዩ ሞዴሎች የተደራጀው የማቆያ ቁጥር በጥቅሉ 1 ሺህ 155 የደረሰ ሲሆን፣ 27 ሺህ 302 ሕፃናት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል።
ይህ ስኬታማ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም በመዲናችን የሚገኙ 1.3 ሚሊዮን ገደማ ሕፃናትን፣ በተለይም አነስተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች 330 ሺህ ታዳጊዎችን ተደራሽ ለማድረግ ያለመና 5 አንኳር ጉዳዮችን ያካተተ ነው።
አዲስ አበባ ዛሬ ዓለምን ያስገረመችው እና የትኩረት ማዕከል የሆነችው በአስደናቂው የኮሪደር ልማቷ፣ በወንዝ ዳርቻዎቿ ውበት ወይም በሌሎች ፕሮጀክቶቿ ብቻ አይደለም።
ብሩህ አእምሮ ያለው ጤናማ ትውልድ በማፍራት ህፃናትን ለማሳደግ ምርጧ ከተማ መሆኗን በተግባር በማሳየትና የዜጎችን በተለይም የሕፃናትን ሕይወት በሚቀይር የሰብዓዊ ልማት ሥራዋ ጭምር ነው።
ይህ በሰብዓዊነት እና በትውልድ ላይ የተደረገው ጥልቅ ኢንቨስትመንት የመንግሥትን የመደመር እሳቤ መሬት ያወረደና ዜጎችን በአንድነት በማስተባበር ከተማዋን እውነተኛ የብልፅግና ተምሳሌት ያደረጋት ነው።
አዲስ አበባ ተደጋጋሚ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን እንድትቀዳጅ ያስቻላት ዋነኛ ምስጢርም ይኸው መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ይገልጻል።
#ethiopia #addisababa #adanechabiebie #championforearlychildhood #ebc

Comments