25 days ago
"መሮጥ ካልቻልኩ እራመዳለሁ መራመድ ካልቻልኩ እሳባለሁ ነገር ግን ማቆም አልችልም"
#ethiopia | የዓለም አቀፉ የሙዚቃ ንግሥት ሴሊን ዲዮን የነርቭ እና የጡንቻ ሕመም ጋር ስትታገል ቆይታ ዳግም ወደ መድረክ ብቅ ብላለች።
ወደ ሕዝብ ዳግም መምጣቷ በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ አድናቂዎቿና ለሚሊዮኖች ትልቅ ብርታት ሆኗል።
ሴሊን በሽታው ድምጿን እና አካሏን ቢፈታተነውም "እጄን አልሰጥም" የሚል ጽኑ ውሳኔ ነበራት።
ህመም እና ፈተና በግልጽ የተቀበለች ቢሆንም አላማዋ ግን እንደገና ከመድረክና አድናቂዎቿ ጋር መገናኘት ነበር።
ወደ የቀድሞ ጥንካሬዋ ለመመለስ በቀን እስከ 5 ሰዓታት የሚደርስ ጥብቅ የድምጽና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስታደርግ ቆይታለች።
ይህ ከፍተኛ መስዋዕትነት እና ዲሲፕሊን ለዳግም መነሳቷ ትልቁን ድርሻ ተጫውቷል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁ የመነሻ አጋጣሚዋ የሆነው በ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ በኤፌል ታወር ላይ ሆና የኤዲት ፒያፍን ዘፈን ያቀረበችበት ቅጽበት ነው።
ያ ድንቅ አቀራረብ በሽታውን አሸንፋ መመለሷን ለዓለም ያበሰረ ታሪካዊ አጋጣሚ ነበር።
ሕመሟ የሚያደርስባትን ስቃይ ሳትደብቅ ለሕዝብ ይፋ ማድረጓ አድናቂዎቿ ከእሷ ጋር ይበልጥ እንዲቀረቡ እና ያልተቋረጠ የሞራል እና የፍቅር ድጋፍ እንዲሰጧት አድርጓል።
ከህዝብ ያገኘችው ቅን ድጋፍ ለነፍሷ ትልቅ ብርታት ሆኗታል።
ሴሊን በቃለ መጠይቆቿ ላይ እንደተናገረችው ህይወቷ እና ማንነቷ ከሙዚቃ ጋር የተያያዘ ነው።
"መሮጥ ካልቻልኩ እራመዳለሁ መራመድ ካልቻልኩ እሳባለሁ ነገር ግን ማቆም አልችልም" በማለት ለሙዚቃ ያላትን ጥልቅ ፍቅር እና ቁርጠኝነት ገልጻለች።
ሴሊን ዲዮን አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ ከሕመሙ ባትፈወስም የነበራትን ፈተና አልፋ ወደ መድረክ መመለሷ ለብዙ ሕመምተኞች እና ተስፋ ለቆረጡ ሰዎች ትልቅ የተስፋ እና የመንፈስ ብርታት ምልክት ሆናለች።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #inspiration #celinedioncomeback #musicnews

Comments