17 days ago
የ2 ወር እድሜ ተሰጥቶት የነበረው መምህር የ6 ዓመታት አስደናቂ ተአምር!
#ethiopia | በፈረንጆቹ 2020 ዶክተሮች ጆን ዳቤል በህይወት የሚቆየው ለሁለት ወራት ጊዜ ብቻ ነው አሉ።
ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ግን ጆን አሁንም በህይወት አለ በጽናትም እየኖረ ይገኛል።
የጆን የካንሰር ትግል የተጀመረው ከአስር ዓመታት በፊት በ2009 ነበር።
መምህር የነበረው ጆን የምላሱ ማበጥ አሳስቦት ወደ ህክምና ሲሄድ ከባድ የአንገትና የጭንቅላት ካንሰር እንደያዘው ተነገረው።
ከዚያ በኋላ የገጠመው ህክምና እጅግ አስጨናቂ ነበር።
ለ13 ሰዓታት በተደረገ ከባድ ቀዶ ጥገና ዕጢውና አብዛኛው የምላሱ ክፍል ተቆርጦ ተወገደ።
ከዛም የኬሞቴራፒ እና የራዲዮቴራፒ ህክምናዎችን አጠናቀቀ።
እኛ በየቀኑ የምናደርጋቸው መናገር መብላትና ምራቅን መዋጥ ለጆን በየቀኑ ትልቅ ፈተናዎች ሆኑበት።
ጆን ያንን ሁሉ ተወጥቶ በህይወት ተረፈ።
ነገር ግን በ2020 የኮቪድ ወረርሽኝ መግቢያ ላይ ካንሰሩ ዳግም ተመለሰ።
በዚህ ጊዜ ዶክተሮች በጉሮሮው ውስጥ ደረጃ 4 ላይ የደረሰና ሊድንም የማይችል ዕጢ አገኙበት።
ዶክተሮቹም የቀረው እድሜ የሁለት ወር ብቻ ሊሆን እንደሚችል ነገሩት።
ነገር ግን ሁለት ወሩ ወደ ሶስት ወር አደገ።
ሶስት ወሩ ወደ ስድስት ወር።
ከዚያም ወደ ዓመታት ተቀየረ።
ጆንም የተቀበለውን የጊዜ ገደብ በቁጭት በጥሩ ልብ ነበር።
ጆን በየቀኑ በእግር መጓዝን ልክ እንደ ህክምናው አንድ አካል አድርጎ ያየው ጀመር።
በየቀኑ እስከ 8 ኪሎ ሜትር ያህል ይጓዛል።
ህክምና በሚወስድባቸው ቀናት እና በአስከፊ የአየር ጠባይ ውስጥ እንኳ ሳይቀር ወደ ውጭ ወጥቶ ይራመዳል።
በእግር ጉዞው ወቅት ደግሞ አንድ እጅግ ተራ ግን አስደናቂ ተግባር ያከናውናል ሌሎች የጣሉትን ቆሻሻ ያነሳል።
በእጁ የቆሻሻ ማንሻ ቁሳቁስና ፌስታል ይዞ በየመንገዱ ላይ ያሉ ቆሻሻዎችን ያጽዳል።
በአንድ ወቅት ሲጽፍ “የቀኔ እጅግ ውብ አጋጣሚ ጠዋት ቆሻሻ ስለቅም የማያውቁኝ ሰዎች ቆመው ምስጋና ሲያቀርቡልኝ ነበር” ብሏል።
ሊድን የማይችል ካንሰር አለበት የተባለው ጆን ስለ መኖር ብቻ አይደለም የሚያወራው።
እርሱ የሚያወራው ስለ ህይወት አላማ፣ ስለ ተስፋ እና በእጃችን ላይ ባሉ ጥቂት ነገሮች ላይ እንዴት ቁጥጥር ማድረግ እንደምንችል ነው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #johndabell #cancersurvivor #inspiration #hope #kindness

Comments