8 days ago
ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዛሃራ የአባቷን ስም በህግ ሰረዘች!
#ethiopia | ዛሃራ ጆሊ የአባቷን 'ፒት' የሚለውን የቤተሰብ ስም በህግ ሰረዘች!
ዝነኞቹ የሆሊዉድ ተዋንያን ብራድ ፒት እና አንጀሊና ጆሊ ከኢትዮጵያ በጉዲፈቻ ያሳደጓት ዛሃራ ጆሊ የአባቷን የቤተሰብ ስም "ፒት" የሚለውን በህግ ማሰረዟ ተረጋገጠ።
በሎስ አንጀለስ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀረበውን አቤቱታ ተከትሎ ስሟ ከ"ዛሃራ ማርሊ ጆሊ-ፒት" ወደ "ዛሃራ ማርሊ ጆሊ" እንዲቀየር ውሳኔ ተላልፏል።
ዛሃራ ቀደም ሲል በኮሌጅ ስነ-ስርዓት ላይ "ዛሃራ ማርሊ ጆሊ" በማለት እራሷን አስተዋውቃ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ጉዳዩን ህጋዊ እውቅና አሰጥታዋለች።
ከዛሃራ በተጨማሪም ሺሎህ ማዶክስ እና ቪቪየንም ተመሳሳይ እርምጃ መውሰዳቸው ይታወሳል።
የብራድ ፒት እና የአንጀሊና ጆሊ የፍቺ እና የልጆች አስተዳደግ ውዝግብ ከዓመታት በፊት ቢጀምርም ልጆቹ አሁንም ከአባታቸው መራቃቸውን ቀጥለዋል።"
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #zaharajolie #bradpitt #angelinajolie #hollywoodnews

2 months ago
የዝነኞቹ የጋራ ሀብት የሆነው ቅንጡ ቤት ስጋት ተደቅኖበታል
#ethiopia | በፈረንሳይ በፍጥነት እየተዛመተ የሚገኘው የሰደድ እሳት በዝነኞቹ ቤት አደጋ መደቀኑ ተነገረ።
በፈረንሳይ የተነሳውና በፍጥነት እየተስፋፋ ያለው ከፍተኛ የሰደድ እሳት የሆሊዉድ ዝነኞች አንጀሊና ጆሊ እና ብራድ ፒት የጋራ ሀብታቸው ወደ ሆነው ሻቶ ሚራቨል መኖሪያ ላይ ከፍተኛ አደጋ ደቅኗል።
የሰደድ እሳቱ አካል የሆነው ጥቁር ጢስ ወደ 164 ሚሊዮን ዶላር በሚገመተው የሻቶ ሚራቫል ግቢ እና የወይን እርሻ ቦታ አቅራቢያ እየተቃረበ ይገኛል ተብሏል።
የእሳት አደጋ ሰራተኞች በግቢው ውስጥ የሚገኘውን የሰው ሰራሽ ሐይቅ ውሃ በመጠቀም እሳቱን ለመቆጣጠር በስፋት እየተንቀሳቀሱ እንደሚገኙም ነው የተነገረው።
አንጀሊና ጆሊና ብራድ ፒት በዚህ መኖሪያ ቤት ከተጋቡበት ከ2014 እስከ ተለያዩበት 2021 ድረስ አብረው ኖረውበታል።
በ2021 አንጀሊና ጆሊ ድርሻዋን ለሦስተኛ ወገን ከሸጠች በኋላ በሁለቱ መካከል የተነሳው የባለቤትነት መብት ጋር በተያያዘ የተፈጠረው የህግ ውዝግብ እስካሁን ድረስ መቋጫ አላገኘም።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #france #angelinajolie #bradpitt #wildfires

Comments