2 months ago
በክለቡ ባስ ላይ የማሪዋና ዕጽ ተያዘ
#ethiopia | በሳኦ ፓውሎ ክለብ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ አውቶቡስ ላይ እፅ ተያዘ።
የክለቡ አባላትና አመራሮች ግን በድርጊቱ እንደሌለበት ተገልጿል።
በብራዚል የፖሊስ አባላት ባደረጉት ፍተሻ 86 ኪሎ ግራም የሚመዝን ማሪዋና በአውቶቡስ ላይ መያዛቸው ነው የተገለፀው።
አውቶቡሱ የሳኦ ፓውሎ እግር ኳስ ክለብ ለተለያዩ ጉዞዎች በኮንትራት የሚጠቀምበት የኪራይ ተሽከርካሪ ነው ተብሏል።
በወቅቱ የክለቡ ተጫዋቾችም ሆኑ የስፖርት ቡድኑ አባላት በተሽከርካሪው ውስጥ አልነበሩም ሲሉ ፖሊሶች ተናግረዋል።
የሳኦ ፓውሎ ክለብም በጉዳዩ ላይ እጁ እንደሌለበትና ከድርጅቱ ጋር ያለውን አገልግሎት በተመለከተ ማብራሪያ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #sãoPaulo #bolivia #teambus #𝐌𝐀𝐑𝐈𝐉𝐔𝐀𝐍𝐀

7 months ago
የገንዘብ ኖቶች ተሸክሞ ሲጓዝ የነበረ አውሮፕላን ወድቆ ተከሰከሰ
#ethiopia | በቦሊቪያ መዲና ላ ፓዝ አቅራቢያ የሚገኘው ኤል አልቶ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ዛሬ በአሳዛኝ ክስተት ተርብሾ ውሏል። የሀገሪቱ አየር ኃይል ንብረት የሆነውና አዳዲስ የገንዘብ ኖቶችን ጭኖ ይጓዝ የነበረው C-130 ሄርኩለስ የጭነት አውሮፕላን፣ ከመንደርደሪያ መንገዱ ወጥቶ አውራ ጎዳና ላይ በመከስከሱ የ15 ሰዎች ሕይወት በአሰቃቂ ሁኔታ አልፏል።
ከአደጋው በኋላ የተፈጠረው "የገንዘብ ዝናብ"
አደጋው የሰዎችን ሕይወት ከመቅጠፉም ባለፈ፣ አውሮፕላኑ ጭኖት የነበረው ብዛት ያለው አዲስ የገንዘብ ኖት በአካባቢው መበተኑ ነገሩን ይበልጥ ውስብስብ አድርጎታል። "የሰማይ ሲሳይ" የወረደላቸው የመሰላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች የተበተነውን ገንዘብ ለመልቀም ወደ ስፍራው በመውረራቸው፣ የነፍስ አድን ስራውን ክፉኛ አስተጓጉለውታል። ፖሊስም ይህንን ቁጥጥር ያልተቻለውን ህዝብ ለመበተን አስለቃሽ ጭስ ለመጠቀም ተገዷል።
የደረሰው ውድመት
አውሮፕላኑ አውራ ጎዳናው ላይ ሲከሰከስ በመንገድ ላይ ይጓዙ የነበሩ ከ 12 በላይ ተሽከርካሪዎችን ሙሉ በሙሉ ያወደመ ሲሆን፣ አካባቢውም ወደ ፍርስራሽነት ተቀይሯል። የእሳት አደጋ ሰራተኞች እና የነፍስ አድን ቡድኖች አሁንም በፍርስራሾቹ ውስጥ የተረፉ ሰዎችን ለመፈለግ እና አስከሬኖችን ለማውጣት ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ።
ይህ ክስተት በሀገሪቱ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፣ የአደጋው መንስኤ በዝርዝር እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ቦሊቪያ #የአውሮፕላንአደጋ #ላፓዝ #ዜና #bolivia #planecrash #breakingnews

Comments