2 months ago
የኢትዮጵያ ሠራዊት፤ የጀግንነት እና የሰብዓዊነት ሕያው ተምሳሌት
******************
የኢትዮጵያ ወታደራዊ ታሪክ የሀገር ሉዓላዊነትን ከማስከበር እና ከጦር ሜዳ ጀግንነት ጋር ተያይዞ በስፋት ይነሳል።
ከዚህም ባሻገር የሠራዊቱ መሠረታዊ የሥነ ልቦና ግንባታ ከሰብዓዊነት እና ከሕዝብ ደጀንነት እሴቶች ጋር የተሳሰረ መሆኑ ልዩ ያደርገዋል።
የኢትዮጵያ ወታደር በውጊያ ሜዳ የሚያሳየው ጥንካሬ እንደተጠበቀ ሆኖ በሰላምም ሆነ በግጭት ወቅት ለሰው ልጅ የሚያሳየው ርኅራኄ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያገኘ መገለጫው ነው። ይህ ሰውነትን የማስቀደም ፍልስፍና ከማኅበረሰባችን የዳበረ ባህላዊ እና መንፈሳዊ እሴት የሚቀዳ እውነት ነው።
በዓለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ስምሪቶች የኢትዮጵያ ሠራዊት ከተሰጠው ወታደራዊ ግዳጅ ባሻገር ማኅበራዊ አወቃቀራቸው በወደመባቸው ስፍራዎች ለሚገኙ ዜጎች የሰብዓዊነት አለኝታነቱን በተግባር አሳይቷል።
ይህንንም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በዓለም አቀፍ መድረክ የሚያሳየውን ተነሳሽነት እና ርኅራኄ በማድነቅ በተደጋጋሚ ገልጸዋል።
እንዲሁም የቀድሞው የድርጅቱ ዋና ጸሐፊ ባን ኪሙን የኢትዮጵያ ሠራዊት በሰላም ማስከበር ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለ እና የብዙ ዜጎችን ሕይወት የታደገ መሆኑን መስክረዋል።
ይህ ዓለም አቀፍ ምስክርነት መሬት ላይ ከሚታየው የሠራዊቱ ተግባር የመነጨ ነው። እ.አ.አ በ1994 በሩዋንዳ በነበረው የዘር ማጥፋት እልቂት ማግሥት፣ በላይቤሪያ የሰላም ማስከበር ተልዕኮ፣ እንዲሁም በአብዬ ስምሪት የኢትዮጵያ ሠራዊት ያከናወናቸው ተግባራት ለዚህ አስረጂ ናቸው።
በነዚህ ስፍራዎች ሠራዊቱ የተራራቁ ማኅበረሰቦችን ከማስታረቅ ባሻገር፣ የፈረሱ መንገዶችን፣ ድልድዮችን እና የትምህርት ቤት ሕንፃዎችን በራሱ ጉልበት ጠግኗል።
በተለይም ሰላማዊ ሰዎች በተጠለሉባቸው ካምፖች ውስጥ የምግብ እጥረት በነበረበት ጊዜ የኢትዮጵያ ወታደሮች የራሳቸውን የዕለት ስንቅ (ሬሽን) በመቀነስ ለተራቡ ህጻናትና እናቶች ሲያካፍሉ ቆይተዋል።
በወታደራዊ ሳይንስ የዕለት ስንቅ በከባድ ግዳጅ ወቅት የሚፈስስን ላብ እና የሚቃጠልን ኃይል ለመተካት በካሎሪ መጠን ተሰልቶ የሚሰጥ ነው።
የኢትዮጵያ ወታደር ይህን ጉልበት ማደሻ ስንቁን ቀንሶ ለተቸገሩ ማካፈሉ፣ የራሱን አካላዊ አቅም አሳልፎ በመስጠት እውነተኛ ሰብዓዊነትን በተግባር ያረጋገጠበት የሞራል ልዕልና ማሳያ ነው።
በሀገር ውስጥም የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሀገሩን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ እና ከሕግ ማስከበር ሚናው ባለፈ ከማኅበረሰቡ የዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር የተቆራኘ ነው። ሠራዊቱ ዜጎችን ከውስጥ እና ከውጭ ትንኮሳዎች ከመጠበቅ ባሻገር፣ በምርት ዘመን የአርሶ አደሩ ቀኝ እጅ ነው።
በአቅም ማነስ፣ በበሽታ ወይም በእርጅና ምክንያት ማሳቸውን ማረስ ላልቻሉ አቅመ ደካሞች መሬት ያርሳል፣ ዘር ይዘራል፣ ምርት ይሰበስባል። ይህም የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አልፎ አርሶ አደሩን ከኪሳራ ይታደጋል።
በተጨማሪም የሠራዊቱ አባላት ከደመወዛቸው እና ከስንቃቸው በማካፈል የፈረሱ ትምህርት ቤቶችን እና ማኅበራዊ ተቋማትን ይገነባሉ።
አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና የደንብ ልብስ በነፃ ከማደል አልፈው፣ በቋሚነት በማስተማር የዕውቀት ብርሃን ያካፍላሉ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በዓለም አቀፍም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚያከናውናቸው እነዚህ ተግባራት የእውነተኛ የሕዝብ ልጅነቱ ማረጋገጫዎች ናቸው።
ሠራዊቱ ጠላትን በጀግንነት ከመመከት ባለፈ ለሰው ልጅ ሁሉ የሚያሳየው ርኅራኄ፣ የሚያካፍለው ጉልበት እና የሚለግሰው ዕውቀት የኢትዮጵያዊነት ሕያው መገለጫ ሆኖ ይቀጥላል።
በለሚ ታደሰ
#ethiopia #ebc #ethiopianarmy #humanityfirst #peacekeepers #beyondheroism #militaryforpeace

Comments