10 hours ago
የ25 ዓመት ትዳር አሳዛኝ ፍጻሜ፦ በእስራኤል ቤርሳቤህ የተሰማው ልብ ሰባሪ ክስተት!
#naniamelda #communitynews #beersheba #diasporastories
12 months ago
አንድ ታላቅ ሰው ወደቀ !
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ጥር 1 ቀን 1963 ዓም አዲስ አበባ ከተማ ተወለዱ። አባታቸው አቶ ታደሰ ሮበሌ ሲሆኑ እናታቸው ደግሞ ወ/ሮ (አሁን እማሆይ) እማሙ ገቢ ይባላሉ።
የመጀመሪያና መለስተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በሃዋሳ ታቦር የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በሃዋሳ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያጠናቀቁ ከመሆናቸውም በላይ በ1980 ዓም የተሰጠውን ሃገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ወይንም ESCLC እጅግ ከፍ ያለ ነጥብ በማምጣት በከፍተኛ ማዕረግ With Great Distinction ትምህርታቸውን አጠናቀዋል።
መንግስት በወቅቱ በሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ነጥብ ያመጡ ተማሪዎችን በሚመድብበት የጎንደር ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ተመድበው በ1981 የ Common Course ትምህርታቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ፋኩልቲ ካጠናቀቁ በኋላ ከ1982 ዓም ጀምሮ እስከ 1987 ድረስ ለስድስት ዓመታት የህክምና ትምህርታቸውን ተከታትለው በማዕረግ ወይም በ Distinction በሐኪምነት ለመመረቅ በቅተዋል።
ወደ ስራው አለም በመሰማራትም ከ1987 ዓም እስከ 1988 ዓም ድረስ በተመደቡበት የሆሳዕና ሆስፒታል በጠቅላላ ሐኪምነት፣ ከ1988 ዓም ጀምሮ ደግሞ ወደተማሩበት እና ወደተመረቁበት የጎንደር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዝውውር በማድረግ በቀዶ ጥገና ክፍል ረዳት መምህርነት እና ጠቅላላ ሐኪም በመሆን ለሶስት አመታት ወገኖቻቸውን አገልግለዋል።
ከዚያም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስር በሚገኘው የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚሰጠውን የሶስት ዓመታት የድህረ ምረቃ ትምህርት በመከታተል የቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት ሐኪም ሆነው ከመመረቃቸውም በላይ የረዳት ፕሮፌሰርነት ማዕረግም አግኝተዋል። በመቀጠልም ህንድ ሃገር በሚገኘው ቬሎር ክርስቲያን ሜዲካል ኮሌጅ ውስጥ የፌሎውሺፕ ትምህርታቸውን ተከታትለው በ1999 ዓም የህፃናት ቀዶ ጥገና ሰብ ስፔሻሊስት በመሆን ተመርቀዋል።
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ከዚህ ሁሉ ትምህርት ጎን ለጎን በህክምናው ዘርፍም ከተመረቁበት ጊዜ አንስቶ እስከ 1988 ዓም ድረስ የሆሳዕና ከተማ እና የአካባቢውን ማህበረሰብ፣ ከዚያም እስከ ህዳር 2002 ዓም ድረስ ደግሞ የጎንደር ከተማና የአካባቢውን ማህበረሰብ፣ ከ2002 ዓም በኋላ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ ህሙማንን በተለይም ደግሞ ህፃናት ታካሚዎችን ከፈጣሪያቸው በተሰጣቸው ጥበብና ፀጋ አማካይነት ቀዶ ጥገና በማከናወን እንዲፈወሱ የሚያደርጉ ደከመኝን የማያውቁ ታታሪ የህክምና ባለሙያና ምሁር ነበሩ።
በሌላ በኩል ደግሞ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለማስተማር የሚያስችላቸውን የከፍተኛ ዲፕሎማ ፕሮግራም Higher Diploma Program ተከታትለው ያጠናቀቁ ከመሆናቸውም በላይ በ2011 ዓም ደግሞ በጤና ባለሙያዎች ትምህርት Health Professional Education ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የቀዶ ጥገና ተባባሪ ፕሮፌሰርነት ማዕረግም አግኝተዋል።
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ በርካታ ስልጠናዎችንና የአጭር ጊዜ ኮርሶችን የወሰዱ ሲሆን ከነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ ከዚህ የሚከተሉት ናቸው።
እንግሊዝ ሃገር በሚገኘው Paediatric Surgery at Leicester Royal Infirmary,
እስራኤል ሃገር በሚገኘው University of Negev, Beersheba Soroka Medical Center,
ሲያትል አሜሪካ በሚገኘው University of Washington Institute of Simulation and Interpersonal Skills, Royal College of Surgeons of England and David Nutt Foundation በጋራ ባዘጋጁት Surgery in Austere Environment Course in Manchester University,
እንግሊዝ ሃገር በሚገኘው Global Surgery Course at University of Oxford ይጠቀሳሉ።
ፕሮፌሰር አመዘነ በሰሩባቸው ተቋማት ውስጥ ህክምና ከመስጠት ጎን ለጎን በተለያዩ ደረጃዎች ሃገራቸውን ሲያገለግሉ ቆይተዋል። ከነዚህም ውስጥ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀዶ ጥገና ክፍል ሃላፊ፣ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የህፃናት ቀዶ ጥገና ክፍል ሃላፊ፣ የSurgical Skills Lab ተባባሪ ዳይሬክተር፣ የSimulation Center of College of Social Sciences ተባባሪ ሊቀመንበር፣ በድህረ ምረቃ ትምህርት ክፍል የድህረ ምረቃ ኮሚቴ ሊቀመንበር፣ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ምክትል ፕሬዘዳንት፣ የምስራቅ፣ መካከለኛው እና ደቡባዊ አፍሪካ የህፃናት ቀዶ ጥገና ፕሮግራም Panel Head፣ እንዲሁም የአሜሪካ የቀዶ ህክምና ኮሌጅ አባል ነበሩ።
በአካዳሚክ ዘርፉም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ በአርሲ ዩኒቨርሲቲ እና በሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ለቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ External Examiner የነበሩ ሲሆን የቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል በመሆን አገልግሎት እየሰጡ ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ሞምባሳ ኬንያ፣ ማፑቶ ሞዛምቢክ፣ ኪጋሊ ሩዋንዳ እንዲሁም ካምፓላ ዩጋንዳ ለሚገኙ የህክምና Examiners በተለያዩ ጊዜያት ስልጠና ሲሰጡ ቆይተዋል።
በምርምር ረገድም 34 አርቲክሎችን እና የመፅሃፍ ክፍሎችን አገር አቀፍ እና አለም አቀፍ እውቅና ባላቸውና በተገመገሙ ጆርናሎች ላይ ፅሁፎቻቸውን ከማሳተማቸውም በላይ ስድስት ፅሁፎቻቸው ለመታተም በሂደት ላይ ነበሩ። ከዚሁ ጋር ተያይዞም የተወሰኑ ፅሁፎቻቸውን በሃራሬ ዚምባቡዌ እንዲሁም በካልጋሪ ካናዳ ያቀረቡ ሲሆን የ Surgical Platform የኢትዮጵያ ተወካይ እና Health System Strengthening in Sub-Saharan Africa በሚለው የ ASSET project ውስጥ ተባባሪ ተመራማሪ ነበሩ።
ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ከዚህ በላይ ለተጠቀሱት ዋና ዋና እና ሌሎችም አገልግሎታቸው ከበርካታ ተቋማት ሽልማቶች የተበረከቱላቸው ሲሆን ከነዚህም መካከል
Award for Presenting Best Scientific Paper entitled ‘Implementing Ultrasound Guided Hydrostatic Reduction of Intussusception in a Low Resource Countries, Larry J. Anderson Award for Outstanding Public Health Science in the United States of America, Winner of International Guest Scholars by the American College of Surgeons, Chicago, USA ዋና ዋናዎቹ ናችው።
በአጠቃላይ በህፃናት ቀዶ ጥገና በሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ በሃገራችን ከሚገኙት ሁለት የህክምና ምሁራን ውስጥ አንዱ ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ነበሩ።
በመጨረሻም ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ ከትምህርታቸው እና ስራቸው ባሻገር ባለው ህይወታቸውም ከዶ/ር ራሔል ደምሰው ጋር ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በትዳር በመጣመር ደስተኛ ህይወት ይመሩ የነበረ ሲሆን ከዚሁ ትዳራቸውም ሁለት ወንዶች ልጆች እና አንዲት ሴት ልጅ በድምሩ ሶስት ልጆችን አፍርተዋል።
ከዚህ ሁሉ ልፋት በኋላ እኚህ የሚሊዮኖችን ህይወት ሲታደጉ የኖሩት የሃገር መድሐኒት ለራሳቸው የሚሆን መድሐኒት ሊያገኙ ባለመቻላቸው ባደረባቸው ህመም ምክንያት በአሜሪካን ሃገር እና በኢትዮጵያ ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቢቆዩም የፈጣሪ ጥሪ ደርሷቸው በርካታ አገልግሎት ሊሰጡ በሚችሉበት ዕድሜ ላይ እያሉ ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓም ልክ ከረፋዱ 5 ሰዓት ከሩብ ላይ በተወለዱ በ54 ዓመት ዕድሜያቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
የፕሮፌሰር አመዘን ታደሰ አስክሬን ሽኝት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፡ ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ተካሂዷል ፣ሥርዓተ ቀብራቸው አርብ ጥቅምት 7/2018 ዓ,ም በሀዋሳ ከተማ ይፈፀማል ።
ልዑል እግዜብሔር ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑርልን፣ አሜን።

Comments