12 days ago
የበለጸገች ነፍስ ዓለም ትጠባታለች!
ተስፋዬ እሸቱ (ረ/ፕሮፌሠር)
#ethiopia | የAmerica’s Got Talent (AGT) Season 21 ፍጻሜን አየሁ። ችሎታ እንዲህ ሲከበር ማየት ነፍስን ያስደስታል።
የ16 ዓመቷ ታይላንዳዊት የሮክ ዘፋኝና የጊታር ተጫዋች Nene Royal (Rattikarn Amloy) ውድድሩን አሸነፈች። በ7 ዓመቷ ጊታር መጫወት የጀመረችው ይህች ታዳጊ፣ ከPhuket, Thailand ተነስታ በ16 ዓመቷ የAGT Season 21 አሸናፊ ሆነች። አንድ ሚሊዮን ዶላርም አሸንፋለች።
ከሽልማቷ ባልተናነሰ ሁኔታ የአባቷን ደስታ ማየት በራሱ ሌላ ሐሴት፣ ሌላ መደመም ይፈጥራል። “ታድሎ!” ያስብላል።
ነገር ግን ከማሸነፏ ጎን ለጎን እኔን ያስደነቀኝ ሌላ ትልቅ ቁም ነገር አለ። ይህን እንድጽፍ ያነሳሳኝም፣ የአገሬንና የሕዝቤን የሕሊናዊ ዳኝነት ሚዛን በንጽጽር እንድፈትሽ ያደረገኝ ቁጭት ወለድ ሐሳብ ነው።
ምን መሰላችሁ?
በAGT የፍጻሜ ብያኔ አሸናፊውን የሚወስኑት ዳኞቹ አይደሉም፤ የተመልካቾች ድምፅ ነው። ተመልካቾች በAGT App እና በNBC website ለሚደግፉት ተወዳዳሪ በሚሰጡት ድምፅ የመጨረሻው ውጤት ይወሰናል።
ታዲያ ነገሩ የበለጠ አስደናቂ የሚሆነው እዚህ ጋ ነው።
አሸናፊዋ አሜሪካዊት አይደለችም፤ ታይላንዳዊት ናት። ከNene Royal ጋር ለመጨረሻው የአንደኝነት ምርጫ ውድድር ታጭቶ ሁለተኛ የወጣው Geno Ploeger ግን አሜሪካዊ ነው።
የአሜሪካ ተመልካች “ይሄ የኛ ነው፤ እሷ የታይላንድ ናት” ብሎ ለችሎታው ጀርባውን አልሰጠም። በአጭሩ፣ የቀረበለትን ችሎታ በማየት ድምፁን ሰጠ።
ችሎታ እንጂ ዜግነት ቦታ አልነበረውም!
ችሎታ እንጂ ጎጥ ሥፍራ አልተሰጠውም!!
ችሎታ እንጂ ቋንቋ፣ ብሔር፣ መንደር… ወዘተ ጣልቃ የሚገቡበት ዕድልም ሆነ ተስፋ አልነበራቸውም!!!
“የኔ ሰው” ሳይሆን “የሚገባው ሰው” ነበር መስፈርቱ።
“እኛ ጋ ቢሆንስ?” ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ።
ሕሊናችሁን ሞግቱ።
ልባችሁን ፈትሹ።
ሽልማቶቻችን — “መንደሬ!”
ውግንናችን — “ሰፈሬ!!”
አድናቆታችን — “ብሔሬ!!!”
አስተሳሰባችንም ሁሉ ሳይቀር ዜማውና ቅኝቱ “አገሬ” ሳይሆን “አጥሬ! ቅጥሬ!! ድንበሬ!!!” ነው።
አረ እንደው ስናሳዝን!
“ማን ይገባዋል?” ከማለታችን በፊት “የማን ነው?” የምንልበት ጊዜ ብዙ ነው።
“ምን ሠራ?”
“ምን ያህል ችሎታ አለው?”
“ሥራው ምን ውጤት ይገባዋል?”
ከማለታችን በፊት፦
“ማነው?”
“ከየት ነው?”
“ከነማን ነው?”
“የማን ወገን ነው?”…
ሌላም ሌላም ከመርፌ ቀዳዳ የጠበቡ ጎጠኛ መስፈርቶችን እያወጣን ጎራ እንለያለን። ከዚያም ሜሪት ይሸነፋል፤ መንደር ደግሞ አሸናፊ ይሆናል።
የሰው ልጅ ነፍሱ በእውቀትና በምግባር ስትበለጽግ ግን የሚሰፋው ኑሮው ብቻ አይደለም፤ አስተሳሰቡም ይሰፋል።
ከ“የኔ ሰው” ከሚለው ይወጣና “የሚገባው ሰው” ይላል። ለወንድሙ፣ ለዘመዱ፣ ለጎጡ ሳይሆን ለችሎታና ለሜሪት ወገን ይሆናል።
የወጣበትን መንደር አይክድም፤ መንደሩን ግን የዓለም መለኪያ አያደርግም።
እና ምን ለማለት ነው…
ያልበለጸገ አስተሳሰብ ሰፊውን ዓለም ወደ ጠባቧ መንደሩ ያጠባታል።
የበለጸገች ነፍስ ግን ዓለም ትጠባታለች።
የራሷ ዓለም ድንበር፣ አጥር፣ አድማስ፣ አገር፣ አህጉር፣ ዓለም፣ ስፔስ የማይገድባት ሰፊ ናትና!
#agt #americasgottalent #talent #mindset #reflection #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments