3 months ago
በማህበራዊ ሚዲያ መተግበርያዎች ላይ የእድሜ ገደብ ሊቀመጥ ነው።
#ethiopia |የአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን የማህበራዊ ሚዲያ መተግበርያዎች ለመጠቀም ዝቅተኛ የእድሜ ገደብ ሊቀመጥ ይገባል ብለዋል።
በአውሮፓ ህብረት ሀገራት ውስጥ ለህጻናት ሱስ የሚያስይዙ እና ጎጂ የሆኑ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መተግበርያዎች መለየትና መቆጣጠር ያስፈልጋል ብለዋል።
የማህበራዊ ሚዲያ መተግበርያዎች ህጻናትን ለመጠበቅ የተሻለ ስራ መስራት እንዳለባቸው እና በአገልግሎታቸው በሚፈጠሩ አደጋዎችም ተጠያቂ መሆን እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል።
ላይ ለእድሜ ተገቢ የሆነ ገደብ እንደሚያስፈልገን ግልጽ ነው።
ይህ ጉዳይ ህጻናት ማህበራዊ ሚዲያን መጠቀም ይችላሉ ወይ የሚል ሳይሆን ማህበራዊ ሚዲያዎች ህጻናት ሊያገኙ የሚችሉት መቼ እና እንዴት ነው የሚለው ነው በማለት ተናግረዋል።
የአውሮፓ ህብረት በእቅድ የያዘው የእድሜ ማረጋገጫ አፕሊኬሽን (age verification app) የእድሜ ገደቦችን ለማስፈጸም እንደ አንድ መሳሪያ ሊያገለግል እንደሚችል ገልጸዋል።
ከሶስት ዓመት በታች የሆኑ ህጻናት በስክሪን መቆየት እንደሌለባቸው ገልጸዋል።
እንደዚሁም እድሜያቸው ከፍ ያሉ ህጻናት ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያን መጠቀም ያለባቸው በወላጆች በአሳዳጊዎች ወይም በአስተማሪዎች ቁጥጥር ስር ሆኖ በተወሰነ ጊዜ ብቻ መሆን እንዳለበት አክለዋል።
ፕሬዝዳንቷ አክለውም የአውሮፓ ህብረት በመጀመሪያ የትኞቹ መተግበርያዎች ለህጻናት ከፍተኛ አደጋ እንደሚያስከትሉ መለየት አለበት ብለዋል።
ሱስ የሚያስይዙ ባህሪያት ያላቸውን እና ለህጻናት እድሜ የማይመጥን ይዘት የሚያቀርቡ መተግበርያዎች መለየት ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #eucommissionchief #ageappropriaterestrictions #socialmediaplatforms

Comments