4 months ago
“ኢትዮጵያም ጠንካራ መሪ እንዳላት ሰምቻለሁ"
#ethiopia | የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ በአባይ ጉዳይ ኢትዮጵያና ግብፅ ከስምምነት መድረስ እንደሚችሉ እንደሚያምኑ ተናግረዋል።
ትራምፕ በዳቮስ የምጣኔ ሀብት ፎረም ላይ ከግብፁ ፕሬዝደንት አብድል ፋታህ አል-ሲሲ ጋር በነበራቸው የጎንዮሽ ውይይት ወቅት፣ የዓባይ ግድብ “የናይል ወንዝ እንዳይፈስ” ያደርጋል ሲሉ የተናገሩ ሲሆን፤ ሁለቱን ሀገራት ወደ ድርድር ለማምጣት እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን አናዶሉ የዜና ወኪል ዘግቧል።
“አደገኛ ሁኔታ ነው። ግድቡን የሠሩት [ግብፆች] ለሚሊዮን ዓመታት ውሀ በሚያገኙበት መንገድ ላይ ነው። አሁን የውሀ ፍሰቱ በአንድ ትልቅ ግድብ ምክንያት ተገድቧል” ሲሉ ከሲሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
“ግድቡን በተለመከተ የሆነ ነገር ማድረግ እንዳለብን አስባለሁ። ግድቡ ትልቅ ችግር ነው። የሆነ ነገር እናደርጋለን” ሲሉ ትራምፕ አክለዋል።
ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በካይሮና አዲስ አበባ መካከል ድርድር የማስጀመር ሐሳብ እንዳላቸው መናገራቸው ይታወሳል።
“አንተ ጠንካራ ፕሬዚዳንት ነህ” ሲሉ ሲሲን ያደነቁት ትራምፕ፤ ከግብፅ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚሠሩ በውይይታቸው ወቅት መግለፃቸውን ፎክስ ኒውስ ዘግቧል።
“ኢትዮጵያም ጠንካራ መሪ እንዳላት ሰምቻለሁ። እርግጥ ነው እንዳንተ አላውቀውም ግን ጠንካራ ሰው ነው። ሁለታችሁን አቀራርበን ከስምምነት ለመድረስ እንሞክራለን።” ብለዋል፤ ትራምፕ፡፡
**
ወዳጆቼ፤ እስካሁን ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የናይልንም ሆነ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ጉዳይን በተመለከተ የሚሰጧቸው አስተያየቶች ሁሉ የመካከለኛ ምስራቅ አጋራቸው የሆነችውን ግብጽ (በተለይም ፕሬዚዳንት አል ሲሲን) ለማስደሰት ወይም ውለታ ለመመለስ አሊያም ቀብድ ለመክፈል ያለሙ መሆናቸውን መገመት አያዳግትም፡፡ በዚህ መሃል ታዲያ ዋጋ የምትከፍለው አገራችን ኢትዮጵያ ናት፡፡ የኢትዮጵያ መንግሥት ብልህነት በተሞላበት ዲፕሎማሲ ነገሩን ፈር ያሲዘዋል ብዬ ባምንም፣ የግብጽም ሆነ የትራምፕ አካሄድ ግን ምኑም አላማረኝም፡፡
ትራምፕ ከተናገሩት ትንሽ ደስ ያለኝ “ኢትዮጵያም ጠንካራ መሪ እንዳላት ሰምቻለሁ። እርግጥ ነው እንዳንተ አላውቀውም ግን ጠንካራ ሰው ነው።" ሲሉ ለግብጹ ፕሬዚዳንት የነገሯቸው ብቻ ነው፡፡ ድርድሩ ቀላል እንደማይሆን ከወዲሁ መጠቆማቸው መሰለኝ - ለአል-ሲሲ፡፡
ለማንኛውም ግን ፈጣሪ ይርዳን፡፡ #addisadsmas