3 months ago
ዛሬ የኢትዮጵያ የመጨረሻው ንጉሥ የልደት ቀን ነው
#ethiopia | ቁመታቸው ከ1 ሜትር ከ 60 ሴንቲ ሜትር አይበልጥም፣ክብደታቸውም ከ50 ኪግ የሚዘል አይደለም፡፡በጣም አጭር እና ቀጭን ነበሩ፡፡
ግን ግርማ ሞገሳቸው ልዮ ነው፡፡ ቤተሰቦቻቸው 8 ጊዜ ወልደው ከእርሳቸው በስተቀር አላደገላቸውም፡፡በእርግጥ እናታቸው ወይዘሮ የሺእመቤትም በልጅነታቸው ስለሞቱባቸው ያለ እናት፣በአባት ብቻ አድገዋል፡፡
አባታቸው ራስ መኮንን በባዶ እግራቸው በሮም አደባባይ ኢትዮጵያን ብሎም አፍሪካን የሸመገሉ መሪ ነበሩ።ግርማዊነታቸው ከአባታቸው ዲፕሎማሲን ተምረዋል፡፡በዓለም ላይ ከ 160 በላይ ሀገራትን የጎበኙ እሳቸው ሳይሆኑ አይቀሩም፡፡የሁለተኛው የዓለም ጦርነት በአሜሪካ አሸናፊነት ሲያከተም፣የሂትለር ባድማ ጀርመን ዓለም ፊቱን አዞረባት፡፡ጀርመን እንደ ሲኦል መንደር ተቆጠረች፡፡ጃንሆይ ግን የተዘጋ በር ከፍተው ጀርመንን ጎብኝተዋል፡፡አስታርቀዋል፡፡አሜሪካ ከጆርጅ ዋሽንግተን እስከ ትራምፕ ድረስ 45 ፕሬዝዳንቶችን ሹማለች፡፡
እነዚህ ፕሬዝዳንቶች በሙሉ አየር ማረፊያ ድረስ ሂደው የሀገር መሪ አይቀበሉም፡፡ጃንሆይን ግን ፕሬዝዳንት ኬኔዲ መንገድ ወጥተው ተቀብለዋቸዋል፡፡ለጥቁር የነፃነት አውጭ ናቸው፡፡
ኤርትራን ከኢትዮጵያ አዋህደዋል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን ከግብፅ ጣልቃገብነት ነፃ አውጥተዋል፡፡የፊውዳሊዝም ሥርዓትን አሻሽለዋል፡፡ስነፁሁፍ እንዲያድግ ነፃነትን ሰጥተዋል፡፡1960 ዎቹ ወርቃማው የስነፁሁፍ ዘመን ነበር፡።
የተፃፈ ህግን፣ ህገመንግስትን ጨምሮ አሰንደዋል፡፡ ከአፍሪካ ህብረት እስከ ተመድ ድረስ እንዲመሰረት ዋና ተዋናይ ነበሩ፡፡
የኒወክርክ ታይምስ ጋዜጣ ጃንሆይን የዓመቱ ምርጥ አፍሪካዊ ንጉስ አድርጎ ከማውጣቱም ባለፈ፣የኖቤል ሽልማት ሊሸለሙ እያለ በ 1953 ዓም በተነሳው አለመረጋጋት ምክንያት ሽልማቱ አልፏቸዋል ፡፡
የአፍሪካ መስራች ቢሆኑም፣ሀውልት ለጃንሆይ ሳይገነባ ለጋናዊው ክዋሜ ንኩርማህ ብቻ ተገንብቶ ቆይተዋል፡፡በሗላ ከመሸምቢሆን የአፍሪካ ህብረት የጃን ሀውልት በግቢው አቁሟል።
ለነባር ዕውቀት ዕድገት ተግተዋል፡፡
ጃንሆይ ለፈረንጅ የማያጎበድዱ ይልቁንም ጃንሆይ ና ህዝቦቻቸው ለነጭ ንቀት ያላቸው ብቸኛ የዓለማችን ሰዎች ናቸው ይላሉ ፈረንጀች፡፡እንዳውም ፈረንጆች አማርኛ ቋንቋ እንዲናገሩ ይገደዳሉ፡፡የኢትዮጲያን ባህል እንዲላበሱ ይወተወታሉ።
በእርግጥም ጃንሆይ፣ሀገር በቀል እውቀት እንዲለማ ከጣና ገዳማት እስከ አክሱም ፅዮን ያሉ አብያተክርስቲያናት እንዲታደሱ እና ለታሪክ ምርምር እንዲውሉ አድርገዋል፡፡
የዓለም ስልጣኔ መነሻው ውሃ እንደሆነ በመረዳት አባይን ከመገደብ ጀምረው ጣናን እስከ ማልማት እንቅስቃሴ ጀምረው ነበር፡፡ግን በነሩሲያ የፖለቲካ ጫና እና በነጣሊያን ውስጣዊ ሴራ መክኗል፡፡
ለሙስሊም ህብረተሰብ የሀይማኖቱን ምሁራንን ከየአካባቢው በመሰብሰብ ቁርዐንን ከአረብኛ ወደ አማርኛ እንዲተረጉሙ ታላቅ ድጋፍ እና አስተዋፅዎ አድርገዋል።
ጃንሆይ ሀምሌ 16 ቀን 1884 ዓም በሀረርጌ ኤጀርሳ ጎሮ ተወለዱ፡፡ ሐምሌ 16 የመጨረሻው የኢትዮጵያ ንጉስ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የልደት በዓላቸው ነው፡፡ራስታዎችም( ጃይማካዎች) የጃንን ልደት ይዘክራሉ።
ደጋፊና ነቃፊዎቻቸው መሳ ለመሳ ቢሄዱም ሟች አይወቀስምና ምንዳው ምንዳው ብቻ ተጻፈ
📸 ተስፋዬ ወልደሚካሄል
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

5 months ago
የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የቅዳሴ ቤት በዓል እና 85ኛው የድል ቀን በታላቅ ድምቀት እየተከበረ ነው
#ethiopia | በአዲስ አበባ የሚገኘው የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ዓመታዊ የቅዳሴ ቤት በዓል ከ85ኛው የኢትዮጵያ የድል በዓል ጋር በመሆን በከፍተኛ ስነ ስርዓት በመከበር ላይ ይገኛል።
በዚህ ታላቅ ሃይማኖታዊና ብሔራዊ በዓል ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ ሌሎች ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የቤተክህነት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን እንዲሁም በርካታ ምእመናን ታድመዋል።
የገዳሙ በዓል በየዓመቱ ሚያዚያ 27 ቀን በልዩ ሁኔታ የሚከበርባቸው አምስት ዋና ዋና ምክንያቶች አሉት። የመጀመሪያው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በስደት እንግሊዝ ሀገር በነበሩበት ወቅት የገዳሙ ቅዳሴ ቤት የተከበረው በዚህ ዕለት በመሆኑ ነው።
ሁለተኛው በ1933 ዓ.ም የኢትዮጵያ ነጻነት ታውጆ የድል በዓል መከበር የጀመረው ሚያዚያ 27 በመሆኑ ሲሆን፣ ሦስተኛው ደግሞ ከጃንሆይ ጋር ወደ ሀገር የተመለሰው ታቦተ ሕጉ በቤተ መንግሥት ለሁለት ዓመታት ከቆየ በኋላ አሁን የካቲት 12 ሆስፒታል በሚገኝበት ስፍራ ወደ ተሠራው መቅደስ የገባው በ1935 ዓ.ም ሚያዚያ 27 በመሆኑ ነው።
በተጨማሪም አሁን ያለው ቤተክርስቲያን የመሠረት ድንጋይ በ1940 ዓ.ም የተጣለውና በ1942 ዓ.ም ታቦቱ ወደ አዲሱ ሕንፃ የገባው በዚሁ ታሪካዊ ቀን በመሆኑ ዕለቱ በገዳሙ ዘንድ በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
#መድኃኔዓለም #ምስካየኅዙናን #ሚያዚያ27 #የድልበዓል #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ኢትዮጵያ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

11 months ago
የዓለም ማዕከላዊ ቦታ በሆነቸው ኢየሩሳሌም በጎልጎታ ተራራ ላይ የሚገኘዉ የዴር- ሱልጣን ገዳም ያለው የኢትዮጵያ ይዞታ ክርክር አሁንም መቋጫ አላገኘም ተባለ
የጎልጎታ ባለይዞታዎች የስድስት ሃገራት አብያተ ክርስትያናት ናቸዉ። ከስድስቱ መካከል አንደኛዉ እኛ ነን። የጎልጎታ አባል የጎልጎታ ባለይዞታዎች ነን ይላሉ የገዳማቱ የሒሳብ ክፍል ሐላፊ መላከሰሌም አባ ገ/ኪዳን፡፡
ከስድስቱ መካከል ሦስቱ ታላላቆች ግሪክ፤ ላቲን እና አርመን ሲሆኑ ፤ መለስተኛ አብያተ ክርስትያናት ተብለዉ የሚመደቡት ደግሞ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ- ክርስትያን ፤ የግብጽና የሶርያ ናቸዉ። የጎልጎታ ቀራንዮ በእነዚህ በስድስቱ የተያዘ ነዉ።
ገዳሙ ከንጉሥ ሰሎሞን ዘመን ጀምሮ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያውያን ርስት ሆኖ መቆየቱ ሲገለገሉበት መቆየታቸው ይነገራል ፡፡ይሆን እንጂ አሁንም ድረስ ይህ ጥንታዊ ፤ ታሪካዊ ስፍራ በሌሎች ሊነጠቅ የሚችልበት ሆኔታ እንዳለ ስጋታቸውን ይናገራሉ እኚህ አባት ፡፡
በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ በዴር ሱልጣን ጉዳይ የኢትዮጵያ መንግሥት ከጃንሆይ ጊዜ ጀምሮ ጥረት ያላደረገ ያልደከመ እንዴሌለ ይናገራሉ፡፡
በቅርቡ እንኳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር ) በእስራኤል በነበራቸው ቆይታ ስፍራው ድረስ በመሄድ ከአባቶች ጋር መመከራቸውን እና ከእስራኤሉ አቻቸው ጋርም በጉዳዩ ላይ መምከራቸውን ተናገረዋል፡፡
በስፍራው ያሉ መነኩሳት ያሉባቸውን ችግሮችም ለመቅርፍ ሰፊ ጥረት የተደረገ ቢሆንም 200 መቶ አመታት ሲንከባለል የቆየ በመሆኑ በሚፈለገው ልክ ምላሽ ማግኘት እንደልተቻለ ገልጸዋል፡፡
በእስራኤል (ባለበት ይቆይ የሚባል ህግ አለ በጎለጎታ ያሉት የኢትዮጲያ ቤክርስቲያናት (መድኋኒአለም እና ሚካኤል ) እየተገለገለችባቸው ትገኛለች ፡፡ግብጹችም ስፍራውን አልወሰዱም እኛም አገልግሎቱን አላቋረጥንም ፡፡መነኩሳቱ ያሉባቸውን የመብራት ፤የውሃ የማዘጋጀበታዊ አገልግሎቱችን ለማግኘት አስቸጋሪ እንደሆነ አንስተዋል፡፡
ከጥቁር ሕዝብ መካከል በእስራኤል ይዞታ ያላት ኢትዮጲያ መሆኗን የሚመሰክሩት በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር አቭራም ንጉሤ ይህ ይዞታ በጎልጎታ ተራራ ላይ ብቻ ሳይሆን በቀድሞ ጊዜ ነገሥታቱ እና መኳንንቱ የሰሩት ብዙ ሕንፃና ንብረት እንዳለ አንስተው፡፡የእስራኤል መንግስት በተለያዩ ጊዜት ለአቤተክርስቲያናቱ ድጋፍ እና ጥገና እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
የእስራኤል ምክር ቤት አባል ጸጋ ፋንታሁን (ዶ/ር)በበኩላቸው በእስራኤል በኩል ችግሮን ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት የተደረገ ቢሆንም የሚመለከታቸው አባቶችን በሰአቱ ማግኘት ባለመቻላችን ችግሮ መቁየቱን አንስተዋል፡፡
የርስቱ ባለቤት ነኝ የምትለው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንም ይህንን ጉዳይ ለመፍታት አንድም ጊዜ ጫና አድርጋ አታውቅም ተብላ ተወቀሳለች።
ርስቱ በመካከለኛው ምሥራቅ የኢትዮጵያን መንግሥት የሚወክል ሀብት ሆኖ ሳለ ይህንን ሀብት እንደሀገራዊ ሀብት ለማስከበር መንግሥትም ጠንከር ያለ ጫና ሊያደርግ ይገባዋል ተብሏል ።
Ethio Fm

ጥቅምት 23 ቀን 1923 ዓ.ም.
የግርማዊ ቀዳማዊ የዘውድ በዓል ሲዘከር።
"በክብር የነገሡት፤ በግርማ የታጀቡት"
► #በአበው ሥርዓት በግርማ ነግሠዋል፤ በአበው ሕግ ተገዝተዋል፤ ሀገራቸውን ያገለግሉ ዘንድ በሕያው አምላክ ፊት ቃል ኪዳን ገብተዋል፤ ቃል ኪዳናቸውን ይፈጽሙ ዘንድ ታትረዋል።
#ከአበው የተቀበሏት፤ በዓምላክ ፈቃድ ዙፋን ተቀምጠው የሚመሯት፤ በበትረ መንግሥታቸው መንገዷን የሚጠርጉላት ሀገራቸው ከፍ ከፍ ትል ዘንድ ሠርተዋል።
#ተናግረው ይሰማሉ፤ መክረው ይመልሳሉ፤ ገስጸው ያስተካክላሉ፤ ዘምተው ያሸንፋሉ፤ አስበው ያደርጋሉ፤ ጀምረው አምላካቸውን ይዘው ይፈጽማሉ።
#አበው ስለ ጠበቋት ሀገራቸው በጽናት ቆመዋል፤ ከአበው ስለተቀበሏት የከበረችው ሠንደቅ ዓላማቸው በጀግንነት ተፋልመዋል፤ ነጻነቷን እንዳታጣ ከጠላቶቿ ጋር ተጋጥመዋል፤ ዓለም ሁሉ ፊቱን ባዞረባቸው ጊዜ እውነትን፣ ቃል ኪዳንን እና ተስፋን ይዘው ብቻቸውን ቆመዋል።
#ሃሰተኞች በሚፈርዱበት፣ ሀሰተኞች በሚመሰክሩበት፣ ሀሰተኞች የፍርዱን ውሳኔ በሚያጸኑበት፣ የፍርድ ሚዛን ሁሉ ወደ ቅኝ ገዢዎች በምታዘነብልበት በዚያ ጊዜ በተስፋ ቆመዋል፤ ከእውነት ጋር ቆመው የእውነት፣ በእውነት፣ ስለ እውነት ለሀገራቸው ነጻነት ታግለዋል።
#እውነትን ይዘው ሀሰተኞችን በፍርድ ዓደባባይ አሸንፈዋል፤ ቅኝ ገዢዎችም በጦር ሜዳ ድል መትተዋል፤ በድል አድራጊነትም በግርማ እና በከፍታ በዓደባባይ ታይተዋል፤ በዙፋን ላይ እንደ ጫካ አንበሳ በአስፈሪ ክብር ተቀምጠዋል ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ።
#በቅኝ ገዢዎች የተበተኑትን ሰብስበዋል፤ መለያየትን አውግዘው አንድነትን አምጥተዋል፤ የአንድነቱን መሠረት አጥብቀዋል፤ የተረሱትን አስታውሰዋል፤ አንገታቸውን የደፉትን ቀና እንዲሉ አድርገዋል፤ የተገፉትን ደግፈዋል፤ ስለ ራሳቸው በራሳቸው የማይመክሩትን ስለ ራሳቸው እንዲመክሩ፣ መፍትሔም እንዲያበጁ አድርገዋል።
#በቅኝ ገዢዎች የተበተኑትን በአንድነት ሰብስበው አቅማቸውን አደርጅተዋል፤ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲናገሩ መንገዱን አሳይተዋል፤ ስለ እነርሱ ከእነርሱ በላይ እንደሌለ አሳይተዋቸዋል፤ በቅኝ ገዢዎች ምክንያት የጨለመችባቸውን የነጻነት ጀንበር እንዲመለከቱ አድርገዋል፤ በነጻነት ጀንበር በብርሃን ይመላለሱ ዘንድ አድርገዋል ጃንሆይ።
#እኒህ አያሌ ታሪክ የሚነገርላቸው፤ አፍሪካውያን የአንድነታችን አባት የሚሏቸው ንጉሠ ነገሥት ዘውድ የጫኑት፣ በከበረው ዙፋን ላይ የተቀመጡት፣ በትረ መንግሥቱን የጨበጡት፤ ቅብዓ መንግሥቱን የተቀቡት፤ የአበውን አደራ ይሸከሙ ዘንድ እጃቸውን ከፍ አድርገው ቃል ኪዳን የገቡት በዛሬዋ ቀን ነበር፤ ጥቅምት 23/1923 ዓ.ም።
#የነገሡበት ቀን በሃያ ሦስት፣ የነገሡበት ዓመተ ምኅረት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ሦስት፣ የነገሡበት ደብርም ክብረ በዓሉ የሚከበረው በሃያ ሦስት ነው። ሃያ ሦስት የተገጣጠመላቸው ባለ ግርማው ንጉሥ።
#ግርማዊ ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሕይዎቴ እና የኢትዮጵያ እርምጃ በተሰኘው መጽሐፋቸው ስለ ንግሥናቸው ሲጽፉ መስከረም 17/1909 ዓ.ም ንግሥት ዘውዲቱ ሲነግሡ እኔም ለአልጋ ወራሽነቱ እና ለእንደራሴነቱ ስለተመረጥሁ በባለ ሙሉ ሥልጣን እንደራሴነቴ የመንግሥቱን ሥራ እየሠራሁ 14 ዓመታት ቆየሁ።
#ንግሥት ዘውዲቱ መጋቢት 24/1922 ዓ.ም ስላረፉ በማግሥቱ የንጉሠ ነገሥቱ ዐዋጅ ተነግሮ በዙፋኑ ተቀመጥሁ።
#ወደ ፊት ያለው ወራቱ ክረምት ስለነበረ የዘውድ በዓላችን ሰባት ወራት እንዲቆይ አደረግን። በኢትዮጵያ ያሉ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ፣ ባላባቶችም ሁሉ፣ በየገዳማቱ ያሉ አባቶች፣ የየአድባራቱ አለቆች፣ መጥተው የደስታችን ተካፋዮች እንዲኾኑ የጥሪ ደብዳቤ ተላከላቸው። ለዘውድ በዓሉም ዝግጅት ተደረገ ብለዋል።
#ልብሠ መንግሥቱ፣ ዘውዱ እና ሉሉ፣ በትረ መንግሥቱ እና ሰይፉ፣ ቀለበቱ ይህንም የመሰለው ሁሉ በተለየ በወርቅ እና በአልማዝ እየኾነ ተሠራ። ለመሳፍንቱ፣ ለመኳንንቱ፣ ለጦር አበጋዞች ሁሉ እንደየ ክብራቸው የክብር ልብስ ተዘጋጀላቸው።
#በዘውድ በዓሉ ዋዜማ በጅሮንዱ የንጉሠ ነገሥቱን ልብሰ መንግሥት እና ዘውዱን፣ ሉሉን፣ በትረ መንግሥቱን፣ ሰይፉን፣ የአልማዝ ቀለበቱን፣ የእቴጌይቱንም ልበሰ መንግሥት እና ዘውድ፣ የአልማዝ ቀለበት በሠረገላ አስገብቶ በታላቅ ሰልፍ ወስዶ በመናገሻው በቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ለሊቀ ጳጳሳቱ አስረክቦ ሌሊቱን ሙሉ ሲጸለይበት አደረ ይላሉ።
#ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱ በሌሊት ወደ መናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን አቀኑ። ጸሎቱም ማካሄዱን ቀጠለ።
#ጃንሆይ ሲጽፉ ሥርዓተ ንግሡ ከመጀመሩ አስቀድሞ ሊቀ ጳጳሳቱ አቡ ቄርሎስ ገበታው የወርቅ የኾነ ወንጌል ይዘው ቀርበው የመሐላ ቃል እንድንፈጽም አደረጉ ብለዋል።
#ብላቴ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በተሰኘው መጽሐፋቸው ሲጽፉ የዘውዱ ዋና በዓል ጥቅምት 23/1923 ዓ.ም እሑድ ነበር። ቅዳሜ ማታ የመናገሻ ጊዮርጊስ ካህናት እና ከየአድባራቱ ተመርጠው የመጡ መዘምራን ከማታው ጀምረው ማኅሌት ቆመው አደሩ።
#እኩሌቶቹ መወድስ ሲቆሙ እኩሌቶቹ ክስተት አርያም ያደርሱ ነበር እና ማኅሌቱ ደምቆ አደረ።
#ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱም በሌሊት በመሳፍንቱ እና በመኳንንቱ ታጅበው ወደ ቤተክርስቲያን መጥተው ለዚህ ማዕረግ ላበቃቸው ከዚህ ዕለት ላደረሳቸው አምላክ ምስጋና ካቀረቡ በኋላ ወደ ማረፊያ ድንኳን ሄደው ጸሎተ ሕሊና ሲያደርሱ አደሩ።
#ጠዋት ሲነጋ መሳፍንቱ እና መኳንንቱ ሙሉ የማዕረግ ልብሳቸውን ከኒሻን ጋር ለብሰው የራስ ሉል እና የራስ ወርቅ ደፍተው በአዳራሹ ውስጥ በተሰናዳላቸው ስፍራ በየማዕረጋቸው ተቀመጡ። ጳጳሳት እና መምህራን ለሥርዓቱ ተዘጋጁ።
#ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ አጼ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓተ ንግሥ ወደሚፈጸምበት ገቡ። በመንበሩ አጠገብ ተሳልመው ጸሎት አደረሱ። ጸሎታቸው እንደጨረሱ በተሰናዳው ዙፋን ላይ ተቀመጡ።
#በዚህም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ አቡነ ቄርሎስ ፊታቸውን ወደ መሳፍንቱ እና ወደ መኳንንቱ አዙረው እንዲህ አሉ።
"እናንት የኢትዮጵያ መሳፍንት እና መኳንንት፣ የጦር አለቆች ወታደሮች እና ሠራዊቶች፣ በቤተ ክህነትም ያላችሁ ሊቃውንት እና አለቆች መምህራን እና ቀሳውስት ሁሉ ንጉሠ ነገሥታችን ግርማዊ ኃይለ ሥላሴ ከሰሎሞን እና ከንግሥተ ሳባ ከተወለደው ከቀዳማዊ ምኒልክ ጀምሮ ሳይቋረጥ ከመጣው መኾኑን ታውቃላችሁ።
#አሁን በእግዚአብሔር ፈቃድ እና ቸርነት ዘውድ ጭኖ እንዲነግሥ ልቀባው ነው እና በሥጋዊ እና መንፈሳዊ ሥራው ሁሉ ሀገርም በማሠልጠን ሃይማኖትም በማጽናት በዘመኑም ኢትዮጵያ በዕውቀት እና በትምህርት በጥበብም ከፍ ከፍ እንድትል በመትጋት ከወሰን እስከ ወንሰን የኢትዮጵያ ባንዲራ እንዲዘረጋ በማድረግ ይህንንም በመሰለው በመልካም ሥራው ሁሉ እንድትገዙለት እና እንድትረዱት አደራ እላችኋለሁ" አሉ።
#ሕዝቡም በዕልልታ አጀባቸው።
#ከዚያም ልብሰ መንግሥቱን አለበሷቸው፤ ቤተ መንግሥቱን አስጨበጧቸው፤ ሉሉንም ሰጧቸው፤ የአልማዙን ቀለበቱንም አጠለቁላቸው፤ የንግሥና ወግ እና ማዕረግ የኾነው ሰይፉን እና ጦሩንም ሰጧቸው፤ ቅብዓ መንግሥቱንም ቀቧቸው፤ ዘውዱንም ባርከው ደፉላቸው፤ በዚህም ጊዜ እልልታው አስተገባ፤ ታላቅ ደስታም ኾነ።
#ንጉሡም በግርማ ኾነው ከዙፋናቸው ላይ ተቀመጡ። የእተጌዋም በሥርዓቱ መሠረት ተፈጸመ። የአልጋ ወራሹም ከዙፋኑ ግርጌ ኾነው ቃል ኪዳን አሠሩ። እልልታውና ጭብጨው ከዳር እስከ ዳር አስተጋባ። ንጉሡና እና ንግሥቷ ከፍ ባለ ሥፍራ ኾነው በታዩ ጊዜ እልልታው ቀለጠ።
#በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን የተፈጸመው ሥርዓት በተጠናቀቀ ጊዜ ንጉሠ ነገሥቱና እቴጌይቱ በስድስት ፈረሶች በሚሳብ በወርቅ ሠረገላ ተቀምጠው፣ ከፊትም ከኋላም በመሳፍንት እና በመኳንንት ታጅበው፣ በሠራዊት ሰልፍ መካከል አልፈው ወደ ቤተ መንግሥታቸው ተመለሱ።
#መሳፍንት እና መኳንንት የመንግሥታት መልእክተኞችም በየማዕረጋቸው በሠረገላ እና በአውቶሞቢል ኾነው አጀቡ። እምቢልታውና መለከቱ ሲንካለል፣ ነጋሪቱ እየተጎሰመ ገብር ገብር ሲል እጅግ ደስ ያሰኝ ነበር።
#በመንገድ ዳር ኾኖ ለማየት የተሰበሰበውም ሕዝብ ሰላምታ እየሰጠና እጅ እየነሳ ሺህ ዓመት ያንግሥዎ እያለ አጨበጨበ። ከቤተ መንግሥት በደረሱ ጊዜም ንጉሠ ነገሥቱ እና እቴጌይቱ ለመሰናበቻ በተሰናዳው ሥፍራ ቆመው ሲያዩት ሕዝቡ ሁሉ እንደገና እያጨበጨበ ሺህ ዓመት ያንግሥዎ እያለ እየመረቀ ተሰናበተ። የዘውዱ በዓል ግብርም ተገባ ተብሎ ተመዝግቧል።
#አምባሳደር ዘወዴ ረታ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት በተሰኘው መጽሐፋቸው ንጉሠ ነገሥቱ እና ንግሥቲቱ በወርቅ ሰረገላ ኾነው ወደ ቤተ መንግሥታቸው ሲያመሩ ከሕዝቡ የጎረፈላቸው የደስታ መግለጫ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ ነው እየተባለ ይነገራል ብለው ጽፈዋል።
#ከቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን እስከ ገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት ድረስ በተደረገው የአንድ ሰዓት የእርጋታ ጉዞ ላይ እምቢልታው እና መለከቱ ሲነፋ፣ ነጋሪቱ ሲጎሸም፣ ካህናቱ ሲዘምሩ፣ ወታደሩ ሲሸልል፣ ከዚህ ሁሉ ጋር የሴቶች እልዕልታ እና የወንዱ ጭብጨባ ሲያስተጋባ፣ የአዲስ አበባን የጥቅምት ፀሐይ እጅግ ያጋላው ይመስል ነበር።
#በዋዜማው ቅዳሜ ከማታው በአራት ሰዓት የተጀመረው ጸሎተ ቅዳሴ እና የንግሥ በዓል ሥርዓት የተፈጸመው በማግሥቱ እሑድ ከቀኑ ስድስት ሰዓት ሲኾን ነው።
#ለአሥራ አራት ሰዓታት ያለማቋረጥ በተካሄደው ሥነ ሥርዓት ላይ ንጉሠ ነገሥቱ እና ንግሥቲቱ ያሳዩትን ጥንካሬ እና የመንፈስ ጽናት ያላደነቀ አልነበረም።
#በተለይም በበዓሉ ተካፋይ ለመኾን ከአውሮፓ፣ ከእስያ እና ከአሜሪካ የመጡት የአሥራ አንድ ሀገራት እንደራሴዎች ከዚህ ቀደም በየትኛውም ዓለም ያላዩትን ይህን እጅግ ረጅም እና ከፍተኛ የኾነ ሥነ ሥርዓት ሲመለከቱ ኢትዮጵያ ያላት ጥንታዊ ባሕል ምን ያህል የሚደንቅ እና የሚከበር መኾኑን መገንዘብ የሚያስችላቸው ነው ብለው ጽፈዋል።
#ዘውድ በጫኑበት ዕለት በእርስዎ መሪነት ኢትዮጵያ ዘመናችን ያፈለቀውን ሥልጣኔ አግኝታ በዓለም ላይ የክብር ቦታ እንድትይዝ የሚያደርጉት ጥረት የተባረከ ይኹን ተብለው እንደተመረቁ ሁሉ ንጉሠ ነገሥት አጼ ኃይለ ሥላሴ በነጻነት የተቀበሏት ሀገራቸውን ታላቅ እና ገናና ትኾን ዘንድ አቅማቸው የፈቀደውን ሳይሰስቱ ሰጥተዋል።
#የኢትዮጵያን ክብር እና ጥቅም አስከብረዋል፤ ገናናቷን በአፍሪካ እና በቀረው ዓለም ደጋግመው አስመስክረዋል። የአፍሪካውያንን የአንድነት መሠረት ጥለው አልፈዋል።
#ኢትዮጵያን ስላገለገሉ እናመሰግንዎታለን፤ ስለ ኢትዮጵያ ታላቅነት፣ ነጻነት፣ ሉዓላዊነት እና ክብር ስለታተሩ እናከብረዋታል።
✍️በታርቆ ክንዴ(አሚኮ)
#ethiopianhisoryandtourism #ethiopianhistoryandtourism #enkssm

1 year ago
ውይይይ ሬዲዮ እኮ! የልቤና ሱሴም ነው! "ያለሽቦ ቃል ሚያሳልፍ የንፋስ ስልክ የተባለው 'ሬዲዮ'-የኢትዮጵያው 90ኛ የልደት ሻማውን ለኮሰ።
#ethiopia | መስከረም 2/1928 ዓ.ም ግርማዊ ጃንሆይ ለመጀመሪያ ጊዜ በሬዲዮ ስርጭቱ ንግግር አደረጉ፤ ልዕልት ጸሐይ በእንግሊዝኛ መልዕክት አስተላልፈውበታል፤ ኢጣሊያም ኢትዮጵያን ልትወር ያንዣበበችበት ዋዜማ ነበር።
ሬዲዮው በ9 ሀገራዊና በ3 የውጭ ቋንቋዎች ዜናና ፕሮግራሞችን እንደሚያስተላልፍ ያመሳከርኩት የታሪክ ሰነድ ያመለክታል።
በሞያ ብቃት የተገራሁበትን የድሮ ቤቴን ዛሬም ቢሆን በአፍሪካ ብዙዎች ከኋላው ተፈጥረው ቢቀድሙትም ከነጉድለቶቹ እወደዋለሁ።
ዋናው የኢትዮጵያ የሕዝብ ሀብት ነው ፥ ሲቀጥል ፈር ቀዳጁ የሀገር ልጆች የመሰረቱት አፍሪካዊ ሚዲያ መሆኑ እና ከሕዝብ ጋር ተሳስሮ ክፉና ደጉን እየተጋራ የዘለቀም ስለሆነ።
የኢጣሊያ አንሶልዶ ኩባንያ በሰራው የንፋስ ስልክ ጣቢያ ስርጭት የጀመረው ሬዲዮ እስከ1956 ዓ.ም ድረስ በአጭር ሞገድ ማሰራጨቱ ፉጨትና ጩኸት ስለሚቀላቀልበት በጥራት አይሰማም ነበር።
ሬዲዮን ጨምሮ ቴሌቪዥንና ጋዜጣ ያኔ ድሮ ዋነኞቹ የመረጃ ምንጮች (mainstream media)፥ ቀጥሎ የተለመዱ የዜና አገልግሎት መስጫዎች (traditional media) ሲባል ቆየና ከ10 አመት ወዲህ ስያሜው በውርስ መገናኛ ብዙኀንነት (በ-legacy media) ይጠራሉ።
ቀደምቱ ሚዲያ ፈተና ተጋርጦባቸው እየተንገዳገዱ ነው። የታዳሚያን በሩጫ በተሞላ አኗኗራቸው ሳቢያ ቤት ቁጭ ብለው ሚዲያ የመጠበቅ ዝንባሌ ከመቅረቱ ጋር የተያያዘው የባህሪ ለውጥ መምጣቱ (Shift in audience behaviour) አንዱ ነው።
ፈጣን የዲጂታል ቴክኖሎጂው እንቅስቃሴን የዋጁ መረጃን በፈለጉት ጊዜና ቦታ እጅ መዳፍ ላይ
ማምጣቱ (Swift changes in technology) ሌላው በጥንቶቹ ሚዲያ ላይ የተደቀነ ፈተና ነው።
በተጨማሪም የገበያ ውድድሩ አቅጣጫ ከፍጥነት፥ ተደራሽነት፥ ዋጋ፥ ጥራትና አዋጭነት አኳያ በአማራጭ ብዛት ትኩረቱ መለወጡ (Shift in Market competition) አስተማማኝ ዘላቂ ገቢን ለማረጋገጥ እየተፈተኑ ነው።
እናም የዲጂታል ቴክኖሎጂው ፈጣን ለውጥ -"If you can't change, the change will change you" - ወቅቱን በሚዋጅ መልኩ ካልተለወጥክ - ለውጡ ራሱ ይለውጥሃል ነው ቅኔው።
እናም ውድድሩ ትንቅንቅ በሆነበት ዘመን የዕድሜ ረዥምነት ላይ ብዙ ከመመፃደቅ ያለፈ ፋይዳው የቀጠለ (Relevant) እና የገቢ አዋጭነቱ አዝላቂ (Viable) የሆነ ተጨባጭ ስራን መስራት ይጠይቃል።
እናም የአናሎግ ዘመኖቹ የሕትመትና የብሮድካስት ሚዲያዎች በቴክኖሎጂ የዝማኔ ለውጥ ከመጡት የዲጂታልና የማህበራዊ ሚዲያዎች እንዲሁም ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር የተዋጁ አሰራሮች ጋር አጣጥሞ የማስኬድ ስልትን መከተል የግድ ይላቸዋል፤አሰራሩም Media convergence strategy በሚል ይጠራል።
ሬዲዮ ለሚለው ቃል ወካይ አማርኛ ሲሰጠው - "ያለሽቦ ቃል የሚያሳልፍ መኪና" ተብሎ ተተርጉሟል።
የመሰረት ድንጋይ በተቀመጠበት ቦታ የተጻፈ-'በንፋስ የሚሄድ ስልክ' የሚል ነበርና ዛሬ አካባቢውም 'ንፋስ ስልክ' የሚል መጠሪያውን ይዞ ቀረ።
በኢትዮጵያ ሬዲዮ-ዜና ፋይል፥የሰሞኑ ታላቅ ዜናና ዓለም በዚህ ሳምንት እጅግ ተወዳጅ ከነበሩት የዜናና መዋዕለ ዜና መካከል ይጠቀሳሉ።
ከፕሮግራሞች መካከል "የእሁድ ጠዋት" ፥ "የቅዳሜ ከሰአት መዝናኛ" ፥ "ኢትዮጵያን እንቃኛት"፥ "የኪነ - ጥበባት ምሽት"፥ "ከመድሀፍት ዓለም"፥"ከአድማስ ባሻገር"፥ "አውደ ገጠር" እና "ኢኮኖሚያችን" ጥቂቶቹ ናቸው።
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ሲመሰረት ሂደቱን የቀረጸው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ነው፤ የመሪዎቹ ንግግሮች የታሪካዊ ሁነት (Historical events Speech) ተብሎ በኢትዮጵያ ሬዲዮ የድምፅ ማህደር ተሰድሮ ይገኛል።
የጥበቡ ሰውና የሸገር ሬዲዮ አንዱ መስራች ተፈሪ አለሙ፥ ከያኒውና የኢትዮ ኤፍ.ኤም ሬዲዮ አንዱ መስራች ሰራዊት ፍቅሬ እና ጋዜጠኛ መሳይ አለማየሁ ታሪክን ከትናንት፥ ዛሬና መጪውንም አክለን ተወያየን።
የእናትፋንታ ውቤ ውይይቱን ስትመራ መሳይዬ የድሮ የስቱዲዮ ማጋፈሩ ታውሶት እንደ እኛ እንግዳ ብቻ አልነበረም።
ቀዳማዊ አፄ ኃ/ሥላሴ ሐምሌ 14/ 1923 ዓ.ም በነፋስ ስልክ ለሬዲዮ ጣቢያ መቋቋም የመሰረት ድንጋይ አኖሩ፤ ጣቢያው ተመርቆ አገልግሎት የጀመረው ግን በ1927 ዓ.ም ነው።
ስርጭቱ ኢትዮጵያን እንዲሸፍን ተጠንቶ በ9 ከተሞች የሬዲዮ ማሰራጫ ጣቢያ ቢሰራ ተብሎ ታቀደ - በ1956 ዓ.ም።
ይሁንና የአካባቢ ሽፍታ በቀላል መሳሪያ ጣቢያውን ተቆጣጥሮ "ንጉሥ ሆኛለሁ" ቢል ችግር ይፈጥራል ተባለ።
ስለዚህ ጣቢያዎቹ አ/አ፥ ሐረር እና አስመራ ላይ ብቻ ተቋቁመዋል።
ስርጭቱ ርቆ ስለማይወጣም የአዲስ አበባው ሬዲዮ በሚል ይተረብ ነበር።
የትራንስሚተር ድክመቱ ፍሪኩዌንሲ እንዳይረጋ ሆኖ ሞያተኛውንም ለፍቶ መና ሲያደርገው ቆይቷል።
በ1959ዓ.ም ግን ቀ/ኃ/ሥላሴ 35ኛ የዘውድ በአላቸው ወቅት የሚዲየም ዌቭ ማሰራጫ መርቀው ከፈቱ።
አዲሱን የማሰራጫና መቅረጫ መሣሪያዎች ተጠቅሞ በምዕራብ አፍሪካና ለምዕራብ አውሮፖ በእንግሊዝኛና ፈረንሣይኛ፤ ለምስራቅና መካከለኛው እስያ በአረብኛ፤ እንዲሁም ለመካከለኛው እና ለምስራቅ አፍሪካ በስዋህሊ ቋንቋዎች ፕሮግራሞችን በማስተላለፍ የተደራሽነቱን አድማስ አሰፋ።
እናም ይህ ከአፍሪካም አልፎ አለም አቀፍ ሚዲያ ለመሆን አልሞ ብዙ ርቀት የተጓዘው በነፃዪቱ ኢትዮጵያ የተመሰረተው የኢትዮጵያ ሬድዮ ዛሬ ከዕድሜ ቆጠራ በዘለቀ ይህን ራዕይ የት አደረሰው?
የሬዲዮ ቴክኒክ ክፍሉም በቴሌ ስር ስለነበር - አብዛኞቹን ማስተላለፊያና ማሰራጫ መሳሪያዎችን የመትከልና መጠገን አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው በቴሌኮምዩኒኬሽን መ/ቤት ነበር።
እሸቱ ገለቲ

መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም አፄ ኃይለሥላሴ ከዙፋናቸው የወረዱት እለት !
‹‹ … ለሀገርና ለህዝብ ደህንነት ሲባል በዛሬው ዕለት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከስልጣን ወርደዋል፤ ለደህንነትዎ ሲባልም አስተባባሪው ኮሚቴ ወዳዘጋጀልዎ ቦታ እንዲሄዱ ተወስኗል …››
መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም
ከዓለም ስመጥር ነገሥታት መካከል አንዱ የነበሩት፣ የሰለሞናዊ ስርዎ መንግሥት የመጨረሻው ንጉሥ፣ እግራቸው በረገጠበት ምድር ሁሉ የነበረው ሕዝብ የሚሰግድላቸው፣ አንበሳ አጉራሹ … ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ የባለቤታቸው የእቴጌ መነን አስፋው፣ የልጆቻቸውና የቅርብ ሰዎቻቸው ሞት፣ የመንግሥታቸው ሹማምንት ንቅዘት፣ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ተደማምረው የአስተዳደራቸውን ምሰሶ አናጉት፡፡
በኢትዮጵያ የዘመን መለወጫ ሁለተኛው ቀን ልክ በዛሬዋ እለት ፤ መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም የጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ አፄ ኃይለሥላሴን ከዙፋናቸው አውርዶ ቤተ መንግሥቱን በመቆጣጠር የኢትዮጵያ መንግሥት መሆኑን ያወጀበት እለት።
አጼ ኃይለ ሥላሴ በርግጥም በውጪው በጣም ነበር የሚከበሩት፡፡ የሚናገሩት ቃልም ተሰሚነት ነበረው፡፡ የአፍሪቃ አንድነት ድርጅትንና የገለልተኝነት ንቅናቄ ሀገራት ማህበርን በማቋቋም ረገድ ቁልፍ ሚና ተጫውተዋል፡፡ በቅኝ ግዛት ስር የነበሩ የአፍሪቃ ሀገራት ነጻነታቸውን እንዲቀዳጁ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አሰምተዋል፡፡ በሀገር ቤቱ ጉዳይ ግን ብዙም አልተሳካላቸውም፡፡ በሀገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያውን ህገ መንግሥት ያረቀቁት እኚሁ መሪ እውነተኛው ስልጣን የህዝብ ይሆን ዘንድ አልፈቀዱም፡፡ የባሪያ ንግድን በማጥፋት የዘመናዊነት ተስፋን የፈነጠቁት ንጉሥ በኢጣሊያ ቅኝ ገዥዎች እንኳ ተወግዶ የነበረውን የገባር ስርዓት እንደገና በህዝብ ላይ ጭነዋል፡፡ ውሳኔዎችን በፓርላማ የማሳለፍ ባህልን ያስተዋወቁት “አጼ” ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ላለማስፈን በብርቱ ታግለዋል፡፡
በአገዛዝ ዘመናቸው የሀገሪቱን “አፈር ገፊ” አርሶ አደር አላንቀሳቅስ ካለው የመደብና የኢኮኖሚ ጭቆና በተጨማሪ የሀይማኖትና የብሔር ጭቆናዎች የሀገሪቷን ቀፍደደው ይዘዋታል፡፡ ሀገሪቷ ወደፊት መንቀሳቀስ አቅቷት ትዋትት ነበር፡፡
ለበርካታ ዘመናት ህዝቡ ጭቆናውንና መከራውን በግላጭ መቃወም ያልቻለው ህዝብ በውስጡ እየነፈረ ኖረ፡፡ ብሶቱ በቁጭት ሲያንተከትከው ከቆየ በኋላ የመጨረሻው ጥግ ደረሰ፡፡ ከ1965 መጨረሻ እስከ 1966 አጋማሽ ድረስ ሲታዩ የነበሩት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውጥንቅጦች ህዝቡን በስርዓቱ ላይ አነሳሱት፡፡ በየካቲት 1966 አብዮት ፈነዳ፡፡ ስልጣን ከንጉሠ ነገሥቱ እጅ አመለጠች፡፡ ለብዙ ክፍለ ዘመናት ሲወራረስ የቆየው የሰለሞናዊው ስርወ መንግሥት ግብአተ መሬትም ሊፈጸም ተቃረበ፡፡
ከየጦር ክፍሎቹ የተላኩት ተወካዮች በአራተኛ ክፍለ ጦር ተሰባሰቡ፡፡ በሰኔ 21/1966 “የጦር ሀይሎች፣ የፖሊስ ሰራዊትና የብሔራዊ ጦር አስተባባሪ ኮሚቴ” የሚባል 120 አባላት ያሉት ወታደራዊ ሸንጎ መሰረቱ፡፡ ከሶስተኛ ክፍለ ጦር የመጡት ሻለቃ መንግሥቱ ሀይለማሪያም የኮሚቴው ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ የአራተኛ ክፍለ ጦሩ ሻለቃ አጥናፉ አባተ ምክትል ሊቀመንበር ተብለው ተሰየሙ፡፡ በሊቀመንበር መንግሥቱ ጠያቂነትም የሶስተኛ ክፍለ ጦሩ ሻለቃ ገብረየስ ወልደሃና የኮሚቴው ዋና ጸሓፊ ጠያቂነት ሆኑ፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ኮሚቴው “ለምን በፈረንጅ ስም እንጠራለን” በሚል ምክንያት “አስተባባሪ ኮሚቴ” የተሰኘውን መጠሪያውን “ደርግ” በማለት ቀየረው (“ደርግ” የሚለውን ስም ያመነጨው የደርጉ የባህል ኮሚቴ ሰብሳቢ የነበረው ሻለቃ ናደው ዘካሪያስ ነው፤ በደርግ ወገን ሆነው ታሪኩን የጻፉ ወገኖች እንደገለጹት “ደርግ” የግዕዝ ቃል ሲሆን እኛ “ኮሚቴ” ከምንለው ጋር ተቀራራቢ ፍቺ አለው)፡፡
ወታደሮቹ ያቋቋሙት “ደርግ” እንቅስቃሴውን ጀመረ፡፡ ከሁሉም በፊት ህጋዊነትን ማግኘት አስፈላጊው ስለነበረ ከንጉሠ ነገሥቱ ዘንድ ቀርቦ ታማኝነቱን ገለጸላቸው፡፡ አጼውም ደርጉን በይሁንታ ተቀበሉት፡፡ በዚህ መሰረት ወታደራዊው ደርግ ከሲቪሉ የልጅ እንዳልካቸው ካቢኔ ጎን ለጎን ሆኖ አመራር መስጠት ጀመረ፡፡ በስልጣናቸው ባልገዋል የተባሉ ባለስልጣናትንም አሰረ፡፡ ይሁንና ሁለቱ የአመራር አካላት በሚወስዷቸው የተቃረኑ እርምጃዎች ሊጣጣሙ ባለመቻላቸው አብረው መቀጠል ተሳናቸው፡፡ ይባስ ብሎም በሐምሌ መገባደጃ ላይ ወታደራዊው ደርግ የልጅ እንዳልካቸውን ካቢኔ አፈረሰው፡፡ ከሚኒስትሮቹም መካከል በርካቶቹ ታሰሩ፡፡
የወታደሮቹ ደርግ የንጉሠ ነገሥቱን ስልጣን ቀስ በቀስ መገዝገዝ ጀመረ፡፡ እንደ ዘውድ ምክር ቤት፣ የዙፋን ችሎትና የጸጥታ ካቢኔ (ልዩ ካቢኔ) የመሳሰሉ ተቋማትን አፈረሰ፡፡ በጥናት ላይ የነበረው አዲሱ ህገ መንግስትም እንዲታገድ ወሰነ፡፡ ፓርላሜንቱም ዳግመኛ ላይሰበሰብ ተበተነ፡፡
ከዚህ ጎን ለጎን ደርግ የህዝቡን ስነ-ልቦና ለራሱ አመራር ዘመን የማዘጋጀቱን ተግባር ተያያዘው፡፡ የንጉሡንና የዘውዳዊውን ስርዓት ገመና ማጋለጥ ጀመረ፡፡ ንጉሡ ከጊዮርጊስ ቢራ ፋብሪካና ከከተማ አውቶቡስ አገልገሎት ከፍተኛ ገቢ እንደሚዝቁ የሚገልጹ ፕሮግራሞችን በመገናኛ ብዙሀን አስተላለፈ፡፡ በመጨረሻው ላይ ግን መላውን ህዝብ ያስለቀሰውንና የ1965ቱን የወሎ ረሐብ የሚዘግበውን ዶክመንተሪ ፊልም አሳየ፡፡ በዚህም ህዝቡ ለስርዓቱ ያለውን ገደብ የለሽ ጥላቻ አሳየ፡፡
መስከረም ሁለት/1967….. ከጧቱ 3፡00 ሰዓት… በብሔራዊ ቤተ መንግሥት…..
በደርጉ ውስጥ የአስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሊቀመንበር ሆነው የተሰየሙት ሻለቃ ደበላ ዲንሳ ንጉሠ ነገሥቱ ከስልጣን መውረዳቸውን እንዲያረዳቸው የተመረጠውን አስራ ሶስት አባላት ያሉትን ቡድን እየመሩ ከቤተ መንግሥት ደርሰዋል፡፡ ነገር ግን ቡድኑ ንጉሡ ፊት ቀርቦ መልዕክቱን የሚነግርበትን ድፍረት አጣ፡፡ ጥቂት ካሰቡ በኋላ ግን ሻለቃ ደበላ አንድ ዘዴ ብልጭ አለችባቸው፡፡ የንጉሡ የቅርብ የስጋ ዘመድ የሆኑት ልዑል ራስ እምሩ ሀይሥ ስላሴ “ለደሃው ገበሬ የሚቆረቆሩ ተራማጅ መስፍን ናቸው” ማለትን ስለሰሙ እርሳቸው ባሉበት ንጉሡ መልዕክቱን እንዲሰሙት ቢደረግ ግዳጃቸውን ያለ አንዳች ችግር መፈጸም የሚችሉ ሆኖ ታያቸው፡፡ በዚህም መሰረት ጉዳዩን ለራስ እምሩ አስረዱ፡፡ ራስ እምሩም ይሁንታቸውን ገለጹላቸው፡፡ በቀጣይ የሆነውን ሻለቃ ደበላ ዲንሳ እንደሚከተለው ተናግረውታል፡፡
“የደርጉ መልዕክተኞች ሆነን የመጣነው አስራ ሶስታችንም ስድስት በአንድ በኩል፣ ስድስት በሌላ በኩል ተሰልፈው፣ እኔ መሀከላቸው ሆኜ ነበር የቆምኩት፡፡ ትንሽ ከጠበቅን ኋላ ጃንሆይ ከፎቅ እየወረዱ መሆናቸው ተነገረንና በተጠንቀቅ ቆምን፡፡ ትልቁ የዙፋን አዳራሽ ውስጥ ነበርን፡፡ ንጉሠ ነገሥቱ ገብተው ወንበራቸው ላይ እንደተቀመጡ አንድ እርምጃ ወደፊት ሄጄ በመቅረብ ወታደራዊ ሰላምታ ግጥም ካደረግኩ በኋላ በደርጉ ተዘጋጅቶ የተሰጠኝን ጽሑፍ አነበብኩና እንደገና ወታደራዊ ሰላምታ ሰጥቼ አንድ እርምጃ ወደኋላ በመራመድ ከጓደኞቼ ጋር ተቀላቅዬ ቆምኩ፡፡ ከስልጣን መውረዳቸውን የሚገለጽ ከሁለት፣ ሶስት መስመር ያልበለጠ አጭር ጽሑፍ ነበር፡፡”

ግዮን ሆይ አግሣ‼️
#ethiopia | ዓባይ መንገደኛው ወዴት ትሄዳለህ ?
እናትህን ኢትዮጵያን ለማን ትተዋለህ?
እያለ ዜመኛው...
በአራራይ በርክርክ ያንቆረቆረልህ፤
በአዲሱ ዓመት ብስራቱ ሰመረ፤
ግዮን አገሣ ዓባይ ተሞሸረ።
አምላክ ኢትዮጵያን ባረካት ወንዟንም አደላት፤
በብርቱ ልጆቿ እራት መብራት ኾናት።
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
ለእልፍ ዘመናት...
ስንት ሀሳብ ተነሳ ስንቱ ተረቀቀ፤
ለ14 ክረምት ስንት ወገን ወደቀ፤
ስንት ላብ ፈሰሰ ስንቱ ሀብት አለቀ፤
ስንት አየን መከራ ሰማን እንጉርጉሮ ፤
ሀሩር ከባዕድ ፊት ጠበሰን ተጣምሮ።
አሰናካዮቹ ወደታች ወረዱ በላይ አንጋጠጡ፤
በጉልበት በቁጣ ቆመው አፈጠጡ፤
በብልጠት በለቅሶ በእጅ አዙርም መጡ፤
በመረጡት ሁሉ እውነት የለምና በመጡበት ወጡ።
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
ሰከላ ተወልደህ ጉባ ላይ ያደግኸው፤
800 ምዕራፍ ቤትህን የዞርኸው፣
በ14 ሃምሳ በአንድ የስልክ ጥሪ፤
ትባል የነበረ የሰው ቤተ ሠሪ የሰው አኗኗሪ፤
ዓባይ ስመ ብዙ ፈለገ ዐቢይ የፈውስ ወንዝ፤
ጌዖን፣ ጊሖን፣ አባዊ ከገነት የሚመዘዝ፤
ፈፋ ቆላውን አቋርጦ ጉድጓድ ሸለቆ ሰንጥቆ፤
በበረሃ የሚጮህ በፏፏቴ ድምፁ ደምቆ፤
"ግዮን ወተት ኾኖ ገነትን ካጠጣት፤
የግዮን መነሻ ኢትዮጵያ ምንድናት?"
ቢልም ባለቅኔው መፍቻ አለው ብልኃት፤
የጥበባት መፍለቂያ የምስጢራት መገኛ፤
ኢትዮጵያ ሀገር ናት ምድረ ቀደምት የኛ።
ያገር ልጅ የማር እጅ ያባይ ልጅ ሳቢሳ፤
በጥቅሻ ተጠርቶ የስንፍናን መግነዝ በጥሶ ተነሳ፤
ምስጋና ለእናንተ ለዓባይ ወንዝ ልጆች ፤
የሙላቱን ብስራት ላሰማችሁ ጀግኖች ፤
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
ጃንሆይ ዘክረው ጉልበት ቢከዳቸው፤
ወረታቸው ቢጎድል ጥሪቱም ቢያጥራቸው፤
"በትውልድ ይገንባ"
የሚል ጦማር ጻፉ አደራ ፈርመው፤
እኛም ትውልድ ነን ያባት ቃል አክባሪ፤
የዘመናት ቁጭት መርገምን ሰባሪ፤
መንገድ የሳተውን በመስመሩ መሪ፤
ራዕይ ፈጻሚዎች ትልም ተላሚዎች፤
ትዕምርት የምናቆም ጡብም ደርዳሪዎች፤
ወረት ሰብሳቢዎች ጥሪት ቋጣሪዎች፤
የአባት ሕልም ፈተን ለልጅ የምናወርስ፤
በዘመን ሀዲድ ላይ የልብ የምናደርስ፤
ተደግፈን ያለምን በአበው መከዳ፤
ስብራት ጠጋኝ ነን የምፍቅ እዳ።
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
የዓባይን ልጅ ውኃ ጠማው የሚል ተረት ተሰረዘ፤
የውጪ አልጋ የውስጥ ቀጋ መርገምህ ተደለዘ፤
ወርቅ ግንዱን ይዞ አይዞርም በያገሩ፤
ልብ ገዝቶ ተመልሷል ወደ ምድሩ፤
ገባር ወንዞች በኅብር ቆመን የተጋመድን፤
ጨለማ አሳብ ረገፈ እንደችቦ ስለበራን፤
ዓባይ ምግብ መጠጥ ዓባይ ኃይል ኾነ፤
የተሠበረው ስማችን በአደባባይ ተጠገነ፤
የጎደፈው ክብራችን በዓለም ላይ ገነነ ፤
ወድቀን ተነስተናል ጀምረን ጨርሰናል ፤
ከእንግዲህ ለመብረር የቱ ያቆመናል፤
ዓባይ ዘረ ብዙ ዓባይ ስመ ብዙ፤
ተበጣጥሶ ወድቋል ሴራና መዘዙ።
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
የሀገሬ ልጆች የሀገሬ አፍላጋት በሉ ተደሰቱ፤
የጠፋው ልጅ ዓባይ ተመልሷል ቤቱ፤
አዲስ ልብስ አልብሱት አብሉት ከሙክቱ፤
ቀለበት አርጉለት በጌጠኛ ጣቱ፤
"ከሰው ቤት እንጀራ ከተሞናሞነው፤
የእናት ቤት ይሻላል የዋለ ያደረው፤"
የሚል ዜማ ሰምቶ ዓባይ ልብ ገዛ፤
ገብር ኄር ተባለ ፊቱ በጠል ወዛ፤
ከእንግዲህ እናትህን አገልግል ተነሳ፤
በበጎ ፈቃድህ ጎረቤት አትርሳ ፤
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
አክሱም፣ ላሊበላ፣ ጎንደር፣ ጀጎል፣ ጢያ፤
የተጋድሎው ትዕምርት..
ከዓባይ ላይ ደረሰ ሐረግ ማስቀጠያ፤
የድል ታሪክ ብስራት በዓለም መታያ፤
ዳግማዊ አድዋ የእድገት መብቀያ፤
የአደባባይ ኩራት ጠላት በመቀያ፤
የእውነት ምስክር ሀቅ የኢትዮጵያ ፤
እባብ ጊንጥ እሾሁን እየተራመድነ፤
ይቻላል ያልነውን ችለን አሳየነ፤
በብርቱ ልጆቿ ደም ላብና ፍቅር፤
በጽኑ ተጋድሏቸው ወዝና ክብር፤
ኢትዮጵያ ሀገሬ ለዘላለም ትኑር።
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
የሀብከ ብርሃኔ ጥላሁን
#ethiopia | ዓባይ መንገደኛው ወዴት ትሄዳለህ ?
እናትህን ኢትዮጵያን ለማን ትተዋለህ?
እያለ ዜመኛው...
በአራራይ በርክርክ ያንቆረቆረልህ፤
በአዲሱ ዓመት ብስራቱ ሰመረ፤
ግዮን አገሣ ዓባይ ተሞሸረ።
አምላክ ኢትዮጵያን ባረካት ወንዟንም አደላት፤
በብርቱ ልጆቿ እራት መብራት ኾናት።
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
ለእልፍ ዘመናት...
ስንት ሀሳብ ተነሳ ስንቱ ተረቀቀ፤
ለ14 ክረምት ስንት ወገን ወደቀ፤
ስንት ላብ ፈሰሰ ስንቱ ሀብት አለቀ፤
ስንት አየን መከራ ሰማን እንጉርጉሮ ፤
ሀሩር ከባዕድ ፊት ጠበሰን ተጣምሮ።
አሰናካዮቹ ወደታች ወረዱ በላይ አንጋጠጡ፤
በጉልበት በቁጣ ቆመው አፈጠጡ፤
በብልጠት በለቅሶ በእጅ አዙርም መጡ፤
በመረጡት ሁሉ እውነት የለምና በመጡበት ወጡ።
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
ሰከላ ተወልደህ ጉባ ላይ ያደግኸው፤
800 ምዕራፍ ቤትህን የዞርኸው፣
በ14 ሃምሳ በአንድ የስልክ ጥሪ፤
ትባል የነበረ የሰው ቤተ ሠሪ የሰው አኗኗሪ፤
ዓባይ ስመ ብዙ ፈለገ ዐቢይ የፈውስ ወንዝ፤
ጌዖን፣ ጊሖን፣ አባዊ ከገነት የሚመዘዝ፤
ፈፋ ቆላውን አቋርጦ ጉድጓድ ሸለቆ ሰንጥቆ፤
በበረሃ የሚጮህ በፏፏቴ ድምፁ ደምቆ፤
"ግዮን ወተት ኾኖ ገነትን ካጠጣት፤
የግዮን መነሻ ኢትዮጵያ ምንድናት?"
ቢልም ባለቅኔው መፍቻ አለው ብልኃት፤
የጥበባት መፍለቂያ የምስጢራት መገኛ፤
ኢትዮጵያ ሀገር ናት ምድረ ቀደምት የኛ።
ያገር ልጅ የማር እጅ ያባይ ልጅ ሳቢሳ፤
በጥቅሻ ተጠርቶ የስንፍናን መግነዝ በጥሶ ተነሳ፤
ምስጋና ለእናንተ ለዓባይ ወንዝ ልጆች ፤
የሙላቱን ብስራት ላሰማችሁ ጀግኖች ፤
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
ጃንሆይ ዘክረው ጉልበት ቢከዳቸው፤
ወረታቸው ቢጎድል ጥሪቱም ቢያጥራቸው፤
"በትውልድ ይገንባ"
የሚል ጦማር ጻፉ አደራ ፈርመው፤
እኛም ትውልድ ነን ያባት ቃል አክባሪ፤
የዘመናት ቁጭት መርገምን ሰባሪ፤
መንገድ የሳተውን በመስመሩ መሪ፤
ራዕይ ፈጻሚዎች ትልም ተላሚዎች፤
ትዕምርት የምናቆም ጡብም ደርዳሪዎች፤
ወረት ሰብሳቢዎች ጥሪት ቋጣሪዎች፤
የአባት ሕልም ፈተን ለልጅ የምናወርስ፤
በዘመን ሀዲድ ላይ የልብ የምናደርስ፤
ተደግፈን ያለምን በአበው መከዳ፤
ስብራት ጠጋኝ ነን የምፍቅ እዳ።
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
የዓባይን ልጅ ውኃ ጠማው የሚል ተረት ተሰረዘ፤
የውጪ አልጋ የውስጥ ቀጋ መርገምህ ተደለዘ፤
ወርቅ ግንዱን ይዞ አይዞርም በያገሩ፤
ልብ ገዝቶ ተመልሷል ወደ ምድሩ፤
ገባር ወንዞች በኅብር ቆመን የተጋመድን፤
ጨለማ አሳብ ረገፈ እንደችቦ ስለበራን፤
ዓባይ ምግብ መጠጥ ዓባይ ኃይል ኾነ፤
የተሠበረው ስማችን በአደባባይ ተጠገነ፤
የጎደፈው ክብራችን በዓለም ላይ ገነነ ፤
ወድቀን ተነስተናል ጀምረን ጨርሰናል ፤
ከእንግዲህ ለመብረር የቱ ያቆመናል፤
ዓባይ ዘረ ብዙ ዓባይ ስመ ብዙ፤
ተበጣጥሶ ወድቋል ሴራና መዘዙ።
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
የሀገሬ ልጆች የሀገሬ አፍላጋት በሉ ተደሰቱ፤
የጠፋው ልጅ ዓባይ ተመልሷል ቤቱ፤
አዲስ ልብስ አልብሱት አብሉት ከሙክቱ፤
ቀለበት አርጉለት በጌጠኛ ጣቱ፤
"ከሰው ቤት እንጀራ ከተሞናሞነው፤
የእናት ቤት ይሻላል የዋለ ያደረው፤"
የሚል ዜማ ሰምቶ ዓባይ ልብ ገዛ፤
ገብር ኄር ተባለ ፊቱ በጠል ወዛ፤
ከእንግዲህ እናትህን አገልግል ተነሳ፤
በበጎ ፈቃድህ ጎረቤት አትርሳ ፤
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
***
አክሱም፣ ላሊበላ፣ ጎንደር፣ ጀጎል፣ ጢያ፤
የተጋድሎው ትዕምርት..
ከዓባይ ላይ ደረሰ ሐረግ ማስቀጠያ፤
የድል ታሪክ ብስራት በዓለም መታያ፤
ዳግማዊ አድዋ የእድገት መብቀያ፤
የአደባባይ ኩራት ጠላት በመቀያ፤
የእውነት ምስክር ሀቅ የኢትዮጵያ ፤
እባብ ጊንጥ እሾሁን እየተራመድነ፤
ይቻላል ያልነውን ችለን አሳየነ፤
በብርቱ ልጆቿ ደም ላብና ፍቅር፤
በጽኑ ተጋድሏቸው ወዝና ክብር፤
ኢትዮጵያ ሀገሬ ለዘላለም ትኑር።
ግዮን ሆይ አግሣ እንደ ጥቁር አንበሳ፤
እንደ እንግጫ ደንፋ ፈንድቅ እንደ እንቦሳ፤
እንጉርጉሮህ በቃ መርገምህ ተነሳ።
የሀብከ ብርሃኔ ጥላሁን
1 year ago
የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዜና ዕረፍት
ነሐሴ 21 ቀን 1967 ዓ.ም
#ethiopia | መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም ወታደራዊው የደርግ ሥርዓት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴን ከስልጣናቸው አወረደ ፤የንጉሱ መውረድም በብሔራዊ ራዲዮንና ቴሌቭዥን አማካይነት ዜናው ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ሆነ ።
ይህ ከሆነ ከ 11 ወራት በሁዋላ በነሀሴ 21 ቀን 1967ዓ.ም የኢትዮጵያ ራዲዮ ለአርባ አመታት ኢትዮጵያን በንጉሰ ነገሥትነት የመሩት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ማረፋቸውን ይፋ አደረገ፤የጃንሆይ ዜና ዕረፍት ብዙዎችን አስደነገጠ ፤በወቅቱ የንጉሱ አሟሟት ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን የአለምን ማህበረሰብ ጭምር አነጋገረ ።
ወታደራዊው መንግስት ባወጣው መግለጫ ንጉሰ ነገስቱ ተፈጥሮዋዊ ሞት ነው የሞቱት ቢልም ንጉሰ ነገስቱ መገደላቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየጎሉ መጡ ፤በወቅቱ የጤናቸውን ሁኔታ እስር ቤት ድረስ በእየለቱ እየሄዱ ይከታተሉ የነበሩት እውቁ ኢትዮጵያዊው የህክምና ሰው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ንጉሱ ፍጹም ጤነኛ እንደነበሩና ለሞት የሚያደርስ የጤና እክል አልነበራቸውም ሲሉ ገልጸው ነበር ።
ጃንሆይ በእስር ላይ በነበሩበት ወራት በስደት የነበረው ልጃቸው ልዑል አስፋ ወሰን ኃይለስላሴ "አባቴ እጅግ ጤነኛ ነበር ፤ለሞት የሚያደርሰው ምክንያት የለም ፤አባቴ ተገድሏል ይህም በአለም አቀፋ ቀይ መስቀልና በገለልተኛ ዶክተሮች የአሟሟቱ ሁኔታ ይጣራልኝ ሲል መንግስትን ጠይቋል ፤ ወታደራዊው መንግስት ግን ይህንን ከንጉሳውያን ቤተሰቦች የተነሳውን ጥያቄ አልተቀበለውም አስከሬናቸውንም ሊሰጥ ፈቃደኛ አልነበረም ።
***
የጃንሆይ አስከሬን የተገኛው ከ 1983 ዓ.ም የመንግስት ለውጥን ተከትሎ ከተካሄደው የአመታት ፍለጋ በሁዋላ በምኒሊክ ቤተመንግስት በደርግ ፅ/ቤት ህንጻ ስር ነው ።
***
የቀብር ሥነስርዓታቸውም እጅግ ደማቅ በሆነ ሥነስርዓት በቅድስ ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
Via: ኢዮብ ዘለቀ

Sponsored by
Surafel
1 year ago
የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዜና ዕረፍት
ነሐሴ 21 ቀን 1967 ዓ.ም
መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም ወታደራዊው የደርግ ሥርዓት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴን ከስልጣናቸው አወረደ ፤የንጉሱ መውረድም በብሔራዊ ራዲዮንና ቴሌቭዥን አማካይነት ዜናው ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ሆነ ።
ይህ ከሆነ ከ 11 ወራት በሁዋላ በነሀሴ 21 ቀን 1967ዓ.ም የኢትዮጵያ ራዲዮ ለአርባ አመታት ኢትዮጵያን በንጉሰ ነገሥትነት የመሩት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ማረፋቸውን ይፋ አደረገ፤የጃንሆይ ዜና ዕረፍት ብዙዎችን አስደነገጠ ፤በወቅቱ የንጉሱ አሟሟት ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን የአለምን ማህበረሰብ ጭምር አነጋገረ ። ወታደራዊው መንግስት ባወጣው መግለጫ ንጉሰ ነገስቱ ተፈጥሮዋዊ ሞት ነው የሞቱት ቢልም ንጉሰ ነገስቱ መገደላቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየጎሉ መጡ ፤በወቅቱ የጤናቸውን ሁኔታ እስር ቤት ድረስ በእየለቱ እየሄዱ ይከታተሉ የነበሩት እውቁ ኢትዮጵያዊው የህክምና ሰው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ንጉሱ ፍጹም ጤነኛ እንደነበሩና ለሞት የሚያደርስ የጤና እክል አልነበራቸውም ሲሉ ገልጸው ነበር ።
ጃንሆይ በእስር ላይ በነበሩበት ወራት በስደት የነበረው ልጃቸው ልዑል አስፋ ወሰን ኃይለስላሴ "አባቴ እጅግ ጤነኛ ነበር ፤ለሞት የሚያደርሰው ምክንያት የለም ፤አባቴ ተገድሏል ይህም በአለም አቀፋ ቀይ መስቀልና በገለልተኛ ዶክተሮች የአሟሟቱ ሁኔታ ይጣራልኝ ሲል መንግስትን ጠይቋል ፤ ወታደራዊው መንግስት ግን ይህንን ከንጉሳውያን ቤተሰቦች የተነሳውን ጥያቄ አልተቀበለውም አስከሬናቸውንም ሊሰጥ ፈቃደኛ አልነበረም ።
*************)*************************
የጃንሆይ አስከሬን የተገኛው ከ 1983 ዓ.ም የመንግስት ለውጥን ተከትሎ ከተካሄደው የአመታት ፍለጋ በሁዋላ በምኒሊክ ቤተመንግስት በደርግ ፅ/ቤት ህንጻ ስር ነው ።
**************************************************
የቀብር ሥነስርዓታቸውም እጅግ ደማቅ በሆነ ሥነስርዓት በቅድስ ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
Via: እዮብ ዘለቀ

ሸክላ ሰሪው አጣድፎ የጠራው ዘመን ተሻጋሪ !!፻
አቀንቃኝ- ተስፋዬ ወርቅነህ
መዚቃ የምንላት የሁላችን መግባባያ ግጥምና ዜማ ተዋህደው ቅንብር እና ድምፅ ተዛምደው ትንፋሽና ጣቶች ተዋደው እንደውሁ ኩልል ፍስስ እያሉ ብንሰማ ብናያቸው የውስጣችንን ደስታና ብሶት ትውስታና ተስፋ የምታዜምልን ጥበብ ነች !!
ዘመን የማይሽረው የጆሮ ድግስ ትቶልን አልፏል !!
የማርቆሱ የሞጣው ልጅ ተስፋዬ ወርቅነህ !!
ኧረ አንቺ የዝና
ተማሪ ነኝና !!
#
ጊዜው ዕረፍት ቢነሳንም ባለታሪኮችን ማውሳት፣የተረሱትን ማስታወስ፣መልካም ሰርተው ያለፉትን መዘከር ግዴታችን ነው።
የዛሬው ባለታሪክ በ1990ዎቹ ቦግ ፍልቅ ብቅ ብሎ ገና በለጋ እድሜው የመኖር ግዳጁን የዚችን ዓለም ድካም ንቆ የጠፋው ድንቅ ድምፃዊ ተስፋዬ ወርቅነህ ነው።
ድምፃዊ ተስፋዬ ወርቅነህ ዘፈኖቹ የከፋውን ከልብ የሚያስለቅሱ፣ መልሰው በማፅናናትት ዕንባን የሚያብሱ ናቸው። ያፈቀረ፣ የናፈቀ፣ ትዝታ ያለበት፣ የመከዳት ዕጣ የደረሰው ሁሉም ፈልጎ የሚሰማው ወጣት ተስፋዬ ወርቅነህ ነው።
የዘፈን ግጥሞቹ በብዙዎቻችን ልብ እንደታተሙ ናቸው።
በአብዛኛው ወጣት የፍቅር ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ ካላቸው የባህል ዘፈን አቀንቃኞች አንዱም ነበር።
በዘፈኖቹ ውስጥም መውደድ፣ መከፋት፣ብሶት ተስፋዬ ዘፈኖች ውስጥ አሉ።
ተስፋዬ ወርቅነህ በአድማጭ የሚወደደው አዳም ሙሉ የሚሆነው በሔዋን መዓዛ ውስጥ መሆኑን በዘፈን ስለነገረን ብቻ አይደለም።
####
የሕይወት ጣዕም፣ የምድር በረከት፣የመንፈስ ጥንካሬ አንድ ላይ የሚገኘው ሴት የተባለች ፍጡር ላይ መሆኑን ስላስታወሰንም አይደለም።
ምድር የጨቆነችው፣ተስፋውን የተቀማ፣ አማዕልክት ያራቁት ሁሉ መድሃኒቱን ከሔዋን እንደሚያገኝ በውብ ድምፁ እያቀነቀነ ስላስደመጠን ብቻም አይደለም። ይኼማ ምኑ ይካዳል ሁላችንም የምናውቀው እውነታ ነው የሚል አንድ ፅሁፍ ማህበራዊ ገፅ ላይ ስለድምፃዊው የፃፈውን አይቻለሁ !!
ተስፋዬን ከሚያምር ድምፁ ባሻገር ወጣትነትን ፍቅርን በጥዑም ዜማ በግሩም ቅንብር የተሰሩ ዘመን አይሽሬ ስራዎቹ ነው።
በወቅቱ ባህላዊ ሙዚቃንም ወደ ዘመናዊ ሳይንጋደድ ሳይጣመም አዋዶ ከከተማ እስከ ገጠር ኧረ አንቺ የዝና ተይ አታንገላቺኝ ተማሪ ነኝና እያለ ዝናን በቀላሉ እጁ አስገብቶ ነበረች
ተስፋዬ ወርቅነህ !!
*
በዚያ ዘመን የ1980 እና 1990 ትውልዶች" ተማሪ ነኝ እኔማ" የሚለውን ዘፈን በት/ቤቶችና በሚኒሚዲያና በተለያዩ ክበቦች ያንጎራጎሩት ጓደኞቻችንን አንረሳም እንዴትስ ይረሳሉ !!
በጊዜው የተስፋዬን ዘፈኖች መስማት ያፈቀሩትን ሰው ገላ እንደመንካት ተቆጥሮ ሕይወት ያለመልም ነበር። "አለ ነገር፣ የብር ወለባ፣ ከኔ ተለይተሽ፣ ተማሪ ነኝ፣ ሙሉ፣ከሚላ፣ ውቢቱ ጎጃም፣ ፍቅር በእኔ ላይ፣ ከመርካቶ፣ ደራ ነው" በሚሉት ዘፈኖች ውስጥ የብዙ ሰዎች ፍቅር፣ትዝታ፣ ናፍቆት፣ብሶት አለ።
ከሰዎቹ ሁሉ የተለየሽበት
አለሽ አንድ ምስጢር ያስወድድ ያለበት።" እያለ ወስዶ ይመልሰናል !!
እናቴን አባቴን ዘመድን ልይ ብሎ
የናፈቀማ ሰው ይመጣል ኮብልሎ።
ሲል ከባሏ ከከንፈር ወዳጇ ከፍቅረኛዋ ዘንድ መምጫ ብልሃቱን ሁሉ ይጠቁማል። ችግሩን ከነመፍትሄው ይሉሃል ይኼ ነው። መምጣቷ በቂ አይደለም። ቀጥሎ የሚሆነውን ተስፋዬ እንዲህ ይነግረናል።
ተይ አታስጨንቂኝ በሆነ ባልሆነው፣
መድሃኒቱን ሰጥተሽ ብታድኝኝ ምነው።
መድሃኒቱ ምንድን የሚል ይኖር ይሆን ? የሆነው ሆነና በዚህ ዘፈን መድሃኒት ፍለጋ ያልተማፀነ አፍቃሪ አይኖርም።
ተስፍሽ ምኞቱን በኪሱ ከትቶ መድሃኒቱን ሳያገኝ የቀረ ከመሰለህ ግብዳ ስህተት ተሳስተሃል።ከበረከቱ ተቋድሷል። እንዲህ ሲል የአልጋ ላይ ምስክርነቱን ሰጥቷል።
አልጋ ላይ ስትጥይ ቀበቶ አስፈትተሽ፣
ማሩኝ ታስብያለሽ ወንድ ልጅ አስተሽ።
እኔና ተስፋዬ የሚያመሳስለን አንድ ነገር ምኞታችንን በእርግጫ ብለን አንገለውም። ምኞታችን መልስ ያገኛል።( ጉረኛ እኮ ነኝ!)
ውበቷን፣ ደም ግባቷን፣ ጨዋታ አዋቂ፣ አንሶላ አድማቂ የአልጋ ላይ ንግስት መሆኗን በውብ ድምፁ እንዲል ይላታል።
እጥር ምጥን ብላ ተሰርታ እንደሙዳይ
ተቀምጣ አጫዋች ተኝታ ሰው ገዳይ።
ተስፋዬ የመልክአምድር አድናቂም ነው። ጣናን በዘፈኑ ጎብኝቷል። አቀንቅኖላታል። እንዲህ ብሎ:-
የታንኳው ሽርሽር የመንፈስ ማደሻ፣
ከጣና እስከዘጌ ፍቅር መጨረሻ።
አምላክ ታሪክ ትቶ ተጨንቆ የሰራሽ፣
ለምለሟ አገራችን አባይ ጣና እንዴት ነሽ።
አብዛኛው የዘመኑ ሙዚቃ ፈርጀ ጠባብ ነው።ዘፋኞች ነጠላ ጭብጥ ይዘው ነው ደክመው የሚያደክሙን፥ሰልችተው የሚያሰለቹን። ተስፋዬን ልዩ የሚያደርገው ፍቅር ላይ ብቻ ሙጭጭ አይልም።ሰምተን የማንሰለቸውን የአያቶቻችንን የጀግንነት ታሪክ ወደኋላ መልሶ ያስኮመኩመናል። "ማደሬ" ነው የሚለው ዘፈኑ በጀግኖች ታሪክ የታጀበ ነው።
ፅናትን አሸንፎ ማሸነፍን የደሃን ቁርጠኝነትና ሲገልፀው
እምዬ ሚኒሊክ ቢያስፈልጉ አጡሽ
ጎንደር አፄ ፋሲል ቢያስፈልጉ አጡሽ
ጥሩ ንጉስ ጦና ቢያስፈልጉ አጡሽ
ደሃ ቁርጠኛ ነው እኔ አገኘሁሽ ሲል ተቀኝቷል።
*
የደጃዝማች በላይ ዘለቀን አያያዝ፣ የፍርድ ሂደት እና የሕይወቱን ፍፃሜ አስመልክቶ ዘፋኙ ያንጎራጎረውን ባለአራት ስንኝ ግጥሞች መልዕላስታውሳችሁ እወዳለሁ...
አታለሉት አሉ በላይ ዘለቀን
መከሩበት አሉ በላይ ዘለቀን
አሰቃዩት አሉ በላይ ዘለቀን
ክፉ የክፉ ቀን የሚሆነውን።
በላይ ደብረ ማርቆስ ላይ ንጉሱን በተቀበለ ጊዜ ስልጣን ስጡኝ አላለም። የመጀመሪያ ጥያቄው " እኔ አገር አማን ከሆነ አርሼ እበላለሁ፥ ወታደሮቼን ተረከቡኝ እና ስራ ስጧቸው" ነበር። ጃንሆይ ታዲያ ለወታደሩ ምንም መፍትሄ ሳይሰጡ በላይ አዲስ አበባ መጥቶ እንደሚነጋገሩ መልዕክት አስተላፈው ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።
በኋላ ዝቅ ያለ ማዕረግ ( ከሰራው ጀብድ አንፃር) ደጃዝማች ተብሎ ቢቸናን ቆርሰው ሰጡት። እንዲህም ሆነ በጦርነት ጊዜ ባንዳ የነበሩ ሰዎች በላይን ሊያሰሩት አልቻሉም። በነገር ጠምደው ያዙት። መከሩበት፣ ከንጉሱ ጋር አጣሉት። ተከሰሰ፣ ተሰቀለ። "አታለሉት አሉ" የሚለው ተስፋዬ ይኼን በሂደት ነው።
" አሰቃዩት አሉ" የሚለው ለዋዛ ተስፋዬ አልተጠቀመውም የኔው አካሉም አልገጠመውም። ነገሩ ወዲህ ነው። የበላይን ስቅላት የሚያስፈፅሙ ወታደሮች ገመዱን ከማንቁርቱ ከፍ አድርገው በጆሮ ግንዱ በኩል ስላስገቡት ነፍሱ ቶሎ አልወጣ ብላ ብዙ ተሰቃይቷል። ይኼን ነገር ብርሃኑ አስረስ " ማን ይናገር የነበረ- የታህሳሱ ግርግር እና መዘዙ" እና አበራ ጀምበሬ " አባ ኮስትር" በተሰኘው ስራቸው ጠቅጠሰዋል።ጌታ በለጠ እንደዚህ ይህን ወንድም የምናስታውስበትን ስለከተብክልን ከልብ ለማመስገን እንገደዳለን።ድምፃዊ ተስፋዬ ወርቅነህ አይረሳም።
ለተስፋዬ ወርቅነህ ግጥምና ዜማ ከሚያቀብሉ ሰዎች መካከል ፀሐይ በየነ ዛሬ በሕይወት የለችም ነብሷን ይማረው።
ግጥም
የኔው አካሉ
ፀሃይ በየነ ሲሆኑ !!
ሙዚቃ ቅንብር
ይሳቅ ባንጃው
ሰለሞን እያሱ
ደጀን ማንችሎት
ዳዊት አበራ
*
በነገራችን ላይ ተስፋዬ ወርቅነህ ከመርካቶ የሚለው ስራው ላይም የአዲስ አበባ ሰፈሮቿን ከእነ ውብ ልጆቿ በስራው ዳሷል አሞካሽቷል።
የቦሌዋ መጣች የቦሌዋ
ጠየም ያለች ቆንጆ ሽንጠ ለግላጋዋ
ከጉለሌ መጣች ከጉለሌ
ደግሞ ልትነካካኝ ታወቃለች ባመሌ
ከላምበረት መጣች ከላምበረት
በአይኗ እየገረፈች ልትነዳኝ እንደከብት
ከለገሃር መጣች ከለገሃር
ድሬ ልትከተኝ እኔን-----
ከፒያሳ መጣች ከፒያሳ
ልታለማምደኝ ፍቅር በጠቀሳ
ወዘተ እያለ ቆንጆ ስራ አበርክቶልናል።ይሁንና ግን የተስፋዬ ወርቅነህን ስራዎች ብዙ ወጣትና አንጋፋ ሙዚቀኞች ስራውን ሲሰሩ ይሰማል ይስተዋላል።
ግን የተስፋዬ ወርቅነህ የቀደመው ታሪኩ የሙዚቃ ህይወቱ ምን ነበር ?
የሙያ አጋሮች አብሮ አደገ ጓደኞቹ ስለድምፃዊ ተስፋዬ ወርቅነህ የምትሉንስ ነገር ይኖር ይሆን ?
ወዳጆቼ እኔ ከማውቀው ከማህበራዊ ሚዲያም ቃርሜ ለእናንተ ያደረስኩት ስራዎቹን ስለምወድለት ነው እንጂ የሞላ ታሪኩን ልሰንድ አልተቻለኝም::
#
ነብሱን ይማር ድምፃዊ ተስፋዬ ወርቅነህ።
#
አቤል ወርቁ ዘ-ኮተቤ

የክብር ግብዣ
#ethiopia | ለቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ በኋይት ሐውስ የተደረገላቸው የክብር የእራት ግብዣ
ዕለተ ማክሰኞ የካቲት 7 ቀን 1959 ዓም
State Dinner for His Imperial Majesty Haile Selassie I, Emperor of Ethiopia
Location: State Dining Room, White House, Washington, DC
ከምስሉ ላይ መመልከት እንደሚቻለው ጃንሆይ ወደ ግብዣው ቦታ የሄዱት ባዶ እጃቸው አልነበረም። የመጨረሺያውን ምስል ይመለከቷል።
Credit: LBJ Library photo by Mike Geissinger #jemal_abdulaziz

የፊታውራሪ አመዴ ለማ ታሪክ በድምፅ ትረካ ሊቀርብ ነው
#ethiopia | አገራቸውን በልዩ ልዩ መንገድ ያገለገሉት ፊታውራሪ አመዴ ለማ የፃፉት የሕይወት ታሪክ መፅሀፍ በተወዳጅ ሚድያ አማካይነት በድምፅ ሊተረክ ነው፡፡
"የሕይወት ታሪኬ" በሚል ርዕስ የዛሬ 14 ዐመት መፅሐፍ ያሳተሙት ፊታውራሪ አመዴ ከልጅነት እስከ አዛውንትነት ዕድሜያቸው ለሀገር የሚጠቅም ተግባር በማከናወን ያለፉ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ናቸው፡፡
ይህን የሀገር አበርክቷቸውን፣በመፅሐፋቸው ላይ ግልፅ በሆነ መልኩ ያስቀመጡ ሲሆን በድምፅ ትረካ ሲቀርብም ለብዙዎች ተደራሽ እንደሚሆን ይገመታል፡፡
የድምፅ ትረካው በጋዜጠኛ ዕዝራ እጅጉ የተተረከ ሲሆን ከፊታውራሪ አመዴ ለማ ቤተሰቦች ጋርም በትብብር የተዘጋጀ ቅንብር ነው፡፡
የአክሱም ሀውልት መመለስ ላይ ፊታውራሪ አመዴ ለማ ትልቅ ሚና የነበራቸው ሲሆን የታሪክ፣ የባህልና የንግድ ዕውቀታቸው ብስለትን የተላበሰ ነው፡፡
እርሳቸው የሦስቱን መንግስታት ዘመን በደንብ ያውቁ ስለነበር ከዚያ ቀደም የአክሱም ሀውልትን ለማስመለስ ያልተሳኩ ሙከራዎችን አብጠርጥረው ይረዱ ነበር።
በ1948 ዓ.ም በህዝብ ጥቆማ በጃንሆይ የፓርላማ አባል በመሆን በቅንነት እና በታማኝነት ያገለገሉት ፊታውራሪ የሕዝብን ጥያቄ ያለ ፍርሀት በማንሳት የተከበሩ ነበሩ፡፡
.
ፊታውራሪ አመዴ ለማ፣ ከንጉሡ እስከ ኢሕአዴግ ባሉት መንግስታት ውስጥ የተመለከቷቸውን ጥሩ ነገሮች ማድነቅ እንደሚችሉት ሁሉ ያላመኑበትንም ትህትና በታከለበት ግልጽነትና በድፍረት በመናገር ይታወቃሉ፡፡ ለዚህ ማስረጃ በንጉሡ ዘመን ለተለያዩ አካላት የፃፏቸው ደብዳቤዎች ናቸው፡፡
ፊታውራሪ አመዴ ለማ የአክሱም ሀውልት ብቻ ሳይሆን ሌሎች የአክሱም ስልጣኔ ማሳያ የሆኑ ቅርሳ ቅርሶች እንዲመለሱ ያደረጉት ጥረት በሙሉ የተሳካ ነበር። የእስልምና ሀይማኖት አባት ቢሆኑም በጣልያን መንግስት ለተዘረፉ የአብያተ-ክርስትያናት ቅርሶች ወገባቸውን ይዘው የዲፕሎማሲ ሥራቸውን አከናውነዋል፡፡
በ1908 ዓ.ም የተወለዱት ፊታውራሪ አመዴ ለማ (ረቡዕ ሚያዝያ 14 ቀን 2001 ዓ.ም.) በ89 ዓመታቸው አርፈዋል፣ በሞቱ ወቅት 10 ልጆች፣ 34 የልጅ ልጆች እና 6 የልጅ ልጅ ልጆችን አይተዋል፡፡
የእርሳቸውን የሕይወት ታሪክ የያዘው ተከታታይ ትረካ 20 ክፍሎች የሚኖሩት ሲሆን ከሰኔ 30 2017 በኃላ ከምሽቱ 3ሰዐት አንስቶ tewedajemedia tube ላይ መተረክ ይጀምራል፡፡
ተወዳጅ ሚድያ እና ኮምዩኒኬሽን መፅሀፎችን ወደ ድምፅ መተረክ ከጀመረ 7ዓመት ያስቆጠረ ሲሆን በእነዚህ ጊዜያት 30 በላይ መፅሐፎችን በትረካ ያቀረበ ሲሆን ከእነዚህም መሐል የኤርትራ ጉዳይ፣የአሰብ ወደብ ሥራ፣ ማማ በሰማይ፣የሀይሌ ፊዳ ታሪክ፣ የዶክተር አክሊሉ ሀብቴ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ እና ሌሎችም መፅሐፎች ይገኙበታል፡፡https://youtube.com/tewed...

Comments