1 month ago
"I Will Always Love You" ያገናኛቸው ሁለቱ ንግስቶች!
#ethiopia | በፈረንጆቹ 1994 በተካሄደው የ36ኛው የግራሚ (Grammy Awards) ሽልማት ስነስርዓት ላይ፣ በዓለም ሙዚቃ ታሪክ ውስጥ በወርቃማ ፊደላት ተጽፎ የሚኖር የማይረሳና ታሪካዊ ክስተት አስተናግዶ ነበር።
ዶሊ ፓርተን በ1970ዎቹ አጋማሽ የጻፈችውንና በራሷ ድምፅ አቀንቅናው የነበረውን "I Will Always Love You" የተሰኘውን ሙዚቃ ዊትኒ ሂውስተን በ "The Bodyguard" ፊልም ላይ በከፍተኛ ብቃት መጫወቷ የሚታወስ ነው።
በዚያ ድንቅ ምሽት ዶሊ ፓርተን ራሷ ወደ መድረክ በመውጣት በእሷ ብዕር ተጽፎ በዊትኒ ሂውስተን ህያው ድምፅ ዓለም አቀፍ ክስተት የነበረው ሙዚቃ "የዓመቱ ምርጥ ዘፈን" በማለት የግራሚ ሽልማቱን በእጇ አስረክባለች።
ሁለቱ ድምጻውያን በመድረኩ ላይ ያሳዩት ፍቅር መከባበርና ደስታ የብዙዎችን ልብ የነካ ነበር።
ያ ቀን ሁለት የሙዚቃ ንግስቶች በአንድ ድንቅ የታሪክ አጋጣሚ እና ዘመን ተሻጋሪ የሆነው ሙዚቃ ስራ የፈጠረው ክስተት ለዘላለም ሲያበራ የሚኖር ታላቅ ምሽት ሆኖ ተመዝግቧል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #whitneyhouston #dollyparton #iwillalwaysloveyou #grammys #musichistory #worldnews

“አባቷ መሬት ሲያርስ፣ እሷ ግን ዜማንና ደስታን አረሰች”
#ethiopia | ይህ አንጀት የሚበላ ንግግር ያደረገው የዶሊ ፓርተን የወንድሟ ልጅ የህይወት ጉዞዋን የሚያሳይ የሀዘን መግለጫ ነው።
የፓርተን ህልፈት በአሜሪካ የመዝናኛና የሙዚቃ ዓለም ብቻ ሳይሆን በፖለቲካውና በህዝብ ዘንድም ትልቅ ሀዘን ፈጥሯል።
ከአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጀምሮ በርካታ የሙዚቃና የፊልም ዓለም ሰዎች ለአርቲስቷ የህይወት ቅርስ ክብር ሰጥተዋል።
ዶሊ ፓርተን ከ60 ዓመታት በላይ በዘለቀ የሙዚቃ ስራዋ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አድናቂዎችን አፍርታለች።
“Jolene”፣ “I Will Always Love You” እና “9 to 5” ከታዋቂ ስራዎቿ መካከል ይጠቀሳሉ።
በሙዚቃ ስራዋ ብቻም ሳትወሰን በፊልም፣ በንግድ ስራና በሰብአዊ እርዳታ ዘርፎችም ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥራለች።
በተለይም የህፃናትን የንባብ ባህል ለማሳደግ Imagination library
ፕሮግራም ለህፃናት ከ150 ሚሊዮን በላይ መጻሕፍት እንዲደርሱ አስተዋፅኦ አድርጓል።
ዶሊ በሙዚቃ ስራዋ ብቻም ሳትወሰን በፊልም፣ በንግድ ስራና በሰብአዊ እርዳታ ዘርፎችም ትልቅ ተፅዕኖ ፈጥራ ይህንን አለም ተሰናብታለች።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #countrymusic #usa #dollyparton #jolene #iwillalwaysloveyou

(ዘ-ሐበሻ ሕይወት) ዝነኛዋ የካንትሪ ሙዚቃ ንግሥት ዶሊ ፓርተን በሰማንያ ዓመቷ ከዚህ ዓለም ድካም ማረፏን ተከትሎ፣ ድምፃዊት ቢዮንሴ ጥልቅ ሐዘኗን በስሜት ገልጻለች። የሁለቱ የጥበብ ከዋክብት ቁርኝት እ.ኤ.አ. በሁለት ሺህ ሃያ አራት በወጣውና የቢዮንሴ የሙዚቃ አብዮት ማሳያ በሆነው "ካውቦይ ካርተር" የተሰኘ አልበም ላይ በደመቀ ሁኔታ ተንጸባርቋል። በዚህ አልበም የፓርተን የሺ ዘጠኝ መቶ ሰባ ሦስት የማይጠወልግ የጥበብ ፍሬ የሆነው "ጆሊን" የተሰኘው ሙዚቃ በአዲስ ዜማና አቀራረብ ዳግም ሕይወት ዘርቶ ቀርቧል።
ቢዮንሴ በድረገጿ ላይ ባሰፈረችው ልብ የሚነካ መልእክት፣ "ዶሊ ሆይ፣ አንቺ ለሁላችንም የልቀት መለኪያና የሰሜን ኮከባችን ነበርሽ" በማለት የጥበብ እናቷን አሞግሳለች። አክላም "አንቺ ደፋርና ድንቅ፣ ተሰጥኦ የተረፈሽና ወደኋላ የማትዪ ጀግና ነሽ። ማንነትን በልዩ ሁኔታ እንዴት መግለጽ እንደሚቻል ለብዙዎቻችን አብነት ሆነሻል። ለጥበብሽ፣ ለሰፊው ልብሽ፣ ለለጋስነትሽ፣ ለፈገግታሽና ለስራ ፈጣሪነትሽ ምንጊዜም ዕዳ አለብኝ" ስትል የልቧን አውጥታለች።
ድምፃዊቷ አብረው ያሳለፉትን ወርቃማ ጊዜ ወደኋላ መለስ ብላ በማስታወስ፣ የፓርተንን የዘመን ተሻጋሪ አሻራ በክብር አንስታለች። "ካንቺ ጋር አብሮ የመስራት ጸጋን በማግኘቴ እጅግ እኮራለሁ፤ ይህንንም ትዝታ በልቤ ጓዳ ለዘላለም በክብር አኖረዋለሁ" ስትል ገልጻለች። በመቀጠልም "በዚህች ዓለም ላይ ላሳረፍሽው ጥልቅና በጎ ተጽእኖ ልባዊ ምስጋናዬ ይድረስሽ። በሚያፈነድቀው ጥበብሽ ይህችን ምድር የተሻለችና የደመቀች ስፍራ ያደረግሽ የሰላም መልአክ ነሽ። አንቺ በእውነት በምትክ የማይገኝልሽ ልዩ ፈጠራ ነሽ፤ ነፍስሽ በሰላም ትረፍ" በማለት የመጨረሻ ስንብቷን አድርጋለች።
በአልበሙ ውስጥ በአዲስ መልክ ከተቀነቀነው "ጆሊን" ባሻገር፣ ዶሊ ፓርተን በ"ካውቦይ ካርተር" አልበም ላይ የማይረሱ የድምጽ አሻራዎቿን አኑራለች። በዘጠነኛው ትራክ ላይ "ዶሊ ፒ" በሚለው አጭር ትረካ፣ እንዲሁም በሃያ አምስተኛው ትራክ መጀመሪያ ላይ ልዩ በሆነውና ማራኪ አንደበቷ የራሷን ድምቀት ፈጥራለች።
ቢዮንሴ "ቴክሳስ ሆልድ ኤም" በተሰኘው ሙዚቃዋ የቢልቦርድ የካንትሪ ሙዚቃ ሰንጠረዥን በመምራት በዘመናዊው የካንትሪ ሙዚቃ ታሪክ ይህን ክብር ያገኘች የመጀመሪያዋ ጥቁር ሴት ሆና ታሪክ ስትሰራ፣ አልበሙ ገና ለዕይታ ከመብቃቱ በፊት ፓርተን አድናቆቷን ችራላት ነበር። በወቅቱም የቢዮንሴ ትልቅ አድናቂ መሆኗንና የካንትሪ ሙዚቃ አልበም በመስራቷ እጅግ መደሰቷን በመግለጽ፣ ሙሉ አልበሙን ለማድመጥ በጉጉት እንደምትጠብቅ ስሜቷን አጋርታ እንደነበር ይታወሳል።

"ሁልጊዜ ከምሰበስበው ገንዘብ ይልቅ የተቀበልኩትን የእግዚአብሔር በረከት እቆጥራለሁ!"
#ethiopia | የካንትሪ ሙዚቃ ንግስት በመባል የምትታወቀው ዝነኛዋ ድምፃዊት የዜማ ደራሲና ተዋናይ ዶሊ ፓርተን በተወለደች በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ቤተሰቦቿ አረጋግጠዋል።
ለአስርት ዓመታት በዘለቀው ስኬታማ የሙዚቃ ህይወቷ በርካታ ሽልማቶችን ገናናነትን እና ከፍተኛ ሀብትን ማፍራት ችላለች።
ፓርተን በፈረንጆቹ 2019 ከ ሲቢኤስ ሰንደይ ሞርኒንግ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ለሷ ዋናውና ብቸኛው ትርጉም ያለው ነገር የሙዚቃ ጥበቡ እንጂ ገንዘብ እንዳልሆነ ተናግራ ነበር።
በቃለ-ምልልሷ "ሁልጊዜም ቢሆን ከምሰበስበው ገንዘብ ይልቅ የተቀበልኳቸውን በረከቶች እቆጥራለሁ ለገንዘብ ብዬ ሰርቼ አላውቅም።
ዋናው ነገር ጥበቡ እና ስራውን መውደዴ ነው።
በስራዬ ውጤታማ በመሆኔም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ" ስትል የነበራትን የጥበብ ፍቅር ገልጻ ነበር።
የዶሊ ፓርተን በሞት መለየት በዓለም አቀፍ የሙዚቃ አፍቃሪዎችና አድናቂዎቿ ዘንድ ከፍተኛ ሀዘንን ፈጥሯል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #countrymusic #usa #dollyparton #jolene #iwillalwaysloveyou
#ethiopia | የካንትሪ ሙዚቃ ንግስት በመባል የምትታወቀው ዝነኛዋ ድምፃዊት የዜማ ደራሲና ተዋናይ ዶሊ ፓርተን በተወለደች በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ቤተሰቦቿ አረጋግጠዋል።
ለአስርት ዓመታት በዘለቀው ስኬታማ የሙዚቃ ህይወቷ በርካታ ሽልማቶችን ገናናነትን እና ከፍተኛ ሀብትን ማፍራት ችላለች።
ፓርተን በፈረንጆቹ 2019 ከ ሲቢኤስ ሰንደይ ሞርኒንግ ጋር ባደረገችው ቃለ ምልልስ ለሷ ዋናውና ብቸኛው ትርጉም ያለው ነገር የሙዚቃ ጥበቡ እንጂ ገንዘብ እንዳልሆነ ተናግራ ነበር።
በቃለ-ምልልሷ "ሁልጊዜም ቢሆን ከምሰበስበው ገንዘብ ይልቅ የተቀበልኳቸውን በረከቶች እቆጥራለሁ ለገንዘብ ብዬ ሰርቼ አላውቅም።
ዋናው ነገር ጥበቡ እና ስራውን መውደዴ ነው።
በስራዬ ውጤታማ በመሆኔም እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ" ስትል የነበራትን የጥበብ ፍቅር ገልጻ ነበር።
የዶሊ ፓርተን በሞት መለየት በዓለም አቀፍ የሙዚቃ አፍቃሪዎችና አድናቂዎቿ ዘንድ ከፍተኛ ሀዘንን ፈጥሯል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #countrymusic #usa #dollyparton #jolene #iwillalwaysloveyou
1 month ago
"ጆሊን፣ ጆሊን - ባሌን አትውሰጂብኝ!"
የሀገር በቀል ሙዚቃ ንግስት ዶሊ ፓርተን
#ethiopia | የዓለም አቀፍ የከንትሪ ሙዚቃ ንግስት፣ ድምፃዊትና የበርካታ በጎ አድራጎት ስራዎች ባለቤት የሆነችው ዶሊ ፓርተን በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።
በስድስት አስርት ዓመታት የኪነ-ጥበብ ጉዞዋ ከ100 ሚሊዮን በላይ የሙዚቃ አልበሞችና ስራዎቿን በመሸጥ 11 የግራሚ አዋርዶችን ማሸነፍ ችላለች።
እንደ ጆሊን፣ አይ ዊል ኦልዌይስ ላቭ ዩ እና 9 ቱ 5 ያሉ ዓለም አቀፍ ተወዳጅነትን ያተረፉ ዜማዎችን በመጫወት ከ60 ዓመታት በላይ በሙዚቃው ዓለም ቆይታለች።
ከበርካታ ስኬታማ ሥራዎቿ መካከል በፈረንጆቹ 1973 ለአድማጭ የቀረበውና እስከ ዛሬ ድረስ በብዙዎች ዘንድ የማይረሳው ጆሊን የተሰኘው ዘፈኗ ይጠቀሳል።
ዶሊ ፓርተን እንደተናገረችው ይህ ዘፈን የተፃፈው ባለቤቷ ካርል ዴቪድ ዲን በባንክ ውስጥ በሚሠራበት ወቅት ከአንዲት ቆንጆ የባንክ ሰራተኛ ጋር ያሳየው የነበረውን ቀረቤታና ለእሱ ያደረገችውን ቅናት መሰረት በማድረግ ነው።
ጆሊን የሚለው ስም የመጣው ደግሞ በሙዚቃ ትርኢቷ ላይ ካገኘቻትና ፊርማዋን ከጠየቀቻት አንዲት ህፃን ልጅ ስም የተወሰደ ነው።
ዘፈኑ የተለመደውን የቁጣ ስሜት ሳይሆን አንዲት ማራኪና ውብ ሴት ፊት ተንበርክካ እባክሽን ባሌን አትውሰጂብኝ በማለት የምታቀርበውን የልመና ስሜት የሚያንፀባርቅ ነው።
የዘፈኑ መግቢያ የጊታር ምት እና የዶሊ ፈጣንና ስሜታዊ ድምፅ ዘፈኑ በሰዎች አእምሮ ውስጥ በቀላሉ እንዲቀረፅ አድርጎታል።
ስራው ከተለቀቀበት ጊዜ ጀምሮ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ አድናቂዎችን ያፈራ ሲሆን በሮሊንግ ስቶን የዓለማችን 500 ታላላቅ ዘፈኖች ዝርዝር ውስጥ ተካቷል።
ከማይሊ ሳይረስ እስከ በርካታ ዓለም አቀፍ ድምፃውያን ድረስ በራሳቸው የሙዚቃ ቅdirect መልሰው የተጫወቱት ዘመን ተሻጋሪ ስራ መሆን ችሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#countrymusic #usa #dollyparton #jolene #iwillalwaysloveyou #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Sponsored by
Surafel
1 month ago
የአሜሪካ ባንዲራ በግማሽ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ትዕዛዝ ሰጡ!
#ethiopia | የዶሊ ፓርተን ህልፈት በአሜሪካ የፖለቲካና የመዝናኛ ዓለም ታላላቅ ሰዎች ዘንድ ሰፊ ሀዘን ቀስቅሷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዶሊ ፓርተን ህልፈት ተከትሎ ጥልቅ ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም የዶሊ ፓርተን ሞት የትውልዱ ነው ሲሉም ሀዘኑ ከባድ መሆኑን ገልጸዋል።
አሜሪካ ክብሯን ለመግለጽ ለአንድ ሳምንት ሰንደቅ ዓላማዋን ዝቅ አድርጋ እንድታውለበልብ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
ትራምፕ የዶሊ ፓርተንን ሞት “ለሚሊዮኖች ሰዎች እውነተኛ ኪሳራ” በማለት ገልጸው፣ የአሜሪካ ባንዲራ ከነሐሴ 25 ከምሽቱ 6:00 ጀምሮ እስከ መስከረም 1 ድረስ በግማሽ ዝቅ እንዲል አዘዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት Donald Trump በማህበራዊ ሚዲያ ባሰራጩት መልዕክት ፓርተንን “ከታላላቅ የካንትሪ ዘፋኞች አንዷ” በማለት ገልጸዋታል።
ትራምፕ በተጨማሪም ህልፈቷ “ለሚሊዮኖች ሰዎች እውነተኛ ኪሳራ” መሆኑን ገልጸው፣ “እንደ እሷ ያለ ሰው ከዚህ በፊት አልነበረም፣ ወደፊትም አይኖርም” በሚል አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #countrymusic #usa #dollyparton #jolene #iwillalwaysloveyou
#ethiopia | የዶሊ ፓርተን ህልፈት በአሜሪካ የፖለቲካና የመዝናኛ ዓለም ታላላቅ ሰዎች ዘንድ ሰፊ ሀዘን ቀስቅሷል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የዶሊ ፓርተን ህልፈት ተከትሎ ጥልቅ ሀዘናቸውን ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ አክለውም የዶሊ ፓርተን ሞት የትውልዱ ነው ሲሉም ሀዘኑ ከባድ መሆኑን ገልጸዋል።
አሜሪካ ክብሯን ለመግለጽ ለአንድ ሳምንት ሰንደቅ ዓላማዋን ዝቅ አድርጋ እንድታውለበልብ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።
ትራምፕ የዶሊ ፓርተንን ሞት “ለሚሊዮኖች ሰዎች እውነተኛ ኪሳራ” በማለት ገልጸው፣ የአሜሪካ ባንዲራ ከነሐሴ 25 ከምሽቱ 6:00 ጀምሮ እስከ መስከረም 1 ድረስ በግማሽ ዝቅ እንዲል አዘዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት Donald Trump በማህበራዊ ሚዲያ ባሰራጩት መልዕክት ፓርተንን “ከታላላቅ የካንትሪ ዘፋኞች አንዷ” በማለት ገልጸዋታል።
ትራምፕ በተጨማሪም ህልፈቷ “ለሚሊዮኖች ሰዎች እውነተኛ ኪሳራ” መሆኑን ገልጸው፣ “እንደ እሷ ያለ ሰው ከዚህ በፊት አልነበረም፣ ወደፊትም አይኖርም” በሚል አድናቆታቸውን ገልጸዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #countrymusic #usa #dollyparton #jolene #iwillalwaysloveyou
1 month ago
እውቋ የአገረሰብ ሙዚቃ ንግሥት ዶሊ ፓርተን ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
******************
በአገረሰብ ሙዚቃ በዓለም ዙሪያ ከፍተኛ እውቅናን ያተረፈችው አንጋፋዋ አሜሪካዊት የሙዚቃ ደራሲ፣ አቀንቃኝ እና የፊልም ተዋናይ ዶሊ ፓርተን በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
ዶሊ ፓርተን በ60 ዓመታት የሙዚቃ ሕይወቷ፣ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች ዘንድ የሚወደዱትን እንደ “ጆሊ”፣ “አይ ዊል ኦልዌይስ ላቭ ዩ”፣ “9 ቱ 5”፣ “ኮት ኦፍ መኒ ከለርስ” እና ሌሎች በርካታ የጥበብ ስራዎቿን አበርክታለች።
የዶሊን ሕልፈት ተከትሎ በርካታ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የሞያ አጋሮቿ እና አድናቂዎቿ ሀዘናቸውን በማህበራዊ ሚድያዎች ላይ እየገለጹ ሲሆን የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶላንድ ትራምፕ የአገሪቱ ባንዲራ ለአንድ ሳምንት ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ማዘዛቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል።
በዘመን አይሽሬ ስራዎቿ የ"ካንትሪ ሙዚቃ ንግሥት" የሚለውን የክብር ስም ያተረፈችው ዶሊ ፓርተን ከሙዚቃ ሕይወቷ ባሻገር በደግነቷ፣ በሰው ወዳድነቷ እና በሰብዓዊነት ተግባሮቿ ለብዙዎች አርዓያ በመሆኗ ትታወሳለች።
49 የስቱዲዮ አልበሞቿ እና ከ200 በላይ ነጠላ ዜማዎቿ በቢልቦርድ 'ሆት ካንትሪ ሶንግስ' ቻርት ላይ 25 ቁጥር አንድ ዘፈኖችን ያስገኙላት ሲሆን፣ ይህም በማንኛውም ሴት የካንትሪ ሙዚቃ አርቲስት ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።
ዶሊ ፓርተን ባስደናቂ ስራዎቿ 11 የግራሚ ሽልማቶችን ያገኘች ሲሆን ከ20 በላይ በሚሆኑ ፊልሞች ላይም በተዋናይነት ተሳትፋለች።
Ethiopian Broadcasting Corporation EBC-መዝናኛ #ዶሊ #dolly

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአንጀት ሰርስሪ ድምጿ፣ በማይነጥፍ የቃላት ቋቷ እና ወደር በማይገኝለት የደግነት ልቧ የዓለምን መድረክ ስታደምቅ የኖረችው አንጋፋዋ አሜሪካዊት ድምፃዊት፣ ተዋናይት እና በጎ አድራጊ ዶሊ ፓርተን በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች።
“አባቷ መሬት ሲያርስ፣ እሷ ግን ዜማንና ደስታን አረሰች” ሲል የወንድሟ ልጅ ባወጣው የሀዘን መግለጫ የህይወት ጉዞዋን መስክሯል። በብርሃን ታጅባ የኖረችው ዶሊ፣ ክብደታቸው ለሚያታክት አንጸባራቂ ጌጣጌጦች ጀርባዋን ሰጥታ፣ በመጨረሻው የዕረፍት አልጋዋ ላይ በሰላም ማሸለቧን ቤተሰቦቿ አረጋግጠዋል።
በአስርት ዓመታት የጥበብ ዘመኗ 10 የግራሚ ሽልማቶችን የሰበሰበችው እና "የካንትሪ ሙዚቃ ንግሥት" የሚል የክብር ስም የተጎናጸፈችው ዶሊ፣ በተለይም “Jolene” እና “I Will Always Love You” በተሰኙት ዘመን ተሻጋሪ ስራዎቿ በዓለም ዙሪያ የትዝታ ዙፋን ዘርግታለች።
ከጥበብ ልዕልናዋ ባሻገር በስሟ ባቋቋመችው ፋውንዴሽን በሚሊዮን የሚቆጠሩ መጻሕፍትን ለህፃናት በማደል የምትታወቅ የዘመናችን የርህራሄ ተምሳሌት ነበረች። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገጠማት የጤና እክል ምክንያት ከህዝብ እይታ ርቃ የቆየች ሲሆን፣ ቀደም ብሎም ለህክምና ስትል የሙዚቃ መድረኮቿን ሰረዛለች።
ይህንን የጥበብ ዋርካ መውደቅ ተከትሎ፣ ሀዘኑ የትውልድ እንደሆነ የገለጹት ፕሬዝዳንት ትራምፕ፣ አሜሪካ ክብሯን ለመግለጽ ለአንድ ሳምንት ሰንደቅ ዓላማዋን ዝቅ አድርጋ እንድታውለበልብ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል። ዶሊ በምድር ላይ የዘራችው የጥበብና የፍቅር ብርሃን፣ ከትውልድ ትውልድ ሲዘከር ይኖራል።

የሙዚቃዋ ንግሥት ዶሊ ፓርተን በከዚህ ዓለም በሞት ተለየች
#ethiopia | የሀገሬው (ካንትሪ) ሙዚቃ ንግሥትና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚወደዱ በርካታ ዜማዎች ደራሲ የሆነችው አሜሪካዊቷ ድምፃዊት ዶሊ ፓርተን በ80 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት መለየቷን ቤተሰቦቿ በዛሬው ዕለት ባወጡት መግለጫ አስታወቁ።
ለስድስት አስርት ዓመታት ያህል በሙዚቃው ዓለም ውስጥ በነበራት ታላቅ ተፅዕኖ፣ ልብ የሚነኩ ግጥሞቿ እና ሳቢ ስብዕናዋ የሚታወቀው ዶሊ ከ100 ሚሊዮን ዶላር በላይ አልበሞችን በመሸጥ በታሪክ ውስጥ እጅግ ስኬታማ ከሆኑ ሴት ድምፃውያን መካከል አንዷ ለመሆን በቅታለች።
"ኮት ኦፍ ሜኒ ካለርስ"፣ "ጆሊን" እና "አይ ዊል ኦልዌይስ ላቭ ዩ" የተሰኙት ዝነኛ ዜማዎቿ በዓለም ዙሪያ በሚሊዮኖች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፉላት ሲሆን፣ የ11 ግራምይ ሽልማቶች ባለቤትም ነበረች።
ከሙዚቃ ሥራዎቿ በተጨማሪ በፊልም ተዋናይነት፣ በቴሌቪዥን ፕሮግራሞች አዘጋጅነት እና የልጆች መጻሕፍትን በማበርከት የሚታወቀው ፓርተን፣ በተለይም "ዶሊዉድ" የተሰኘውን ታዋቂ የቱሪስት መዝናኛ ፓርክ በገዛ ሀገሯ በመገንባት ትልቅ ስም አትርፋለች።
ከሕዝብ ጋር የነበራት ጥልቅ ቁርኝትና የበጎ አድራጎት ሥራዎቿ፣ የኮቪድ-19 ክትባት ምርምር ድጋፍን ጨምሮ በበርካታ ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ ንቁ ተሳታፊ እንድትሆን አድርጓታል።
በሕይወት ዘመኗ ከ3,000 በላይ ዘፈኖችን የሰራችው ይህች ድንቅ የኪነ-ጥበብ ሴት ታላቅ ስሟ ሁልጊዜ ሲታወስ ይኖራል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

ውሃ ላይ እንደ ልቧ ስትዘንጥ ውላ፣ ስትንሳፈፍ የምታነጋው ቬነስ!
የጉዞ ማስታወሻ
ተስፋዬ እሸቱ (ረዳት ፕሮፌሰር)
ከቬነስ፣ ጣሊያን #ethiopia | ለመጀመሪያ ጊዜ ቬነስን ለማየት የተመኘሁት፣ አንጀሊና ጆሊ እና ጆኒ ዴፕ የተወኑበትን The Tourist የተሰኘውን ፊልም ካየሁ በኋላ ነው። ፊልሙን ካየሁት ዓመታት ስለተቆጠሩ ታሪኩ ብዙም ትዝ አይለኝም።
ቬነስ ግን ከአእምሮዬ አልወጣችም። የውሃ መንገዶቿ፣ ድልድዮቿ፣ በውሃው ላይ የሚንሸራሸሩት ጀልባዎች፣ ዕድሜ ጠገብ ሕንፃዎቿ.... አንድ ቀን በዓይኔ ላያቸው የምመኛቸው ምስሎች ሆነው ቀሩ።
አንዳንድ ጊዜ ፊልም ታሪክን ብቻ አይነግረንም፤ የማናውቀውን ቦታም ያስናፍቀናል። “የማያውቁት አገር አያናፍቅም” የሚለው ለቬነስ አይሠራም። ቬነስን ናፈቅኋት። “ባየኋት!” አልኩ በምኞት። እንዴት እንደማያት ግን አላውቅም ነበር፤ ምኞት ብቻ።
እነሆ ታዲያ ዛሬ ምኞቴ ሰምሮ ቬነስ እገኛለሁ፤ ደስ አይልም?!
ከብዙ ዓመታት በፊት በፊልም ስክሪን ያየኋቸውን የቬነስ መንገዶች ዛሬ በእግሬ ተራመድኩባቸው፤ ውሃዋን በጀልባ አቋረጥኩ፤ በድልድዮቿ ላይ ቆሜ ከተማዋን አየሁ።
ወቸው ጉድ! አልኩ።
ከ180 ዓመታት በፊት ቬነስን የጎበኘችው የFrankenstein ደራሲ Mary Shelley፣ “ቬነስ ከዓለም ከማንኛውም ስፍራ ፈጽሞ የተለየ ነገር አላት” ስትል ጽፋ ነበር። እኔም ቬነስን በዓይኔ ሳይ የተሰማኝ ይኸው ነው። ከ180 ዓመታት በኋላ የMary Shelleyን አባባል እንደገና ለመድገም የሚያስገድድ አንድ ነገር በቬነስ አለ። ከተማ ናት፤ ግን የለመድነውን አይነት ከተማ አትመስልም።
በቬነስ የለመድነው የከተማ ድምፅ የለም። የመኪና ጥሩምባ የለም፤ የሞተር ጩኸት የለም፤ የትራፊክ መብራት ፊት ቆሞ መንገድ እስኪከፈት መጠበቅም የለም፤ ትራፊክ ራሱ የለም፤ ለመቅጣት ያሰፈሰፈ ትራፊክም አታዩም፤ የታክሲ ግፊያም የለም። “መርካቶ! መርካቶ!” የሚሉ ሰማያዊ ታክሲዎች የሉም ብቻ ሳይሆን፣ ከነጭራሹ አይታሰቡም። የራሷ ብቻ የሆነ የከተማ ለዛ አላት።
በቬነስ ውሃ መንገድ ነው። ጀልባ አውቶቡስ ነው፤ ጀልባ ታክሲያቸውም ነው። በቬነስ ውሃ ላይ ብቻውን መዘነጥ ላሰበም፣ ጎንዶላ የተባለ የግል ጀልባ አለ። ከኋላ ቆሞ በጣሊያንኛ እያወራ፣ ተሳፋሪውን በውሃ ላይ የሚያንሳፍፈውን የጀልባ ቀዛፊ “ጎንዶሊየር” ይሉታል። ተሳፋሪውን ምን እንደሚሉት ግን አልጠየኩም። ጎንዶሊየሩ ጣሊያንኛ ሲያወራ የሚለው ገባኝ አልገባኝ ብሎ መጨነቅ የለም፤ ፈገግ ብለው “ሲ!” ካሉ ይበቃል። ጀልባቸው ይቅርብኝ ካሉ ደግሞ፣ ዕድሜ ለእግርዎ! “ልወዝወዘው በእግሬ” ብለው ሲወዘወዙ ይውላሉ።
በነገራችሁ ላይ፣ ቬነስ ውሃ የከበባት ከተማ ብቻ አይደለችም፤ ውሃ መንገዷ፣ ውሃ እንጀራዋ ነው። ቀና ስትል ውሃ፣ ዞር ስትል ውሃ። ውሃ ላይ እንደ ልቧ ስትዘንጥ ውላ፣ ስትንሳፈፍ የምታድር ትመስላለች። እኔም ሳልፈራ ስንሳፈፍ ነው ያደርኩት።
ግን ከመጠየቅ ወደኋላ አላልኩም።....
“እንዴት ነው እንዲህ ያለች ከተማ ውሃ ላይ ቀጥ ብላ የቆመችው?”
የብዙዎች ጥያቄ ይሄው ይመስለኛል። ጠይቄ ብቻ ግን አልቀረሁም፤ አነበብኩ። ቬነስ በላጎን ውስጥ ባሉ ትናንሽ ደሴቶች ላይ የተገነባች ሲሆን፣ የብዙዎቹ ታሪካዊ ሕንፃዎቿ መሠረት ወደ መሬት በተተከሉ የእንጨት ምሰሶዎች የተደገፈ ነው።
በድጋሚ፣ ወቸው ጉድ!
ግን...እንዴት ቀኑን ሙሉ ውሃ ሲመታው፣ ውሃ ሲጠጣ እየዋለ እንጨቱ አይነቅዝም?....
በዚህ ረገድ ቬነሳውያን ተፈጥሮን በእጅጉ የተረዱ ሰዎች ሆነው አገኘኋቸው። እንጨቶቹ በጭቃና በውሃ ውስጥ ተቀብረው ስለሚቆዩ ኦክስጅን በብዛት አያገኙም። ይህም በተለይ ፈንገሶች እንጨቱን በፍጥነት እንዳያበሰብሱት ያደርጋል። መበስበሱን ሙሉ በሙሉ አያስቆመውም፤ በእጅጉ ግን ያዘገየዋል። ለዚህም ነው እነዚህ የእንጨት ምሰሶዎች ለዘመናት የሕንፃዎቹ መሠረት ሆነው ሊቆዩ የቻሉት።
ልብ በሉ፤ ይህን ሲያስቡ ዛሬ ያለን ዘመናዊ የኢንጂነሪንግ ቴክኖሎጂ የለም፤ ኮምፒውተር የለም፤ AI የለም። የነበራቸው አንድ ነገር ተፈጥሮን መታዘብና በተሞክሮ ያካበቱት ዕውቀት ነበር። ይህን ሳስብ በውሃው መካከል ለዘመናት የጸናው የሰው ልጅ ጥበብ ደነቀኝ። ሰው ሆኖ መፈጠር እንዴት ያለ ጸጋ ነው! አልኩ፣ ደግሜ።
ከደሴት ወደ ደሴት፣ ከመንደር ወደ መንደር ለመጓዝ በቬነስ ከ400 በላይ ድልድዮች አሉ። ከእነዚህ መካከል ዝነኛው Rialto Bridge ነው። በፎቶ ብዙ ጊዜ ያየሁትን ሪያልቶ በእግሬ ስሻገረው፣ “ፎቶና ቦታውን በአካል ማየት አንድ አይደሉም” የሚለው አባባል እንደገና ትዝ አለኝ።
ከዚያም ቀጠልኩና ወደ ቅዱስ ማርቆስ አደባባይ (Piazza San Marco) አቀናሁ። የቅዱስ ማርቆስ ባዚሊካ፣ የዶጅ ቤተ መንግሥት፣ የዘመናት አርክቴክቸር፣ በየአቅጣጫው የሚፈሱ ጎብኚዎች... አረ ስንቱ ይነገራል!
ታዲያ በቬነስ ያየሁት አንድ ትልቅ ችግር አለ፤ “ነፃ” የሚባል ነገር ብዙም አይወዱም!
ቬነስ ውበቷን በነፃ አታሳይም። እንደማንኛውም ታዋቂ የቱሪስት ከተማ አረ ከዚያም በላይ ምንም ነገር በዋዛ አይቀመስም። ቡናው አለ፣ ምግቡ አለ፣ ጀልባው አለ፣ ጎንዶላው አለ። ብቻ በየቦታው “Paghi, per favore!” ነው።ቬነስ ከመጣሁ የተማርኩት አንድ የጣሊያንኛ ሐረግ ቢኖር፣ ይሄው ብቻ ነው፣ “እባክዎ ይክፈሉ!” የሚለው።
የሆነ ጊዜማ ተናድጄ፣ “ውሃውን እግዚአብሔር በነፃ አይደለ እንዴ የሰጣችሁ? ምናለ ይሄንን እንኳ ብትምሩኝ!” አልኩት።
ፈገግ ብሎ፣ “እግዚአብሔር ውሃውን በነፃ ቢሰጠንም፣ እኛ ግን እንዴት መሸጥ እንዳለብን አስበናል፤ የምትከፍለው ለውሃው ሳይሆን ለሐሳባችን ነው!” አለኝ፤ እውነት አለው።
ምን አለፋችሁ እያስጎበኙ የዓለምን ቱሪስት ያልቡታል። ቱሪስቱም እምቢ አይልም፤ ደስ እያለው ኪሱ ውስጥ ያለውን ያራግፋል። ባወጣው ግን ቅር አይሰኝም። ቬነስ ኪስህን ታራቁተዋለች፤ ልብህን ግን በሆነ ስሜት ትሞላዋለች።
እና እንዳልኳችሁ... ለቬነስ ውሃ እንጀራዋ ብቻ ሳይሆን ስጋቷም ነው። ቬነስ ከውሃ ጋር የኖረችውን ያህል፣ ዛሬ ውሃው ራሱ የወደፊት ሕልውናዋን እየተፈታተነው ነው። ቀስ በቀስ የመስመጥ ስጋትም ተደቅኖባታል። ይሄን ሳስብ ዝም ብሎ እንደ ሰው ስጋት ገባኝ።
ዋ! የፍቅር ከተማ የተባለችው ቬነስ፣ ልክ እንደ ታይታኒክ የብዙዎችን ፍቅርና ትዝታ ይዛ አንድ ቀን ውሃ ውስጥ ትሰምጥ ይሆን?...መቼስ ደግ አይበረክት! እያልኩ ማሰብ ጀመርኩ፤ ሐሳቡን ግን አልቀጠልኩበትም። ምክንያቱም የቬነስን የመጨረሻ ቀን ለመተንበይ አልመጣሁምና!!
መልካም ቀን!

2 months ago
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዛሬ ሐሙስ ኦገስት 13 በሁለቱም የአሜሪካ የባህር ዳርቻዎች አዳዲስ ትሮፒካል ማዕበሎች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ የተገመተ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል አንዱ በሐዋይ ደሴቶች ላይ ያልተለመደ ቀጥተኛ አደጋ ሊያደርስ እንደሚችል ተነግሯል። የብሔራዊ የአውሎ ነፋስ ማዕከል እንዳስታወቀው፣ ወደ ሐዋይ አቅጣጫ እየተጓዘ ያለው ይህ የአየር መዛባት ወደ ትሮፒካል ማዕበልነት ሊቀየር እንደሚችል እና ከተፈጠረም "ላላ" የሚል ስያሜ እንደሚሰጠው ይጠበቃል።
ይህ ማዕበል ከአርብ ኦገስት 14 ምሽት ጀምሮ በዋና ዋናዎቹ የሐዋይ ደሴቶች ላይ ከፍተኛ ነፋስ፣ ከባድ ዝናብ እና ግዙፍ ማዕበሎችን ሊያስከትል ይችላል ተብሎ ተሰግቷል። በዚሁም መሰረት የደሴቲቱ ነዋሪዎች ለጎርፍ እና ለከፍተኛ ነፋስ አደጋ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ ባለስልጣናት እያስጠነቀቁ ይገኛሉ። የዝናቡ መጠን እንደ ማዕበሉ አቅጣጫ የሚወሰን ቢሆንም፣ በአብዛኛው ከ5 እስከ 10 ኢንች፣ በአንዳንድ አካባቢዎች (በተለይም በማዊ እና በቢግ አይላንድ) ደግሞ እስከ 20 ኢንች ሊደርስ እንደሚችል ተነግሯል። ይህም ፈጣን የጎርፍ መጥለቅለቅን እና የውሃ ሙላትን ሊያስከትል ይችላል። በተጨማሪም ከ15 ጫማ በላይ የሆኑ ግዙፍ የባህር ሞገዶች ሊፈጠሩ እንደሚችሉ የሜትሮሎጂ ባለሙያዎች አስታውቀዋል። ማዕበሉ ከመድረሱ አስቀድሞ ባለው ደረቃማ እና ነፋሳማ የአየር ጸባይ ምክንያት፣ አርብ ዕለት ከፍተኛ የሰደድ እሳት አደጋ ሊከሰት እንደሚችልም ብሔራዊ የአየር ሁኔታ አገልግሎት ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።
ከሐዋዩ ስጋት በመቶዎች የሚቆጠሩ ማይሎች ርቆ በምስራቃዊው የፓስፊክ ውቅያኖስ ደግሞ “ኸርናን” የተባለ ሌላ ትሮፒካል ማዕበል ሐሙስ ማለዳ ላይ ተፈጥሯል። ሆኖም ይህ ማዕበል አቅጣጫውን ወደ ደቡብ ምዕራብ በመቀየር አርብ ዕለት ኃይሉ እንደሚቀንስ እና በየብስ ላይ ምንም ዓይነት ቀጥተኛ ጉዳት እንደማያደርስ ተገምቷል።
ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ስንመጣ፣ በአፍሪካ የባህር ዳርቻ እና በሌሰር አንቲልስ መካከል ወደ ምዕራብ አቅጣጫ እየተጓዘ ያለው የአየር መዛባት ሐሙስ ወይም አርብ ትሮፒካል ማዕበል ሆኖ ሊፈጠር እንደሚችል ከፍተኛ ግምት ተሰጥቶታል። ማዕበሉ ከተፈጠረ “ዶሊ” የሚል ስያሜ የሚሰጠው ሲሆን፣ በደረቅ አየር እና በነፋስ መቆራረጥ ምክንያት ቅዳሜና እሁድን አልፎ ሊቆይ እንደማይችል ባለሙያዎች ይገምታሉ። ምንም እንኳን ማዕበሉ ከፍተኛ አደጋ ባያመጣም፣ በድርቅ ለተጠቁት ቨርጂን ደሴቶች እና ፖርቶ ሪኮ መልካም ዜና የሆነ ዝናብን ሊያመጣ ይችላል ተብሏል።
በሌላ በኩ ከኬፕ ቨርዴ ደሴቶች በስተደቡብ ሌላ የአየር መዛባት እየተከታተለ የሚገኘው ማዕከሉ፣ ክስተቱ በሳምንቱ መጨረሻ ወደ ምስራቅ እና መካከለኛው አትላንቲክ ሲጓዝ ወደ ትሮፒካል ዲፕሬሽን ሊያድግ እንደሚችል አስታውቋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በበርሙዳ እና በአዞሬስ መካከል ወደ ምስራቅ እየተጓዘ ያለው ሶስተኛው “ክሪስቶባል” የተባለው ማዕበል እየተበታተነ መሆኑ ተገልጿል። በአጠቃላይ አሁን ላይ ከሚፈጠሩት የአትላንቲክ ማዕበሎች በአሜሪካ ዋናው ምድር ላይ የሚያደርሱት ቀጥተኛ ተጽዕኖ እንደማይኖር ታውቋል።

#ቤተልሔም_ሸረፈዲን - " የልጅ ልብና የአዋቂ ጆሮ ያላት "
( የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ )
**********************************************
ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ
#በመጨረሻም ፦ ጽሑፉ ለፌስቡክ ረጅም ( አረፍ አረፍ እየተባለ ተነቦ የሚያልቅ ) ነው ። አጥሮ ሁሉም ጋ ከሚደርስ ረዝሞ የሚመለከታቸውና የሚያስፈልጋቸው ቢያነቡት መርጬ ነው ። ሆነ ብዬ ነው ማለት ነው ። ይሁን ። እንግዲህ እያረፋችሁም ፣ እያለፋችሁም አንብቡት ።
ለግጥምም ፣ ለዜማም አልፎ ሂያጅ ነኝ። ( በተለይ ) ለግጥም አልፎ ሂያጅ መሆኔ ያስቆጨኛል ። ግጥም ምኞቴ ነው ፤ ጉድለቴም ። ማንም እንደሚሰማውና እንደሚረዳው ነኝ ። አዚያዚያምን መረዳትም ላይ ጨዋ አላዋቂ ነኝ ። ቤተልሔም ሸረፈዲን " ደስተኛ " ብላ ስለሰየመችው አዲሱ አልበሟ የተሰማኝን ልላችሁ ነው ዳር ዳር የምለው ።
እኔ የምለው ፣ ቤተልሔም ሸረፈዲን ግን ስንት ዓመቷ ነው ? በቅርቡ ትንሽ ልጅ አልነበረችም እንዴ ? ከመቼው አደገች ? ከምኔው አብባ አፈራች ? አልበሟ በተለቀቀበት " ኩራ ስትሪም " ላይ ገጣሚው ናትናኤል ግርማቸው ( ናቲ ) እንደ ገጣሚነቱ ቃላት ቆጥቦና ሀሳቡን አስውቦ " የልጅ ልብና የአዋቂ ጆሮ አላት
" እንዳላት ሆና ነው የመጣችው ። የጥበብ ስራ አመዛኙን ሁለቱን ይፈልጋል ። እውቀትም ፣ ተሰጥዖም በዝቶ ኖሯቸው የትም ሳይደርሱ የቀሩ " እገሌ ፣ እገሌ " የምንላቸው ጥቂት የማይባሉ የጥበብ ሰዎች በየአልባሌው ወድቀው ቀርተዋል ። እስቲ እነዚህን ሰዎች አስቧቸው ። የህጻን ልብም ፣ የአዋቂ ጆሮም አታገኙባቸውም ።
10 ዘፈኖች የያዘው " ደስተኛ " አልበም ናትናኤል ግርማቸውና ታምሩ አማረ በጥምረት ፕሮዲዩስ ያደረጉት ነው ። ከጀርባቸው ደግሞ ከብዙ ጥበባትና የጥበብ ሰዎች ጀርባ ያለው ዘላለም ኩራባቸው " ኩራ ስትሪም " ን ይዞ አለ ። ቅንብሩን ፣ ሚክሲንግ እና አሬንጅመንቱን ታምሩ አማረ ፣ ግጥሞቹን ( በሙሉ ) ናትናኤል ግርማቸው ( ናቲ ) ፣ " ባለቤቴ " እና " እንዴት " ዜማዎችን ዮሴፍ በቀለ ( ጆ ) ፣ " አይታለፍም " ዜማ እሱባለው ይታየው ( የሺ ) ፣ የቀሪዎቹን 7 ስራዎች ዜማዎች በምህረተአብ ደስታ ሲፈጠሩ ከእነዚህ ውስጥ የእበሙ መጠሪያ የሆነው " ደስተኛ " ን ዜማ ናቲና ምህረተአብ በጋራ ሰርተዋቸዋል ።
በአሁኑ ጊዜ አንድ ነጠላ ዜማ መስራት የምረቃ ፕሮግራም ያዘጋጃል ፤ ወዳጅ ዘመድ ያጠራራል ፤ " ሰይፉ በኢቢኤስ " ላይ ያስቀርባል ፤ ማህበራዊ ሚዲያው ላይ አላስቆም አላስቀምጥ ያስብላል ። አልበም መስራት ( አድማጭ ያልተቀበለውም ቢሆን እንኳ ) እንደ አራሷ ሴት " ምጡን ተዪው ፤ ልጁን እዪው " እየተባለና የስቃዩ ጊዜ እየተረሳ እንጂ ደጋግሞ በስሜት ሞቶ መነሳት ነው ። የሚያገጫጭ ፣ የሚያነጫንጭ ፣ የሚያቀያይምንና " ሁለተኛ ብንገናኝ ! " የሚያባብል ነው ። የምጡ ጊዜ አልፎ ልጁ ሲታይ እየተረሳ ነው አንዱ ሙዚቀኛ ከሌላው ጋር የኖረው ። ቤተልሔም መልካሞችና ህልም ያላቸው ሙያተኞች እጅ ላይ አሳርፏት እንጂ ጀምሮ አለመጨረስ ፣ ወድቆ አለመነሳትም አለ ። ገና በመጀመሪያው አልበም ፣ በትንሽ እድሜ ፣ በጀማሪነት አረዳድ እንዲህ ያለ ስኬታማ አልበም መስራት ደጋግሞ የማያጋጥም ነው ። ህብስት ጥሩነህ እነ አየለ ማሞ ( ማንዶሊን ) እና ታንጎ ሙዚቃ ቤትን እንዳገኘችው አይነት እድለኛነት ይጠይቃል ። የናቲ እና ታምሩ ጥምረት ደግሞ የእነ ኤሌክራትን እና አምባሰልን ዘመን ያስታውሰናል ።
ናቲ " ኩራ ስትሪም " ላይ 4 ዓመት ስላለፈው " ደስተኛ " አልበም ሲናገር " አልበሙን ጀምረነው ባልነው ጊዜ ያልጨረስነው እኛ በዚያ ውስጥ እየተሰራን ስለነበረ ነው " ይለዋል ። ፕሮዲዩሰሮቹ በምን በምን እንደተሰሩ አላውቅም ። ቤተልሔምን ግን በእርግጥም ሰርተዋታል ። አፈሩን ቆፍረውና አልመው ፣ አቡክተው ቤተልሔምን እንደ ውቡ ሸክላ አስጊጠው ሰርተዋታል ። እሷ እንደምትለውም ትንሿ ቤተልሔም " ከብዙ ልምምድ በኋላ የመጣ አልበም " ባለቤት እንትሆን አድርገዋታል ። ቤተልሔም ሸረፈዲን የተባለች ጥንቅቅ ፣ ጥፍጥ ያለ ስራ ያላት ድምጻዊትን ለዘመኑ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ( ? ) አበርክተዋል ። አሁን የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ቤተልሔም ሸረፈዲን የምትባል ብስል ፣ ትክን ያለች ድምጻዊት አለችለት ። ቤተልሔም ስለ አዲሱ አልበሟ ለኩራ ስትሪም ስትናገር " ይሄን አልበም እንደ መጀመሪያም ፣ እንደ መጨረሻም ስራ አድርጌ ነው የማየው ። " ብላለች ።
ናትናኤል ግርማቸው ገጣሚነት ተሰጥቶታል ። ገጣሚነቱ የቃላት ድርደራ ሳይሆን የሀሳብ ስፋት የታደለው ነው ። ናቲን በራሄል ጌቱ " ኢትዮጵያዬ " ነው ያወቅኩት ። የራሷን የራሄል ጌቱን " ያገሬ ሰው " ፣ በኋላም " ወረት " ን ሰርቶ አስደንቆኛል ። ናቲን በራሄል ጌቱ ( በስራዎቿ ) በኩል ነው ያገኘሁት ። ይህ ሰው ነው ደግሞ ከታምሩ አማረ ጋር ሆኖ ቤተልሔም ሸረፈዲንን ያገኛት ። ሁለቱ በፕሮዲዩሰርነት ባይከሰቱ ቤተልሔም ሸረፈዲን ቢያንስ በዚህ ጊዜ አትወለድም ። የጀርባ አቅሟን ባላውቅም የ10 ግጥም ፣ የ10 ዜማ ፣ የ10 ዜማዎች ቅንብር ፣ ሚክሲንግ እና ማስተሪንግ ክፍያን አትወጣውም ( ብዬ እገምታለሁ ) ። ከሁሉም በላይ ደግሞ ዘላለም ኩራባቸውን አታገኘውም ። ዘላለም ኩራባቸው ወደ ሙዚቃ ማምረት ስራ ሲገባ ከገንዘብ የነፍስ ጥሪ ትርፉን አስቦ እንደሚሆን አምናለሁ ። ካሁን ቀደም በተናጠል ሲያደርግ የነበረውን ሙያውንና ሙያተኛውን እንደ ታላቅ ወንድም አጋር የመሆን ዝንባሌውን ተቋማዊ ቅርጽ ሰጥቶት መምጣቱ ይመስለኛል ። ቤተልሔም እድለኛ ናት ። እነ ንዋይ ደበበ ፣ ሀመልማል አባተ ፣ ጸሐዬ ዮሀንስ እና ዘመንኞቻቸው በመጡበት መንገድ ነው የመጣችው ። ሌላም እድለኛነት ( ከችሎታ ጋር ) አላት ።እነ ጠረፍ ካሳሁን ፣ ራሄል ጌቱ ፣ ለምለም ኃ/ሚካኤል ፣ ዘቢባ ግርማ ተሰርተው የወጡበት " የኛ " ፕሮጀክት ፣ የእነ አይዳ አሸናፊ እጅም አርፎባታል ።
ከአስሩ የ " ደስተኛ " አልበም ስራዎች በተሸከመው ሀሳብ ( ለእኔ ) " ባለቤቴ " ን የሚያህልልኝ አላገኘሁም ። ለዚህ ዘፈን ከ " ባለቤቴ " ይልቅ " አትክልተኛው " ስምም ሆኖልኛል ። ምናልባት ግን " አትክልተኛው " ለዘፈን ርዕስነት ያንስ ( አይሆን ) እንደሆን አላውቅም ። ሙሉ ዘፈኑን ስንሰማው ገጸባሕሪዋ በምናቧ ከዋለለችለት የምናብ ባለቤቷ ይልቅ የሰው ያልሆነ ፣ ለሰው አዕምሮ " ሞኝ " የሚባል ፣ ለፍጽምና የቀረበ በዝናብም ፣ በጸሐይም ስራውን የማያስተጓጉል ፣ ብርሀን መርጦ የማይመጣ ፣ በጭለማ የማይሸሸግ ፣ የማግኘትም ፣ የማጣትም ጊዜ ወዳጅ ፣ እንደ አምላክ ያለ ብርቱ ሰው ነው ። ባለቤትነቱ ህልም ሲሆን ብርቱ አትክልተኝነቱ ግን እውን ነው ። ይህ ሰው ትትርናውና ቸርነቱ እንደ አምላክ ያለ ነው ። ከማንም ፣ ከምንም የማይጠብቅ ። መስጠት ብቻ የሆነ ። በአበቦቹ መሐል ብቻ አይደለም ያለው ። ልብ ባለበት ሁሉ ነው ።
" በዝናብ አካሉም በዶፉ እየረሰረሰ
የአትክልቶቹን ስር ሲያጠጣ የልምዱን ውሀ እያፈሰሰ
አሉት የማን ነው ጅል ያን አትክልተኛ
ሳቁበት እንደሞኝ ወይኔ
አላወቁም የእሱ ዝናብ መጣ ቀረ
ንፍገትን ለልቡ እንዳላስተማረ ።
*************************
አሰብኩት ከሆነ እንዲህ ለአትክልቱ
እንዴት መልካም ይሆን ለሚወዳት ሚስቱ "
ያለችውን ብርቱና ቸር ሰው ነው . . .
" ቢዘንብም ቢያካፋም ከጎኔ የማይጠፋ
እንደ ባለ አጸዱ ጽኑ ለመውደዱ
ሳላውቅህ ልንገርህ የነገ ውሀ አጣጬ
አርገኝ እንዳልከስም ፍቅርን ተጠምቼ "
እያለች ምኞቷን ፣ መሻቷን ፣ የወደፊት ህልሟን ትነግረናለች ። መልካምነት መስጠት ብቻ ሳይሆን መቀበልንም ይፈልጋል ። ምርጥ ዘር ምርጥ አፈርንም ይፈልጋል ። በተዘራበት ሁሉ አይበቅልም ። እንደ እሷ የሚረዳ ካልተገኘ ሌሎቹ እንዳሉት " የማነው ሞኝ ? " ያስብላል ።
በርዕሰ ጉዳይ ደረጃ የዚህ የወደድኩት ብርቱ አትክልተኛ ተቃራኒ ቢሆንም የእኔ ከ1ኛ - 3ኛ " ቻው ( ዎ ) " ነው ።
" አልነበረም ከዓይን የተሰወረ
መንገድህን ሳላየው መች ቀረ
ሰነባብቷል መንፈስህ ሸፍቷል
ልቤን ልብህ ቻው ካለው ቆይቷል ።
አልታወጀም እንጂ ፊትም የእኛ ነገር
የተለያየነው አብረን ሆነን ነበር ።
እንባዬ ተማጽኖህ እንዳያስታርቀን
ያለቀው ያኔ ነው ልብህ የሄደ ቀን ።
እያንዳንዱን ቀናት በእንባ እየሰፈርኩኝ
ቻው ስልህ ኖሬያለሁ እየሸራረፍኩኝ ።
ዛሬም ለበደልህ አረከኝ ጣል ጣል
ቻው ማለት ብቻ ነው የቀረኝ አንድ ቃል ። "
ይኽ መቸም በየፍቅር ጎጆው ፣ በየትዳር ማጀቱ ፣ በየጓደኝነቱና ወዳጅነቱ አደባባይ የሚታይ የወቅቱ እውነታ ነው ። በየግንኙነታችን " ቻው ማለት ብቻ ነው የቀረኝ አንድ ቃል " ። አብዛኛዎቻችን አንድ ላይ ቆመናል እንጂ አብረን አይደለንም ። " አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል " እንዳለው ድምጻዊው ። እግሮቻችን ብቻ አብረው ይጓዛሉ ፤ አካላችን አንድ ላይ ይታያል ፤ ነፍስ የሌለው ስጋ ነው ። አብረን ውለን እናድራለን ፤ በልባችን ግን ተለያይተናል ። አልታወቀን ይሆናል እንጂ እንደ ግልም ፣ እንደ ሀገርም እንዲህ ሆነናል ። ለዚህ ነው አሁን ያለንበት ላይ ያለነው ። ለዚህ ነው በየሰበቡ ሕይወት የሚታክተን ። ለዚህ ነው መኖር ትግል ፣ አብሮነት መተናነቅ የሚሆንብን ( የሆነብን ) ። የቤተልሔም ሸረፈዲን " ቻው " ለአንድ ተፈቃሪ ወንድ የተሰራም ቢሆን ሀሳቡ ግን እዚህ ድረስም የሚመጣ ነው ። ናቲ " ቃሉ ከዜማው ጋር ነው የመጣው " ያለውና ራሷን ድምጻዊቷን አስለቅሶ የተገለጠው " ቻው " ገና ብዙውን ልብ የሚነካ ስራ ይሆናል ።
" ልቤን " ን ላልወደው አስቤ ነበረ መሰለኝ ። የእድሜም ፣ የፍላጎትም ጉዳይ ሆኖ ፈጠን ላሉ ምቶች አልደነግጥ ሆኖ ይሆናል እንጂ ምን ሆኜ ነው ዜማው ፣ ምቱ ፣ በተለይ የድምጻዊቷ አዘፋፈን ከፍ ብሎ የታየበትን ይህን ስራ " ይቆየኝ " ያልኩት ? ባልወደውና ደጋግሜ ባልሰማው ይቆጨኝ ነበር ። ( ለነገሩ ካልወደድኩት ለምን ይቆጨኛል ? ) " ደስተኛ " ርዕስና ሀሳቡ ደስተኛ ካልሆነች ፣ " አልወድሽም " ከተባለችና ከተገፋች ገጸባህሪ የተገኘ ነው ። " ቢከፋም ፣ ቢለማም ባለኝ ደስተኛ ነኝ " ትላለች ። " አልወድሽም " ተብላና " ብትጎዘጉዝ አበባ ዛሬ አይረባ " ያለች ሴት ራሷን ማታለል ሳይሆን " ቢከፋም ፣ ቢለማም ባለኝ ደስተኛ ነኝ " ስትል ካዋጣትና ከተቻላት ያድርግላት ። ከእሷ እንባና የልብ ስብራት ምን ጉዳይ አለን ? ብቻ ከአፏ ሳይሆን ከልቧ ይሁን ።
" እንደ ውሀ መውረድ ፣ እንደ ጸሐይ መውጣት
እንደ ጊዜው መክነፍ ፣ እንደ አሸዋ መብዛት
እውነታ መሆኑን ቅንጣት ሳልጠረጥር
እኔስ አምነዋለሁ የልብህን ፍቅር "
ያለችበት " አካልዬ " ለረጋ ያለ ሙዚቃ አፍቃሪ ይሁነኝ ተብሎ የተቀመረ ስራ ነው ። በምርጤነት ከተቀበልኳቸው መካከል አንዱ ነው ።
አንደኛው ሙዚቃ አስተያየት መስጫ ውስጥ ገብቼ ሳነብ " የዚህ አልበም ትልቁ ችግሩ ውስጡ ያሉት ዘፈኖች 10 ብቻ መሆናቸው ነው " ሲል " አድናቆቱን " ገልጿል ። እኔም እንደዚያ ሆኖ ይሰማኛል ። ከአስሩ ሰባቱን ስራዎች በልዩ ሁኔታ ወድጃቸዋለሁ ። አንዱ የዋለልኩበትና ሁለቱ ደግሞ ልብ ያልሰጠኋቸው ናቸው ። ይህ በአንድ አለበም ውስጥ ከበቂ በላይ ስኬታማነት ነው ። ከብዙ ዓመት በኋላ ተሟልቶ ያገኙሁት ምርጤ ነው " ደስተኛ " አልበም ።
እዚህ አልበም ላይ ያለኝ አንድ ( ግላዊ ) ቅሬታ አስሩም ስራዎች የተቃራኒ ጾታ ፍቅር ላይ ብቻ ያተኮሩ መሆናቸው ነው ። እንዳይሆኑ የሚከለክል ደንብ የለም ። ፕሮዲዩሰሮቹ የቤተልሔምን እድሜና የፍቅር ጊዜዋን አስበው ያደረጉት ሊሆን ይችላል ። ያም ቢሆን በዚህ ውጥንቅጡ የወጣ የመከራ ጊዜ ፣ በብዙ ሰው ሰራሽና የአስተሳሰብ ሰንሰለት እግር ከወርች ታስረን መሔጃ ባጣንበት ዘመንና ሀገር ፣ ላለንበት ጊዜ ፣ ለስሜታችን ፣ ለህመማችን ፣ ለሰለለው ተስፋችን የሚሆን አንድ ስራ ልናጣ አይገባም ብዬ አስባለሁ ። ናቲና ምህረተአብ ለራሄል ጌቱ እንደሰጧት " ያገሬ ሰው " ያለ ስራ ቢመርቁልን እንዴት መልካም ነበረ ?
ከቀናት በፊት አስቴር አወቀ ( በድጋሚ ስራዎቿም ቢሆን ) በትንሿ ቤተልሔም ሸረፈዲን ላይ ተደርባ አልበሟን መልቀቋ አስፈርቶኝ ነበረ ። ይህን የመሰለ አልበም ፣ የ4 ዓመት የሚነገርና የማይነገር እልህ አስጨራሽ ድካም መና እንዳይቀር ሰግቼ ነበረ ። ስጋቴ ስጋት ብቻ ሆኖ ቀርቷል ። ቤተልሔም የዋርካው ጥላ ሳያርፍባት አልፋለች ። ገና ገና ትቀጥላለች ፤ ትቀጣጠላለች ።

4 months ago
የሰው ፂም የሚመስል የተፈጥሮ ፀጉር ያላት ድመት በኢንተርኔት ዓለም መነጋገሪያ ሆነች!
ምንም ዓይነት ሰው ሰራሽ ቅብ፣ የፀጉር ማስተካከል ወይም የፎቶ ማጭበርበር ሳይደረግባት፣ በትክክል የሰውን ወፍራም ጥቁር ፂም የሚመስል የተፈጥሮ ፀጉር ይዛ የተወለደች ድመት በመላው ዓለም በሚገኙ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ መደነቅን ፈጥራለች። ይህ በድመቷ አገጭ ላይ የሚታየው "ፂም" ሙሉ በሙሉ ተፈጥሯዊ ሲሆን፣ ድመቷ እያደገች ስትሄድ በጄኔቲክስ ምክንያት የተፈጠረ ልዩ የቆዳ ቀለም መዋቅር ውጤት ነው።
ድመቶች በጄኔቲክስ ስብጥር ምክንያት እንደ ፂም፣ ቅንድብ፣ ልብ ቅርጽ፣ ጭምብል እና የሰውን የፊት ገጽታ የሚመስሉ አስደናቂ የተፈጥሮ ምልክቶችን በፀጉራቸው ላይ ይዘው ሊወለዱ ይችላሉ። የዚህች ድመት ፂም ግን እጅግ ማራኪ እና የተለየ ያደረገው፣ ልክ እንደ ሰው ልጅ ፂም ግራና ቀኙ እኩል ተስተካክሎ እና በትክክል መሆን ባለበት ቦታ ላይ ተፈጥሮ ያቀለመችው በመሆኑ ነው።
የዚህ ዓይነቱ ድመት ፎቶዎች በኢንተርኔት ላይ በፍጥነት ታዋቂ የሚሆኑት ፓሬዶሊያ (Pareidolia) በሚባለው የስነ-ልቦናዊ ክስተት ምክንያት ነው። የሰው ልጅ አእምሮ በማንኛውም ነገር ላይ የሰውን መልክ ወይም የታወቁ ቅርጾችን ፈጥኖ የመለየት ተፈጥሯዊ ዝንባሌ ስላለው፣ ድመቷን ስንመለከት አእምሯችን ወዲያውኑ ከሰው ፂም ጋር በማገናኘት ነገሩን እጅግ አስቂኝ እና የማይረሳ ያደርገዋል።
Seledadotio

"እውነተኛ ማንነቴን ይዤ ለመኖር ስል፣ ባለፉት ዓመታት ውስጥ ከብዙ ሰዎች ጋር መጋፈጥ ግድ ብሎኝ ነበር። እኔ እንደማምነው፣ እያንዳንዱ ሰው የራሱን እውነተኛ ማንነት ይዞ እንዲኖር እና ልቡ የፈቀደውን እንዲያፈቅር ሙሉ ነፃነት ሊሰጠው ይገባል።" ድምጻዊት ዶሊ ፓርተን
10 months ago
ህንድ እና ህንዳውያን:- የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጆች!!
በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን)
"... የጥንታዊት ታሪክና ገናና ሥልጣኔ ባለቤት፤ የአፍሪካና የጥቁር ሕዝብ ታላቅ የነጻነት ተጋድሎ ምልክት ከሆነች አገር- ኢትዮጵያ ይሄ የክብር ኒሻን ስለተበረከተልኝ ደስታዬ እጥፍ ድርብ ነው፤ በ1.4 ቢሊዮን በሚሆነው የአገሬ የህንድ ሕዝብ ስም ምስጋናዬን ለመግለጽ እወዳለሁኝ...፤"
በአገራችን ኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የህንዱ ጠቅላይ ሚ/ር ናኔድራ ሞዲ- በጠቅላይ ሚ/ር ዐብይ አሕመድ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ኒሻን በተበረከተላቸው ጊዜ ከላይ በመግቢያዬ ላይ ከጠቀስኩት ንግግራቸው ባሻገር በንግግራቸው - ህንድና ህንዳውያን አገራችን ኢትዮጵያ በፋስሽት በተወረረች ወቅት ከጎናችን መቆማቸውን ታሪክ አጣቅስው ተናግረዋል።
ህንድ እና ህንዳውያን:- የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ወዳጆች!!
የቅኝ ገዥዎችን ቅስም ካነካከተውና መላው አውሮፓንና ነጮችን በድንጋጤ እጃቸውን በአፋቸው ላይ እንዲጭኑ ያደረጋቸውን፤ አንፀባራቂውን የዐድዋውን ድል- ለመበቀል ፋሽስት ኢጣልያ ከ40 ዓመታት ዝግጅት በኋላ በአየርና በምድር የጦር መሳሪያ እስከ አፍንጫው ታጥቆና እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሕግ የተከለከለ የመርዝ ቦምብ ሳይቀር ተሽክሞ ነበር የመጣው።
"... ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያን በዓለም ፊት የሚኮሩበት ነጻነታችውና ሉዓላዊነታቸው በቅኝ ግዛት ቀምበር ስር እንዲወድቅና ኢትዮጵያውያን ዳግመኛ አንገታቸውን ቀና አድርገው እንዳይሄዱ ለአፍሪካና ለመላው ጥቁር ሕዝብ መቀጣጫ ሊሆኑ ይገባል!!" በሚል እብሪትና ትእቢት ፋስሽቱ ቤኒቶ ሞሶሎኒ የበቀልና የጭካኔ ሰይፉን በኢትዮጵያውያን ላይ መዘዘብን።
በዛ የመከራና የጭንቅ ዘመን ህንድና ህንዳውያን ከኢትዮጵያ ጋር ቆመዋል፤ በዓለም መድረክ ድምፅ ሆነውናል። ታሪክን ምስክር እናድርግ፤ በወቅቱ የህንድ ጠቅላይ ሚ/ር የነበሩት ጃኋራል ኔህሩ በህንድ ፓርላማ ባሰሙት ንግግራቸው እንዲህ ነበር ያሉት፤
"We in India can do nothing to help our brethren in distress in Ethiopia… But we can at least send them sympathy… in the hour of their trial. We stand with them today in their sorrow…" (quoted in Indian government records and MEA speeches).
"... ምንም እንኳን ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያውያን ለጊዜው ምንም ማድረግ ባንችልም- ለነጻነታቸው በሚያደርጉት ተጋድሎአቸው ከጎናቸው መሆናችን የሚገልጽ ልባዊ መልእክታችንን ልንልክላቸው እንወዳለን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ለኢትዮጵያውያን የፀረ-ፋሽስት እና የፀረ-ቅኝ ግዛት ተጋድሎ የጋራ ድምፅ እንሆናቸዋለን...፤"
ኢትዮጵያ እና ህንድ በቀደመው ዘመን
ጥንታዊት፤ የገናና ታሪክና የግዙፍ የሥልጣኔ ባለቤት የሆነችው አገራችን ኢትዮጵያ- እንደ አገራችን ሁሉ የሺህ ዘመናት ታሪክና የሥልጣኔ ባለቤት ከሆነችው ህንድ ጋር ለ2000 ሺህ ዓመታት በፊት በህንድ ውቅያኖስ እና በቀይ ባሕር አማካኝነት የአፍሪካን ድንበር የተሻገረ የንግድ ግንኙነት/Martime Trade እንደነበረን የታሪክ ድርሳናት የአርኪዮሎጂ ሳይንስ ግኝቶች ይመሰክራሉ።
ወጌን ፈር ለማስያዝ ይረዳኝ ዘንድ ከታሪክ ድርሳናት በጥቂቱ ላጣቅስ፤
Neville Chittick, የተባለ ምሁር፤ "Indian Relations with East Africa before the Arrival of the Portuguese" በሚል በጻፈው መጽሐፍ በህንድ በኩሻን ሥርወ-መንግሥት ዘመን መገበያያ የነበሩ የወርቅ ሳንቲሞች በአርኪዮሎጂ ጥናት በአክሱምና በደብረዳሞ መገኘታቸውን ተጽፏል። ይኸው ምሁር፤ የህንድ የጉፕታ ዘመነ መንግሥት አሻራ የሆኑ ቁሳቁሶች፤ የከበሩ ጌጣጌጦችና ጨሌዎች በጥንታዊቷ አክሱም ከተማና የኢትዮጵያ ወደብ በሆነችው አዶሊስ መገኘቱን አትቷል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ/በአክሱም ታሪክና ሥልጣኔ ላይ የተጻፉ በርካታ የታሪክ ድርሳናትና የጉዞ ማስታወሻዎች እንደሚጠቁሙት፤ አክሱማውያን የዝሆን ጥርስ፣ ወርቅ፣ ዕንቁ፣ ሃርና የከበሩ ማዕድናትን... ወዘተ. በቀይ ባሕርና በህንድ ውቅያኖስ አማካኝነት ከህንድና ከመካከለኛው ምሥራቅ አጋራት ጋር የንግድ ልውውጥ ያደርጉ ነበር።
የግሪክ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መነኩሴና ተጓዥ የነበሩት አባ ኮስሞስ ኢንዲክሎፕተስ፤ "the Periplus of Eritrean Sea" በሚል አርእስት ከ 1500 ዓመታት ገደማ በፊት በጻፉት የጉዞ ማስታወሻቸው፤
"... ኢትዮጵያውያን/አክሱማውያን በጥንት ዘመን በቀይ ባሕር በኩል- ከመካከለኛው ምሥራቅ፣ ከዐረቢያ፣ ከቻይና ከህንድ ጋር የጠበቀ የባሕር ላይ የንግድ ግንኙነት እንደነበርን፤" ጽፈዋል።
እንደ ማጠቃለያ፤
የህንድና የኢትዮጵያ ግንኙነት ሺሕ ዘመንን የተሻገረ ጠንካራ የታሪክና የሥልጣኔን እሤቶችን የሚጋራ ነው። በግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት የኢትዮጵያና የህንድ ዲፕሎማሲ ግንኙነት ጠንካራ መሠረትን ይዞ ተጀመረ። በደርግም ሆነ በዘመነ ኢሕአዴግ መንግሥታት ቢቀያየሩም የሁለቱ አገራት ግንኙነት ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።
ኢትዮጵያና ህንድ በትምህርት፣ በጤና፣ በግብርና፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ... ወዘተ. ረገድ የጠበቀ ትስስር አላቸው። በዓለም ዙሪያ በሰላም ማስከበር ዘመቻ ሁለቱ አገራት- ኢትዮጵያና ህንድ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ አገራት ናቸው። በብሪክስ አገራትና በደቡብ ደቡብ ትብብር መድረክ ህንድና ኢትዮጵያ የጎላ ሚናን እየተጫወቱ የሚገኙ ሀገራት ናቸው።
የዛሬውን ኢትዮጵያንና ህንድን የተመለከተውን ወጌን- በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስና የዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር/ፕሮፌሰር፤ በአንድ ወቅትም በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር ዶ/ር ትዝታ ሙሉጌታ አባባል ለመቋጨት ወደድኹ፤
"የኢትዮጵያና የህንድ ግንኙነት በማይናወጽ ጠንካራ የታሪክ መሠረትና የእርስበርስ ትብብር ላይ የቆመ ነው፤"
የኢትዮጵያና የህንድ ግንኙነት ይለምልም!!

የቀይ ባህር እንቁ አሥመራ ሽኮሪና
የአለማችን የመጀመርያዋ የቅርስ ከተማ!
( በታዴ የማመይ ልጅ )
#ethiopia | በእርግጥም በምስራቅ በፅሎትና ቤተ ጊዮርጊስ ፣ በምዕራብ በፀራራት ፣በሰሜን በአክሪያና ባዕታ አስመራ፣ በደቡብ አዲ ጓእዳ ኮረብታዎች ደጀን የሆኗት በፅዳቷ ፣ በእርጋታዋ ፣ እንደሚፈርጥ እንቁላል በጥንቃቄ በተደረደሩት እፁብ ህንፃዎቿ በተንዠረገጉት ዘንባባዎቿ፣ የአፍሪካ ዘመናዊ ከተማ ፣የቀይ ባህር እንቁ ትመስላለች ።
በዛሬዉ የአፍታ ቱሪዝም ጉብኝታችን ባለፉት ሦስት አስርት አመታት ክፉ ክፉዉን አግዝፈው የሚነግሩን ቤኒቶ ሙሶሊኒም “ፒኮላ ሮማ” ወይም “ትንሿ ሮም” ሲል ያሞካሻት የኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ ገብተናል ።
በቆይታችን ደግነትና ባህል አክባሪነት መገለጫው ሰዉን ያለልዩነት የሚወደው ቸርነት ከባህሪዉ የሆነው የአስመራ ህዝብ አለና ወደኋላም ከመነሻዋ ወደፊትም ከገፅታዋ መለስ ቀለስ እያልን በጎዳናዎቿ ሸር ብትን እንላለንና አብራችሁን ዝለቁ ።
ጥንት ከሁለት ሺህ ዓመት በላይ ታሪክ ያለዉ አዶሊስ በዝያን ጊዜ ከነበሩ ከታወቁ የተለያዩ ሃገሮች ጋር ትልቅ የንግድ ግንኙነት የነበረዉ፤ አዶላዉያን በዝያን ጊዜ እስከ ሕንድ አልፈዉ እስከ ቻይና ግንኙነት ያደርጉባት የነበረዉ የወደብ ከተማ ናት የሰሜን ፈርጧ አስመራ።
በአሥመራ በሠምበል አካባቢ የተገኘው የአርኪዮሎጂ ማስረጃ ከተማዋ ስያሜ በ 800 ዓ.ዓ. ይወስደናል ።
የኦና ባህል ተብሎ የሚጠራውን የአሥመራ ታሪክ በ 800 ዓ.ዓ. እና በኤርትራ ትግሪኛ ቃል ባሕላዊ ታሪክ መሠረት፣ በቀበሳ አምባ ላይ በአስመራ አካባቢ አራት ጎሳዎች ይኖሩ ነበር።
በዘመኑ ተበታትነው የነበሩት ገዛ ጉርቶም። ገዛ ሽሌሌ፣ ገዛ ሴሬንሰር እና ገዛ አስመኤ የተባሉ ግዛቶች ጎሳዎች በአንድነት በመሆን ከተማ በመመስረት "አርባተ አስመራ" የሚል ስም ሰጧት ይባላል ይህም አርባተ አስመራ ማለት በትግርኛ ቋንቋ 'አራቱ ጎሳዎች' ማለት ነው።
ከባህር ጠለል በላይ ከ2,300 ሜትር በላይ ከፍታ ላይ የምትገኝ ሲሆን ከአካባቢው ዝቅተኛ ቦታዎች ሙቀት ጋር የሚቃረን መለስተኛ የአየር ንብረት ያላት አስመራ ግብፆች፤ ቱርኮች፤ጣልያኖች እንጊሊዞች ተዋግተዉባታል። ከተማዋን የጎዳ ማንም ኃይል ግን አልነበረም ወዘናዋ ዛሬም በእርጋታ ተዉቦ ይገኛል ።
ከተማዋና ዙርያዋ ታሪክ ከ 2000 ዓመት ወደኋላ ይወስደናል 2000 አመታት በላይ ስልጣኔ የነበረዉ ታሪካዉ" መጠራ በለዉ ከለዉ" የተባለ በአፍሪቃዉ ቀንድ ላይ ለሚገኙ ሁለቱም ሃገሮች የሥነ-ጽሑፍ የተከሰተበት ታሪካዊ ቦታ ሲሆን በሃዉልቱ ላይ አናባቢ የሌለዉ የግዕዝ ጽሑፍ ሰፍሮ ይገኛል ።
ሰፊ ከተማ የነበረችዉ 17 ኪሎሜትር ስፋት የነበራት ቆሃይቶ እስከ ትልቅ የአፍሪቃ ከተማ ያደርጋታል። ከዚህም ባሻገር በአፍሪቃ እስልምናን ከተቀበሉት አካባቢዎች የመጀመርያዉ የሆነው ዳህላክኬሪስ
ጥንታዊ መቃብሮች ጥንታዊ የዉኃ ማጠራቀምያ ገንዳዎች መገልገያዎች አስመራና ዙርያዋ የረጂም ታሪክ እንዳላት ህያው እማኝ ይሆናሉ ።
ይሁንና የዛሬውን ገፅታ የያዘችው በጎርጎረሳዉያኑ 1930ዎቹ በቅኝ ግዛት ኤርትራን የያዘዉ ኢጣልያዊዉ ፋሺስት ሞሶሎኒ በምስራቅ አፍሪቃ ለሚያካሂደዉ የቅኝ ግዛት ዘመቻ ማዕከል እና መነሻ እንድትሆነዉ ዓይኑን ከጣለባት በኋላ ነበር ።
የጣልያንን መምጣት ተከትሎም አስመራ የምትባለዉ ትንሽ መንደር ሞቅ ደምቅ ማለት ጀመረች ። በአፍሪካ የመጀመሪያው የቴሌቪዥን ስርጭት ፣ የመጀመሪያው Am FM አጭር መካከለኛ ረጂም ሞገድ ራዲዮ ፣
የኤርትራ የባቡር መስመር በጊንዳ ከተማ በኩል በካርሎ ካቫና መሪነት ወደ ምጽዋ የባህር ዳርቻ የሚያመራ ሀዲድ ፣ ሲኒማ
ፋብሪካዎች በብዛት ተገንብተው በአፍሪካ ምድር ላይ የአውሮፓ ዘመናዊነት እውነተኛ ማሳያ ያደርጋታል ።
ሲኒማ ኢምፔሮ፣ የፊያት ታግሊየሮ አገልግሎት ጣቢያ እና የቅዱስ ጆሴፍ ካቴድራል ያሉ ታዋቂ ሕንፃዎች ለዚህ የፈጠራ ኃይል ምስክር ናቸው። ፊያት ታግሊየሮ፣ እንደ አውሮፕላን ለመነሳት ዝግጁ የሆነ አውሮፕላን ቅርጽ ያላቸው የተጠናከረ የኮንክሪት ክንፎቹ ያሉት፣ የዘመኑን የቴክኖሎጂ፣ የእድገት እና የፍጥነት ውበት ያለውን ማራኪነት መገለጫዎች ናቸው ።
ጋዜጠኛ ጆን ጉንተር እ.ኤ.አ. በ 1955 እንደገለጸው "ጣሊያኖች [አስመራን] እንደ ትሪፖሊ በጥሩ ሁኔታ እንደገነቧት ጽፏል።
በሚያማምሩ ሰፊ ጎዳናዎች ፣ ያጌጡ የህዝብ መገልገያ ሕንፃዎች እና የሥልጣኔ ምልክት የሆነው በከተማዋ የተገነባው ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት ... የጣልያኖች የስራ ውጤት መሆኑን ጽፏል።
የኢጣሊያ መንግሥት በአስመራ እና በአስመራ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በኢንዱስትሪ ልማት ላይ ኢንቨስት አድርጓል ።
ከሥነ ሕንፃዋ ባሻገር፣የጂኦሜትሪክ ዲሲፕሊን እና የሜዲትራኒያን ጸጋ ድብልቅ አሰራሯ አስመራን ልዩ ውበት ይሰጣታል ።
አስመራ ሙሉ በሙሉ በዘመናዊነት ሀሳብ ዙሪያ ለተቀረፀ የከተማ ፕላን ትታወቃለች፤ ሰፊ አውራ ጎዳናዎች፣ ሥርዓታማ ሰፈሮች፣ ለጋስ የሕዝብ ቦታዎች እና ቀልጣፋ መሠረተ ልማቶች የጣልያኖች የስራ ዉጤት የተመለከተው ፋሽስት ሞሶሎኒም በዝያን ጊዜ አስመራን አፍሪቃዊትዋ ትንሽዋ የሮም ከተማ ሲል አንቆለጳጽሷታል።
ሲኒማ ቤቶቹ ራሳቸዉ ድንቅ ናቸዉ ሲኒማ ኤንፔሮ፤ ሲኒማ ዳንቴ፤ ሲኒማ ካፒቶል፤ ሲኒማ ሮማ፤ ሲኒማ ኦዲዎን የሚባሉ ሲኒማ ቤቶች አሉ።ሁሉም ሲኒማ ቤቶች የተሰሩት በአዉሮጳ ደረጃ ነዉ። ሌሎቹ ሕንጻዎች ቡናማ ሰማያዊ አረንጓዴ ቀለም ያላቸዉ ሲሆኑ የአስመራ ቅድስተ ማርያም ቤተ ክርስትያን ዉብ ቪላ ቤቶች ፤ ፋብሪካዎች አስመራ የሚገኘዉ ትልቁ መስጊድ የመሳሰሉት ሁሉ የሚያማልሉ ናቸዉ።
ከተማዋ እድለኛ ከተማም ናት 30 እና 40 ዓመት ጦርነት ተካሂዶ ከተማዋ ምንም አልተጎዳችም ከተማዋን የጎዳ ኃይል የለም። በመጀመርያ ከተማ አስመራን በኦቶማን ኤምፓየር በሚባለዉ ዘመን ቱርኩች ያዙ፤ ከዝያ በኋላ ግብጾች ያዙ ከዝያ በኋላ ጣልያኖች ያዙ ከዝያ በኋላ እንጊሊዞች ያዙ። ይህ ሁሉ ትርምስ ሲካሄድ ግን ከተማዋ አልተጎዳችም ።
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ድርጅት አስመራ የዓለም ቅርስ ሆና እንድትመዘገብ በፖላንድ ዋርሶ ባካሔደው ጉባዔ ላይ የአለማችን የመጀመርያዋ የቅርስ ከተማ ክብር መዝገብ አስፍሯታል ።
በአስመራ የሚገኙትና ቅኝ ግዛቱ ዘመን የተሰሩት ከ 50 በላይ ሕንፃዎች በሙሉ በዓለሙ መንግሥታት የቅርስ መዝገብ በመስፈራቸዉ ኤርትራ ጥንታዊና የባህል ቅሪቶች በሙሉ የተመዘገበላት ቀዳሚዋ የዓለም ሀገር ያደርጋታል ።
UNESCO ስለ ከተማዋ ሲገልፅ
«አስመራ በጣም ዉብ የሆነች ከተማ ናት። ከሁሉ ደግሞ ሕዝብዋ በዉስጥዋ እየኖረ ባህሉን እየጠበቀ ሥነ ሕንጻዉን እየጠበቀ በመሆኑ ነዉ። የአስመራ ሕንጻዎች ለየት ያለ ንድፍና ቅርስ የያዙ ናቸዉ። ጣልያኖቹ በቅኝ ግዛት ወቅት ሃገራቸዉ ዉስጥ የሌለ ነጻነት አስመራ ዉስጥ፤ ቅኝ ሃገር ዉስጥ ነጻነት ተሰምቶአቸዉ ፤ በምህንድስናዉ ረገድ አብዮት ያካሄዱ ይመስላል። ምክንያቱም ኢጣልያ ዉስጥ የማይገኘዉ ሕንጻ አስመራ ዉስጥ አለ።» ሲል ገልጿል ።
አስመራ ከተማ በኪነ ሕንጻ ብቻ ሳይሆን በጽዳትዋ ፤ በአየር ፀባይዋና በተለያዩ ሁኔታዎች ከአፍሪቃ የታወቁ ከተማ በመሆንዋ አስመራ በዓለሙ የቅርስ መዝገብ መመዝገብዋ ለኛ ለኢትዮጵያዉያን ለዓለም ሕዝብ ሁሉ ኩራት ነዉ ሲሉ የወቅቱ የበኢትዮጵያ ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ገልጿል ።
አስመራ ሕያው ሙዚየም እና ሕያው የስልጣኔ ከተማ የአፍሪካን ዘመናዊነት ማሳያ የተረጋጋች እጅግ ማራኪ ብትሆንም ከተማዋ ከቱሪዝም ዘርፉ ተጠቃሚ አልሆነችም።
ሜሳረጊያዉን የባለቅኔዉን የሎሬት ፀጋዬ ገ/መድህን ግጥም እንገባበዝና ለዛሬው ይብቃን ።
አስመራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ
ያውራ ጎዳናሽ ጠለላ ፡
ሁሉን በአክናፉ እየጠራ
አስር ሰዓት ላይ ሲደራ
ለመንገደኛሽ መዝናኛ ፣ሲያጠላ ሲያብብ ሲያፈራ
ምነው ሁሉ እንዳንቺ አስመራ
አደባባይ ሲያነጥፉ
አድባራትና መስኪዱን ፣ ካቴድራሉን በየረድፉ
ገበያውን በየመልኩ ፣ እንደ አውታር እያሰለፉ
በወግ እየደረደሩ ፣በስምረት እያሰመሩ
በውበት እያዳበሩ ፣እያሳመሩ ቢያደሩ
በየክፍሉ በየበሩ በየመልኩ በየተራ
ፋኖሱን እንደ ደመራ
ቡና ቤቱን እንደ ሦራ
ምነው ሁሉ እንደ አንቺ አስመራ
እንደ ከተሞች መዲና አቀያየሱ ቢጠራ፡፡
እሳት ወይ አበባ (ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን )

11 months ago
«ድል አባቷ ብዙ ነው" - ጆኔፍ ኬኔዲ
🌎 እኔም ሀገር አለኝ የሚታይ በሩቁ ...
የጉዞ ማስታወሻ ✈️
#ethiopia | በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሥፍራ ቆሚያለሁ።
የቀድሞው ዝነኛና ተወዳጁ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በቴክሳስ ግዛት፣ ዳላስ ከተማ፣ በክፍት መኪና፤ በጉብኝት ሳሉ ነበር እኤአ በኅዳር 22፣ 1963 ቀትር ላይ በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት። ፕሬዚደንት ኬኔዲ ስልጣን ላይ ከወጡ ሦስተኛ ዓመታቸን ሊይዙ ትንሽ ወራት ይቀራቸው ነበር።
ከዚያች ቅጽበት ጀምሮ ሰውየውን ( ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ ) ማን ገደላቸው? ... ለምን ተገደሉ? ... በሚለው ዙርያ ሺህ ምርመራዎች ተደርገዋል።
እነዚህ የምርመራ ሂደቱን የያዙ ዶሴዎችም በምሥጢር ሲከማቹ ነው የኖሩት።
የ1964 የእውነት አፈላላጊው ‘ዋረን ኮሚሽን’ ፕሬዝዳንት ኬኔዲ የተገደሉት ሊ ሐርቬይ ኦስዋልድ በተባለ ግለሰብ ነው ብሎ ነበር።
ሊ ሐርቬይ ቀደም ሲል በሶቭየት ኅብረት ለአጭር ጊዜ የኖረ አሜሪካዊ ሲሆን ድርጊቱን የፈጸመውም በግሉ ነው ተብሎ ነበር።
በቁጥጥር ሥር በዋለ በሁለተኛው ቀን ግን ብዙም ግልጽ ባልሆነ መንገድ በዳላስ ፖሊስ ምድር ቤት ውስጥ ተገድሏል።
ይሁንና የኬኔዲ አገዳደል፣ ገዳያቸው ነበር የተባለው ሰው በፖሊስ ምድር ቤት መገደል ምሥጢርና ተያያዥ ጉዳዮች ለዐሥርታት ለብዙ መላምቶች ክፍት ሆኖ ቆይቷል።
የሴራ ፖለቲካ ተንታኞች ደግሞ ግድያውንና ግድያውን ተከትሎ የሆነውን ነገር ሁሉ የተለያዩ ትርጉም ሲሰጡት ኖረዋል። ዛሬም ድረስ ...
አንዳንዶች ወጣቱን ፕሬዝዳንት ኬኔዲን የገደላቸው ሴአይኤ ራሱ ነው፤ ለዚያም ነው ገዳያቸው ነው የተባለውን ሰው ፈጥነው የገደሉት ብለው ያምናሉ።
ሲአይኤ ግን "የኔ እጅ የለበትም!" ይላል።
ገዳያቸው ነው የተባለው ኦስዋልድ በሜክሲኮ አገር ከኬጂቢ ሰላይ ጋር ተገናኝቶ እንደነበር ወደ በኋላ የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
የመጀመርያው የሮማን ካቶሊክ እምነት ተከታይ ፕሬዝዳንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ በጊዜያቸው ገናና የነበሩ 35ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከመሆናቸውም ባሻገር በንግግር አዋቂነታቸው ይደነቃሉ።
ከንግግራቸው አንዳንዶቹ ዛሬም ድረስ እንደ ጥቅስ ይወሳሉ፤ ከነዚህም መሀል ‘አገሬ ለኔ ምን አደረገችልኝ ሳይሆን እኔ ለአገሬ ምን አደረኩላት ብለን እንጠይቅ’ የሚለው የበዓለ ሲመት ንግግራቸው በይበልጥ ይታወሳል።
***
እንደምታውቁት የፕሬዝዳንት ኬኔዲን ግድያ የተመለከተ የምርመራ ዶሴ ከ60 ዓመት በኋላ ይፋ ሆኗል።
ይህ ዶሴ ለሕዝብ ይፋ እየሆነ ያለው ከ60 ዓመታት ጥብቅ ምሥጢርነት በኋላ ነው።
ብዛቱ ከ10ሺህ በላይ ይሆናል የተባለው ይህ ሰነድ ይፋ እንዲሆን የወሰኑት ፕሬዝደንት ጆ ባይደን ናቸው።
ይሁንና አንዳንድ ሰነዶች አሁንም በምሥጢር የሚቆዩ ይኖራሉ። ይህም ለአንዳንድ ሰዎች ደኀንነት ሲባል ነው።
ምንም እንኳ የጆን ኤፍ ኬኔዲ ግድያ ለዐሥርታት እያወዛገበ ቢቆይም በዚህ ሰነድ የሚገለጥ አንዳች ታላቅ ምሥጢር ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም።
ይሁንና ዶሴው በፕሬዝዳንቱ ግድያ ዙርያ ጥናትና ምርምር ለሚያደርጉ ግን ልዩ ዕድል ነው ተብሏል።
የ1992 የአሜሪካ ሕግ ዶሴዎቹ በጥቅምት 2017 ለሕዝብ ይፋ እንዲደረጉ አስገዳጅ አድርጎ ነበር።
የአሜሪካ ብሔራዊ ቤተ መዛግብት ለሕዝብ ይፋ የማይደረጉት ሰነዶች ብዛት 515 ነው ብሏል።
ከጠቅላላው ሰነድ 2ሺህ 545 ሰነዶች ደግሞ ይፋ የሚሆኑት በከፊል ናቸው።
***
ታሪክን የኋሊት
ፕሬዚደንት ጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ከኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር ጥሩ ግንኙነት ነበራቸዉ። በተለይ ጆን ኤፍ ኬኔዲ ከመገደላቸዉ ከአንድ ወር ቀደም ብሎ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ አሜሪካንን መጎብኘታቸዉ ይነገራል።
ኢትዮጵያ በጆን ኤፍ ኬኔዲ፤ ዘመነ ሥልጣን ከዩኤስ አሜሪካ ጋር ጥሩ የወዳጅ ነት ግንኙነት እንደነበራት ቢታወቅም ጆኔፍ ኬኔዲ በተለይ ከኢትዮጵያዉ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ጋር የጠበቀ ግንኙነት እንደነበራቸዉ ዘገባዎች ያመላክታሉ።
በደቡብ ቴክሳስ ዳላስ ከተማ፤ በተተኮሰባቸው ጥይት የተገደሉት ፕሬዚደንት ኬኔዲ ሥፍራ ቆሚያለሁ።
«ድል አባቷ ብዙ ነው" እንዲል ጆኔፍ ኬኔዲ ብዙ የታሪክ ምዕራፍ ለመሰነቅ ወደ ሙዚየሙ ገባሁ።
The joy and excitement of John Fitzgerald Kennedy's life belonged to all men.
So did the pain and sorrow of his death.
When he died on November 22, 1963, shock and agony touched human conscience throughout the world. In Dallas, Texas, there was a special sorrow.
The young President died in Dallas. The death bullets were fired 200 yards west of this site.
by Philip Johnson, This memorial, designed by was erected by the people by the people of Dallas. Thousands of citizens contributed support, money and effort.
It is not a memorial to the pain and sorrow of death, but stands as a permanent tribute to the joy and excitement of one man's life.
Pohn Fitzgerald Kennedy's life.
***
የዓይን ነገር በዳላስ
ዓይን በአሜሪካዊው አርቲስት ቶኒ ታሴት የሁለት ቅርፃ ቅርጾች ርዕስ ነው። ትላልቅ ዓይኖች ሰማያዊ አይሪስ ያላቸው እና ከፋይበርግላስ፣ ሙጫ እና ከብረት በዘይት ቀለም የተዘረዘሩ ናቸው። የዓይን ሐውልት የመጀመሪያው በ2007 የተሰራው በ12 ጫማ (3.7 ሜትር) ዲያሜትር ሲሆን በሴንት ሉዊስ፣ ሚዙሪ ውስጥ በላሜየር ቅርፃ ቅርፅ ፓርክ ይገኛል። ሁለተኛው እ.ኤ.አ. በ 2010 በ 30 ጫማ (9.1 ሜትር) ዲያሜትር የተሰራ እና በአሁኑ ጊዜ በዳላስ ፣ ቴክሳስ ውስጥ በThe Joule ሆቴል ባለቤትነት ይተዳደራል።
እኔና መንጌ ( በዳላስ - የክብር ስፖንሰሬ) ጉብኝቱን አቋርጠን የ“ቶክ ዳላስ “(talk Dallas)
***
ጋዜጠኛና ደራሲ መሐመድ ሰልማን ‹‹ፒያሳ መሓሙድ ጋ ጠቢቅኝ›› (2004) "ትዝታዋ የቀረው የፒያሳዋ ዳላስ" ጣፋጭ ሥራው ትዝ አለችኝ።
ፍቅረኛህን "ማሀሙድ ጋር ጠብቂኝ" ስትላት ተሳስታ ማዶ ተሻግራ ከጠበቀችህ እድለኛ ናት፡፡ ካንተ በላይ የሚያስደስቷትን ሙዚቃዎች እየሰማች ነው ማለት ነው፡፡ ከዳላስ ሙዚቃ ቤት፡፡ ይህ ቤት የየመን ዝርያ ባላቸው ሐበሾች የተያዘ ነው፡፡ ከፒያሳ ፍቅር እንዲይዝህ ከሚያስችሉ አዚሞች አንዱ ነው፤ ዳላስ፡፡
በማለዳ ፒያሳ ከመጣህ በነ‹‹ያኒ›› ዜማ ትታደሳለህ፡፡ በሩቅ ምሥራቅ ረቂቅ ሙዚቃዎች ትፈወሳለህ፡፡ ረፋድ ላይ ፒያሳ ከደረስክ በነ መሀመድ ወርዲ፣ በነ አህመድ ሙስጠፋ፣ በነ ከማል ተርባስ በነ ሳይድ ከሊፋ ሱዳንኛ ዜማ ትደንሳለህ፡፡ በሱዳን ዜማ ለመደነስ አትሽኮርመም እንኳን አንተ ጠቅላይሚኒስትርህም ደንሰዋል፡፡
ከቀትር በኋላ ፒያሳን ከረገጥክ ደግሞ ዳላስ በብሉይየእንግሊዝኛ ሙዚቃዎች አቅልህን ያስትሃል፡፡ በነ ሳም ኩክ፣ በነ ሬይ ቻርለስ፣ በነ ኢታ ጀምስ፣ በነ ዶና ሰመር፣ በነ ዳያና ሮዝ፣ በነ ማርቪንጌ፣ በነ ቲና ቻርለስ፣ በነ ሮድ ስቴዋርት ዜማዎች ትሰክራለህ፤ ትሳከራለህ፡፡ ደግሞ ማምሻ ላይ እነ ዶን ዊሊያምስ፣ እነ አለን ጃክሰን፣ እነ ሩኒ ሚልሳፕ፣ እነ ዶሊ ፓርተን፣ እነ ኬኒ ሮጀርስ በአገረ-ሰብ ሙዚቃ አለምህን ያስቀጩኻል፡፡
ዳላስ ብሉይ በኾኑ ነገር ግን በሚጣፍጡ ሙዚቃዎች የፒያሳን ዜጎች የማዝናናት ተግባር ላይ የተሰማራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ይመስለኛል፡፡ ዛሬም ድረስ ሳይታክት ጆሮ ገብ ሙዚቃዎችን ያስኮመኩማል፡፡ በነፃ!
ከዚህ ቤት የሚደመጡ ሙዚቃዎች ዘፋኞቹ በሕይወት የሌሉ ወይም ደግሞ ዘፋኞቹ ራሳቸው የረሷቸው ሙዚቃዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ‹‹ኦልዲስ-በት-ጉዲስ››፡፡ ታዲያ በቲቪ የምታውቀው ጥቃቅንና አነስተኛ ጀማሪ ዘፋኝ እዚህ ዳላስ ሙዚቃ ቤት አካባቢ ሲያንዣብብ ካየኽው አንድ ነገር ጠርጥር፡፡ ሊከትፍ ወይ ሊመነትፍ ነው፡፡
ዳላስ በብሉይ ሙዚቃዎች በይበልጥ ይታወቅ እንጂ በዓለም ላይ ዝናው ከፍ ያለ የሮክ፣ የጃዝ፣ የብሉዝ ወዘተ ሙዚቀኛን ሲዲ በመያዝም ይታወቃል፡፡ ዳላስ ገብተህ በትክክል የዘፈን ስም ከጠራህ ሲዲው ያለምንም ጥርጥር ይሰጥኻል፡፡ ድንገት እንኳ ሲዲው አልቆ ቢኾን ስለ አቀንቃኙ አንዳንድ ማብራሪያዎች ተሰጥቶህ ሌላ ጊዜ ብትመለስ ግን ሲዲው ከነልባሱ እንደሚዘጋጅልህ ተነግሮህ ነው የምትሰናበተው፡፡ ዳላስ ከተወለደ ጀምሮ ሙዚቃ አድናቂን አስቀይሞ አያውቅም፡፡ ሙዚቃ በእውቀት የሚነገድበት ቤት ነው፡፡
በነገርህ ላይ እዚያ አካባቢ የሚሠሩ የታክሲ ወያላዎች ዳላስ ሙዚቃ ቤት ተፅዕኖ ስላሳደረባቸው ይመስለኛል ተሳፋሪ ሲጠሩ ራሱ በዜማ ነው፡፡ የወያላዎቹን ድምፅ በደንብ አስተውህ ካዳመጥከው ሙዚቃዊ ቅላፄ አለው፡፡ ይስረቀረቃል፡፡ ‹‹22 ካዛንቺስ…መገናኛ!!!...መገናኛ ካዛንቺስ 22!!፣ አምስት ኪሎ..…ቅድስት ማርያም...አምስት ኪሎ!!!››
ፒያሳ ከመጣህ እንደ ወይን እያደር የሚጣፍጥ ዘፈኖችን ከዳላስ ሙዚቃ ዘወትር ትኮመኩማለህ፡፡ አምስት ሳንቲም ሳትከፍል፡፡ በዚህ ዘመን አንድን ሙዚቃ ሦስት ታክሲ ውስጥ ተከፍቶ ከሰማኸው እጅ እጅ ማለት እንደሚጀመር አንተም ሳትገነዘብ የቀረህ አይመስለኝም፡፡ የድሮ ሙዚቃ ግን ውብ ነው፡፡ ሄዶ ልብህ ላይ ነው የሚቀመጠው፡፡ አይጎረብጥህም፡፡ ካላመንከኝ ፒያሳ ዳላስ ሙዚቃ ቤት ደጅ ላይ ተሰየም፡፡
አንድ ድረ-ገጽ አንባቢዬ ዳላስ ሙዚቃ ቤትን እንዴት ገለጸው
A "The soundtrack of Piassa"
***
የደራሲና ዳይሬክተር ዮሐንስ ፈለቀ ( Yoni Cash ) እና ተገኔ ( እንደስሙ ተገን✈️
በእዝነ ልቦና ሀገር ቤት ገብቼ ነበር።
የተወዳጇ፤ የሶል ንግሥቷ አስቴር አወቀ "ሀገሬ" አልበም ከፍ ብሎ ይሰማኝ ነበር።
"ይሄም ሀገር ሀገር ይላል ሀገር ይሄ ሀገረ ብርቁ
እኔም ሀገር ሀገር ሀገር አለኝ ሀገር የሚታይ በሩቁ....❣️
1 year ago
ሀገር ያለ ታሪክ አትቆምም!!
የዚህ የደምና አጥንት የታሪክ መሠረት በዕምነት ፣ በፍቅርና በህብረት ምሶሶ ላይ ተንጣሎ ዛሬ ላይ ስሟ አድማስ ተሻጋሪ የሆነ የጥቁር ህዝብ አርማ የምትሆን ኢትዮጵያ ይሏት ታላቅ… ታሪካዊ የሆነች ሀገር ላይ ደርሰናል
…. ምንም እንኳ አባቶቻችን ለአንዲት አፍሪካ ሲታገሉ እንዳልኮራን እኛ ልጆቻቸው ዛሬ አንዲት ኢትዮጵያን ለመፍረስ ስንጫረስ …..ቢያሸማቅቅና ቢያሳፍርም !!......
እኛ ግን ባለታሪክ ነን !!
ከነዚህም መሀል ፣ ከዘመናት በፈት የሆነው የንጉሥ አርማህ ታሪክ አንዱ ድንቅ ማሳያ ነው።
በመልካሙ ዘሪሁን ውብ ተደርጎ ተፅፎ በዶክተር ተሻለ አሰፋ ድንቅ ሆኖ የተዘጋጀው ንጉሥ አርማህ ቲያትር፣ አሉን በምንላቸው ድንቅ ተዋናዮየቻችን ህያው ሆኖ ለዕይታ ተሰናድቷል!!
የትላንቷን ኢትዮጵያ በዛሬ መነፅር እሰከነገ እዩ !!.......
*********
“ የድላችን መታሰቢያ ፤ በብራና ተፅፎ ፣በሀውልት ላይ ተቀርፆ ፣በአዶሊስ በራፍ ላይ ለዘለዓለም ይቁም !!
ሀውልቱን ያበላሸ ወይም የጣለ ፣ እርሱና ልጆቹ የተረገሙ ይሁኑ!!....”
ንጉሥ አርማህ !

“ሥልጣኔዎቿ ከባሕር ጋር ይያያዛሉ፣ ታሪኮቿ ከባሕር ጋር ይተሳሠራሉ”
#ethiopia | እርሷ ባሕሩን ከየብሱ ጋር አስማምታ ገዝታለች፤ ሀገረ መንግሥትን ከዘመናት በፊት አጽንታለች፤ ሕግና ሥርዓትን አስተምራለች፡፡
ለዘመናት በረቀቀ እና በጸና ሥርዓት ኖራለች፡፡ ጥላ ላጡት ጥላና ከለላ ኾናለች፡፡ አርዓያና ምሳሌ ተደርጋ በዓለሙ ሁሉ ተጠርታለች፡፡ መንገድ ለጠፋባቸው መንገድ አሳይታለች፤ ሥልጣኔ ለራቃቸው የሥልጣኔን መስመር አስተምራለች፡፡
በጥበብ እና በሥልጣኔ ጎዳናዎች ተረማምዳለች፤ የድል አድራጊነት ሐውልቶችን አቁማለች። ከዓለሙ በተለየ ኪነ ሕንጻን አንጻለች። ነጻነትን ከዓለት አጠንክራ አጽንታለች፤ በነጻነት ላይ የመጡባትን ሁሉ ድል መትታለች፤ እርሷ በባሕር ንግድ የዓለም ዳርቻዎችን አካልላለች፡፡
በእርሷ ምድር ብቻ የሚገኙትን ዕንቁ ሀብቶች በባሕር እና በየብስ ለዓለሙ ገበያ አቅርባለች፡፡ ከዓለም ዳርቻዎች የሚመጡትን ነጋዴዎችም በወደቦቿ ተቀብላለች፡፡ በጎዳናዎቿም በሰላም እንዲመላለሱ ፈቅዳለች፡፡
በበዙት ወደቦቿ የሚወጣውን ሸኝታለች፤ የሚገባውን ተቀብላለች፡፡ በየብሱ እና በባሕሩ በገነባችው ሠራዊት ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ ዘመናትን ተሻግራለች፡፡ አይነኬ ሀገርነቷን በዓለሙ ሁሉ አስመስክራለች። ሥልጣኔዎቿ ከባሕር ጋር ይያያዛሉ፡፡ ታሪኮቿ ከባሕር ጋር ይተሳሰራሉ፡፡ እርሷን ያለ ባሕር ማሰብ አይቻልም፡፡
ቀይ ባሕር ቀለሟ ነው ታሪኳን የጻፈችበት፣ ቀይ ባሕር ብራናዋ ነው ታሪኳን ያሰፈረችበት፣ ቀይ ባሕር ማንነቷ ነው ሥልጣኔዎቿን ያሳያችበት፤ ቀይ ባሕር መንገዷ ነው ወደ ከፍታ የተጓዘችበት፤ ቀይ ባሕር ድልድዩዋ ነው ከዓለማት ጋር የተገናኘችበት፣ ቀይ ባሕር ማሕተሟ ነው የታሪክ እውነታዎቿን ያተመችበት፣ ቀይ ባሕር አዋጅ ነጋሪዋ ነው ታላቅነቷን ለዓለም ሁሉ የነገረችበት፣ ቀይ ባሕር እልፍኟ ነው የውጩ እና የውስጡን ያሰባሰበችበት።
ኢትዮጵያ በቀይ ባሕር እና አካባቢው ያለውን ግዛቷን ባሕረ ነጋሽ እያለች ስታስተዳድር ኖራለች። ይህም እስከ ደርግ ዘመነ መንግሥት ፍጻሜ ድረስ ቀጥሏል። ኢትዮጵያ እና ቀይ ባሕር በታሪክ እና በማንነት ባይለያዩም፣ ቀይ ባሕር ያለ ኢትዮጵያ ባይታሰብም፣ ኢትዮጵያም ያለ ቀይ ባሕር ታሪኳ ባይነገርም ለዓመታት ሃብቷን አጥታ ኖራለች። ይህም ብዙ አጉድሎባታል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገር ባሕረ ነጋሽ የአሁኗ ኤርትራ ሀገር ከኾነች ጀምሮ ኢትዮጵያ ታሪክ የቀመረችባቸውን፣ ሥልጣኔዋን ከፍ ከፍ ያደረገችባቸውን፣ ጥበብ እና ሃይማኖት የነገረችባቸውን፣ ወዳጆቿን የተቀበለችባቸውን ወደቦቿን አጥታ ኖራለች። ይህም ብዙ አጉድሎባታል።
የአፍሪካ አብነት፣ የጥቁሮች እመቤት የኾነችው ኢትዮጵያ ታላላቆች ልጆቿ አስከብረውት የኖሩት የታሪኳ እና የማንነቷ ውብ ቀለም ቀይ ባሕር ያስፈልጋታል። የእርሷ ነበርና ለእርሷ ይገባታል።
ቀኝ አዝማች ታደሰ ዘወልዴ የእቴጌ ጣይቱ ብጡል አጭር የሕይወት ታሪክ በተሰኘው መጽሐፋቸው ሰው ሁሉ በተፈጥሮው እኩልነት ያለው ነው፡፡ በታሪኩ ግን ይለያያል፡፡ አንዱ ከአንዱ በልጦ ይገኛል፡፡ አንዱ ለቆመለት ከፍተኛ ዓላማ የግል ጥቅሙን መስዋዕት ለማድረግ የሚያበቃው ጀግንነት ሲኖረው ሌላው ተቃራኒው ፈለግ በመከተል ኑሮውን ይመራል፡፡
የጀግና ልቦና ለሀገሬ እንጂ ለራሴ ከሚል ግላዊ ሀሳብ የራቀ ነው ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያውያን ጀግኖችም ለሀገሬ እንጂ ለራሴ ከሚል ግላዊ እሳቤ ወጥተው ለኢትዮጵያ ኖረዋል፤ ስለ ኢትዮጵያ አልፈዋል፡፡ ኢትዮጵያ የምትከበርበትን እና ከፍ ከፍ የምትልበትን አድርገዋል። ሁሉንም ለሀገራቸው ሰጥተዋል፡፡ ነፍሳቸውን ሳይቀር ለኢትዮጵያ ከፍታና ልዕልና አድርገዋል፡፡
በተቃራኒው ደግሞ ለራሴ በሚል ግላዊ እሳቤ የነበሩ ጥቂቶች ደግሞ ኢትዮጵያን ብዙ ነገር አሳጥተዋል። ለዚህ ማሳያው ደግሞ ቀይ ባሕርን ያጣችበት መንገድ ነው። በዚህ ዘመን ደግሞ ቀይ ባሕር ለኢትዮጵያ እንደሚያስፈልጋት እና እንደሚገባት በግልጽ የጠየቁ መሪዎች መጥተዋል። ይህም ከራስ አልፎ ለሀገር እና ለወገን ማሳብ ነው።
ሐሪ አትክንስ የኢትዮጵያ ታሪክ በተሰኘው መጽሐፋቸው ኢትዮጵያን የባሕር በር ያላት፣ ጥንታዊት ሀገር መኾኗን ጽፈዋል፡፡ እርሷ ከቀደሙ ጥንታውያን ሥልጣኔ ከነበራቸው ሀገራት በአዶሊስ እና በሌሎች ወደቦቿ አማካኝነት በመርከብ ንግድ ታሳልጥ እንደነበር እና ከሀገራት ጋር ጥብቅ ግንኙነት ታደርግ እንደነበር መዝግበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ታሪክ ከተመዘገበበት ዘመን ጀምሮ ቀይ ባሕር ብቻ ሳይኾን ከቀይ ባሕር ባሻገር የነበሩ ሀገራትም የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ሲነገር ኖሯል። ለዚህም ደግሞ በዓላት ላይ የተቀረጹ፣ በብራና የሰፈሩ፣ በወረቀት የተከተቡ አያሌ ማስረጃዎች ሞልተዋል። ይህ ብቻ አይደለም በሕይወት ያሉ አያሌ ሰዎችም ኢትዮጵያ እና ቀይ ባሕር እንደማይነጣጠሉ ዛሬም በሕይወት ይመሰክራሉ።
የፖለቲካ ሳይንስ ምሁሩ ፕሮፌሰር ቡሩክ ኃይሉ ኢትዮጵያ የኋላ ታሪኳ ሲነገር፣ ሥልጣኔዋ ሲመዘዝ የዳህላክ፣ የአዶሊስ እና የሌሎች ወደቦች ባለቤት እንደነበረች፣ በባሕሯ በቀይ ባሕር አማካኝነት ከግሪክ እና ከሮማውያን ጋር ትገናኝ ነበር ነው የሚሉት፡፡
የሺህ ዘመናት ታሪኳ ሲነገር ኢትዮጵያ እና ባሕር በር አይነጣጠሉም፡፡ እርሷ አንድ ብቻ ሳይኾን በርከት ያሉ ወደቦች የነበሯት ሀገር ናት ይላሉ፡፡
ኢትዮጵያ በባሕር ላይ ሥልጣኔዋ በታሪክ አንቱ የተባለች ናት፡፡ የቀይ ባሕር ባለቤት ብቻ ሳትኾን ከዚያም ተሻግራ ሀገራትን ታስተዳድር እንደነበር ታሪክ ይመዝዛሉ፡፡ ቀይ ባሕር ቤቷ፣ መግቢያ እና መውጫዋ ነው ይላሉ፡፡ የቀይ ባሕር ለኢትዮጵያ እንደ አዲስ የሚተረክ አይደለም የእርሷ ነውና፡፡
ኢትዮጵያ ከጥቂት ዓመታት ወዲህ ነው የባሕር በር ያጣችው የሚሉት ምሁሩ አሁን ላይ የራሷ የነበረውን የባሕር በር እንደሚገባት በግልጽ ጠይቃለች፤ ጥያቄዋም ታሪካዊ፣ ሕጋዊ እና እውነትን መሠረት ያደረገ ነው ይላሉ፡፡ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጥያቄ ዓለም አቀፍ ሕግም እንደሚደግፋት ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ እንደማንኛውም ሀገር የባሕር በር ያስፈልጋታል፡፡ ይገባታልም ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያ እስካኹን ድረስ መጠቀም የሚገባትን ሳትጠቀም ቆይታለች፤ በሚያሳዝን ኹኔታ የባሕር በሯን ተነጥቃ ቆይታለች ነው የሚሉት፡፡
የኢትዮጵያ አኹናዊ ቁልፍ የዲፕሎማሲ ሥራ ታላቋ፣ ታሪካዊቷ እና ጥንታዊቷ ሀገር የባሕር በር እንዲኖራት ማድረግ ነው ይላሉ፡፡ ኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት እንዳለባት፣ በዚህ መንገድ ታፍና መኖር እንደሌለባት እየተሠራ ነው፤ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባሕር በር ለማግኘት ጥረት ታደርጋለች፤ ጥረቷን ከጎረቤቶቿ ሀገራት ጋር አጠናክራ ትቀጥላለች ይላሉ፡፡
ኢትዮጵያ ለባሕር በር የቀረበች መኾኗን ነው የተናገሩት፡፡ በርካታ ሀገራትም የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ፍትሐዊ እንደኾነ፣ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ማግኘት ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ እየገለጹ ነው ይላሉ፡፡
ሕዝብ እና መንግሥት ሲናበቡ ታላላቅ ሥራዎችን ይሠራሉ የሚሉት ምሁሩ የፖለቲካዊ ልዩነቶች ሊኖሩ ይችላሉ፤ ነገር ግን በሀገራዊ ጉዳይ ልዩነት ሊኖር አይገባም፣ ኢትዮጵያውያን አንድ ሲኾኑ የማይሠሩት ታላቅ ሥራ የለም ነው የሚሉት፡፡ ሀገርን በማስቀደም፣ ሀገር የምትጠይቀውን በመስጠት የታሰበውን ማስፈጸም የዚህ ዘመን ትውልድ አደራ ነው ብለዋል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የዚህ ዘመን መንግሥት ጥያቄ ብቻ አይደለም፣ የኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያውያን ጥያቄ ነው፤ መንግሥት በሕዝብ ተደግፎ ሲሠራ የባሕር በር ጥያቄው ይሳካል ነው የሚሉት፡፡
ወጥ እና የተባባረ ኀይል ይዘን ከቀጥልን የትኛውም ችግር ሊበግረን አይችልም ይላሉ፡፡ የባሕር በር ጥያቄ የሀገር እና የሕዝብ ጥያቄ ነው። ጥቅሙም ለሕዝብ እና ለሀገር ነው። የቀደመውን ታሪክ እና ታላቅነት ለመመለስ በአንድነት እና በፍቅር ሰላማዊ በኾነ መንገድ መሥራት የዚህ ዘመን ትውልድ አደራ ነው።
በታርቆ ክንዴ #amico

Comments