2 days ago
🇪🇹 A milestone. A movement. A shared responsibility.
#june 16/2026
ELiDA Ethiopia proudly celebrates the establishment of the National Anti-Technology Facilitated Gender-Based Violence (Anti-TFGBV) Network.
We extend our sincere gratitude to government institutions, civil society organizations, media, social media influencers, justice actors, academia, and development partners who have united behind one clear message: online violence must end.
Together, we are building a stronger movement for safer digital spaces, survivor-centered responses, effective laws, accountability, and justice.
This is not just a network—it is a national commitment to ensure that every woman and girl can participate, lead, and thrive online without fear.
🇪🇹 ታሪካዊ ምዕራፍ። ታላቅ ንቅናቄ። የጋራ ኃላፊነት።
ኤሊዳ ኢትዮጵያ (ELiDA Ethiopia) ብሔራዊ የፀረ-TFGBV (ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃት) መረብ መመስረቱን በኩራት ያበስራል።
«የኢንተርኔት ጥቃት ሊቆም ይገባል!» በሚለው አንድ ግልጽ ዓላማ ሥር ለተሰለፋችሁ፦
ለመንግሥትና ለፍትህ ተቋማት፣
ለሲቪል ማኅበረሰብ እና ለልማት አጋሮች፣
ለሚዲያ፣ ለማኅበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ለአካዳሚዎች የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በጋራ በመሆን፦ ደህንነቱ የተጠበቀ ዲጂታል ምኅዳር፣ ተጎጂዎችን ማዕከል ያደረገ ምላሽ፣ ጠንካራ ሕጎች እና ተጠያቂነት የሰፈነበት ሥርዓት እንገነባለን።
ይህ ዝም ብሎ መረብ አይደለም፤ እያንዳንዱ ሴት እና ሴት ልጅ ያለ ፍርሃት በዲጂታል ዓለም ውስጥ እንዲሳተፉ፣ እንዲመሩ እና እንዲበለጽጉ የተገባ ብሔራዊ ቃል ኪዳን ነው!
#የፀረTFGBVመረብ #tfgbvይብቃ #tfgbv #elidaethiopia ! #antitfgbvnetwork #endtfgbv #digitalsafety #technology #የቴክኖሎጂ_ጥቃት_ይቆም #ዲጂታል_ደኅንነት
Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር Ethiopian Civil Society Organizations Council Ethio telecom Sustainable Technology Solutions-STS Christian Aid Institute for Peace and Security Studies UN Trust Fund to End Violence against Women Ethiopian Women Development Organization - EWDO የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር Ministry of Women and Social Affairs የኢትዮጵያ የሲቪል ሰርቪስ የመንግሥት ሰራተኞች

4 days ago
ኩባንያችን የቴሌኮም እና ዲጂታል ደኅንነትን ለማረጋገጥ ያለመ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ለፍትሕ ተቋማት ሰጠ!
ኩባንያችን ኢትዮ ቴሌኮም የሀገሪቱን የዲጂታል ደኅንነት ለማስጠበቅ እና የቴሌኮም መሠረተ ልማቶችን ከጥቃት ለመከላከል እንዲቻል፣ ከተለያዩ የፍትሕ ተቋማት ለተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ሀገር አቀፍ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በተለያዩ ከተሞች ሰጥቷል።
“የኢትዮ ቴሌኮም እና የፍትሕ ተቋማት ጥምረት ለዲጂታል ኢትዮጵያ ደኅንነት” በሚል መሪ-ቃል በድሬደዋ፣ በሐዋሳ እና በአዳማ ከተሞች በተካሄዱት በእነዚህ የሥልጠና መድረኮች ላይ፤ ከፌዴራልና ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ በአጠቃላይ 171 ዳኞች፣ አቃቤያነ ሕግ እና የፖሊስ አባላት ተሳትፈዋል።
የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናው ኩባንያችን የሦስት ዓመት ስትራቴጂውንና የኢትዮጵያን የዲጂታል ሽግግር ለማፋጠን ከሚያደርገው ግዙፍ የ4ጂ እና 5ጂ ኔትወርክ መሠረተ ልማቶች ማስፋፊያ ባሻገር የእነዚህን መሠረተ ልማቶች ዘላቂነት ለማስቀጠልና የዲጂታል ሥነ-ምህዳሩን ደኅንነት ለማረጋገጥ ከፍትሕ አካላት ጋር ተቀናጅቶ መሥራት ወሳኝ በመሆኑ የተዘጋጀ ነው።
ሥልጠናው በዋናነት በዲጂታል ፋይናንስና በቴሌኮም ዘርፍ የሚፈጸሙ የማጭበርበር ወንጀሎችን (Telecom & Financial Fraud) ለመከላከል እንዲሁም በቴሌኮም መሠረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን በሕግ አግባብ ለመቆጣጠር በሚቻልባቸው ስልቶች ላይ ያተኮረ ነው።
በሥልጠናው መድረክ ላይ የተሳተፉ የፍትሕ ተቋማት ሀላፊዎችና ባለሞያዎች በበኩላቸው፤ መድረኩ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ለመረዳትና ተገቢውን የሕግ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ግንዛቤ የፈጠረላቸው መሆኑን የገለጹ ሲሆን የቴሌኮም መሠረተ ልማትን እንደ ሀገር ሀብት በመጠበቅና ወንጀሎችን በብቃት በመከላከል ረገድ ከኩባንያችን ጋር በቅንጅት ለመሥራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ኩባንያችን ተመሳሳይ ሥልጠናዎችን በሌሎች ከተሞችም አጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን፤ ይህ መድረክ ኩባንያችን ለሀገራዊ የዲጂታል መሠረተ ልማት መስፋፋት ከሚያደርገው ጥረት ባሻገር፣ ከቁልፍ የፍትሕ ባለድርሻ አካላት ጋር የላቀ አጋርነት በመፍጠር የዲጂታል ኢኮኖሚው ደኅንነቱ የተረጋገጠ እንዲሆን የሚያስችል መሆኑ ይታመናል።

Comments