2 months ago
የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ጋር የሐዋሳን ከተማ ልማት ፕሮጀክት ለማፋጠን ያለመ ስትራቴጂካዊ ውይይት አደረጉ!
በዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ፍሬሕይወት ታምሩ የተመራው የኩባንያችን ከፍተኛ ማኔጅመንት ቡድን፣ ከሐዋሳ ከተማ ከንቲባ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ እና ከከተማዋ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በከተማዋ እያስመዘገበችው የሚገኘውን ፈጣን የዲጂታል ዕድገት እንዲሁም የመጻኢ የቴክኖሎጂ ትስስርን ለማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ስትራቴጂካዊ ውይይት አካሂዷል።
ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ ኩባንያችን እያከናወናቸው የሚገኙ መጠነ ሰፊ የሪፎርም ሥራዎችን በማድነቅ፤ በተለይም የኢትዮጵያን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በማፋጠን ረገድ ኢትዮ ቴሌኮም እያበረከተ ለሚገኘው ቁልፍ ሚና እውቅና ሰጥተዋል፡፡
ክቡር ከንቲባው ቀደም ሲል በከተማዋ ለተከናወኑ የልማት ፕሮጀክቶች ኩባንያችን ላደረገው ሁለገብ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው፤ ሐዋሳ ከአዲስ አበባ በመቀጠል ዋነኛ የቱሪዝም እና የኮንፈረንስ መዳረሻ እንድትሆን ለማስቻል ያለመ አዲስ የሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ውጥን ይፋ ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም በመካሄድ ላይ ያለውን የ"ስማርት ሲቲ" ፕሮጀክት እና የሐዋሳ ሐይቅ ዳርቻ ልማት ለማፋጠን የኢትዮ ቴሌኮም ድጋፍ ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ በበኩላቸው፤ ኩባንያችን መሰል የከተማ ልማት ውጥኖችን ለመደገፍ ያለውን ዝግጁነት አረጋግጠዋል። ሐዋሳ በፋይበር መሰረተ ልማት እንዲሁም በ4ጂ እና በ5ጂ የሞባይል ቴክኖሎጂ የታጠቀች ከተማ መሆኗን ገልጸው፤ በአሁኑ ወቅት አስተማማኝ የሆነ የኔትወርክ ሽፋን እና ጥራትን ማሳደግ ታሳቢ ያደረግ መጠነ ሰፊ የማስፋፋት እና የማዘመን ሥራ በተጠናከረ ሁኔታ በመካሄድ ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የከተማ አስተዳደሩን አገልግሎት በዲጂታል ቴክኖሎጂና በቴሌብር በማዘመን፣ የሥራ ቅልጥፍናንና የገቢ አሰባሰብን ማሳደግ እንደሚቻል ዋና ሥራ አስፈጻሚያችን ገልጸዋል። በተመሳሳይ፣ በዘመን ገበያ አማካኝነት ለነጋዴዎች የገበያ ትስስርን በማስፋፋት ረገድ ሰፊ የዲጂታላይዜሽን ዕድሎችና የሥራ ፈጠራ አጋጣሚዎች መኖራቸውን አስገንዝበዋል።
ሐዋሳን ንፁህ፣ ደህንነቱ የተጠበቀና በዲጂታል የታገዘ የሕዝብ መዳረሻ ለማድረግ እንዲሁም የተቀናጀ የዲጂታል ሥነ-ምህዳርን ለመፍጠር ያለመ ሰፊ ስትራቴጂካዊ ውይይት ተደርጓል። በዚሁ መሠረት የኩባንያችንን አቅም በመጠቀም የሐዋሳ "ስማርት ሲቲ" ልማትን ለማፋጠን፣ የቴሌብር አገልግሎቶችን በሙሉ አቅም ማቀናጀት፣ የማዘጋጃ ቤት አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ፣ የትራፊክ እና የሞቢሊቲ መፍትሔዎች፣ የመሠረተ ልማት ጥበቃ እንዲሁም የኔትወርክ ዝርጋታን የሚያቀላጥፉ የኮሪደር ልማት ትብብሮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም፣ የኩባንያችን ማኔጅመንት ለሐዋሳ ከተማ ዕድገትና ለአዲሱ የሐዋሳ ሐይቅ ልማት ፕሮጀክት አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት ያረጋገጠ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያን በቴክኖሎጂ የማብቃትና ዲጂታል መጻኢን የመገንባት ትልቅ ራዕያችን አካል መሆኑ ተመላክቷል።
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ !
#ethiotelecom #telebirr #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia #smartcity #hawassa #digitalethiopia

የላቀ ፍጥነት ያለውን የ4ጂ LTE ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በሀገራችን 52 ከተሞች ማስጀመራችንን በደስታ እንገልፃለን፡፡
በከተሞቹ የምትገኙ ደንበኞቻችን 4G LTE የሞባይል አገልግሎት ተጠቃሚ በመሆናችሁ እንኳን ደስ አላችሁ እያልን በፈጣኑ 4ጂ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎታችን እንድትደሰቱ እንጋብዛለን!
የሚገለገሉበት ሲም ካርድ 4G የሚያስጠቅም ከሆነ የሞባይል ሴቲንግዎን ኔትወርክ ሞድ LTE/3G/2G (Auto connect) ያድርጉ፤ የማያስጠቅም ከሆነ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ የአገልግሎት ማዕከል ጎራ ብለው በነጻ በማስቀየር ልዩ የጥቅል ስጦታ ያግኙ!
#ዲጂታል_ኢትዮጵያን_ዕውን_በማድረግ_ላይ
#4glte #ethiotelecom #nexthorizon #ruralconnectivity #telebirr #digitalethiopia #realizingdigitalethiopia

Sponsored by
Surafel
Comments