28 days ago
(ዘ-ሐበሻ መዝናኛ ዜና) ታዋቂዋ ካናዳዊት ድምጻዊት ሴሊን ዲዮን ጡንቻን እና ጉሮሮን ክፉኛ ከሚያጠቃው 'ስቲፍ ፐርሰን ሲንድረም' ከተባለው ከባድ የነርቭ ሕመም ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ስትታገል ከቆየች በኋላ፣ ከስድስት ዓመታት መራቅ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ሙሉ የሙዚቃ ድግሷን በፈረንሳይ ናንቴር ከተማ በሚገኘው ፕሌኒቱድ አሬና በስኬት አቀረበች። በአውሮፓውያኑ 2022 በበሽታው መያዟ ከተረጋገጠ ወዲህ የሙዚቃ መድረኮችን አቋርጣ የቆየችው የ58 ዓመቷ ኮከብ፣ ከ30 ሺሕ በላይ አድናቂዎቿ ፊት በመቅረብ ለሁለት ሰዓት ከ15 ደቂቃ ባደረገችው ቆይታ 25 ታዋቂ ሙዚቆቿን ያለምንም እንከን ተጫውታለች።
አርቲስቷ በመጀመሪያው ሙዚቃዋ ላይ በስሜት ተሞልታ እንባዋን መቆጣጠር ያቃታት ቢሆንም፣ አድናቂዎቿን "ደህና ነኝ" በማለት አጽናንታለች። በተለይም ከፍተኛ የድምፅ እርከን የሚጠይቀውን "All By Myself" የተሰኘውን ዘፈኗን ድምጿን አውጥታ ስትጫወት፣ አዳራሹ በታዳሚዎች የደስታ ጩኸት ተናውጧል። ይህ አስገራሚ የመድረክ ላይ ትንሳዔዋን ያሳየችበት የሙዚቃ ድግስ መጀመሪያ ሲሆን፣ በቀጣዮቹ አምስት ሳምንታት ውስጥ 16 ተጨማሪ ተመሳሳይ ትዕይንቶችን በተከታታይ እንደምታቀርብ ተገልጿል።

2 months ago
የጋዜጠኛና መምህር ዐቢይ ይልማ 5ኛ መጽሐፍ
“ደህና ነኝ – እግዚአብሔር ይመስገን” ቅዳሜ ይመረቃል
#ethiopia | የጋዜጠኛ፣ ደራሲና መምህር ዐቢይ ይልማ አምስተኛ መጽሐፍ የሆነው “ደህና ነኝ – እግዚአብሔር ይመስገን” ቅዳሜ ነሐሴ 2፣ 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 ጀምሮ በቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ይመረቃል።
መጽሐፉ በዘመናችን በብዙ ሰዎች የሚስተዋሉ እንደ ጭንቀት፣ ፍርሃት፣ የባዶነት ስሜት፣ ተስፋ መቁረጥ፣ ሱሰኝነት፣ የገንዘብ ችግርና ሌሎች የሕይወት ፈተናዎች ዙሪያ መንፈሳዊና ሳይንሳዊ እይታዎችን በማቀናጀት ለአንባቢያን ተስፋና መነሳሳት ለመስጠት ያለመ ሥራ መሆኑን አዘጋጆቹ ገልጸዋል።
ደራሲው ዐቢይ ይልማ በሕይወቱ ያጋጠሙትን ለ12 ዓመታት የዘለቀ ከባድ የጤናና የሕይወት ፈተና በድል ካለፉ በኋላ ያገኙትን ልምድና እውቀት በዚህ መጽሐፍ አካፍለዋል።
አዘጋጅ ኮሚቴው በዕለቱ የሚካሄደውን የመጽሐፍ ምረቃ ሥነ ሥርዓት እንዲታደሙ የደራሲውን ወዳጆች፣ የሥነ ጽሑፍ አፍቃሪዎችና መላውን ሕዝብ በክብር ጋብዟል።
ቅዳሜ ነሐሴ 2፣ 2018 ዓ.ም.
ጠዋት 4፡00 ሰዓት
ቦሌ ዓለም ሲኒማ
እንኳን ወደ መጽሐፉ ምረቃ በደህና መጡ!

"ደህና ነኝ!" ሊመረቅ ነው!
የጋዜጠኛና መምህር ዐቢይ ይልማ 5ኛ “ደህና ነኝ - እግዚአብሔር ይመስገን” የተሰኘ መንፈ-ሳይንሳዊ መፅሐፍ የፊታችን ነሐሴ 2/2018 ዓም ፣ ቅዳሜ ጠዋት 4፡00 ቦሌ በሚገኘው ዓለም ሲኒማ ይመረቃል፡፡
መፅሐፉ አሁን በትውልዱም ፣ በሐገራችንም የገባውን የጭንቀት ፣ የፍርሃት ፣ የባዶነት ስሜት ፣ የተስፋ መቁረጥ ፣ የካንሰር ፣ የስኳር ፣ ስትሮክና መሰል በሽታዎች ጥቃትን በዕውቀት ያክማል፡፡ በራስ ኩነኔ ፣ በሱሰኝነት ፣ በገንዘብ እጦት ወዘተ (ብቻ) ሕይወትም ኑሮም ለከበዳት ነፍስ አስገራሚ ምስጢራትን ይበታትናል፡፡ ፀሐፊው ዐቢይ ይልማ በሕይወቱ ፣ በመኖርና መሞት መካከል ከተፋለመባቸው የ12 ዓመታት የሕይወት ጦርነት አሸናፊነት ውስጥ “ደህና ነኝ ፤ እግዚአብሔር ይመስገን!” መጽሐፍ ተወልዳለች።
በምረቃው ዕለት ታላላቅ እንግዶች የሚታደሙ ሲሆን መርሀ ግብሩንም የሚያዋዙ የጥበብ መሰናዶዎችም እንደሚኖሩ ከኮሚቴው ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

5 months ago
''ማንቺስተር ያሸነፈ ቀን !''
ትናንት አርሰናል አሸነፈ! በህይወቱ ሙሉ ሲመኘው የነበረውን ይህን ድል ቆሞ ማየት የነበረበት አንድ ሰዉ ነበር።
ብዙ ጊዜ ማንቺስተር አሸንፎ ደጋፊዎቹ መሬት አልበቃቸው ብሎ ሳይ እንደሁሌውም ትዝያለኝ ያ ራሱን 'የአርሰናል ቁልፍ ሰው' አድርጎ ይቆጥር የነበረው ታናሽ ወንድሜ ነው
በፍቃዱ ብርሃኑ ይባላል… እማዬ “ፍቃዴ” ትለው ነበር፡፡ እኔን ጨምሮ እሱን የሚያውቁት ሁሉ “ፍቄ” ብለው ነበር የሚጠሩት፡፡ በህጻን አዛውንቱ ተወዳጅ የነበረ ወንድሜ .... ዛሬ በህይወት የለም።
ፍቄ ሁሌም ማታ የጠንቋይ መጣፍ የመሰለ ደቃቅ ጽሁፍ የታጨቀበትን ሊብሮ ጋዜጣ ይዞ ወደቤት ይመጣል። ገና ጎረምሳ ነው፡፡ ረጅም ...1 ሜትር ከ87 ሳ.ሜ ቁመቱን በአሮጌው ሶፋ ላይ ዧ አድርጎ እንሩን አንፈራጦ ይቀመጥና …. ፊቱን ጋዜጣው ውስጥ ቀብሮ …ኮስተር ፈታ እያለ ‘የነቡናን እና የነአርሴን' ወግ ይጨመጭማል።
“… ምንድነው ግን የምታነበው?” ትለዋለች እማዬ፡፡ ”ስፖርት ነው እማ.. ብዙም አታውቂውም” ይላታል።
”ኡኡቴ! አዋቂ ነኝ ብለህ ሞተሃል..ደሞ ለቅሪላ ወሬ!” ትላለች።
” ጭንቅላትህን በኳስ ዕወቀት ከምትሞላ ትምህርትህ ላይ አትበረታም ነበር? …ደደብ!! …ነገ አርሰናል መጥቶ ይፈተንልህ መሰለህ? ..” ብዬ ልጮህበት እፈልጋለሁ።
ግን ብዙ ጊዜ ይህንን ብዬው ጉሮሮዬን አመመኝ እንጂ ያመጣሁት ለውጥ የለም።
እማዬ ማለዳ ወደቤተክርስቲያን በምትሄድባቸው ቀናት ወደእግዜር ከምትወስደው የራሷ ጥያቄዎች በተጨማሪ ፍቄ የሚያዛት ተጨማሪ ፀሎት አለ። ጨዋታ ያለ ቀን ወይ ቡና… ወይ አርሰናል እንዲያሸንፍ እንድትጸልይለት ይነግራታል፡፡
የሆነ ጊዜ የቡና ረከቦቷን የምትሸፍንበትን ጨርቅ አነስቶ ጥሎ በምትኩ ሁለት የቡና አርማ ያለበትን ባንዲራ አሰርቶ አመጣና አንዱን “የቡና ስኒ በቡና አርማ ነው መሸፈን ያለበት” ብሎ ሰጣት፡፡ አንዱን ደግሞ የቤታችን ግድግዳ ላይ በሚስማር መትቶ ሰቀለው፡፡ ቤት ስገባና የሆነውን ሳይ ተናደድኩና ገንጥዬ ጣልኩበት፡፡ የረከቦቱን ግን እማዬ ከለከለችኝ፡፡ "ይሁን፣በገዛ ሲኒዬ ምን አገባህ" ብላ ፡፡ እነዚያ ጨርቆች ዛሬም ድረስ ቤታችን አሉ፡፡
እማዬን “ እሙ!” ነበር የሚላት፡፡ የሚተኛው ከሷ ጋር ነው፡፡ የመጨረሻ ልጅ ስለሆነ ነው መሰለኝ እንደነፍሷ ትወደዋለች፡፡ ጨዋታ ያለ ቀን ታዲያ እማዬ ማለዳ ወደቤተክርስቲያን ለመሄድ ስትነሳ የተሸፈነበትን ብርድልብስ ገለጥ ያደርግና “እሙ! ዛሬ የኔ ቡድን ይጫወታል።እንዲያሸንፍ ጸልዪልኝ ...ካሸነፍን ስለት ታስገቢልኛለሽ! ” ይላታል፡፡
“አይ እዳዬ!..... ደሞ ዛሬ አቡነ ተክለሃይማኖት እንዴት ያረጉኝ ይሆን” ትላለች ። እማዬ ስትምልም ስትለምንም በአቡነ ተክለሃይማኖት ነው፡፡
አንድ ቀን 'የምር ስለሱ ኳስ ጨዋታ ትጸልያለሽ?' ብዬ ጠየቅኳት፡፡ “እንዴ አዎና!...ተክልዬ !! የዚህን ልጅ ልብ የበሉት ባለኳሶች እንዲያሸንፉ እርዱልኝ…..ጉድ እንዳይሰሩኝ ኋላ! እላቸዋለሁ” አለችና አሳቀችኝ።
ምን ታድርግ? የርሱ ክለብ የተሸነፈ’ለታ ቤታችን የሚፈጠረውን ነገር ስለማውቅ አልፈረድኩባትም፡፡
ጨዋታ ያለ ቀን ገና በጠዋቱ አጠገቤ ቆም ይልና…”መላ’ዬ …ጨዋታው 3 ከ 45 ይጀምራል። ከዚያ በፊት ሃይላይት አለ። ወደ አምስት ሰዓት አካባቢ ያልቃል። እንደጨረስኩ ወዲያው እመጣለሁ።” ይላል።
ማስፈቀዱ ነው፡፡ ዝም እላለሁ።ቆሞ ያየኛል።ዝም እላለሁ። አይሄድም፡፡ እኔ ጥዬው እሄዳለሁ።
አንዳንዴ የሆነ ልቡን ስልብ አድርጎ ራሱን የሚያስተው ነገር አለ፡፡ ሲጨነቅ ወይም ሲበሳጭ እንዲያ ይሆናል፡፡
አርሰናል የተሸነፈ’ለት ታዲያ ብዙ ጊዜ ያ ህመም ይነሳበታል፡፡ ቤት እንደገባ በዚያ ቁመቱ ሶፋ ላይ ዧ ብሎ ይወድቃል፡፡ ጸጥ ነው የሚለው፡፡ አንዳንዴ ሞተ ብለን የምንጮህበት ቀን አለ።ውሃም ጸበልም ደፋፍተንበት ነፍስ ከዘራ በኋላ “ደህና ነኝ እኮ” ሲል ደግሞ የኔ ንዴት በተራው አናቴ ላይ ይወጣል።
“አንተ በማይረባ ኳስ እየመጣህ ትዘረጋለህና እኛ መጨነቅ አለብን?” ብዬ እጮህበታለሁ፡፡ መልስ አይሰጠኝም፡፡ሌላ ቀንም እንዲሁ ይሆናል፡፡
የሆኑ ከሌላ ሰፈር የሚመጡ የጊዮርጊስ ይሁኑ የማንቺስተር ደጋፊዎች እሱን ሁሌም እንደተቃረኑት ነበር። ኳስ የሚያዩት አብረው መሰለኝ ፡፡
ጨዋታ ያለ ቀን ታዲያ...ብዙ ጊዜ እኩለ ሌሊት ከእንቅልፌ የሚያባንነኝ በራችን አቅራቢያ የምሰማው የብዙ ልጆች ዘፈን የሚመስል ጫጫታ ነበር። እኛ ቤት በር ላይ አርሰናልን የሚሳደብ ዘፈን ከሰማሁ በቃ ነገር አለ ማለት ነው !።
ፍቄን ለማብሸቅ የሚዘፈን ዘፈን መሆኑን አውቃለሁ።
ልጆቹ የሚሉት ነገር አይገባኝም። ግን ሁለቱ ቡድኖች ከማንም ጋር ይጫወቱ ብቻ አርሰናል ከተሸነፈ ወይም ማንቺስተር ካሸነፈ እሱን ለማብሸቅ እኩለ ሌሊት በራችን ላይ ይመጡና ይጨፍራሉ።
አንድ ቀን ከነሱ ጋር ሲደባደብ ፖሊሶች ደረሱና ብዙዎቹን ያዟቸው፡፡ እሱንም ይዘውት መኪና ላይ ከጫኑት በኋላ የኔ ወንድም መሆኑን ሲነግራቸው ደውለው ጠርተውኝ ፊቴ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ ሰጥተው ለቀቁት፡፡ ለእማዬ ብዬ እንጂ እስር ቤትን ትንሽ ቢቀምሳት ቅር አይለኝም ነበር፡፡
እሱ የሚደግፈው ቡድን ያሸነፈ’ለት ደግሞ ታሪክ ይገለበጣል፡፡እማዬ ይህንን ስትሰማ ወደሰማይ እያንጋጠጠች “ዛሬስ ተክለሃይማኖት ገላገሉኝ !” ትላለች።
የዚያን ቀን ታዲያ ሌሊቱን ሙሉ እንቅልፍ አይወስደውም። ብቻውን ይስቃል። አልጋው ራስጌ ፎቷቸውን የሰቀለውን ማንነታቸውን የማላውቃቸውን ተጨዋቾች በተኛበት አንጋጦ ያያቸዋል፡፡ ጸጥ ባለው ሌሊት ድንገት ይነሳና “ይሄ የተረገመ ልጅ! ሰራላቸው እኮ!” ብሎ በሳቅ ፍርስ ይላል።
አንዳንዴ ዝም ብዬ ሳየው ጤነኛ ሁሉ አይመስለኝም ነበር ።እማዬ ግን “ተወው ልጅ አይደል? ብቻ አይመመው እንጂ ሲለፈልፍ ቢያድር እኔ ምን ቸገረኝ…ሲያድግ ይተወዋል” ትላለች፡፡
ፍቄ ገና በ21 ዓመቱ አንድ እሁድ ቀን ድንገት ራሱን ስቶ ወደቀ፡፡ ሆስፒታል በገባ በሶስተኛ ቀኑ …እኛንም የሚወዳቸውን ቡናና አርሰናልንም ሳይሰናበት በዚያው ሄደ።
የቀብሩ ዕለት የነበረው ህዝብ ብዛት እስካሁን ሳስበውም ይገርመኛል። በዚያ እድሜው ትምህርቱን ትቶ በሚሰራው ስራ የሚያገኘውን ደመወዝ ሁሉ የሰፈር አቅመደካሞችን ፣ ልጅ ያላቸው የኔ ቢጤዎችን ወዘተ በቋሚነት ይረዳበት እንደነበር ያወቅኩት የለቅሶው ሰሞን ሰዎች ስለርሱ ሲያወሩ በሰማኋቸው ታሪኮች ነው፡፡
በስሙ ትልቅ የእግር ኳስ ግጥሚያ ተዘጋጅቶለትም ነበር፡፡ የዋንጫው ቀን አሸናፊውን ቡድን ስሸልም ስሜቴን መቆጣጠር አቅቶኝ ነበር ፡፡
አሁንም ታዲያ ኳስ በሚታይባቸው ቤቶች በኩል ሳልፍ የደጋፊዎችን ጩኸት ስሰማ ፊቴ ላይ ድቅን የሚልብኝ አሱ ነው ። ምን ያደርጋል ያንን ምድር የማይበቃው የሚመስል ዋልያ …ያች ቀዝቃዛ ቀን እንደዋዛ ይዛው ሄደች....የርሱ መጉደል በቤታችን ይዞት የመጣው ከባድ ሃዘን እናቴን ህመምተኛ አድርጓት ኖሯል፡፡ ባሰብኩት ቁጥር የሚናፍቀኝ ከፊቱ የማይጠፋው ፈገግታ ነው፡፡
ፍቄ ወንድሜ ! ….ነፍስህ በሰላም ትረፍ !!
የሚናፍቅህ ወንድምህ
መላኩ ብርሃኑ

Sponsored by
Surafel
7 months ago
📹በኩዌት የወደቀው አሜሪካዊ ፓይለት እና የነዋሪዎቹ ምላሽ
ዛሬ ጠዋት በኩዌት ሰማይ ላይ በ'ስህተት ተመታ የወደቀችውን የአሜሪካ አየር ኃይል F-15E Strike Eagle አውሮፕላን ፓይለት፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ቀርበው እርዳታ ሲያቀርቡለት የሚያሳይ አዲስ ተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) ወጥቷል።
ነዋሪዎች፦ 'ደህና ነህ?'
ፓይለቱ፦ 'አዎ።'
ነዋሪዎች፦ 'የሚረዳህ ነገር ትፈልጋለህ?'
ፓይለቱ፦ 'አይ፣ ደህና ነኝ።'
ነዋሪዎች፦ 'ችግር የለም፣ ሰላም ነህ። ሰላም ነህ። ሰላም ነህ። እኛን በመርዳትህ እናመሰግናለን።'"

9 months ago
#ethiopia | የሞት ፍርድ ተወሰነ | "እጃችን ምላጩ ላይ ነው!" | የአሜሪካ ዕዳ
| ደህና ነኝ
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...
9 months ago
"በጸሎት አስቡን" – የቅዱስነታቸው ልብ የሚነካ መልእክት በሕክምና ላይ
ባለፉት ቀናት በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ምዕመናን ዘንድ "ቅዱስነታቸው የት አሉ?" የሚለው ጥያቄ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል። ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በሰጡት መግለጫ ስለ ጤንነታቸውና ስላላቸው ተስፋ በግልጽ ተናግረዋል።
📊 የሰጡት መረጃዎችና ዋና ዋና ነጥቦች፦
የጤና ሁኔታቸው፦ ቅዱስነታቸው ባጋጠማቸው ድንገተኛ የጤና መታወክ ምክንያት ባለፉት የጥምቀት እና የቃና ዘገሊላ ታላላቅ በዓላት ላይ በአካል መገኘት አልቻሉም። ሆኖም በአሁኑ ወቅት በሕክምና ክትትል ላይ መሆናቸውንና "ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን" ሲሉ ምዕመናንን አረጋግተዋል።
የምዕመናን ስጋት፦ በማኅበራዊ ሚዲያና በተለያዩ መድረኮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስለ ቅዱስነታቸው ጤንነት ሲጠይቁና ሲጨነቁ መቆየታቸውን ተከትሎ፣ ቅዱስነታቸው ይህን ፍቅርና አሳቢነት እንደሚሰሙ ገልጸው "ስለ ሐሳባችሁ እግዚአብሔር ይስጥልኝ" ብለዋል።
ሐዘንና ጸሎት፦ በኮየ ፈጨ ፋንታ መድኃኔዐለም ደብር በከተራ ዕለት በደረሰ አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ልጆቻቸው ያላቸውን ጥልቅ ሐዘን ገልጸው፣ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን ተመኝተዋል።
ታላቅ ተስፋ፦ ቅዱስነታቸው በመጪዎቹ በዓላት (በተለይ የዐቢይ ጾም ዋዜማና ተያያዥ በዓላት) ላይ እንደወትሮው በዐውደ ምሕረት ተገኝተው ቡራኬ ለመስጠት በከፍተኛ ተስፋ እግዚአብሔርን እየለመኑ መሆኑን ገልጸዋል።
"አሁን በሕክምና ላይ ነው ያለሁት፤ ደህና ነኝ እግዚአብሔር ይመስገን። በሀገር ውስጥም በውጭም ያላችሁ ወገኖቼ... ሁላችሁም በጸሎት አስቡን።" — ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ

ፕሬዝዳንት ትራምፕ በእጃቸው ላይ ስለታየው መቁሰል ማብራሪያ ሰጡ!
ከዳቮስ የዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ወደ ዋሽንግተን በመመለስ ላይ ሳሉ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ በግራ እጃቸው ላይ ስለታየው ግልጽ የሆነ መቁሰል (bruising) በኤር ፎርስ ዋን (Air Force One) ላይ ለተገኙ ጋዜጠኞች ምላሽ ሰጥተዋል።
* እንዴት ቆሰሉ ሲባሉ ?
ፕሬዝዳንቱ እንደገለጹት እጃቸውን ጠረጴዛው "መታ" (Clip) እንዳደደረጋቸው እና ሁኔታው አሳሳቢ እንዳልሆነ ተናግረዋል። "እጄን ጠረጴዛው መታኝ ፣ ከዚያም ትንሽ ቅባት ተቀባሁበት" ብለዋል።
* ለቁስሉ መታየት በየቀኑ የሚወስዱትን አስፒሪን እንደ ምክንያት ጠቅሰዋል። "ለልባችሁ ጤንነት አስፒሪን ውሰዱ፤ ነገር ግን ትንሽ መቁሰልን ካልፈለጋችሁ አስፒሪን አትውሰዱ" ሲሉ በቀልድ መልክ ገልጸዋል።
* ጋዜጠኞች "ደህና ነዎት ወይ?" ብለው ላቀረቡላቸው ጥያቄ፣ "በጣም ደህና ነኝ" ሲሉ አረጋግጠዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የፕሬዝዳንቱ የጤና ሁኔታ በብዙዎች ዘንድ ትኩረት ተሰጥቶት የነበረ ቢሆንም፣ አሁን የሰጡት ማብራሪያ ጉዳዩ ከቀላል ግጭት የመነጨ መሆኑን አመልክቷል።
seledadotio

በብርጭቆ ውስጥ የተደበቀው ሞት፡ የገርጂው ሌሊት የዝምታ ጩኸት
በአዲስ አበባ ሌሊት፣ የገርጂ መብራት ኃይል መንገዶች በብርሃን ተውጠዋል። ነገር ግን በዚያ ብርሃን ውስጥ ጥቁር ጥላ ያጠላባቸው 38 ታሪኮች ትናንት ተመዝግበዋል። በቦሌ ትራፊክ ማኔጅመንት የተያዙት 38 አሽከርካሪዎች ለብዙዎች "ቁጥር" ሊሆኑ ይችላሉ፤ ለሚወዷቸው ቤተሰቦች ግን ሊቆም የነበረ የልብ ትርታ፣ ሊፈርስ የነበረ ትዳር እና ሊጨልም የነበረ ተስፋ ነበሩ።
የአንድ ሰከንድ ክህደት
አልኮል በሰው ልጅ ስነ-ህይወት (Biology) ላይ የሚያደርሰው ተጽዕኖ እጅግ አታላይ ነው። አንድ አሽከርካሪ መጠጥ ሲጀምር፣ አንጎሉ ውስጥ ያለው ዶፓሚን (Dopamine) የተሰኘ ኬሚካል የሀሰት በራስ መተማመን ይሰጠዋል። "ደህና ነኝ፣ እችላለሁ" የሚለው ድምፅ ከአንጎሉ ይወጣል። ነገር ግን በሳይንሳዊ እውነታ፣ የአልኮል መጠን በደም ውስጥ 0.05% ሲደርስ፣ የአይን ትኩረት (Focus) መበተን ይጀምራል።
በገርጂ ኦፕሬሽን የተያዘው አንዱ አሽከርካሪ፣ የትንፋሽ መመርመሪያው ላይ ሲተነፍስ ውጤቱ 0.80 ext{ mg/L} አሳይቷል። ይህ ማለት አሽከርካሪው መኪናውን እየነዳ ሳይሆን፣ መኪናው አሽከርካሪውን እየወሰደው ነበር ማለት ነው። በዚህ ደረጃ ላይ ያለ ሰው፣ ከፊት ለፊቱ የሚሻገርን ህፃን ለማየት ያለው ብቃት በ60% ይቀንሳል። ያ ህፃን የሰካራሙ አሽከርካሪ የገዛ ልጁ ሊሆን ይችላል - ይሄ ነው አሳዛኙ እውነት።
የ3,000 ብር ቅጣት ወይስ የህይወት ዋጋ?
በደንብ ቁጥር 557/2016 መሠረት ከፍተኛው ቅጣት 3,000 ብር ነው። በምሁራን እይታ፣ ይህ ቅጣት "ተመጣጣኝ" የሚባለው አደጋው ሳይደርስ ሲቀር ነው። ነገር ግን አደጋው ከደረሰ በኋላ 3,000 ብር የፈሰሰን ደም አይመልስም፣ የተሰበረን አጥንት አይጠግንም።
የአለም ጤና ድርጅት (WHO) መረጃ እንደሚያሳየው፣ በአፍሪካ በየዓመቱ ከሚሞቱት 1.3 ሚሊዮን ሰዎች መካከል ከፍተኛው ድርሻ የሚይዙት ወጣቶች ናቸው። በገርጂ የተያዙት 38 አሽከርካሪዎች አብዛኞቹ በሀገር ግንባታ ላይ ሊሰማሩ የሚችሉ ወጣቶች መሆናቸው የጉዳቱን ጥልቀት ያሳምመዋል።
አለም አቀፍ ትምህርት፡ ከሞት የታደጉ ህጎች
እንደ ጃፓን ያሉ ሀገራት "የዜሮ መቻቻል" (Zero Tolerance) ፖሊሲን ይከተላሉ። አንድ አሽከርካሪ ጠጥቶ ከተገኘ፣ አሽከርካሪው ብቻ ሳይሆን አብረውት የነበሩ ተሳፋሪዎችና መጠጥ ያቀረበለት ባር ጭምር በህግ ይጠየቃሉ። ይህ "የጋራ ሃላፊነት" ስሜት ይፈጥራል።
በገርጂ የተደረገው ኦፕሬሽን የሚነግረን አንድ ትልቅ ትችታዊ ነጥብ አለ፦ "ቁጥጥሩ መቆም የለበትም።" 780 አሽከርካሪዎች ተፈትሸው 38ቱ ብቻ መያዛቸው፣ ቀሪዎቹ በሺዎች የሚቆጠሩ አሽከርካሪዎች በሌላ መስመር አልፈው ሊሆን እንደሚችል ያሳስባል።
የምሁራን ድምፅ፦ "መንገዱ ማደሪያችን እንዳይሆን"
የከተማ ፕላንና የደህንነት ተመራማሪዎች እንደሚሉት፣ አዲስ አበባ እንደ ገርጂ ባሉ የመዝናኛ ስፍራዎች ላይ ልዩ "የምሽት ትራንስፖርት" ስልት ሊኖራት ይገባል። መጠጥ ቤቶች ደንበኞቻቸው ሰክረው ሲወጡ ቁልፍ እንዲቀበሉ ወይም ታክሲ እንዲጠሩ የሚያስገድድ ማህበራዊ ውል ያስፈልጋል።
መግለጫው እንደሚያሳየው፣ ፍተሻው የተካሄደው ከሌሊቱ 9 ሰዓት ድረስ ነው። ያ ሰዓት የሰው ልጅ የመከላከል አቅሙ ዝቅ የሚልበት፣ እንቅልፍና ስካር የሚደራረቡበት ሰዓት ነው። በዚያ ሰዓት የሚደረግ ፍተሻ ቅጣት ሳይሆን "የህይወት አድን ኦፕሬሽን" ነው።
ማጠቃለያ
የገርጂው 38 አሽከርካሪዎች ዛሬ ቤታቸው ገብተዋል። ምናልባትም 3,000 ብሩን ከፍለው ረስተውት ይሆናል። ነገር ግን በዚያች ሌሊት በመንገዱ ላይ ያልነበረች አንዲት እናት፣ ያልተገጨ አንድ እግረኛ፣ እና ያልፈረሰ አንድ ታክሲ አለ።
አልኮልና መሪ መቼም ቢሆን ጓደኛሞች አይደሉም። አንዱ ሌላውን ለመግደል የሚቆም ጠላት ነው። በብርጭቆ ውስጥ የሚታየው ደስታ፣ በአስፋልት ላይ የሚፈስ ደም እንዳይሆን ሁላችንም ነቅተን ልንጠብቅ ይገባል።

የሳቁ ማኅተም፦ የመጨረሻው መጋረጃ
ፒያሳ ማለዳዋ ሁሌም ትኩስ ናት። የካፌ ማኪያቶ ሽታ፣ የጫማ ጠራጊዎች ጩኸትና የታክሲ ተራ ረብሻ መሀል ግን አንድ ድምፅ ጎልቶ ይሰማ ነበር— የነፃነት ሳቅ። ያ የልጅነት ትዝታን፣ የብሔራዊ ቴአትርን መጋረጃ፣ እና የአባቱን የወርቅነህ ታደሰን የጥበብ ፈለግ የተከተለ ሳቅ። ነፃነት ወርቅነህ ለፒያሳ ጎዳናዎች እንግዳ አልነበረም፤ የሰፈሩ ልጅ፣ የጥበብ ፍሬ፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ኩራት ነበር።
ከወራት በፊት ከህንድ ሀገር ታክሞ ሲመለስ አዲስ አበባ በደስታ አብዳ ነበር። በህንድ ሆስፒታል አልጋ ላይ ሆኖ የጻፈው ያ መልዕክት ዛሬም በሰዎች ልቦና ውስጥ ያስተጋባል። "የሰው ሁሉ ክብር አይጉደልባችሁ... ትራምፕን የጨረፈው ጥይት ነጺንም ጨርፎታል አሉኝ" ብሎ ሲቀልድ፣ ሞትን እንኳ በሳቅ ሊያሸንፈው የሞከረ የጥበብ ጀግና ነበር። "በጣም ደህና ነኝ፣ በቅርብ ቀን እመለሳለሁ" ብሎ ሲፈርም፣ ያ የማይነበብ ፊርማው የህይወት ዋስትና መስሎን ነበር።
ትላንት በኢቢኤስ ስቱዲዮ ተገኝቶ ነበር። ያ የተለመደ ፈገግታው፣ ያ ጨዋታ አዋቂነቱ አልተለየውም ነበር። ለካስ ያ የ"ቤተሰብ ጨዋታ" መሪ፣ የ"ዘመን" ድራማው "ውዴ"፣ የመጨረሻ ስንብቱን እያደረገ ነበር። ያዝ ለቀቅ የሚያደርገው በሽታው ለጥቂት ጊዜ ፋታ የሰጠው መስሎን ብንታለልም፣ የህይወት መጋረጃው ሊዘጋ ጥቂት ሰዓታት ብቻ ቀርተውት ነበር።
ነፃነት ገና በሰባት ዓመቱ "የልጆች ጊዜ" ላይ ሲታይ ጀምሮ የኢትዮጵያ ህዝብ የራሱ ልጅ አድርጎት ነበር። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቴአትር ጥበብ ሰልጥኖ ሲወጣ፣ ጥበብ በደሙ ውስጥ እንደነበረች ማረጋገጫ ሆነ። "የወንድም አማች"፣ "የሞግዚቷ ልጆች" እና "አንድ ለናቱ" በሚሉ ፊልሞቹ የኢትዮጵያን ሲኒማ በሳቅና በቁምነገር አድምቋል። በተለይም በ2016 የህዳሴ ግድብ አዲስ ዓመት መቀበያ ላይ የነበረው ጉልበትና ለሀገሩ የነበረው ፍቅር፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሳይቀሩ "ሁላችንም አዲሱን ዓመት በደስታ እንድንቀበል አድርጎን ነበር" ብለው እንዲመሰክሩለት አስገድዷል።
ዛሬ ግን ፒያሳ ዝም ብላለች። የኢቢኤስ ስቱዲዮ መብራቶች የጠፉ ይመስላሉ። ያ የሦስት ልጆች አባት፣ ያ የብዙዎች ወንድም፣ ያ የጥበብ ቤተሰብ ድምፅ በድንገት ተገታ። "የሲኒማው ፈገግታ በአርባዎቹ መጨረሻ ሞተ" የሚለው ዜና እንደ መብረቅ ሲወርድ፣ ተመልካቹ "ይሄም አንዱ ቀልዱ ቢሆን" ብሎ ተመኘ። ነገር ግን እንደ "ወሬ ነጋሪ" ድራማው፣ ይሄኛው ወሬ እውነተኛና መራራ ሆነ።
ነፃነት ጥበብን የኖራት እንጂ የሰራው ብቻ አልነበረም። ከልጅነት እስከ እውቀት፣ ከመድረክ እስከ ሲኒማ፣ ከህመም እስከ ሳቅ የዘለቀው ጉዞው ዛሬ ፍጻሜ አግኝቷል። የማይነበብ ፊርማው አሁን ትርጉም ሰጠ— ህይወት አጭር ናት፣ ነገር ግን በውስጧ የምናኖረው ሳቅና ፍቅር ዘላለማዊ ነው።
የኢትዮጵያ የጥበብ ሰማይ አንድ ትልቅ ኮከብ አጣ። ነፃነት ወርቅነህ ግን በአድናቂዎቹ ልብ ውስጥ፣ በሰሩት ስራዎቹና በዛ ድንቅ ፈገግታው መቃብር የሌለው ህያው ሆኖ ይኖራል።
ሰላም እረፍ የጥበብ ልጅ፤ አንተ ሰውን ሁሉ ደስ እንዲለው አድርገሃል፣ ዛሬ ግን ተራው የሀዘን ሆኗል።

10 months ago
ባንቺ ተከስተ (ቡቡ)
#ethiopia | በቅርበት ከማውቃቸውና ልዩ ከምላቸው ሰዎች ውስጥ ነበረች።
ድንገት በታወቀ የካንሰር ህመም፤ አደጋ በሚመስል ፍጥነት ተለየችን። የሚያውቃት ሁሉ ምነው ባላወኳት ሲል ልቡ ተሰበረ። እኔ ግን እላለሁ እንኳንም አወኳት። እንኳንም እህቴ ሆነች።
በዚህ ዘመን እንደመልዓክ በዙሪያችን ተከስተው፤ ፈገግ እንዳሉ ብርሃናቸውንና ፍቅራቸውን ነስንሰው፤ ድንገት እንደመጡት ድንገት የሚሄዱ ጥቂት ሰዎች አሉ። እነሱን ማግኘት መታደል ነው። መባረክም ነው። ልባችንን በፍቅር ሞልተው፤ አይምሯችንን በመልካም ሃሳብ ወልውለው፤ ወደውን አፅድተውን የሚሄዱ ጥቂት ናቸው።
ግን እንኳንም አወቅናቸው።
እግዚዓብሄር ሆይ!
እንዲህ አይነቶቹን ቶሎ ትፈልጋቸው ሳለ ግን ደግሞ ስለሰጠኸን እናመሰግንሃለን እንበለው እንጂ አናማረው። የሰጠንም እሱ ነውና!
ህመሟን ልትነግረኝ ደወለችልኝ... እንዴት ነሽ ቡቡዬ? አልኳት።
እግዚዓብሄር ይመስገን! አለችኝና ስራ ይዘሃል? አለችኝ።
ሁልግዜ ነፃ መሆኔን አረጋግጣ ነው ወሬ የምንጀምረው... በቀደም ሳምፕል የተላከው ውጤት መጣ ስትለኝ ፈገግታም ደስታም ያለበት ድምፅ ስለነበር... ውይ ጎሽ ብዬ ውጤቱ ጥሩ ሆነ አይደል? አልኳት...
አዎ ምንም አይልም ያው የሚያሳይ ነገር አለ። አለችኝ
ምን? ስላት... መደንገጥ የለም! በጣም ደህና ነኝ ። ግን እንዲህ እንዲህ ነው... ብላ በሽታውን ቀለል አርጋ ፈገግ እንዳለች እንደቀልድ ነገረችኝ!
ለቀልድም ስለማትዋሽ እኔ ስብርብር አልኩና የሷን ጥንካሬ እንዳልሰብር ብዬ አንዴ ስልክ ልመልስ ብዬ ዘወር ብዬ እራሴን አረጋግቼ ተመለስኩ!
ይህን ነገር የምታውቁት አንተና እልፌ ብቻ ናችሁ ብላ የምትወዳት ጓደኛዋ እልፍነሽ እንደምታውቅ ነገረችኝ። በጣም የምትወዳቸው ሁለት ወንድሞችና አምስት እህቶች አሏት። ከራሷ በላይ የምትወደው ባልና ከአይን የማትለያቸው ሁለት ልጆች አሏት። ታዲያ ይህንን ለኔ የነገረችኝ ጠንካራ ነህ ብላ አይደል?! ለመጠንከር ሞከርኩ። ግን እሷ እንዳሰበችኝ ጠንካራ አማኝ እንዳልሆንኩ ገባኝ።
ያኔ... የኔን እምነት ከሷ እምነት ጋር ለካሁትና ለራሴ አዘንኩ።
ቡቡዬ.... አይዞህ አልሞትም እንዳልሽው አዎ አትሞቺም። መልካም ሰው ነበርሽ ደግሞም ፍፁም ወደ ሆነው አባትሽ ሄድሽ እንጂ አልሞትሽም።
የታመምኩት ለበጎ ነው። የተኮራረፈ እንዲታረቅልኝ፤ የተጠፋፋው እንዲገናኝልኝ ነው አልሽ….
ማነው በስቃይ ውስጥ ሆኖ ሞትን አርግዞ ይህንን የሚያስብ? መልዓክ ካልሆነ በስተቀር!
አይዟችሁ! ለበጎ ነው! ፈገግ በሉ! አላመመኝም! ቀላል ነውኮ!....
የምትያቸው ቃላቶችሽ ጆሮዬ ላይ ናቸው። ፈገግ እንዳልሽ እዝች አለም ላይ ስንመጣ እንጂ ስንሄድ ልናለቅስ እንደማይገባን አስተምረሽናል። ከሺህ ቃላት ይልቅ ያንቺ ተግባር ያነቃል።
ሰው በዚህ ልክ እምነት አለው?!
ሰው በዚህ ልክ መልካሙን ብቻ ያስባል?!
ያንቺስ የተለየ ነው።
ለክፉ ሰው እንጂ ለደግ አይለቀስ እል ነበር። ብችል ባላለቀስኩ! ግን አቃተኝ!
ያንቺ ጥንካሬ፣ ያንች እምነት የለኝም!
ለባለቤቷ ለሃይሉ ተክለስላሴ (ዶ/ር)፤ ለልጆቿ ለጄሪዬና ለናቲ፤ ለወንድሞቿና ለእህቶቿ፤ ለጓደኞቿና በልጅነቷ በኢትዮጵያና አሁንም በአሜሪካን ቨርጂኒያ ግዛት ስትኖር ለምታውቋት ለምትቀርቧት ሁሉ ከዚህ ከባድ ሃዘን እግዚዓብሄር እንዲያፅናናችሁ ምኞቴ ነው።
አብርሃም ወልዴ

ለነፍስ ይሆናችኋልና አግዙኝ!
#ደህና_ነኝ_እግዚአብሔር_ይመስገን " ሲል
ደካማነቴን የነገረኝ #ዐይኑንም_እግሩንም_ያጣው የቀድሞ ሠራዊት መኮንን ሻለቃ አለሙ በዳሳ!
የራዲዮ አፍቃሪ ነው። ራዲዮ ያዳምጣል፣ በአቅሙ ያህልም ይሳተፋል። በተለይ የግጥም ጨዋታችን ላይ ሳያሰልስ ይጫወታል። ከዚህ ባለፈ ፕሮግራሙን ጨርሸ ስወጣ ሁሌም ከሚደርሱኝ ጥሪዎች አንዱ የሻለቃ አለሙ በዳሳ ነው!
ባለፈው ማክሰኞም ደውሎልኝ እንደሁሌውም የፕሮግራማችንን ጥሩነት አድንቆና መርቆኝ ከመሰነባበታችን በፊት፤
#አንተስ_እንዴት_ሰንብተሃል ? አልኩት። #ደህናነኝ_እግዚአብሔር_ይመስገን " አለኝ።
"አይዞህ" ብዬው ስልኩን ከመዝጋቴ ውስጤ በከፍተኛ ማዕበል ተናወጠ!
እናም
"ደህና ነኝ! እግዚአብሔር ይመስገን" ያለበት ድምፁ ጆሮዪ ውስጥ አስተጋባ!
ደርዘን አልኩት ረዳቴን "ሰማሃው?" አልኩት! የምናወራው በመኪናዪ ስፒከር ስለነበር የተባባልነውን ሁሉ ሰምቷል።
ሁለት ዐይኖቹን ያጣው፣ በስኳር ህመም ምክንያት እግሩ የተቆረጠውና በምስሉ ላይ እንደሚታዪው ሌላም ሌላም ተደራራቢ የጤና ችግር ያለበት ይህ ረዳት ዐልባ ሰው፤
"ደህና ነኝ! እግዚአብሔር ይመስገን" አለኝ!
ባለፈው ሳምንት እኔ የወቅቱ ጉንፋን ጥሎኝ ምን ያህል እንደተነጫነጭኩ አስታወስኩ!
እና ሻለቃ አለሙም ይህንን ሁሉ አበሳ ተሸክሞ "ደህና ነኝ!" በማለት እኔ ምን ያህል ደካማ እንደሆንኩ ነገረኝ! እነሆ ድምፁ እስከ አሁን ውስጤን ያምሰዋል!
#ደህና_ነኝ ! #እግዚአብሔር_ይመስገን
ምን ያህል ጽናት ይሆን እንዲህ የሚያሰኘው!!
ለነፍስ ያላችሁ እባካችሁ ይህንን ምስኪን ቤተሰብ ትጎብኟቸው ዘንድ እለምናችኋለሁ!!
የሻለቃ አለሙ ስልክ +251977017627 ነው!
እኒህን የሀገር ባለውለታና ጽኑ መኮንን ማገዝ የምትፈልጉ
በሻለቃ አለሙ በዳሳና በባለቤቱ ወ/ሮ ዘነቡ ስም የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጋራ ሂሳብ ቁጥራቸው፤
1000003617835
ALEMU OR ZENEBU
ይህንን የምታደርጉ ሁሉ ስለእኔ ብላችሁ የምታደርጉት ነውና የማይረሳ ውለታችሁ አለብኝ!!
ስለቸርነታችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ!
#መልእክቱን_በማጋራት_ለብዙዎች_እንዲደርስ_ያድርጉልን !
Via Tesfaye Mamo

11 months ago
ትራምፕ “ሞኞች” በሆኑ ሰዎች ላይ ስለጮኹ ድምፃቸው እንደሻከረ ተናገሩ
ጋዜጠኛ፡ ድምጽዎ ትንሽ የሻከረ/የቆየ ይመስላል፣ ደህና ነዎት?
ትራምፕ፡ አሁን ደህና ነኝ። ሞኞች በነበሩ በሰዎች ላይ እየጮህኩኝ ነበር።
ጋዜጠኛ፡ ድምጽዎ ትንሽ የሻከረ/የቆየ ይመስላል፣ ደህና ነዎት?
ትራምፕ፡ አሁን ደህና ነኝ። ሞኞች በነበሩ በሰዎች ላይ እየጮህኩኝ ነበር።
Sponsored by
Surafel
12 months ago
ደስተኛ የሚመስሉ ግን ብቸኛ የሆኑ ሰዎች፡ ሌሎች የማያስተውሏቸው የብቸኝነት ስሜት የሚሰማቸው ሰዎች 10 ልማዶች
ሁልጊዜ ፈገግ የሚል፣ በሕዝብ መሀል የሚገኝ፣ ነገር ግን ውስጡ ባዶ የሆነን ሰው ከማየት የበለጠ ግራ የሚያጋባ ነገር የለም።
ብዙ ሰዎች ደህና እንደሆኑ ማስመሰል ይችላሉ፤ ነገር ግን ከእነዚያ የሚያብረቀርቁ ዓይኖች ጀርባ ድካም አለ፣ ባዶነት አለ፣ በፍጹም የማይገለጽ ብቸኝነት አለ።
ብቸኝነት ብዙ ጊዜ አይታይም፣ ምክንያቱም ከሳቅና ከደስታ ጀርባ መደበቅ ይወዳል።
ብቸኛ የሆኑ ሰዎች በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች የማያውቋቸው ልማዶች አሏቸው። ውስጣቸው ላለመፍረስ እየታገሉ ቢሆንም፣ ልክ እንደተለመደው ሕይወት የሚኖሩ ይመስላሉ።
ከ"Gediting" እንደተዘገበው፣ በዙሪያቸው ባሉ ሰዎች ብዙ ጊዜ የማይስተዋሉ የብቸኛ ሰዎች አስር ልማዶች እነሆ።
1. ከሌሎች ሰዎች ፊት ጮክ ብሎ መሳቅ
የተከፉ መስለው መታየት አይፈልጉም፣ ስለዚህ ሳቃቸው አንዳንድ ጊዜ ከልክ በላይ ጮክ ብሎ ይሰማል።
ሳቃቸው ብቸኝነታቸውን ሌሎች እንዳይገምቱ የሚከላከል ጋሻ ይመስላል። ሳቁ በጨመረ ቁጥር ልባቸውን የወጋውን የብቸኝነት ስሜት የመደበቅ ዕድላቸው የሰፋ ነው።
2. ሌሎችን በማስደሰት ከመጠን በላይ መጠመድ
ብቸኛ የሆኑ ሰዎች ሌሎችን ለማስደሰት ብዙ ጥረት ያደርጋሉ። መስጠትን፣ ማዳመጥን፣ እንዲሁም ትከሻ መሆንን ይወዳሉ።
ሆኖም ግን፣ የውስጣቸውን ስሜት እምብዛም አያጋሩም። ከዚህ አመለካከት ጀርባ፣ በተመሳሳይ መንገድ እንክብካቤ የማግኘት ጥልቅ ምኞት አለ።
3. በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የቀን ተቀን ጉዳያቸውን መጫን (ፖስት ማድረግ)
ብቸኝነት ብዙ ጊዜ በደስታ በሚመስሉ ጽሑፎች (posts) ይደበቃል። የዕረፍት ጊዜ ፎቶዎች፣ የዕለታዊ ታሪኮች፣ ወይም አበረታች ጥቅሶች ለትኩረት ያላቸውን ፍላጎት የሚገልጹበት መንገድ ሊሆኑ ይችላሉ።በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አለማቸው ደስታ ይታያል፣ ግን ልባቸው ግን በእርግጥ ደካማ ነው።
4. ብቻቸውን ጊዜን ማሳለፍ የበለጠ መምረጥ
በትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎቻቸው፣ በማንበብ፣ በመጻፍ፣ ወይም ፊልም ብቻቸውን በመመልከት የተጠመዱ ሊመስሉ ይችላሉ።
በውጪ፣ ራሳቸውን የቻሉ ይመስላሉ። ሆኖም ግን፣ ይህ የልባቸውን ብቸኝነት የሚረዳቸው ሰው ባጡ ጊዜ የሚቋቋሙበት መንገድ ነው።
5. ሁልጊዜ “ደህና ነኝ” ማለት
የብቸኛ ሰዎች በጣም የተለመደው ልማድ ማስመሰል ነው። እንዴት እንደሆኑ ሲጠየቁ፣ መልሳቸው ሁልጊዜ ማለት ይቻላል ተመሳሳይ ነው፦ “ደህና ነኝ።”
በእርግጥ በልባቸው ውስጥ ሸክም እንዳለ፣ የብቸኝነት ስሜት እንዳለ፣ ለማስረዳት የሚከብድ ባዶነት እንዳለ በሐቀኝነት መናገር ይፈልጋሉ።
6. በትናንሽ ተግባራት ውስጥ መሸሸጊያ መፈለግ
ብቸኛ የሆኑ ሰዎች ብዙውን ጊዜ በቀላል ነገሮች ውስጥ መሸሸጊያ ይፈልጋሉ፦ እንዲሁ መዘዋወር፣ በማስታወሻ ደብተር መጻፍ፣ ተመሳሳይ ሙዚቃ ደጋግሞ ማጫወትና እሱን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ማሳየት፣ ወይም ክፍላቸውን በማስተካከል መጠመድን ያካታል።
ይህ ሁሉ የሚደረገው በእውነት ስለወደዱት ሳይሆን፣ አእምሯቸው በብቸኝነት እንዳይጠፋ ነው።
7. ተግባቢ መስሎ መታየት
እነሱ ተግባቢ ናቸው፣ ለማውራት ቀላል ናቸው፣ እና ሁልጊዜ ወዳጃዊ ናቸው። በዙሪያቸው ያሉ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ግልጽ እንደሆኑ ያስባሉ።
ሆኖም ግን፣ ከዚህ ተግባቢነት ጀርባ፣ የልባቸውን በር የሚከፍቱት እምብዛም ነው።
ማንም ሰው ውስጣዊ ዓለማቸው ምን ያህል ብቸኛ እንደሆነ በትክክል እንዳያውቅ ራሳቸውን ያርቃሉ።
8. ብዙ ጊዜ ታማኝ አድማጭ መሆን
ብቸኝነት የሌሎችን ታሪኮች እንዲያዳምጡ ያደርጋቸዋል። ጓደኞች ውስጣቸውን ማውጣት ሲፈልጉ እምብዛም እምቢ አይሉም እና ሁልጊዜም ትኩረት የሚሰጡ ይመስላሉ።
ነገር ግን፣ የሚገርመው፣ የራሳቸውን ታሪክ የሚናገሩበት ቦታ እምብዛም የላቸውም።
9. በትናንሽ ነገሮች በቀላሉ መነካት
ብቸኛ የሆኑ ሰዎች ለቀላል ነገሮች በቀላሉ ስሜታዊ የመሆን ዝንባሌ አላቸው። አጭር መልእክት፣ ትንሽ ሰላምታ፣ ወይም ምግብ አብሮ የመብላት ግብዣ እንኳን ልባቸውን ሊያሞቅ ይችላል።
እነዚያ ትናንሽ ነገሮች ትልቅ ስጦታዎች ከሚሰጡት በላይ ትርጉም ይኖራቸዋል፣ ምክንያቱም ለረጅም ጊዜ እውነተኛ እንክብካቤ ተሰምቷቸው አያውቅም።
10. ጠንካራ መስሎ መታየት፣ ግን ውስጡ ደካማ መሆን
የሚያሳዩት ጥንካሬ መጋረጃ ብቻ ነው። በትጋት ይሠራሉ፣ ይሳካላቸዋል፣ እና ራሳቸውን የቻሉ ይመስላሉ።
ነገር ግን በእርግጥ ያ ጥንካሬ የሚተርፉበት መንገድ ብቻ ነው። ከዚያ ጽናት ጀርባ፣ ዝምታን ብቻውን ከመሸከም የሰለቸ ልብ አለ።

ወጣቷ በሰዉ እጅ ተገ""ድላ ተገኘች 😭
እናንዬ ትባላለች ወጣትና የአንድ ልጅ እናት ስትሆን በጎንደር ከተማ ማራኪ ክፍለከተማ ነዋሪና ህይወትን ለማሸነፍ ምግብና መጠጥ በመሸጥ ራሷን ታስተዳድር ነበር ።
ከወራት በፊት ግን ለወትሮው እለት ከእለት ተዘግቶ የማያዉቀዉ የእናንንዬ ቤት ድንገት ለቀናት ሳይከፈት ይሰነባብታል ። ይህን የታዘቡ አከራዮች ለቤተሰቦቿ ይደዉላሉ ። ቤተሰቦቿም ያለችበትን ለማወቅ እንዳልቻሉና ለእነሱም ደብዛዋ እንደጠፋባቸዉ ይነግሯቸዋል ቤቷ እንደተዘጋ ይሰነብታል ።
ቀናት ቀናትን እየተኩ ሲሄዱ ቤተሰብ መጨነቅ ና ማፈላለግ ይጀምራሉ ። ከዚህ መካከልም ለቀናት ዝግ በነበረው የእጅ ስልኳ ተከፍቶ ለቤተሰቡ ደህና ነኝ አዲስአበባ በድንገት ስለሄድኩ ገንዘብ ስለቸገረኝ ላኩልኝ የሚል አጭር መልዕክት ለሟቿ ወንድም ይደርሳል ።
ወንድምዬዉም መጀመሪያ ክፉ ነገር ይፈጠራል ብሎ አልተጠራጠረም ነበርና ገንዘቡን ይልካል ። ብሩ እንደደረሳት ለማረጋገጥ ሲደዉል ግን ስልኩ መልሶ ተዘግቷል ለቀናት ለማግኘት ሙከራ ሲያደርግም በፅሁፍ መልዕክት ደህና እንደሆነችና በቅርቡ ወደ ጎንደር እንደምችመለስ በመፃፍ እንጂ በድምፅ ማግኘት አልቻለም ። ይሄኔ በመጠራጠር ማፈላለግ ይጀምራል ሆስፒታል እና ሌሎች ቦታዎች በሚያፈላልግበት ወቅት ይህቺው እናንዬ የተባለችው ወጣት አየሁኝ ሰማሁኝ የሚል በመጥፋቱ ጉዳዩን ወደ የህግ አስፈፃሚዎች በመዉሰድ በስልኳ አማካኝነት በተደረገ ክትትል የሟቿ የእጅ ስልክ እንደተባለው አዲስአበባ ሳይሆን ጎንደር እንደሆነ በጅፒኤስ አማካኝነት ይታወቃል ።
ፖሊስ ክትትሉን በመቀጠል የስልኩን አድራሻ ፈልጎ ሲያገኘዉ ግን እንደተባለው ግለሰቧ ሳይሆን ስልኩን የያዘው ሌላ ግለሰብ መሆኑን ያረጋግጣል ። ይህን ግለሰብም በቁጥጥር ስር በማዋል ምርምራ ይጀመራል ።
በምርመራ ወቅትም ይህ የድሮ ደንበኛዋ የነበረዉ ግለሰቡ እናንዬን መግደሉንና አስከሬኑንም ከከተማ ወጣ ባለ አቡነሐራ አካባቢ በተባለ ሰዋራ ስፍራ መጣሉን ያምናል ። ፖሊስም ወደስፍራው በመሄድ ማጣራቱን ሲቀጥል ከወር በፊት አንዲት ግለሰብ አስከሬን መገኘቱንና ምንም አይነት ማንነቷን የሚገልጽ መረጃ ባለመገኘቱ በመዘጋጃ ቤት አማካኝነት መቃብሯን ያረጋግጣል ።
በዚህ መልክ ተገድላ የተገኘችው የእናንዬ አስከሬን በማዘጋጃ ቤት ቤተሰብ ከሌላቸው መቀበርያ ቦታ ወጥቶ ወደ ትዉልድ ከተማዋ ደባርቅ መወሰዱንና በአስከሬን ምርመራ ወቅትም በሰዉ እጅ በአሰ""ቃቂ ሁኔታ መገደሏን ያረጋገጠው ፖሊስ ተጠርጣሪውን በህግ ጥላ ስር በማዋል የክስ ሂደት ላይ እንደሆነ ከጎንደር ካሉ የመረጃ ምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ኃይለኛ የፕሮስቴት ካንሰርን ለመዋጋት የጨረር እና የሆርሞን ሕክምና ጀመሩ
#ethiopia | የ82 ዓመቱ የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ በምርመራ የተገኘባቸውን ኃይለኛ የፕሮስቴት ካንሰርን ለመቋቋም የሚያስችል የጨረር (ራዲዬሽን) እና የሆርሞን ሕክምና መጀመራቸውን ዛሬ አስታወቁ።
ዶክተሮች እንደገለጹት የካንሰሩ ግሊሰን (Gleason) ነጥብ 9 ከፍተኛ ደረጃ ላይ ቢገኝም እና በሽታው ወደ አጥንቶች ቢዛመትም፣ ካንሰሩ ለሆርሞን ስሜታዊ (Hormone-Sensitive) በመሆኑ ውጤታማ በሆነ መንገድ በሕክምና ሊታከም የሚችል ነው።
ባይደን አሁንም በተስፋ እና ብርታት ላይ ሲሆኑ፥ “ትንበያው መልካም ነው... ደህና ነኝ” በማለት ተናግረዋል።
የፕሮስቴት ካንሰር በአሜሪካ ወንዶች ዘንድ እጅግ የተለመደ የካንሰር ዓይነት ሆኖ ቢቀጥልም፣ በጊዜ መታወቅ እና በሕክምናው መስክ የተገኙት ውጤቶች በሕይወት የመቆየት ምጣኔን ከ98% በላይ ከፍ አድርገዋል።#menaheriyafm

Comments