3 days ago
የአስዋን ግድብ ያለ ተፋሰስ ሀገራት ስምምነት የተገነባና በርካቶችን ለጉዳት የዳረገ ፕሮጀክት መሆኑ ተገለጸ
#ethiopia | የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ሃብታሙ ኢተፋ እንደተናገሩት፣ ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ የገነባችው የአስዋን ግድብ ከማንኛውም ቅድመ ውይይትና የጋራ ስምምነት ውጭ በራሷ ውሳኔ ብቻ የተከናወነና የጥፋት አሻራ ያረፈበት ስራ ነው።
ካይሮ የዓባይ ውሃ ዋነኛ ምንጭ የሆነችውን ኢትዮጵያን ሳታማክርና ፈቃድ ሳታገኝ ግድቡን በመገንባቷ፣ ሌሎች ሀገራት ከወንዙ ፍትሃዊ ጥቅም እንዳያገኙ እንቅፋት ሆና ቆይታለች ብለዋል።
ግንባታው በተካሄደበት ወቅት ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኑቢያ ማህበረሰብ አባላት ከቀያቸውና ከተወለዱበት መኖሪያቸው እንዲፈናቀሉ መደረጉን ታሪካዊ መረጃዎች ያረጋግጣሉ።
ይህም በዜጎች ላይ ከፍተኛ የማህበራዊና የኢኮኖሚ ቀውስ አስከትሏል።
በተቃራኒው ኢትዮጵያ የገነባችው የታላቁ ህዳሴ ግድብ እ.ኤ.አ በ2015 በተፈረመው የመርሆች መግለጫ መሠረት በግልጽ ውይይት የተከናወነ ነው።
በመሆኑም ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የምታቀርበው ትችት ምንም ዓይነት የሞራልም ሆነ የምክንያታዊነት መሠረት የለውም።
በመጨረሻም ሚኒስትሩ አክለው እንደተናገሩት፣ ግብፅ የሌሎችን ፍትሃዊ የልማት ጥያቄ ከመኮነኗ በፊት፣ የአስዋን ግድብን ያለ ተፋሰሱ ሀገራት ፈቃድ ለምን እንደገነባችና ንጹሃን ኑቢያውያንን ለምን ለስደትና ለእንግልት እንዳዳረገች ግልጽ ምላሽ መስጠት አለባት።
#ህዳሴግድብ #አባይ #የአስዋን_ግድብ #ኢትዮጵያ #ግብፅ #gerd #nile #aswandam #ethiopia #egypt #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

9 months ago
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማክሰኞ ዕለት እንደተናገሩት አሜሪካ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) ግንባታን በገንዘብ እንደረዳች ገልጸው ይህ ውሳኔ የግብፅን የውሃ ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል "አስከፊ ነገር" ነው ብለውታል።
በዋይት ሃውስ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ትራምፕ እንደገለጹት አሜሪካ በአባይ ወንዝ ላይ ለሚገነባው ለዚህ ግዙፍ ፕሮጀክት የሚሆን ገንዘብ መስጠቷን አረጋግጠው ሆኖም የትኛው አስተዳደር ክፍያውን እንደፈቀደ እርግጠኛ እንዳልሆኑ ተናግረዋል።
ትራምፕ ሲናገሩ ለግድቡ ክፍያውን ማን እንደፈጸመ ታውቃላችሁ? አሜሪካ ናት ብለዋል።
እኛ ነን በገንዘብ የደገፍነውይህች ሀገር አላውቅም ምናልባት የሪፐብሊካን ፕሬዝዳንት ሊሆን ይችላል ግን አይመስለኝምየዴሞክራት ፕሬዝዳንት ይመስለኛል በማለት ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንቱ ግድቡን ለግብፅ "በጣም ከባድ ሁኔታ" እንደሆነ ገልጸውግብፅ ቱሪዝምን እና መሰረታዊ የውሃ ፍላጎትን ጨምሮ ለህልውናዋ በአባይ ወንዝ ላይ በእጅጉ እንደምትደገፍ ተናግረዋል።
ግድቡ የወንዙን ፍሰት "በመግታት" የታችኛው ተፋሰስ ጎረቤቶችን ለአደጋ እንደሚያጋልጥም ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህን ቢሉም በታሪክም ሆነ በሰነድ ደረጃ ኢትዮጵያ የታላቁን የህዳሴ ግድብ የገነባችው በገዛ ራሷ የውስጥ አቅም እና በህዝቧ መዋጮ እንጂ በአሜሪካ መንግስት የገንዘብ ድጋፍ እንዳልሆነ ይታወቃል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ
የታላቁ ህዳሴ ግድብ መፍረስ በሱዳንና ግብፅ ላይ ሊያስከትል የሚችለው የጥፋት ማዕበል
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) በአሁኑ ወቅት ከ70 ቢሊዮን ሜትር ኩብ በላይ ውሃ የመያዝ አቅም ያለው ግዙፍ ግንባታ ነው።
ይህ ግድብ በሰው ሰራሽ ስህተት በተፈጥሮ አደጋ (እንደ የመሬት መንቀጥቀጥ) ወይም በጦር መሣሪያ ጥቃት ቢፈርስ በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት (ሱዳንና ግብፅ) ላይ የሚከተለው አደጋ "ታሪካዊ ጥፋት" ተብሎ ሊገለጽ ይችላል።
1. በሱዳን ላይ የሚደርሰው ፈጣንና አስከፊ ውድመት
ከግድቡ መገኛ ቅርበት የተነሳ ቀጥተኛውንና ከፍተኛውን ድንገተኛ አደጋ የምታስተናግደው ሱዳን ናት።
ግድቡ በድንገት ቢፈርስ የሚለቀቀው የውሃ ናዳ በሰዓታት ውስጥ የሮዚሪስ (Roseires) እና የሴናር (Sennar) ግድቦችን ጠራርጎ ይወስዳል ዋና ከተማዋ ካርቱም በከፊል ወይም በሙሉ ልትጠልቅ የምትችልበት ዕድል ሰፊ ነው።
በአባይ ወንዝ ዳርቻ የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሱዳናውያን ለድንገተኛ ሞትና መፈናቀል ይዳረጋሉ።
የሱዳን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች፣ ድልድዮችና የግብርና ማሳዎች ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጭ ይሆናሉ።
2. በግብፅ ላይ የሚደርሰው የረጅም ጊዜ ስጋት
ምንም እንኳ ግብፅ ከግድቡ ርቃ ብትገኝም አደጋው እስከ ታላቁ የአስዋን ግድብ ድረስ ይደርሳል።
ወደ ግብፅ የሚፈሰው የውሃ መጠን ከአስዋን ግድብ የመሸከም አቅም በላይ ከሆነ የአስዋን ግድብ ደህንነት አደጋ ላይ ይወድቃል የአስዋን ግድብ ካልተቋቋመ ግን መላው የናይል ሸለቆና የካይሮ ከተማ በውሃ የመጥለቅ አደጋ ይጋረጥባቸዋል።
ግድቡ ሲፈርስ ይዞት የሚመጣው ከፍተኛ ደለልና ፍርስራሽ የታችኛው ተፋሰስ ግድቦችን በደለል በመሙላት የአገልግሎት ዘመናቸውን ያሳጥረዋል።
ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅን ተከትሎ የውሃ ወለድ በሽታዎች (እንደ ኮሌራ) በስፋት በመሰራጨት በሕዝብ ጤና ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳሉ።
በሁለቱም ሀገራት የሚገኙ ሰፋፊ የግብርና መሬቶች በመውደማቸው ምክንያት ለዓመታት የሚቆይ የረሃብና የኢኮኖሚ ውድቀት ይከሰታል።

10 months ago
የግብፅ ሚዲያዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ዜጎችን ዋሽተዋል - ግብጻዊ አክቲቪስት
የግብጽ ሚዲያዎች ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሳሳች መረጃ በማቅረብ ሕዝቡን ሲያሳስቱ ነበር አሉ ግብጻዊው አክቲቪስት ሃምዲ ሱሌይማን፡፡
ከፋና አረብኛ ፖድካስት ጋር ቆይታ ያደረጉት ሱሌይማን፥ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በግብፅ እና ሱዳን ላይ ምንም አይነት ስጋት እንደሌለው ተናግረዋል።
ግድቡ በዋነኛነት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨትና ኃይል ካመነጨ በኋላ ውሃው ተፈጥሯዊ ሂደቱን ጠብቆ ወደ ተፋሰስ ሀገራት የሚሄድ በመሆኑ ለግብጽም ሆነ ለሌሎች የተፋሰሱ ሀገራት ስጋት የለውም ነው ያሉት፡፡
ስለ ግድቡ መፍረስና ስለ ግብፅ የውሃ ደህንነት ስጋት የሚሰራጩ የስጋት መረጃዎች ትክክል እንዳልሆኑ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለሰላም፣ ለትብብርና ከግብፅ ጋር ጥሩ ግንኙነት ለመመስረት እውነተኛ ፍላጎት እንዳላት መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡
የግብጽ መንግሥት ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሕዝቦችን የሚመለከትበት መንገድ ልክ እንዳልሆነም አስረድተዋል፡፡
ግብጻዊው አክቲቪስት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን ከኢትዮጵያ ይልቅ የአፍሪካ ፕሮጀክት አድርገው እንደሚመለከቱ አብራርተዋል፡፡
በዚህም የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ባላቸው የተፈጥሮ ሀብት ላይ የራሳቸውን ውሳኔ እንዲሰጡ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡
በግብፅ የአስዋን ግድብ የኑቢያ ነዋሪዎችን እንደሚያፈናቅልና ለበሽታ እንደሚያጋልጥ ገልጸው፥ ግድቡ የግብፅን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ማሟላት አለመቻሉን ጠቁመዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመላው አፍሪካ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጠቅሰው፥ ኢትዮጵያ የባሕር በር በማግኘት የኢኮኖሚ ዕድገቷን ታጠናክራለች ነው ያሉት፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በግብርና እና በመሠረተ ልማት ዘርፍ ልማትን ለማፋጠን የሚያደርገውን ከፍተኛ ጥረት መመልከታቸውንም ገልጸዋል።
FBC

#ethiopia | የግብጽ ሚዲያዎች ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሳሳች መረጃ በማቅረብ ሕዝቡን ሲያሳስቱ ነበር አሉ ግብጻዊው አክቲቪስት ሃምዲ ሱሌይማን፡፡

የኢትዮጵያ መንግሥት በግብርና እና በመሠረተ ልማት ዘርፍ ልማትን ለማፋጠን የሚያደርገውን ከፍተኛ ጥረት መመልከታቸውንም ገልጸዋል። #fmc

1 year ago
ግብፅ ክስ መሠረተች‼️
በኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች የደስታና የፌሽታ ቀን ግብፅ ለተመድ ፀጥታው ምክር ቤት የክስ ደብዳቤ ይዛ ሄዳለች።
ደብዳቤው ምንም የተለየ ነገር የሌለው ሲሆን " ግድቡ ለብቻ በተወሰደ እርምጃ የተሰራና ዓለም አቀፍ ህጉን የጣሰ ነው " የሚል የተለመደ ክሷን የያዘ ነው።
" የግድቡ ምርቃት ኢትዮጵያ ከዚህ በፊት የፈፀመቻቸው ጥሰቶች ላይ የተጨመረ አዲስ ጥሰት ነው " የሚል አስቅኝ ክስም አቅርባለች።
" እኛ እና ሱዳንን የመኖር ጥያቄ ውስጥ የሚከት ተግባርን አልቀበልም። እራሴን አቅቤ ተመድን ጨምሮ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመስራት ስሞክር ቆይቻለሁ በዲፕሎማሲ ላይ መተማመን የመኖር ስጋቴን ለመከላከል አለመቻል አይደለም " የሚል የተለመደ ፉከራዋን አሰምታለች።
" ኢትዮጵያ በብቸኝነት የጋራ የውሃ አካላትን እንድታስተዳድር አልፈቅድም ጥቅሜን ለማስጠበቅ በዓለም አቀፍ ህግ ስር ያሉ ሁሉንም እርምጃዎች እወስዳለሁ " ስትልም ሌላ ፉከራ አሰምታለች።
ግብፅ ከግድቡ መጀመር አንስቶ ባለፉት 14 ዓመታት ተመሳሳይ ክስ ስታሰማና ስትፎክር ነው የኖረችው ነገር ግን ግድቡ ተጠናቆ እንዳይመረቅ ማድረግ አልቻለችም። ሀገሪቱ በይፋ በአደባባይ ግድቡ ዳር እንዳይደርስ ስትሰራ ኖራለች ግን ምንም አላመጣችም።
ኢትዮጵያ ግድቡ ማንንም እንደማይጎዳ ስትገልፅ ቆይታለች።
ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ግድቡ ለጎረቤቶችም ሆነ ለታችኛው ተፋሰስ ሀገራት በረከት እንደሆነ አንድም ቀን ኢትዮጵያ ሌሎችን ለመጉዳት አስባ እንደማታውቅ አስረግጠው ተናግረዋል።
በግድቡ ስራ የተሳተፈው የዊ ቢዩልድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፒትሮ ሳሊኒ የህዳሴ ግድብ ውሃ ሞልቶ በሚፈስበት ጊዜ የአስዋን ግድብ ውሃ አለመቀነሱ ሲወሩ የነበሩ ወሬዎች ሁሉ ውሸት መሆናቸውን ያሳየ እንደሆነ ዛሬ በምርቃቱ ላይ ተናግረዋል።
seledadotio

ግብፅን የጎዳት አባይን እንደሯሷ ማየቷ ነው። በህዳሴ ግድብ መናደድ ሳይሆን ያለባት ከአባይ ወንዝ ውጭ ሌላ የሀይል አማራጭ ማየት ነው ያለባት
ግብፅ በአባይ ወንዝ ዙርያ ኢትዮጵያ ላይ ያደረሰችው በደል አሳፋሪም አሳዛኝም ነው። "ባበላሁ እጄን ተነከስኩ "የሚለው አባባል ለዚህ የሚሰራ ይመስላል።ከኢትዮጵያ ለሚነሳ ወንዝ ኢትዮጵያን እንሰማመስገን አትጠቀሚ ብሎ ማመመፅ ፣መዛት ፣ሴራ መጎንጎን ትዝብት ውስጥ የሚከት ተግባር ነው።
አሁን በኢትዮጵያ አባይ ከሀገሩ ውሃ፣አፈር እና ግንድ ብቻ ይዞ ይወጣል ተብሎ አይወቀሰም። የመጀመሪያ ቤቱን ለኢትዮጵያ ሰርቷል።
‘ግብጽ የናይል ስጦታ ናት’ የሚለው የግሪክ ታሪክ ጸሐፊ ሄሮዶተስ አባባል ስህተት ሲሆን፣ ለዘመናት ሲነገር የኖረ በመሆኑ በየግብጻዊው አእምሮ ውስጥ አሁንም ድረስ በስህተት ተቀርጾ ይገኛል። እንደገናም ለዘመናት የፖለቲካ መሪዎቻቸው የናይል ወንዝ መነሻ ኢትዮጵያ መሆኗን እና ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ረጅሙ ወንዝ 0.1 ዋት እንኳ የኤሌክትሪክ ኃይል እንደማታገኝ ነግረዋቸው አያውቁም። እንዴት ያለ አስገራሚ ነገር ነው! ወንዙ የሚመነጨው ከግብጽ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ስለሆነ፣ ሄሮዶተስ ‘ኢትዮጵያ የናይል ስጦታ ናት’ ብሎ ቢናገር በተሻለ ነበር።
አንድ ቢሊዮን ዶላር ወጥቶበት ከፍተኛ የአስዋን ግድብ ሲገነቡ፣ የወንዙ የውሃ መጠን 85 በመቶ የሚሆነውን ለያዘችው ኢትዮጵያ የምክክር ጥያቄ አላቀረቡም። ነገር ግን፣ ለራሳቸው መብት የሌላቸውን የሌላ አገር ግድብ ለመቆጣጠር ይፈልጋሉ። ይህ ደግሞ ራስ ወዳድነትን ያሳያል።
እንደ አብዛኞቹ የአፍሪካ አገሮች ሁሉ፣ ኢትዮጵያ ከድህነት ወለል በላይ ለመውጣት የሚያስችላት ሀብት ያላት ድሃ አገር ነች። በናይል ወንዝ ላይ ግድብ መገንባት ደግሞ ከ110 ሚሊዮን ሕዝቧ ውስጥ 70 ሚሊዮን የሚሆኑት የኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ያለባቸውንና በምሽት በሻማ ብርሃን የሚኖሩትን ሕዝብ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ለማሟላት ከሚረዱት መንገዶች አንዱ ነው። የግብጽ ፖለቲከኞች ግን ይህንን መስማት አይፈልጉም፤ ናይል ወንዝ ለግብርናቸው እና ለኃይል ፍላጎታቸው ውኃ እስካፈሰሰላቸው ድረስ።
ናይል ወንዝ ከካይሮ ተነስቶ ለኢትዮጵያ እንደ ግብጽ አሁን ለዘመናት ስታገኝ እንደኖረችው ሁሉ ለኤሌክትሪክ ኃይልና ለመስኖ ሥራ ውኃ ቢሰጥ፣ ግብጻውያን ዝም አይሉም ነበር።ነገርን በሰው ጫማ ማየት ጥሩ ነው።
ነገር ግን፣ በግብጽ ያለው ችግር ራሳቸውን በኢትዮጵያውያን ቦታ አድርገው ማየት አለመፈለጋቸው ነው። በነጮች ቅኝ ያልተገዛች እና በጣሊያን ወራሪ ኃይሎች ላይ ድል የተቀዳጀች ብቸኛዋ አገር ኢትዮጵያ፣ እራሷን ለመለወጥ የሚያስችል እጅግ በጣም ብዙ ሀብት እያላት አሁንም በድህነት እየተሰቃየች ነው።
በርካታ የግብጽ ፖለቲከኞች ሁሉንም ከግዙፉ ግድብ ከዓለም ባንክ እና ከሌሎች ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ኢትዮጵያ ብድር እንዳታገኝ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት አድርገዋል። ለቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ምስጋና ይገባቸዋል፣ ‘ግድቡ የሚገነባው በኢትዮጵያውያን እና በኢትዮጵያ መንግስት ነው’ በማለት የአምስት ቢሊዮን ዶላር ወጪ ግድቡን በይፋ አስጀመሩት።
በቀድሞና በወቅቱ የነበሩ የግብጽ መንግስታት ላይ ያለው ችግር፣ ከናይል ውጭ ለመስኖ እና ለሀይድሮ ፓወር ሌላ መፍትሔ የሚያዩበት ‘ፕላን ቢ’ የላቸውም። ኢትዮጵያ ከናይል ወንዝ አንድ ማንኪያ ውኃ እንድትጠቀም አይፈልጉም። ይህ ስግብግብ አስተሳሰብ ነው። ምን ዓይነት የሥነ-ምግባር ጉድለት ነው? ለአፍሪካ ረጅሙ ወንዝ መነሻ ሆና እራሷ በውሃ እጥረት እየተሰቃየች፣ ለብዙ እና ለብዙ ዓመታት ውኃ እንድትጠቀም እየፈቀደች ያለችውን አገር አንቺ አትጠቀሚም ማለት?
በፀሐይ ኃይል፣ በንፋስ ኃይል፣ እና በመስኖ ላይ በሰፊው መስራት ለግብጽ ሌላ መፍትሄ ቢሆንም፣ በጣም በትንሽ መጠን ነው የሚጠቀሙበት። በሚሊዮን የሚቆጠረው ኪዩቢክ ሜትር ውኃው በተለያዩ ቦታዎች እየባከነ ከሚገኘው የኮንጎ ወንዝ ቦይ በመገንባት ውኃ ማግኘት ይችላሉ። ነገር ግን ግብጻውያን ከአማራጭ መፍትሄዎች ላይ ትልቅ እቅድ ማውጣት አይፈልጉም፤ ምክንያቱም ከናይል ውጭ ‘ፕላን ቢ’ ስለሌላቸው ነው።
ይህ ደግሞ በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ የመጣ ሕዝብ ያላት እና የሕዝቧን የኢኮኖሚ ፍላጎት ለማሟላት በሀብቶቿ ላይ የሆነ ነገር ማድረግ የሚገባት የላይኛው ተፋሰስ አገር ላይ ምንም ትርጉም አይሰጥም።
በአባይ ወንዝ ላይ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አንድ ብላ የመጀመሪያ ግድብ ጀምራለች ። ነገም የህዝቧን ፍላጎት እያያች ሌላ ግድብ መገንባቷ አይቀርም። ግብፅ ኢትዮጵያን ግድብ አትገንብቢኝ በማለት መጨቃጨቅ ሳይሆን ከዚህ ወንዝ ውጭ ሌላስ ነገር ምን ልጠቀም? ምን ላይ ምርምር ላድርግ ብላ ነው መጠየቅ ያለባት።

Sponsored by
Surafel
Comments