4 months ago
ትራምፕ ለኢራን መሳሪያ መሸጥ ክልክል ነው አሉ
#ethiopia | የቀድሞውና ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በለመዱትና በወደዱት “የታሪፍ ጦርነት”ስልታቸው ዳግም ብቅ ብለዋል። ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት፣ ለማንኛውም ለኢራን የጦር መሳሪያ ለምታቀርብ አገር የአሜሪካ ገበያ ደጃፍ እንደሚዘጋባት በግልጽ አስታውቀዋል።
ማንኛቸውም የኢራን ወዳጅ ወይም አጋር የሆኑ አገራት ለቴህራን ወታደራዊ ድጋፍ ካደረጉ፣ ወደ አሜሪካ በሚልኩት ማናቸውም ምርት ላይ 50% ታሪፍ ይጣልባቸዋል።
ትራምፕ ማስጠንቀቂያው ሁሉንም የንግድ ዘርፎች እንደሚያካትትና ከአሜሪካ ቀረጥ የሚያመልጥ ምንም ዓይነት ምርት እንደማይኖር አስገንዝበዋል።
አሜሪካ እና ኢራን ለረጅም ጊዜ “የሰላም መንገድ” ሲጓዙ መቆየታቸውን የጠቀሱት ትራምፕ፣ ይህ እርምጃቸው ግን የዋሽንግተንን ቀጣይ ዲፕሎማሲያዊ አቅጣጫ ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል።
ይህ የትራምፕ ጠንካራ ዛቻ የመጣው ቀጣናው በሁለት ሳምንት የተኩስ አቁም ስምምነት ውስጥ ባለበት ወቅት መሆኑ፣ ስምምነቱን አደጋ ላይ ሊጥለው ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሯል። በተለይም ከቴህራን ጋር የንግድና የወታደራዊ ትብብር ያላቸው አገራት በአሜሪካ የኢኮኖሚ ማዕቀብ እና በኢራን ወዳጅነት መካከል እንዲወዛገቡ የሚያደርግ ነው።
“ይህንን እያወቁ ያድርጉት” ሲሉ ያስጠነቀቁት ትራምፕ፣ በቀጣይ የንግድ ግንኙነቶች ላይ የፖለቲካ ታማኝነት ዋነኛው መስፈርት እንደሚሆን ፍንጭ ሰጥተዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ትራምፕ #ኢራን #የንግድጦርነት #ታሪፍ #አሜሪካ #ዓለምአቀፍዜና #trump #iran #tariffs

Comments