21 days ago
3 ልጆቿን በገመድ አንቃ የገደለችው ሌንዚ ክሌንዚ በአንዱ ዳኛ ውሳኔ እስሯ ጸና
#ethiopia | በአሜሪካ ማሳቹሴትስ ሶስት ህጻናት ልጆቿን በማነቅ በመግደል የተከሰሰችው የቀድሞዋ ነርስ ሌንዚ ክሌንዚ ጉዳይ በመላው አለም ከፍተኛ እንደሆነ ቀጥሏል።
ተከሳሿ ጥፋቱን የፈጸመችው ከወሊድ በኋላ በሚከሰት (Postpartum Psychosis) ምክኒያት መሆኑን የተከራከሩት ጠበቆቿ፣ ነጻ እንድትወጣ ሙግት ያቀረቡ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ ከተሰየሙት 12 የዳኞች ስብስብ መካከል 11ዱ «በአእምሮ ህመም ምክንያት ጥፋተኛ አይደለችም» የሚል ውሳኔ ላይ ደርሰው ነበር።
ሆኖም ግን በዳኞች ስብስብ ውስጥ የነበሩት ብቸኛው ጥቁር እና በ30ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኙት አባል ውሳኔውን ባለመቀበላቸው በእስር እንድትቆይ ሆኗል።
ይህ የዳኛው አቋም የችሎቱን ክርክር እንዲቀጥል ያደረገ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የስነ-ልቦና እና የህግ ክርክሮችን ቀስቅሷል።
አንዳንዶች የተከሳሿን የአእምሮ ጤና ሁኔታ በሽፋንነት በመውሰድ ነጻ መውጣቷን ሲደግፉ፣ ሌሎች ደግሞ የተጎዱትን ህጻናት ህይወት በማሰብ በምንም አይነት መስፈርት ያለ ቅጣት ማለፍ የለባትም እያሉ ነው።
የእናንተስ ሃሳብ ምንድን ነው?
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago
ሶማሊያ በአማራ ክልል በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለኢትዮጵያ ማጽናኛ እና ሐዘኗን ገለጸች
#fastmereja I የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በአማራ ክልል በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች፣ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን ገለጸ።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ አገሪቱ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከኢትዮጵያ ጎን እንደምትቆም አስታውቃለች። ሚኒስቴሩ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች ቤተሰቦች እና ወዳጆች መጽናናትን የተመኘ ሲሆን፣ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ደግሞ በፍጥነት እንዲያገግሙ መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።
በተጨማሪም በአደጋው አካባቢ የተጎዱትን ለመታደግ እና የጎደሉትን ለመፈለግ እየተደረገ ያለውን የእርዳታና የመፈለግ ስራ ያደነቀው የሶማሊያ መንግሥት፣ በጸሎት እና በሐሳብ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር እንደሚገኝ አረጋግጧል።

4 months ago
"እስከ መቼ?"
📌ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያናችን እና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።
ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
ቅዱስነታቸው ያስተላለፉት አባታዊ የኀዘን መልእክት እንደሚከተለው ነው፦
መልእክተ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
‹‹ወረሰዩ አብድንቲሆሙ ለአግብርቲከ መብልዐ ለአዕዋፈ ሰማይ፣ ወሥጋሆሙኒ ለጻድቃኒከ ለአራዊተ ገዳም፦ የአገልጋዮችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የቅዱሳንህንም ሥጋ ለምድር አራዊት።››
(መዝሙረ ዳዊት ፸፰፥፪)
በአርሲ ሀገረ ስብከት በአሰኮ፣ በሽርካ፣ በሆንቆሎ፣ በዋቤ እና በሙኔሳ ወረዳዎች በመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችንና በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ ስለደረሰው አሰቃቂ ጥቃት የሰማነው በተሰበረ ልብ ነው።
የእምነት ነፃነት ተደፍሮ መቶ ዓመታት ያስቆጠረው የጠላታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በተቃጠለበት፣ እንዲሁም የካራ ኩፍቴና መድኃኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን በተዘረፈበት በዚህ ክፉ ቀን፤ በርካታ ምእመናን በግፍ መሰዋታቸውና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ቤተ ክርስቲያናችንን በእጅጉ ያሳዘነ ክስተት ነው።
የሰላም፣ የፍቅርና የታሪክ ማህደር የሆነችው ቤተ ክርስቲያን በምድራዊ መከራ ውስጥ ያሉትን ምእመናን በምታጽናናበት በዚህ ወቅት ራሷ በፈተና ውስጥ ሆና ከመቸገሯም በላይ በአርሲ ምድር በተደጋጋሚ የሚስተዋለው በደልና ግፍ በሁላችንም ልቡና ውስጥ "እስከ መቼ?" የሚል የቁጭት እና የኀዘን ጥያቄን ፈጥሯል።
በመሆኑም ይህ መከራ እያበቃ ሳይሆን እየሰፋ በመምጣቱ የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅና ሰላምን የማስፈን አደራ የተጣለባችሁ የጸጥታ አካላትና በየመዋቅሩ ያላችሁ ሓላፊዎች ከምንም በላይ ታሪክ የሚጠይቃችሁ በሥልጣን ዘመናችሁ ለዜጎች ደኅንነት በምትከፍሉት ዋጋ ነውና ይህንን የጥቃት ሰንሰለት በማስቆምና ወንጀለኞችን ለሕግ በማቅረብ ከታሪክ ባለዕዳነት ትድኑ ዘንድ በቤተ ክርስቲያናችን ስም አበክረን እናሳስባለን።
በየአካባቢው የምትገኙ ምእመናንና መላው ኢትዮጵያውያንም በወንድማማችነት መንፈስ ተጋግዛችሁ፣ የተፈናቀሉ ወገኖችን በመደገፍና በጸሎት ከቤተክርስቲያናችን ጎን እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናቀርባለን።
በመጨረሻም ቤተ ክርስቲያናችን ለሰላም፣ ለይቅርታና ለሰው ልጆች ክብር ሁል ጊዜ የምትቆም መሆኑን በመግለጽ ይህንን የኀዘን ሰዓት አምላካችን በምሕረቱ ያሳልፍልን፣ የሞቱትን ነፍሶቻቸውን በመንግሥቱ ይቀበልልን፣ የተጎዱትንም በቸርነቱ ያጽናናልን በማለት አባታዊ የኀዘን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን።
እግዚአብሔር አምላክ ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ!!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
አሜን።
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ግንቦት 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
© የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በአርሲ ሀገረ ስብከት በቤተ ክርስቲያናችን እና በኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በማስመልከት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

7 months ago
ኳታር በኢነርጂ ተቋማት ላይ በደረሰ ጥቃት የ20 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ ገጠማት
በኳታር የኢነርጂ ተቋማት ላይ በደረሰ ጥቃት ሀገሪቱ በየዓመቱ የ20 ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደምታጣ አስታወቀች።
የኳታር የኢነርጂ ሚኒስትር ሳድ ሸሪዳ አል ካቢ እንደገለጹት፣ ጥቃቱ የፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ (LNG) የወጪ ንግድ አቅምን በ17 በመቶ ቀንሶታል።
እንደ ሚኒስትሩ ገለጻ፣ የተጎዱትን የጋዝ ማጣሪያ ተቋማት በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ለመመለስ እና ጉዳቱን ለመጠገን ከሶስት እስከ አምስት ዓመታት ሊፈጅ ይችላል።
ይህ መስተጓጎል በተለይ ከኳታር ጋዝ በሚያስገቡት እንደ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጣሊያን እና ቤልጂየም ባሉ ሀገራት ላይ ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት ተጽዕኖ ይኖረዋል።

Sponsored by
Surafel
7 months ago
የመምህር ዘለዓለም ወንድሙ የሕይወት ታሪክ
ወንድም ተዋበ ወንድሙ እንዳነበበው
#ethiopia | የተወደዳችሁና የተከበራችሁ የቅድስት ቤተክርስቲያን አባቶች፣ ቤተሰቦችና የመምህር ዘላለም ወዳጆች፤ ዛሬ የምንናገረው ስለ አንድ ሥጋዊ ወንድማችን ብቻ አይደለም፤ የምንናገረው ስለ ብዙዎች አባት፣ ስለ ድሆች ረዳትና ስለ ወንጌል ብርሃን ነው። መምህር ዘላለምን በሥጋ መለየታችን ለአንጀታችን እጅግ የሚከብድ፣ ለቤተሰባችንም መሪር ሐዘን ቢሆንብንም፤ እርሱ ግን አስቀድሞ በመልካም ሥራው በሰማይ ቤት ቤቱን ሰርቶ እንደነበር እናምናለን።
ምንም እንኳን በሰውነታችን ብናዝንም፣ በብጹዓን አባቶቻችን ጸሎትና ትምህርት፣ እንዲሁም በዚህ በመካከላችሁ ባላችሁትና "አለንላችሁ" በሚሉን የክርስቶስ ቤተሰቦች ፍቅር ተጽናንተናል። እርሱ የሄደው ወደ ፈጠረው አምላክ ነውና ሐዘናችን በተስፋ የተሞላ ነው።
የመምህር ዘላለም ወንድሙ (ወልደ ሰማዕት) የሕይወት ታሪክ
ውልደትና የልጅነት ዘመን
መምህር ዘላለም ወንድሙ (ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት) ከአባታቸው ከአቶ ወንድሙ ተማም እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ትክክልወርቅ ገብረኢየሱስ ነሐሴ 17 ቀን 1969 ዓ.ም በታሪካዊቷ ደብረ ሲና ከተማ ተወለደ። ገና በለጋነቱ የቤተክርስቲያንን ጠረን እየሳበ፣ በየኔት ታመነ እግር ሥር ተቀምጦ የቄስ ትምህርቱን በመቅሰም ለወደፊቱ መንፈሳዊ ተጋድሎው መሠረት ጣለ።
የትምህርት ጉብዝና እና የቅንነት መገለጫ
በትምህርቱ እጅግ ብሩህ የነበረው ዘላለም፣ በሰበታ ከተማ በነበረው የትምህርት ቆይታው ሁልጊዜም ከአንደኛነት አይወርድም ነበር። በተለይም በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተናዎች 100% በማምጣት አስደናቂ ውጤት አስመዝግቧል።
የሚገርመው ግን ዕውቀቱ ለራሱ ብቻ አልነበረም፤ ለሒሳብ ትምህርት የነበረው ልዩ ተሰጥኦ መምህራኑ በማይኖሩበት ጊዜ እርሱ መምህር ሆኖ ጓደኞቹን ያስተምር ነበር። ይህ "ሌሎችን የማብቃት" መልካም ባሕሪው ገና በልጅነቱ አብሮት ያደገ ጸጋው ነበር።
ከአግሮ ቴክኒክ ወደ ወንጌል አገልግሎት
በወሊሶ አግሮ ቴክኒካል ትምህርት ቤት በኤሌክትሪሲቲ ሙያ በዲፕሎማ ቢመረቅም፣ የልቡ ጥሪ ግን የሰው ልጅን ነፍስ በወንጌል ኤሌክትሪክ ማብራት ነበር። በወሊሶ ቆይታው ከብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እግር ሥር ሆኖ በሰንበት ትምህርት ቤት አገልግሎቱን ጀመረ። የ12ኛ ክፍል ውጤቱ ለከፍተኛ ኮሌጅ ቢያበቃውም፣ እርሱ ግን "የእግዚአብሔር መንግሥት ትቀድማለች" ብሎ ራሱን ለቤተክርስቲያን አገልግሎት አሳልፎ ሰጠ።
የአገልግሎት አሻራዎች፡ ከከተማ እስከ ገጠር
መምህር ዘላለም "የከተማ ኑሮ ይመቸኛል" ብሎ የተቀመጠ አገልጋይ አልነበረም። እግሩ ወንጌል ባልደረሰባቸውና እርዳታ በሚሹ አካባቢዎች ሁሉ ደርሷል፦
በደቡብ ኦሞ ገጠራማ ስፍራዎች፡ ለማሌ፣ ሰሜን አሪ እና በና ፀማይ ብሔረሰቦች አምስት አብያተ ክርስቲያናትን በማነጽ የቃለ ወንጌል ብርሃን እንዲበራ አድርጓል። ሌላው ቀርቶ የሌላ እምነት መሪዎችን አስተምሮ በማስጠመቅ አዳራሻቸውን ወደ ቤተክርስቲያንነት እንዲቀየር አድርጓል።
ለቋንቋ ተናጋሪዎች የሰጠው ትኩረት፡ በ2003 ዓ.ም ከ38 ልዩ ልዩ ቋንቋዎች የተውጣጡ ደቀ መዛሙርትን አምጥቶ፣ ወጪያቸውን ሸፍኖ ካሰለጠነ በኋላ ወደየአካባቢያቸው እንዲያገለግሉ ልኮአቸዋል።
ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት፣የገዳማትና አድባራት አባቶች የሚሰጡትን ምስክርነት ሳያካትት ካከናወናቸው ዋና ዋና ሥራዎች፡
ደቡብ ኦሞ ገጠራማ ሥፍራዎች
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት የከተማ አገልጋይ ብቻ አልነበረም፡፡ በደቡብ ኦሞ ገጠራማ ሥፍራዎች ቃለ ወንጌልን በማስተማር ካበረከተው መንፈሳዊ አልግሎት በተጨማሪ፡
1. ለማሌ ብሔረሰብ -የማሌ ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤተክርስቲያን
2. ለሰሜን አሪ ብሔረሰብ-የዘፍቲ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
3. ለአሪ ብሔረሰብ-የሰልማ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተክርስቲያን
4. ለበና ፀማይ ብሔረሰብ-የሙቃጫ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን
5. የማላተር ቅዱስ ሚካኤል-በጅምር ላይ ያለ፡ በከተማው የነበሩትን ዋና ዋና ፓስተሮች
አስተምሮ በማስጠመቅ፣አዳራሻቸውን አፍርሰው ቆርቆሮውን በማምጣት
እንዲሠራ አድርገዋል፡፡
ጉሙዝ፣ጋምቤላ፣ጂንካ
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት በ2003 ዓ.ም ከጠረፋማዋና ከገጠሪቱ የሀገራችን ክፍሎች የተውጣጡ 38 ልዩ ልዩ ቋንቋ ተናጋሪ ደቀ መዛሙርትን መልምሎና ከየሀገረ ስብከታቸው ማስረጃ አስጽፎ በማስመጣት ሙሉ የሥልጠና ወጪያቸውን በመሸፈን በጽርሐ ጽዮን የሥልጠና ማዕከል እንዲማሩ በማድረግ ሥልጠናቸውን ሲያጠናቅቁ፣ የአገልግ ሎት ልብስ እና መጽሐፍ ቅዱስ ገዝቶ በመስጠት ወደየመጡበት አካባቢ ተመልሰው በቋንቋቸ ው እንዲያገለግሉ አድርጓል፡፡
ጅጅጋ
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት ሐምሌ 28 ቀን 2010 ዓ.ም በጅጅጋ በደረሰው ችግር የተጎዱትን ለማጽናናት በሥፍራው ጉባኤ በማዘጋጀት ማኅበረ ምእመናንን ከማጽናናቱ በተጨማሪ ሰዎችን በማስተባበር ከ1,500,000.00 (ከአንድ ሚልዮን አምስት መቶ ሽህ ብር) በላይ በማሰባሰብ በወቅቱ ለተጎዱ የሀገረ ስብከቱ ማኅበረ ካህናት ድጋፍ እንዲያገኙ በመርዳት የቤተክርስቲያን ልጅነቱን በተግባር አሳይቷል፡፡
ሰበታ ቅዱስ ገብርኤል
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት ለ57 ዓይነ ስውራን በተለያዩ ጊዜያት ድጋፍ ከማድረጉ በተጨማሪ ለዘለቄታው ራሳቸውን የሚችሉበት ቦታ በመግዛት እንቅስቃሴ አስጀምሯል፡፡
በምሁር ኢየሱስ ገዳም
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት 12 ልጆችን ከቤንሻንጉል ጉሙዝ በማስመጣት ዲቁና እንዲማሩና ወደ አካባቢያቸው ተመልሰው እንዲያገለግሉ አድርጓል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን በኤፍራታና ግድም ወረዳ-በጦርነት ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ለ 2591 ሰዎች *3,000 ብር =7,773,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
ሸዋሮቢት፣አጣዬና ከሚሴ-ከተለያዩ አካባዎች ለተፈናቀሉና ጉዳት ለደረሰባቸው ድጋፍ አበርክቷል፡፡
ደብረ ዘይት-መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ከቢሾፍቱ ከተማ በቅርብ ከሚገኘውና የኢትዮጵያ አውሮፕላን ተከስክሶ ብዙ ሰው ባለቀበት ኤጄሬ ቦታ ላይ በአካል ተገኝቶ በማጽ ናናትና የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጎርጎርዮስን በማስፈቀድ የተለያዩ ሰዎችን በማስተባበር የቅድስት ልደታ ቤተክርስቲያንን አስተክሎ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም በአካል በመገኘት አስመርቋል፡፡
ቡታጅራ-በግጭት የተፈናቀሉትን ቦታው ድረስ ሄዶ በአካል በመገኘት በቃለ እግዚአብሔር ከማጽናናት በተጨማሪ የሚታወቅበትን መልካምነት በድጋፍ አሳይቷል፡፡
ከስልጤ ዞን ከቅበት ከተማ በክርስትናቸው ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ለ288 ሰዎች *2,000 ብር =576,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
አርሲ ሻሸመኔ ባሌ
ቤተሰቦቻቸው ለተገደሉ እና ለተፈናቀሉ ክርስቲያኖች ሩዝ፣ዱቄት፣ዘይት እና የማሰያ ዕቃዎችን በማቅረብ መንፈሳዊ ኀላፊነታቸውን ተወጥቷል፡፡
አፋር
በአፋር ክልል ለሚገኙ በዞን 5 ሰሙሮቢ ወረዳ ኩማሜ አካባቢ -በጦርነት ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ለ 495 ሰዎች* 3,000 ብር =1,485,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
ስሙን "ማሩ!" በማለት የሚጠሩት የአፋር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሲኖዶስ አባ ብጹዕ አቡነ ዮናስ በስማቸው በዋሽ ዐርባ ለተቋቋመው አረጋውያን የጡረታ ማእከል የቦርድ ሰብሳቢ በመሆን እና በኀላፊነት በማገልገል ዓመታዊ የምግብ እገዛ አድርጓል፡፡
ደብረ ሊባኖስ ገዳም-ለአበው ካህናት ለአገልግሎት የሚሆን ልብሰ ተክህኖ ሰጥቷል
ደብረ ብርሃን-የአእምሮ ሕሙማን ማገገሚያ እንዲሆን በአርቲስት ፈቃዱ ተክለማርያም ልጅ በተመሠረተው ሀበሻ የአረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ለንጽሕና መጠበቂያ የሚሆኑ ነገሮችን በማቅረብ ሃይማኖቱን በተግባር አስመስክሯል፡፡
ዋግህምራ ዞን ሰቆጣ- በጦርነት ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ለ901 ሰዎች *3,000 ብር =2,703,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
ደባርቅ ወረዳ በጦርነት ለተፈናቀሉና ለተጎዱ ለ294 ሰዎች *3,000 ብር =882,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
ጎንደር-የአብነት ተማሪዎች ሲመረቁ ካባ ሰጥቷል፡፡
አዲስ አበባ
ይዲድያ መንፈሳዊ ማኅበር
እኁድ ከ 5፡00-7፡00 ሰዓት በቃለ እግዚአብሔር በሃይማኖት በምግባር እንዲጸኑ፣ እንዲያድጉና እንዲበረቱ ከማስተማር በተጨማሪ ወላጆቻቸውን በሞት ላጡና ለችግር የተጋላጡ ልጆችን በማስተማር ራሳቸውን እንዲችሉ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በአዲስ አበባ ማረሚያ ቤቶች ለሚገኙ እስረኞች ለዳግም ትንሣኤ የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ይዲድያ የሕፃናት መርጃ
ይዲድያ የሕጻናት መርጃ ድርጅት በመምህር ዘላለም ወንድሙ መሥራችነትና አስባባሪነት በበጎ አድራጎት የተሰማራ አገር በቀል ድርጅት ሲሆን ድርጅቱ ያለ ሃይማኖት፣ያለዘር፣ያለ ቋንቋ ልዩነት ወገናዊ ድጋፍ በማድረግ የሚታወቅ ድርጅት ነው፡፡ በይዲድያ የሕጻናት መርጃ ድጋፍ ለሚደረግላቸው ልጆች ከ2008-2018 ባሉት ለ12 ዓመታት ከ2650 በላይ ለሆኑ ልጆች ከ15,000,000.00 ብር በላይ ወጪ በማድረግ ወገናዊ ደጋፉን በማድረግ ላይ የሚገኝ አገር በቀል ድርጅት ሲሆን በአሁኑ ወቅት 200 ልጆችን በመርዳት ላይ ይገኛል፡፡
በአዲስ አበባ ዙሪያ በዝቅተኛ ኑሮ ለተቸገሩ 1000 ሰዎች 3,000 ብር =30,000.00 ድጋፍ አድርጓል፡፡
በየሳምንቱ ረቡዕና ዓርብ የሚደረግ የምሣ ምገባ
ሀ. ቂርቆስ 80 ልጆችን ፤ለ. ሣሪስ አቦ 148 ልጆችን፤ ሐ. የካ ሚካኤል 72 ልጆችን ባጠቃላይ ለ300 አቅመ ደካሞችን የምሣ የምግብ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ሽንቁሩ ቅዱስ ሚካኤል ለሚገኙ ጸበልተኞች ዘይትና ዱቄት ድጋፍ አድርጓል፡፡
ወንጌለ ዘላለም ከተባለው የዩቲዩብ ቻናላቸው ከሚገኘው ገቢ፡
ግቢ ገብርኤል፣የወደቁትን አንሡ፣እንጦጦ ማርያም….ለሚገኙ ዐቅመ ደካሞች በበዓለ ጰራቅሊጦስ የዘይትና ዱቄት ድጋፍ አድርጓል፡፡
መምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕት ለአገልግሎት በሄዱበት በሀገረ አሜሪካ በገጠማቸው ድንገተኛ ሕመም የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በተወለዱ በ49 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፏል፡፡
የመምህር ዘላለም ወንድሙ ስመ ጥምቀቱ ወልደ ሰማዕትን ነፍስ በቅንነትና በታማኝነት ያገለገሉት አምላክ በአብርሃም፣በይስሐቅና በያዕቆብ እቅፍ ያኑርልን፡፡ለኦርዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ለቤተሰቡ፣ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናትን ያድልልን፡፡
✍️ “ለግሪክ ሰዎችና ላልተማሩም፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉም ዕዳ አለብኝ፤”
በወንጌል አላፍርምና፤
አስቀድሞ ለአይሁዳዊ ደግሞም
ለግሪክ ሰው፥ ለሚያምኑ ሁሉ
የእግዚአብሔር ኃይል ለማዳን
ጻድቅ በእምነት ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ የእግዚአብሔር ጽድቅ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ይገለጣልና። ሮሜ 1÷14
እግዚአብሔር ሆይ የሚሳንህ ነገር የለምና የራቀውን አቅርበህ የረቀቀውን አጉልተህ እየሰማነው ካለነው መርዶና ሰቀቀን ዕረፍተ ሥጋንና ዕረፍተ ነፍስን አትንሣን
ጸልዩ በእንተ ሰላም
ስለ ሰላም እንጸልይ
ስለ ሀገራችን እንጸልይ
ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ
በጭንቅ በመከራ ስላሉት እንጸልይ
በረሀብ በስደት ስላሉት እንጸልይ
በጽኑ ሕመም ተይዘው ስለሚሰቃዩት እንጸልይ
ስለ ሃይማኖት መሪዎች አባቶቻችን እንጸልይ
ስለ ሀገር መሪዎች እንጸልይ
የሰላም የምህረት የቸርነት ባለቤት እግዚአብሔር ሰላሙን ምህረቱን ቸርነቱን አይንሳን
አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ
ዘዝዋይ ገዳም
መጋቢት 3/7/2018 ✍️

ከብፁዕ አቡነ ኤልያስ የጋሞና አካባቢው ጎፋና ባስኬቶ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል በጋሞ ዞነሰ ደጋማ አካባቢዎች በደረሰው የተፈጥሮ አደጋ ለጠፋው የሰው ሕይወት እና ላጋጠመው የንብረት ጉዳት የተሰማቸውን ኃዘን ገለጹ።
ብፁዕነታቸው የሰጡት መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል።
(ብፁዓን እለ ይላሕው ይእዜ እስመ እሙንቱ ይትፌሥሑ፡፡)
“የሚያዝኑ ብፁዓን ናቸው መፅናናትን ያገኛሉና፡፡'' (ማቴ.፭፤፬)
ትናንት በጋሞ ዞን በተለያዩ ደጋማ አካባቢዎች ማለትም በጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ፣ በላካ፣ በቦንኬ ወረዳ የላ ቀበሌ እንዲሁም በከምባ ዙሪያ ወረዳ ባልታ ቀበሌዎች በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በተከሰተው የናዳና የጎርፍ አደጋ የ30 ወገኖቻችን ሕይወት ማለፉን፣ እንዲሁም በአርባ ምንጭ ከተማና ዙሪያው የኩልፎና ስጎ ወንዞች መሙላት በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱን በታላቅ ሐዘን ሰምተናል።
ይህ ድንገተኛ አደጋ በወገኖቻችን ላይ ያደረሰው የሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት ለመላው የአካባቢው ነዋሪና ለቤተ ክርስቲያናችን ትልቅ መርዶ ነው።በመሆኑም በራሴና በሀገረ ስብከቱ ጽሕፈት ቤት ስም እንዲሁም በመላው የኦርቶዶክሳዊያን ምዕመናን ስም የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን እንገልጻለን፡፡
በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ፈጣሪ አምላክ ነፍሳቸውን በገነት እንዲያሳርፍልን፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጥ እንጸልያለን። በንብረታቸው ላይ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችንም ፈጣሪ ጥንካሬውን እንዲሰጣቸው እንመኛለን፡፡
ሀገረ ስብከታችን ይህንን አስከፊ ወቅት ለማለፍና የተጎዱ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ማንኛውም ዓይነት ሰብአዊ ድጋፍና መርሐ ግብሮች ላይየበኩሉን አስተዋጽኦ የሚያደርግ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡።
መላው ሕዝባችንም የተጎዱትን በመርዳትና በማጽናናት የወንድማማችነትና የአብሮነት እናስተላልፋለን። የቆየውን እሴቱን በተግባር እንዲያሳይ ጥሪያችንን
እግዚአብሔር አምላክ ሕዝባችንንና ምድራችንን ከክፉ መከራ ሁሉ ይጠብቅልን !!
ብፁዕ አቡነ ኤልያስ
የጋሞና አካባቢው፣ ጎፋና ባስኬቶ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል !!
መጋቢት 2 /2018 ዓ/ም አርባ ምንጭ

11 months ago
ማርበርግ ቫይረስ
1) በሽታው ምንድን ነው?
#የቫይረሱ አይነት: ማርበርግ ቫይረስ የፋይሎቫይረስ (Filoviridae) ቤተሰብ አባል ሲሆን ይህም ኢቦላ ቫይረስ የሚገኝበት ቤተሰብ ነው። ለዚህም ነው ሁለቱም በሽታዎች ተመሳሳይ የሕመም ምልክቶች እና የሞት መጠን ያላቸው።
#ክብደት : በሽታው ከባድ እና ከፍተኛ የሞት መጠን ያለው ሲሆን፣ በቅርብ ጊዜ በተከሰቱ ወረርሽኞች በበሽታው ከተያዙት ውስጥ እስከ 88% የሚደርስ ሰዎች ሞተዋል (እንደ ወረርሽኙ ሁኔታ ሊለያይ ይችላል)። #ታሪክ : በሽታው ለመጀመሪያ ጊዜ በ1967 ዓ.ም በጀርመን ማርበርግ እና በፍራንክፈርት እንዲሁም በሰርቢያ ቤልግሬድ ከተሞች ተከስቷል። ቫይረሱ የመጣው ከዩጋንዳ በመጡ የላብራቶሪ ምርምር ዝንጀሮዎች አማካኝነት ነው ይባላል።
2) ስርጭት (በሽታው እንዴት ይተላለፋል?)
+++ ዋናው #ምንጭ : የማርበርግ ቫይረስ ተሸካሚዎች ፍራፍሬ ላይ የሚያዘወትሩ የሌሊት ወፎች (Rousettus bats) ናቸው። ሰዎች በቫይረሱ ሊያዙ የሚችሉት በእነዚህ የሌሊት ወፎች ባሉበት ዋሻዎች ወይም ማዕድናት ውስጥ በመገኘት ነው።
+++ ከሰው ወደ ሰው የሚኖረው #ስርጭት : ቫይረሱ ከሰው ወደ ሰው የሚተላለፈው በበሽታው የተያዘ ሰው ወይም እንስሳት በሚወጡ ፈሳሾች (ደም፣ ምራቅ፣ ማስታወክ፣ ሰገራ፣ ሽንት፣ የዘር ፈሳሽ እና ሌሎች) ጋር በቀጥታ በመገናኘት ነው።
3) #ምልክቶች
የበሽታው ምልክቶች በአብዛኛው ከ2 እስከ 21 ቀናት ባለው ጊዜ ውስጥ ይታያሉ።
የሚከተሉትን እንመልከት #የመጀመሪያ ደረጃ ላይ : ከፍተኛ ትኩሳት፣ ከባድ ራስ ምታት፣ ከባድ የጡንቻና የመገጣጠሚያ ህመም፣ ድካም ስሜት። #ሁለተኛ ደረጃ (ከጥቂት ቀናት በኋላ): ከባድ ተቅማጥ፣ የሆድ ቁርጠት፣ ማቅለሽለሽ፣ ማስታወክ፣ የደረት እና የጉሮሮ ህመም። #የከፋ ደረጃ (ከ5-7 ቀናት በኋላ) ከባድ የደም መፍሰስ (ከአፍንጫ፣ ከድድ፣ ከዓይን እና የቆዳ ስር)፣ የጉበት እና የኩላሊት ድካም፣ የንቃተ ህሊና መሳት፣ የብዝሃ-አካል ስራ መቆም (Multi-organ failure) እና ሞት። ከዚህ በተጨማሪ የዓይን መቅላት፣ የቆዳ ሽፍታ (በተለይ በደረት፣ ጀርባና ሆድ አካባቢ)።
4)የሚሰጠው ህክምና እና መከላከያ መንገዶች #ፈውስ : ለጊዜው ቫይረሱን የሚያጠፋ የተረጋገጠ መድኃኒት ወይም ክትባት የለም። #ህክምና : የሚሰጠው ህክምና ምልክቶችን ለማስታገስ (Supportive Care) ነው። #ፈሳሽ መተካት (IV fluids): በከፍተኛ ተቅማጥ እና ማስታወክ የጠፋውን ፈሳሽ መሙላት ነው። #የደም መፍሰስ ቁጥጥር: የደም ግፊትን ማረጋጋት እና የደም መርጋት መከላከል/ማከም። #የተጎዱትን የአካል ክፍሎች (ኩላሊት፣ ጉበት) ድጋፍ መስጠት።
በጣም #አስፈላጊው ነጥብ
-) የግል መከላከያ ቁሳቁስ (PPE): የጤና ባለሙያዎች የታመሙ ሰዎችን ሲያክሙ ጓንት፣ ጋውን፣ ጭንብል እና የዓይን መከላከያ የግድ መጠቀም አለባቸው።
_) ንጽህና: እጅን በአግባቡ በሳሙና መታጠብ፣ በተለይ የታመመ ሰው የነካን ወይም የጎበኘን ከሆነ።
የበለጠ መረጃ ለማግኘት ከፈለጉ
1) የዓለም ጤና ድርጅት (World Health Organization - WHO): Marburg Virus Disease (MVD)
2) የአሜሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከላት (Centers for Disease Control and Prevention - CDC : Marburg Hemorrhagic Fever (Marburg HF)
ባምላኩ አበባው
ፕሮፌሽናል ነርስ እና የማህበረሰብ ጤና ባለሞያ
ከጅማ ዩኒቨርሲቲ ህክምና ማዕከል

በአርሲ የደረሰውን ግድያ ካውንስሉ አወገዘ
ጥቅምት 17 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ባወጣችው መግለጫ ምዕመኖቿ ላይ በምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት የተፈጸመውን ግድያና ድብደባ አሳውቃለች፡፡
ይህንን ኢሰብአዊ ድርጊት የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል በጽኑ ያወግዛል፡፡
ቤተሰቦቻቸውን በሞት ላጡ፣ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው እና በመንፈስ የተጎዱትን ሁሉ እግዚአብሔር መጽናናት እንዲሰጣቸው ከልብ እንመኛለን፡፡
ከኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል!!

" ሁላችንም ካለፈው ጥፋቶቻችን ለምን አንማርም ? እንደ ሀገር ስንት ትውልድ በጦርነት እየበላን እንቀጥላለን ? " - ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)
የምክር ቤት አባሉና የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካዩ ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) ከፀጥታ፣ ከኑሮ ውድነት ፣ ከኢኮኖሚ እንዲሁም ከባህር በር ጋር የተያያዘ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርበዋል።
- " ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር እንደ ፀጥታ ኃይሎች መሪነትዎ ካለፈው ዓመት ወዲህ በአማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች በጦርነቶች ምክንያት የተጎዱትን ሰላማዊ (ሲቪል) ሰዎች እና የሲቪሊያን መሰረተ ልማቶች ቁጥር በግልጽ ሊገልጹልን ይችላሉ ወይ ? "
- " መንግሥት የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት ' ፅንፈኛ እና አሸባሪ ' የሚላቸውን ቡድኖች ከመውጋት ባለፈ ለሁለቱ ክልሎች (አማራና ኦሮሚያ) ከወታደራዊ አማራጭ ውጭ የተለየ ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ለምን አይሰራም ? "
- " የኢትዮጵያ ህዝብ የእርስ በእርስ ጦርነት አንገፍግፎታል ፣ በሀገር ውስጥ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ መብላት ከብዶታል ሀገራችን እንደ ኮሎምቢያ ከውስጥ ታጣቂዎች ጋር 50 ዓመት እየተዋጋች ልትቀጥል አትችልም ከዚህ ጋር በተያያዘ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተዘገበ ያለው የፖለቲካ እና የህሊና እስረኞች ጉዳይ እልባት እንዲሰጠ፣ እስረኞች የተፋጠነ ፍትህ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ብንጠይቅም የፖለቲካ አቅጣጫ የተሰጠበት በሚመስል መልኩ በተደጋጋሚ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ያለ ፍርድ እየተንገላቱ ነው ቤተሰቦቻቸውም ከፍተኛ ችግር ላይ ወድቀዋል። የህግ የበላይነት በማስከበር ስም የሚፈጸሙ የዘፈቀደ የፖለቲካ እስሮች ለሚመጣው 7ኛ ዘር ሀገራዊ ምርጫ ፍትሃዊ፣ ነጻና ተአማኒ እንዳይሆን ላለማድረጉ መንግሥት ምን ዋስትና ይሰጣል ? "
- " መንግሥት የሀገር ውስጥ እድገትና የዋጋ ግሽበት ዝቅ ማለቱን ቢገልጽም የዜጎች የኑሮ ሁኔታ ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ ነው። የዓለም ባንክ በቅርቡ ይፋ ባደረገው መረጃ የኢትዮጵያ የድህነት ምጣኔ በሁለት ዲጅት አድጎ 43% እንደሚያሻቅብ ገልጿል። ይህ ማለት ከሁለት ኢትዮጵያውያን አንዱ በድህነት አረንቋ ውስጥ ይገኛል። ስለዚህ ፦
1. ኑሮ ውድነትና የድህነት ቅነሳ በተመለከተ መንግሥት በሚያቀርባቸው ይፋዊ ስታትስቲክስና በህዝብ የዕለት ተዕለት ኑሮ መካከል ያለውን ሰፊ ልዩነት እንዴት ሊያብራራ ይችላል ?
2. መሰረታዊ የምግብ እና ፍጆታዎች እቃዎች ዋጋ መጨመር ለመከላከልና ተጨማሪ ቤተሰቦች ወደ ድህነት እንዳይገቡ ለማድረግ መንግሥት ያቀደው አስቸኳይ እቅድ ካለ ቢብራራ ? "
- " ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከፍተኛ የእዳ ጫና ውስጥ ናት። ከዩሮ ቦንድ አበዳሪዎች ጋር የነበረው ድርድር ተበላሽቷል። በውጭ ምንዛሬ ጉዳይ በባንክ እና በትይዩ (ባላክ ማርኬት) ገበያው ያለው ልዩነት እየሰፋ ነው። መንግሥት ማህበራዊ ወጪዎችን ሳይቀንስ እንደ ሀገር ያሉብንን ከፍተኛ የውጭ እዳ ለመክፈል እና የፋይናስ ክፍተቱን ለመሸፈን ምን እየሰራ ነው ? "
ስለ ውጭ ግንኘትነት እና ባህር በር ጉዳይ ምን ጠየቁ ?
" መንግሥት የቀይ ባህርን የማስመለስ ጉዳይ እንደ ህልውና ጉዳይ በማቅረብ ዋና ትኩረቱን እና የፖለቲካ ጉልበቱን ከአጣዳፊ የውስጥ ቀውሶች በተለይም ከባድ የፀጥታና የኢኮኖሚ ችግሮችን ከመፍታት ይልቅ በውጭ ጉዳይ ላይ እንዲያርፉ በማድረግ በትችት አቅራቢዎች ዘንድ የህዝብን ትኩረት ከውስጥ አጣዳፊና አሳሳቢ ችግሮች ለመቀየር የተደረገ ጥረት ነው የሚል አስተያየት እልዲሰጥ አድርጓል።
በሀገሪቱ ውስጥ ካለው ችግሮች ክብደት አኳያ መንግሥት ይህን ከፍተኛ የፖለቲካ አቅም ለውጫዊ ግብና አላማ ከማዋል ይልቅ ተመሳሳይ ጉልበትና ትኩረትን የውስጥ ፖለቲካ ግጭቶችን ለመፍታትና ከራሱ ዜጎች ጋር ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ለምን አይጠቀምበትም ?
ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበር የሚደረግ ማንኛውም አይነት ዲፕሎማሲያዊ ጥረትን በግሌ እቀበላለሁ። መንግሥት ጉዳዩን የመራበት መንገድ ግን 10 ድስት ጥዶ አንዱንም ሳያማስል እንደማሳረር አይነት ነው።
መጀመሪያ ከኤርትራ ጋር ሰላም ተፈጠረ የወደብ መጠቀም ውስጥ እንገባለን ተብሎ መንገዶችን ማደስ ተጀምሮ ነበር እሱ በምናውቀው መንገድ ተቋረጠ፣ ከዛ ከሶማሌለንድ ጋር ውል ተፈጸመ፣ ከዛ ከጅቡቲ ጋር ታጁራን ለማልማት ፣ ከዛ ከሶማሊያ ጋር በአንካራ ተሞክሯል ግን እስካሁን ተጨባጭ ውጤት አልታየም። ትላንት እንደውም ሳውዲ የታጁራን ወደብ በረጅም ጊዜ የሊዝ ውል እንደወሰደችው እየሰማን ነው ከኛ በኃላ መጥተው።
አሁንም ከኤርትራ ጋር በጦርነት ዋዜማ የምንገኝ የመስለኛል። በሁለቱ ሀገራት በኩል የተሟላ የጦርነት ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ በዓለማቀፉ ማህበረሰብ ዘንድ በሰፊው ተዘግቧል።
የፌዴራል መንግሥቱ ከትግራይ ኃይሎች ጋር ከፍተኛ መካረር ውስጥ እንደገባ ግልጽ ነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሁላችንም ካለፈው ጥፋቶቻችን ለምን አንማርም ? እንደ ሀገር ስንት ትውልድ በጦርነት እየበላን እንቀጥላለን ? ከትግራይ ኃይሎች ፣ ከፋኖ እና የOLA /ኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት/ ጋር መንግስትዎ የገባበትን ሁኔታ በአርቆ አስተዋይነት እና በድርድር እንዲፈታ፤ የባህር በር ጉዳይን አስመልክቶ ከኤርትራ ጋር የገባንባት እሰጣ ገባ በሰላማዊ ፣ ህጋዊና ሰጥቶ መቀበልን መሰረት ባደረገ አካሄድ እንዲፈታ እጠይቃለሁ። "
ቲክቫህ ኢትዮጵያ

1 year ago
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ አደረገች::
ነሐሴ 1/2017 ዓ/ም በደብረ ብርሃን ከተማ ከ23,000 በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃይ ወገኖች በካምፕ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን የሚገኙበት ሁኔታ እጅግ አስከፊና አስቸጋሪ መሆኑ ታውቋል።
ካምፑ በዚህ ከባድ በሆነው የክረምትና የዝናብ ወቅት የውሀ ችግር ፣ የመጠለያ ችግር ፣የመፀዳጃ ችግር ፣ የመኝታና የሌሊት ልብስ እጦት ችግር ምክንያት ተፈናቃዮቹ እየተሰቃዩ ሲሆን ህጻናት ፣ እናቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ብዙ አቅመ ደካሞች እንደምገኙበት ቤተክርስቲያኒቷ በፌስቡክ ገጿ ላይ አስፍራለች።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን የልማት ኮሚሽንን በመወከል መጋቢ ብርሃኑ ታረቀኝ በድጋፍ መርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን "እንዲህ ዓይነቱን የወገኖቻችንን ስቃይና አስከፊ መከራ መመልከት በእውነት ልብን ይሰብራል፣ እጅግ በጣምም ያሳዝናል እንደ ኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን፣ ይህ ድጋፍ በቂ ባይሆንም ጅማሬ ነው።የተቸገሩና የተጎዱትን መንከባከብ፣ መርዳት የክርስቶስን ፍቅር ማሳየት መንፈሳዊ እና የዜግነት ግዴታችን ነው።” ሲሉ ተናግረዋል።
አያይዘውም በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሁሉም አብያተ ክርስቲያናት፣ ሰብዓዊ ድርጅቶች እና ግለሰቦች አቅማቸው በፈቀደው ሁሉ በጸሎት፣ በገንዘብ ፣ በቁሳቁስ እና በአካል በስፍራው በመገኘት ተግባራዊ ምላሽ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል ።
የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያንና ልማት ኮሚሽኑ ከአስቸኳይ ሰብዓዊ ድጋፍ በተጨማሪም ሌሎች ዘላቂና ቀጣይነት ያለው የህፃናት ልማት እና የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን በአከባቢው ላይ በስፋት እየተሰራ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን ገልጻለች ።
መረጃውን ከኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል አማኞች ቤተ ክርስቲያን አገኘነው።

Comments