8 days ago
አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ‼️
በአላማጣ ከተማ እና አካባቢው አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን #ኮማንድ_ፖስቱ ከዛሬ ቀን ( መስከረም 22/2019 ዓ/ም ) ጀምሮ የሚተገበር የሰዓት_ገደቦችን እና የእጅ_መስጠት ጥሪ ጨምሮ ጥብቅ የሆኑ ድንጋጌዎችንና እገዳዎችን ጥሏል።
የተጣሉ የሰዓት ገደቦችና እገዳዎችም የሚከተሉት ናቸው
#የተሽከርካሪዎች
➡️ #ማንኛውም_ዓይነት ተሽከርካሪ #መንቀሳቀስ የሚችለው እስከ ምሽቱ 12:00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው !!
#የንግድ_ተቋማት
➡️ ማንኛውም ሆቴል ፣ መጠጥ ቤትና የመዝናኛ ቦታዎች አገልግሎት መስጠት የሚችሉት እስከ ምሽቱ 2፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ነው።
#የሰዎች_እንቅስቃሴ
➡️ማንኛውም ሰው ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት #በኋላ_መንቀሳቀስ ሙሉ በሙሉ ተከልክሏል።
#የጦር_መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ
➡️ የፌዴራል_ ፀጥታ_ሃይሎች ውጪ በከተማው ውስጥ ማንኛውም ሰው መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ በጥብቅ የተከለከለ ነው።
#የተሰጡ_ጠንካራ_መመሪያዎችና_ማስጠንቀቂያዎች
#የግል_ትጥቅ_ምዝገባ
➡️ #በገጠርም ሆነ #በከተማ የምትገኙ የግል የጦር መሳሪያ ያላችሁ ግለሰቦችና ድርጅቶች በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የፖሊስ ጣቢያ በአስቸኳይ እንድታስመዘግቡ ታዟል።
➡️ #ለንብረት_ዘረፊዎች የተሰጠ ማስጠንቀቂያ
ማንኛውም አካል የግለሰብ ፣ የህዝብና የመንግስት ንብረት ከመዝረፍ እንዲቆጠብ ይህንን ድርጊት ሲፈፅም በተገኘ ማንኛውም አካል ላይ ግን የማያወላዳ ጥብቅ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድ ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል።
➡️ #የእጅ_መስጠት ጥሪ
የፅምዶ ሃይሎች #በአምስት ( 5 ) ቀናት ውስጥ ለፌዴራል ፖሊስ #ከተደበቁበት እየወጡ #እጃቸውን እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።
Seledadotio

2 months ago
የዴሞክራቲክ ኮንጎ የኢቦላ ወረርሽኝ፡
በአገሪቱ ታሪክ የከፋው ሆኖ ተመዘገበ
በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ በአገሪቱ ታሪክ እጅግ የከፋው ሆኖ መመዝገቡን የጤና ባለሥልጣናት አስታወቁ። ቫይረሱ ግንቦት ላይ መከሰቱ ከተወጀ ወዲህ ከ4,900 በላይ ሰዎች በበሽታው ሲያዙ፣ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ደግሞ 2,325 ደርሷል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የወረርሽኙን የስርጭት ፍጥነት "በየ30 ደቂቃው ሰው እየገደለ ነው" ሲል የገለጸው ሲሆን፣ በሽታው ከኮንጎ ውጪ በዩጋንዳ፣ ጀርመን እና ፈረንሳይ በትንሹም ቢሆን መታየቱ ተገልጿል።
ይህ አሁን የተከሰተው የቡንዲቡግዮ የተባለው የኢቦላ ቫይረስ ዝርያ እጅግ ያልተለመደና እስካሁን የተረጋገጠ ክትባት የሌለው በመሆኑ ሁኔታውን የበለጠ አሳሳቢ አድርጎታል። በአገሪቱ ለዓመታት የዘለቀው ግጭትና የሰዎች እንቅስቃሴ ስርጭቱን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ጥረት አስቸጋሪ ያደረገው ሲሆን፣ የዓለም ጤና ድርጅት የቫይረሱን ስርጭት በሦስት ወር ውስጥ ለመቀልበስ አልሞ እየሰራ ይገኛል።

5 months ago
በኢትዮጵያ ኩርሙክ ከተማ ሱዳን ፈፀመችው በተባለ የድሮን ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ሲገደሉ በእርዳታ ሰጪዎች ላይ ጉዳት ደረሰ!
ከሱዳን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ዞን ኩርሙክ ወረዳ ኩርሙክ ከተማ ውስጥ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት፣ አንድ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (IOM) የሥራ ባልደረባን ጨምሮ ቢያንስ ስምንት ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸውንና ሌሎች በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች እና የአካባቢው የጤና ባለሥልጣናት ገለጹ።
ነዋሪዎች ጥቃቱ የተፈጸመው ሚያዝያ 21 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 5:00 ገደማ መሆኑንና ከአሶሳ ከተማ 94 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው የኩርሙክ ከተማ የሰዎች እንቅስቃሴ በሚበዛበት አካባቢ ላይ ማረፉን ተናግረዋል።የዓይን እማኞች ድሮኑ የመጣው ከሱዳን ብሉ ናይል ግዛት አቅጣጫ መሆኑን ጠቅሰው፣ የሱዳን ጦር ከፈጣን ድጋፍ ኃይሎች (RSF) ጋር እያካሄደ በነበረው ግጭት ወቅት ጥቃቱን እንደፈጸመ አስረድተዋል።
seledadotio

8 months ago
የሜታ ከሞት በኋላ የሚቀጥል የማህበራዊ ሚዲያ ተሳትፎን የሚያስችል ትግበራ
#ethiopia | የፌስቡክ እና ኢንስታግራም እናት ኩባንያ የሆነው ሜታ፣ ተጠቃሚዎች ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ በኋላም ቢሆን የእነሱን ድምፅ፣ የአጻጻፍ ስልት እና ጠቅላላ ባህሪ በመኮረጅ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ "በህይወት" እንዲቆዩ የሚያደርግ አዲስ ቴክኖሎጂ ባለቤት ሆኗል።
ቴክኖሎጂው እንዴት ይሰራል?
እ.ኤ.አ. በ2023 የተመዘገበውና በቅርቡ የፈጠራ መብት (Patent) የተሰጠው ይህ ቴክኖሎጂ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) በመጠቀም የግለሰቡን ዲጂታል አምሳያ ይፈጥራል። ቴክኖሎጂው፦
* ግለሰቡ በህይወት እያለ የጻፋቸውን ጽሁፎች፣ አስተያየቶች እና የግል መልዕክቶች ያጠናል፤
* የተጠቃሚውን ልዩ የቋንቋ አጠቃቀም የሚከተል የቋንቋ ሞዴል ይቀርጻል፤
* ተጠቃሚው በሌለበት አዳዲስ ጽሁፎችን ማጋራት፣ ለጓደኞች ምላሽ መስጠት እና በውስጥ መስመር ማውራት ይችላል፤
* ከዚህም ባለፈ፣ የሟቹን ድምፅና ምስል በመጠቀም የቪዲዮ ጥሪዎችን የማድረግ አቅም እንዳለው በሰነዱ ላይ ተመልክቷል።
የሜታ ምላሽ፦ "ለጥንቃቄ እንጂ ለትግበራ አይደለም"
የኩባንያው የቴክኖሎጂ ዋና ኦፊሰር አንድሪው ቦስዎርዝ በፈጣሪነት የተመዘገቡበት ይህ ፕሮጀክት፣ በብዙዎች ዘንድ ስጋትን ቢፈጥርም ሜታ ግን ጉዳዩን አረጋጋ ለማድረግ ሞክሯል።
የኩባንያው ቃል አቀባይ ለቢዝነስ ኢንሳይደር እንደተናገሩት፣ ኩባንያው በአሁኑ ወቅት ይህንን ቴክኖሎጂ ወደ ስራ የማስገባት ምንም አይነት እቅድ የለውም። የፈጠራ መብቱ የተመዘገበው ሃሳቡ በሌሎች እንዳይወሰድ ጥበቃ ለማድረግ ብቻ እንደሆነ ገልጸዋል።
የስነ-ምግባር አጣብቂኝ እና የ"ዲጂታል መቃብር" ስጋት
ቴክኖሎጂው ይፋ መደረጉን ተከትሎ ከሊቃውንትና ከስነ-ልቦና ባለሙያዎች ጠንካራ ትችት እየቀረበበት ይገኛል። ዋና ዋናዎቹ ስጋቶች የሚከተሉት ናቸው፦
* የሀዘን ሂደት መስተጓጎል፦ ቤተሰቦች የሚወዱትን ሰው በሞት ሲያጡ ሊያልፉበት የሚገባውን የተፈጥሮ የሀዘን ሂደት ቴክኖሎጂው ሊያሰናክል ይችላል የሚል ስጋት አለ።
* ትርፍ Vs ሰብአዊነት፦ ሜታ ተጠቃሚዎች ከሞቱም በኋላ እንኳ በማህበራዊ ሚዲያው ላይ የሚኖረውን የሰዎች እንቅስቃሴ (Engagement) ላለማቀዝቀዝ ሲል የሰውን ልጅ ሞት ለንግድ መጠቀሚያ ሊያደርገው ነው የሚል ወቀሳ እየቀረበበት ነው።
ይህ "ዲጂታል መቃብር" ተብሎ የተፈረጀው ቴክኖሎጂ፣ ወደፊት የሰውን ልጅ ህይወት እና ሞት ትርጉም ምን ሊያደርገው እንደሚችል አሁንም አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #meta #ai #digitalafterlife #technologynews #ethicsintech #facebook #futuretech #አርቴፊሻል_ኢንተለጀንስ #ሜታ

10 months ago
"በሰሞንኛው ጥቃት ብቻ ከ10 በላይ ንጹሐን ተገድለዋል፤ የቆሰሉም በርካቶች ናቸው" - የጋምቤላ ነዋሪዎች
"ከስድስት ሰዎች በላይ ህይወታቸው አልፏል፤ የቆሰሉም ከስድስትና ሰባት በላይ አሉ - የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊና ምክር ቤት አባል
ሰሞኑን በጋምቤላ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች በተፈጸሙ ጥቃቶች ንጹሐን መገደላቸውን፣ የሰዎች እንቅስቃሴ መገደቡን የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።
ነዋሪዎቹ በሰሞንኛው ጥቃት ብቻ ከ10 በላይ ሰዎች ተገድለዋል፤ የቆሰሉትም በርካቶች ናቸው" ያሉ ሲሆን፣ አንዳንዶቹ የሟቾች ቁጥር ከዚህም ሊያሻቅብ እንደሚችል እየገለጹ ነው።
በተለይ አቦል ወረዳና ኢታንግ ልዩ ወረዳ አካባቢዎች "ንጹሐን ዜጎች እየተገደሉ" መሆኑን፣ ጥቃቱ ከዚህ ቀደምም የነበረ ሲሆን፣ በሰሞንኛው ሁነት ደግሞ "የጸጥታ አካላት ጭምር ሟችና ቆስለኛ" መሆናቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች ከስፍራው ወጥተዋል።
ግድያው የሚፈጸመው በተለይ ተሳፋሪዎች ከቦታ ቦታ ሲንቀሳቀሱ መንገድ ዳር በማድፈጥ በተሽከርካሪዎች ጭምር ሲሆን፣ የክልሉ ፓሊስ በበኩሉ፣ ተሳፋሪዎች ላይ ሞትና የመቁሰል ጥቃት መድረሱን ባለፉት ሳምንታት በተደጋጋሚ ማሳወቁ ይታወቃል።
የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከቀናት በፊት፣ "በከተማችን ባለው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ከጸጥታ አካላት ውጭ ማንኛውም ተሽከርካሪና ሰው ከህዳር 30/2018 ዓ/ም ምሽት 1 ሰዓት ጀምሮ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን እንገልፃለን" ሲል ማስታወቁ ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያም ጉዳዩን ይዞ ስለጥቃቱ ማብራሪያ እንዲሰጡ የክልሉን ባለስጣናት የጠየቀ ሲሆን፣ የሰላምና ጸጥታ ቢሮው ፈቃደኛ አልሆነም። በስልክ የጠየቃቸው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ ደግሞ፣ "በኋላ ደውሉ አሁን ስብሰባ እየመራሁ ነው። ከአንድ ሰዓት በኋላ ደውሉ" ቢሉም በድጋሚ ሲደወል ስልክ አያነሱም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተጨማሪ፣ በሰሞንኛው ጥቃት "ንጹሐን ተገድለዋል፤ የጸጥታ አካላትም ተገድለዋል፣ ጉዳት ደርሶባቸዋል" ብለዋል፤ ምን ያክል ሰዎች ተገድለዋል? ሲል የጋምቤላ ብልጽግና ጽ/ቤት ኃላፊ እና የምክር ቤት አባል አቶ አሽኔ አስቲንን ጠይቋቸዋል።
የጽ/ቤት ኃላፊ እና የምክር ቤት አባል አቶ አሽኔ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን መለሱ?
"ከስድስት ሰዎች በላይ ህይወታቸው አልፏል፤ የቆሰሉም ከስድስትና ሰባት በላይ አሉ።
የተፈጠረውን ግጭት ግጭት ነው ብሎ ለማሰብ ትንሽ ያስቸግራል። ለምሳሌ ጋምቤላ ከተማ ላይ የደረሰ ጉዳት አለ፤ አንድ ሰው ሁለት ሰዎች ላይ ጥይት ተኩሶ አንዱ ህይወቱ አልፎ አንዱ ቆስሏል።
ከዚያ በኋላ ማንነታቸው የማይታወቁ ሰዎች ደግሞ በጋምቤላ ወረዳ ከላሬ ሲመጣ በነበረ መኪና ጥይት ተተኩሷል፤ እነማን እንደሆኑ አልታወቁም፤ ዳርና ዳር ጫካ ስለሆነ ከጫካ ወጥተው ነው ጥቃት የፈጸሙት። እዛም የተጎዱ ሰዎች አሉ። አንድ ቡድን ከሌላ ቡድን ጋር የመጋጨት አይነት ነገር ነው፤ ይሄ ግን ጥቃት ነው። የተወሰኑ ግለሰቦች በሆኑ ግለሰቦች ላይ ጥቃት የሚፈጽሙበት ነው።
ግጭት የሚመስለው ሰው ተደናግጦ አንዱ ወደራሱ አካባቢ ሌላውም ወደራሱ አካባቢ ይሸሻል። ይህ ነው ግጭት ተብሎ የተወሰደው እንጅ በግለሰብ ደረጃ የተፈጸሙ ጥቃቶች ናቸው ያሉት።
ጋምቤላ ወረዳ በተፈጸመው የመኪና ጥቃት የተጎዱት ሦስት ሰዎች ናቸው። ወረዳው ላይ የተወሰኑት ነዋሪዎች "ሆ" ተብለው ተነስተው ወደ አመራሮች ወዳሉበት ግቢ ሊገቡ ሲሉ ፓሊስ ባደረገው መከላከል፤ አንድ የፌደራል ፓሊስ ላይ ጉዳት ደርሷል፤ ሌላ ፓሊስም ቆስሏል። ከማህበረሰቡም አንድ ሰው ህይወቱ አልፏል። አሁን ተረጋግቷል" ብለዋል።
በሰሞንኛው ጥቃት የሟቾች ቁጥር " ከ10 በላይ" እንደሚሆን፣ ከዚህ በፊት የተገደሉት ደግሞ "ከ40 እንደሚበልጡ " ነዋሪዎቹ እየገለጹ ነው፤ እርስዎ ደግሞ የሰሞኑ ሟቾች " ከ6 በላይ" ናቸው ብለዋል፤ በትክክል የሟቾች ቁጥር ስንት ነው? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ አቅርቧል።
እሳቸውም፣ " የሟቾቹን ቁጥር በትክክል መረጃ መውሰድ አለብኝ፣ አሁን ካልኩት በላይ ሊሆን ይችላል የሰማሁትና የተነገረኝን ነው የገለጽኩት። ምክንያቱም የቆሰሉም አሉ፤ ቆስለው የሞቱ አሉ፣ ስለዚህ ቁጥሩ ሊጨምር ይችላል። ከ10 በላይ ሊሆኑ ይችላሉ " ብለዋል።
" 'ከ40 በላይ ሰዎች ሞተዋል' የሚባለው፣ ሰዎች ተጣልተው አንዱ አንዱን ሊገድል ይችላል። ይሄ የቆየው የብሄር አስተሳሰብ ወደ ቡድን ይወሰዳል። ነገሩን በጣም ለማጋጋል የሞቱ ሰዎችን ቆጠራ ይጀምራሉ፣ ይሄን የሚያደርጉት ቅስቀሳ ለማድረግ ነው። ችግሩ እንዲቀጥል፣ እንዳይረጋጋ አረቄ ቤት የሞተውን ሁሉ ይቆጥራሉ " ሲሉም አክለዋል።
ምን እየተሰራ እንደሆነ ሲያስረዱም፣ " የማረጋጋት ሥራ እየሰራን ነው ያለነው። ወንጀል የፈጸመ በግሉ እንዲጠየቅ፣ የህዝብ ውይይት እያደረግን ነው። ሥራዎች በነበሩበት መንገድ እንዲቀጥሉ፣ ተቋማት ወደነበሩበት ሥራ እንዲገቡና አካባቢው በሙሉ የተረጋጋ እንዲሆን እየሰራን ነው " ብለዋል።
የክልሉ መንግስት በበኩሉ፦
የክልሉ መንግስት፣ ትላንት በጋምቤላ ከተማ አመራሮችን አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለሰሞንኛው ጥቃት ማብራሪያ የጠየቃቸው የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር፣ የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ስብሰባ መቀጠመጣቸውን ከጠዋት ጀምረው ሲገልጹ ቆይተዋል።
የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ " ሰሞኑን በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ተፈጥሮ በነበረው ግጭት በህይወትና በንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን እንደተሰማቸው " የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ በመድረኩ መናገራቸውን ይፋ አድርጓል።
" ከተፈጠረው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ ግለሰቦችን በህግ ቁጥጥር የማዋል ስራ " እንደሚቀጥል መናገራቸውን ፅህፈት ቤቱ ገልጿል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ

11 months ago
የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር-በር ጥያቄን የሚደግፉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት(IR)ህልዩቶች
(የሀብታሙ ደባሱ አዲሱ የግል ሀሳብ)
#ethiopia | የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ በዓለም አቀፍ ግንኙነት(IR)ህልዮት መሠረት ሲታይ ምን ይመስላል፤የሚለውን በዛሬው አጭር ፁሁፍ በሪያሊዝም፣በሊበራሊዝም፣እንዲሁም በኮንስትራክቲቪዝም በዋናነት በሦስት ትልልቅ የትንተና ማዕቀፎች ለማብራራት እሞክራለሁ፤በእርግጥ እነኝህ ንድፍ ሀሳቦች በእጅጉ ሰፊ ናቸው። የፖለቲካ ሳይንስና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ሊቃውንት በጉዳዩ ላይ ልዩ ልዩ የክርክር እና ሀሳብ መር ውይይት እና መነሻ ፁሁፍ በማቅረብ የሀሳቡን ደርዝ እንዲያሰፉት እጠይቃለሁ ።
🔴ሪያሊዝም ህልዮት(Realism Theory):-
ይህ ህልዮት ቀዳሚ እና የነገረ-ሀሳብ ማንጠሪያ መነፀር ነው፤ዓለም አቀፍ ሥርዓት(International System) የትርምስ ዓለም የሰፈነበት (Anarchic World)ሲሆን፣መንግሥታት ዋነኛ ዓላማቸው ህልውናን ማስጠበቅ እና ኃይልን ማሳደግ ነው።መልካ-ምድራዊ አቀማመጥ የኃይል ምንጭ ወይም ድክመት ነው ብለው ያምናሉ።የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ ሪያሊዝም ንድፈ-ሀሳብ የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ እንደ ምክንያታዊነት የደህንነት እርምጃ ይደግፈዋል።
የደህንነት ስጋት እና የተዘጋ-መሬት (የመልካ-ምድር እስረኝነት) መሆን የአንድን ሀገር ደህንነት በጎረቤቶች ጥገኛ ስለሚያደርግ "የህልውና አደጋ ነው።የባህር-በር ማግኘት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት እና ስትራቴጂካዊ ራስን የመወሰን አቅም ያጠናክራል።የኃይል ሚዛን( Power of Balance)የቀይ ባህር አካባቢ ወሳኝ የጂኦ-ፖለቲካዊ ውድድርና ፉክክር ቀጠና ስለሆነ፣የባህር በር ማግኘት የኢትዮጵያን ቀጠናዊ ኃይል ያሳድጋል እና የውጭ ጫናን የመቋቋም አቅም ያጎለብታል ።
🔴ሊበራሊዝም ህልዮት (Liberalism Theory):-የዚህ ዋና መርህ በዓለም አቀፍ ትብብር፣በኢኮኖሚ ትስስር እና በዓለም አቀፍ ሕግና ተቋማት አማካኝነት የጋራ ጥቅምን ማሳደግ ይቻላል የሚል ትንታኔ ያቀርባል።የጥያቄው ድጋፍ በሊበራሊዝም የኢትዮጵያን ፍላጎት በኢኮኖሚና በዓለም አቀፍ ትብብር አንፃር ይደግፋል፤ያበረታታል።ከኢኮኖሚ ጥቅም(በጋራ ማደግ) አንፃር ስንመለከተው የባህር-በር ማግኘት የንግድ ወጪን በእጅጉ በመቀነስ የሀገሪቱን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ያፋጥናል፣ይህም በዓለም አቀፍ የንግድ ስርዓት ውስጥ የተሻለ ተሳትፎ እንድታደርግ ያስችላታል።
የጋራ ተጠቃሚነት መሰረት ያደረገ ችግሩ በኃይል ሳይሆን( Bilateral and Multilateral በሁለትዮሽ ወይም በብዙ ወገን ስምምነቶች፣በጋራ ልማት እና በኢኮኖሚ ትብብር(ለምሳሌ የአፍሪካ ቀንድ የኢኮኖሚ ኮሪደርን በመፍጠር ለዚህም ኢትዮጵያ ለኢኮኖሚያዊ ውህደት እያበረከተች ያለውን ተግባራት መመልከት ይቻላል) አለመግባባቶችን በመፈታት በመጠቆም ጥያቄውን ሰላማዊ መፍትሔ ይሰጣል የሚል አስረጅ ያቀርባል ።
🔴ኮንስትራክቲቪዝም ህልዮት (Constructivism Theory ):-የዚህ ህልዮት ስለ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች የሚያቀነቅነው የሀገር ማንነትን የሚቀርጹት በቁሳዊ ኃይል ሳይሆን በሀሳቦች፣ በማንነት፣ በባህልና በማኅበራዊ ትርክቶች ነው የሚል እሳቤ ያነሳል የጥያቄው ድጋፍንም ይህ ንድፈ-ሀሳብ የጥያቄውን መነሻ ከብሔራዊ ስሜት አንፃር ያብራራል።
ኢትዮጵያ በታሪክ ስሪት ቀዳሚ እና ከቅድመ-አያቶቻችን ጀምሮ በስፍራው የነበረን የላቀ ተሳትፎ እና ኢትዮጵያ የነበራት የንግድና መርከቦች እንዲሁም የሰዎች እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሆኑን እንመለከታለን ይህን የታሪክ ድልድይ ከአሁን ዘመን ትውልድ ጋር የማንነት ግንባታ ይፈጥራል።መንግስት የባህር በርን እንደ "ታሪካዊ መብት" እና "የህልውና ጉዳይ" አድርጎ ማቅረቡ የዜጎችን የህብረት ስሜት እና የጋራ ማንነት ይቀርጻል፤ፍላጎቱ የሚፈጠረው በሀይል ስሌት ሳይሆን በታሪክ እና በብሔራዊ ክብር ትርክት እንደሆነ ያሳያል።
🖊እንደ መውጫ:-
በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የቀይ ባህር ተጋሪነት እና የባህር በር አቅርቦት ጥያቄ በዋናነት በሪያሊዝም(ለደህንነትና ኃይል) እና በሊበራሊዝም(ለኢኮኖሚ ትብብር እና በጋራ መልማት) ኮንስትራክቲቪዝም ህልዮት(የሀገር ማንነትን መቅረፅ) ንድፈ-ሀሳቦች ጠንካራ ድጋፍ ያገኛል።በመሆኑ የብሔራዊ ጥቅም እሴቶችን በመያዝ በትብብር እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት በማድረግ በዜጎች ትብብር እና አንድነት ጥያቄው ወደ ልማት እና ኢትዮጵያን ወደ ሃያልነት የሚመልስ እንደሆነ እንገነዘባለን ።
ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም መሳካት የድርሻዬን እወጣለሁ !
#ethiopia
ለበለጠ ወዳጅነት የፀሃፊውን የኤክስ(X)ገፅ ይከታተሉ :-
https://x.com/HDebasu?t=Bz...

Comments