6 months ago
በነዳጅ ዋጋ ንረት ሳቢያ የሴኔጋል መንግሥት በባለስልጣናት ላይ ጥብቅ የጉዞ እገዳ ጣለ
#ethiopia | በመካከለኛው ምሥራቅ የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተከሰተውን ከፍተኛ የነዳጅ ዋጋ ንረት ለማቋቋም፣ የሴኔጋል መንግሥት በከፍተኛ ባለስልጣናቱ ላይ የውጭ አገር የጉዞ እገዳ መጣሉን አስታወቀ።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዑስማን ሶንኮ በቀጣይ ጊዜያት ሀገሪቱን "እጅግ ፈታኝ" የሆኑ ሁኔታዎች ሊገጥሟት እንደሚችል ጠንከር ያለ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል። ይህንንም ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ራሳቸው ለሥራ ጉዳይ ወደ ኒጀር፣ ስፔን እና ፈረንሳይ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ በመሰረዝ አርአያነት ያለው እርምጃ ወስደዋል።
አዲሱ የመንግሥት መመሪያ ከሚኒስትሮች ጀምሮ እስከ ተለያዩ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችን የሚያጠቃልል ሲሆን፣ ባለስልጣናቱ ከሚመሩት ተቋም ዋና ዓላማ ጋር ቀጥተኛና ወሳኝ ግንኙነት የሌላቸውን ማናቸውንም የውጭ ሀገር ጉዞዎች እንዳያደርጉ በይፋ ታግደዋል።
የዓለም አቀፉ የነዳጅ ገበያ አለመረጋጋት በሴኔጋል ኢኮኖሚ ላይ ከባድ ጫና እያሳደረ ይገኛል። መንግሥት የዘንድሮውን ዓመታዊ በጀት ሲያቅድ የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 62 ዶላር ይሆናል በሚል ስሌት ላይ ተመሥርቶ የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ በከፍተኛ ፍጥነት አሻቅቦ 115 ዶላር መድረሱ ለሀገሪቱ በጀት አፈጻጸም ትልቅ ፈተና ደቅኗል።
የገጠመውን የነዳጅ ዋጋ ንረትና የኢኮኖሚ ጫና በተሻለ ሁኔታ ለመምራት የሚያስችሉ ተጨማሪና ዝርዝር የመንግሥት መመሪያዎች በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ እንደሚደረጉ ተገልጿል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ሴኔጋል #የነዳጅ_ዋጋ #ዓለም_አቀፍ_ዜና #ዑስማን_ሶንኮ #ኢኮኖሚ #senegal #africanews

Comments