27 days ago
የእናቶች እንባ ታበሰ፤ የብዙዎች ቤት በአዲሱ ዓመት በማዕድ ደመቀ!
#ethiopia | «አንድ እንጀራ ለአንዲት እናት» የበጎ አድራጎት ማህበር በ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት ዋዜማ ያቀደውን ታላቅ የበጎ ሥራ በስኬት አጠናቋል።
በብዙ ደጋግ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ያልተቋረጠ ድጋፍ ከ90 በላይ አቅመ ደካማ እናቶች የአዲስ ዓመት ማዕዳቸውን እንዲያሰናዱ ድጋፍ ተደርጓል።
ለእያንዳንዳቸውም፦
3 ሊትር የምግብ ዘይት
5 ኪሎ ጥራት ያለው ዱቄት
በእጃቸው በማድረስ የአዲስ ዓመት ደስታቸውንና ተስፋቸውን ማደስ ተችሏል።
በባዶ ማዕድ ሊያሳልፉ የነበሩ እናቶች ዛሬ ፊታቸው በፈገግታ ተሞልቷል፤ እጆቻቸውንም ወደ ፈጣሪ ዘርግተው ለረዷቸው ሁሉ በረከት ተመኝተዋል።
ውድ አጋሮችና ደጋፊዎቻችን፣
ይህ ታላቅ ስኬት የእናንተ ርኅራኄ፣ ደግነት፣ ሰብአዊነትና ወገናዊ አለኝታነት ውጤት ነው።
በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ሆናችሁ፣ በገንዘባችሁ፣ በሃሳባችሁና በጸሎታችሁ ከጎናችን ለቆማችሁ ደጋግ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፣ በእናቶቻችን ስም ከልብ እናመሰግናለን!
ፈጣሪ አብዝቶ ይተካላችሁ!
ሀገራችንንና ሕዝባችንን ይባርክ!
❤️
እንኳን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
#አንድ_እንጀራ_ለአንዲት_እናት #ethiopia

9 months ago
"አንድ እንጀራ ለአንዲት እናት"
በጎ አድራጎት ማህበር የተፈናቀሉ እናቶችን ማዕድ አጋራ
• ከ200,000 ብር በላይ በሆነ ወጪ ድጋፍ ተደረገ
#ethiopia | "አንድ እንጀራ ለአንዲት እናት" በጎ አድራጎት ማህበር፤ በካዎ ኮይሻ ወረዳ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ተፈናቅለው በአበላ አባያ ወረዳ ሰፍረው ለሚገኙ አቅመ ደካማ እናቶች እስከ መኖሪያ ስፍራቸው ድረስ በመጓዝ የምግብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ማህበሩ ከ201,000 (ሁለት መቶ አንድ ሺህ) ብር በላይ ወጪ በማድረግ የገዛውን ዘይት እና ዱቄት የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ እና ሌሎች የዞኑ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በይፋ አስረክቧል።
የኃላፊዎች መልዕክት፡-
👤 ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ (የወላይታ ዞን ዋና አስተዳደር)፦
በዚህ በጎ ተግባር ላይ ለተሳተፉ አካላት ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን፤ "እንደዚህ ዓይነት በጎ ተግባራት በዞኑ ውስጥ በሚሰሩ ማህበራትና ግለሰቦች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የመንግስት ድጋፍና ክትትል አይለያቸውም" ብለዋል።
👤 ወጣት ስንታየሁ ሾላቶ (የማህበሩ ሰብሳቢ)፦
ማህበሩ ድንበር የሌለው እና ሰብዓዊነትን ብቻ መሠረት አድርጎ የሚሰራ መሆኑን ገልጸዋል። "ከትንሽ የበጎ ተግባራት ተነስቶ በሕዝቡ ዘንድ ተወዳጅነት እያተረፈ ወደዚህ ደረጃ ደርሷል" ያሉት ሰብሳቢው፤ በቀጣይም ከተለያዩ በጎ ፈቃደኞች ጋር በመተባበር ሰፊ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ስራዎችን ለመስራት ማቀዳቸውን ተናግረዋል።
በጎነት ለራስ ነው!
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#wolaita #charity #andenjeraleanditenat #humanity #abelaabaya #ethiopia

Comments