10 days ago
የታዳሽ ኃይል ልማት ጉዞዋን ያጠናከረችው ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይል ልማትና የቀጣናው ትስስር ጉዞ እየተሻሻለ እና ወደ አስተማማኝ አጋርነት እያደገ ይገኛል፡፡
ለአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ዕድገትና የኢንዱስትሪ ሽግግር እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልጽግና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ወሳኝ ነው፡፡
ኢትዮጵያ ይህንን እውነት በመረዳት በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መሪነት የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት የሚያሰፉና የሚያዘምኑ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነች ትገኛለች።
ይህ ስትራቴጂካዊ ጉዞ በሚሊየን የሚቆጠሩ ዜጎችን ከጨለማ ከማውጣት ባለፈ ሀገሪቱን የምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ማዕከል ለማድረግ ያለመ ታላቅ ብሔራዊ ራዕይ ነው።
የዚህ ግዙፍ የኃይል መሠረተ ልማት ግንባታ ግንባር ቀደም ተምሳሌት የሆነው የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የጽናት፣ የጥበብ፣ የአብሮነትና የመተባበር መገለጫ ነው።
ግድቡ የዓባይን ወንዝ ተፈጥሯዊ ፍሰት ሳይገታና የታችኛውን ተፋሰስ ሀገራት ጥቅም ሳይነካ የውሃውን ኃይል ወደ ንጹህ የኤሌክትሪክ ብርሃንነት በመቀየር ረገድ ታሪካዊ ምዕራፍ እየፈጠረ ይገኛል።
የውሃ አሞላልና የግንባታ ምዕራፎቹን በተሳካ ሁኔታ እያጠናቀቀ የሚገኘው ይህ ግዙፍ ተቋም፣ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ አቅርቦት በእጥፍ ለማሳደግ ታላቅ አቅም ሆኗል።
ግድቡ ለኢንዱስትሪ ፓርኮች፣ ለከተሞች መስፋፋትና ለገጠር አካባቢዎች የብርሃን ምንጭ በመሆን የኢኮኖሚውን ሞተር በማንቀሳቀስ ላይ ነው።
ነገር ግን የኢትዮጵያ የኃይል ስትራቴጂ በውሃ ሀይል ወይም በሕዳሴው ግድብ ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም።ሀገሪቱ የኃይል ምንጮቿን ከማስፋት ረገድ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን እያከናወነች ትገኛለች።
በውሃ ኃይል ረገድ እንደ ኮይሻ፣ ግልገል ጊቤ እና ሌሎች የወንዝ ተፋሰሶች ላይ የተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተጨማሪ በሺዎች የሚቆጠሩ ሜጋ ዋት ሀይልን ለብሔራዊ ኃይል ቋት እያበረከቱ ናቸው።
ከዚህም በተጓዳኝ፣ ኢትዮጵያ ካላት የተፈጥሮ ጸጋ በመነሳት የንፋስ ኃይል፣ የፀሐይ ብርሃን ኃይል እና የምድር ውስጥ እንፋሎት ልማቶችን በስፋት እያከናወነች ትገኛለች።
እንደ አሸጎዳ እና አዳማ ያሉ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች እንዲሁም የአሉቶ ላንጋኖ የምድር ውስጥ እንፋሎት ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን ታዳሽ ኃይል ይበልጥ አስተማማኝ እና ከተፈጥሮ መዛባት የተጠበቀ እያደረጉት ይገኛሉ።
ይህ በሀገር ውስጥ የሚመነጨው ግዙፍ የኃይል አቅም ከኢትዮጵያ ድንበር አልፎ ቀጣናዊ ትስስርን ለመፍጠር ትልቅ መሣሪያ እየሆነ ነው።
ኢትዮጵያ "የምሥራቅ አፍሪካ የኃይል ማማ" የመሆን ራዕይዋን ለማሳካት የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን በመዘርጋት ላይ ትገኛለች።
በአሁኑ ወቅት ለጎረቤት ሀገራት እንደ ኬንያ፣ ሱዳን፣ ደቡብ ሱዳን እና ጅቡቲ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ላይ የምትገኝ ሲሆን÷ ይህ ትስስር ወደ ታንዛኒያ እና ሌሎች የደቡብ አፍሪካ ቀጣና ሀገራት እንዲደርስ ሰፊ የዲፕሎማሲና የቴክኒክ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፤ የሙከራ ሸያጭ የተጀመረባቸው ሀገራትም አሉ።
ይህ የኃይል ሽያጭ ለሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኝ ከመሆኑም በላይ በቀጣናው ሀገራት መካከል ያለውን የሰላምና የኢኮኖሚ ትስስር ይበልጥ ማጠናከሪያ የዲፕሎማሲ መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል።
ኢትዮጵያ በሕዳሴው ግድብና በሌሎች ዘርፈ ብዙ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶች ላይ እያደረገችው ያለው ርብርብ የሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ፍላጎትን ለማሟላት ብቻ ሳይሆን ለአካባቢ ጥበቃና ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዕድገት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው።
ኢትዮጵያ በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከተለያዩ የሃይል ምንጮች 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሃይል አመንጭታለች፡፡
በእመቤት ሲሳይ

6 months ago
የአዳማ ከተማ አንዱ ምልክት የሆነው ማማ ምንድን ነው?
#ethiopia | ዓለማችን ከካርቦን ልቀት ለመላቀቅ በምታደርገው ጥረት፣ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች እንደ ዋነኛ የንጹህ ኢነርጂ ምንጭ ጎልተው እየወጡ ነው። እነዚህ በሜዳዎችና በኮረብታዎች ላይ ተተክለው የሚታዩ ግዙፍ ማማዎች፣ ከተራ ሽክርክሪት በስተጀርባ ውስብስብ የሆነ የምህንድስና ጥበብን አዝለዋል።
ከንፋስ ግፊት እስከ ኤሌክትሮን ፍሰት
የኃይል ማመንጨት ሂደቱ የሚጀምረው የተፈጥሮ ንፋስ የማመንጫውን ግዙፍ ምላጮች (Blades) በመግፋት እንቅስቃሴ ሲፈጥር ነው። ይህ ሂደት አየር ላይ ያለውን የእንቅስቃሴ ጉልበት (Kinetic Energy) ወደ ሜካኒካዊ ኃይል ይቀይረዋል።
ሂደቱ በአጭሩ፦
* የማርሽ ሳጥን ሚና፦ የምላጮቹ ሽክርክሪት ኤሌክትሪክ ለማመንጨት ቀርፋፋ በመሆኑ፣ በማሽኑ ውስጥ የሚገኝ የማርሽ ሳጥን ሽክርክሪቱን በመቶዎች ወደሚቆጠር ፈጣን ዑደት ያሳድገዋል።
* የጄነሬተር ስራ፦ ይህ ፈጣን ሽክርክሪት ከጄነሬተር ጋር ይገናኛል። ጄነሬተሩ ውስጥ የሚገኙ ማግኔቶች በናስ ሽቦዎች ዙሪያ በፍጥነት ሲሽከረከሩ የኤሌክትሮማግኔቲክ መስክ በመፍጠር ኤሌክትሪክን ይፈጥራሉ።
* ስርጭት፦ የተመረተው ኃይል በትራንስፎርመር አማካኝነት ቮልቴጁ እንዲጨምር ከተደረገ በኋላ በከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ወደ ከተሞች ይሰራጫል።
ኢትዮጵያና የንፋስ ኃይል
ይህ ቴክኖሎጂ ምንም ዓይነት የበካይ ጋዝ ልቀትን የማያስከትል በመሆኑ ለዓለማችን የአየር ንብረት ጥበቃ ትልቅ ተስፋ ሆኗል። እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀገራትም ይህን የተፈጥሮ ጸጋ በመጠቀም በአዳማ፣ በአሸጎዳና በሌሎች አካባቢዎች ግዙፍ የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን በመገንባት የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እያገዙ ይገኛሉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ #ታዳሽኃይል #የንፋስኃይል #አረንጓዴኢነርጂ #ኢትዮጵያ #ቴክኖሎጂ #አዳማ #አሸጎዳ #renewableenergy #windpower

Comments