7 months ago
መሪር ሐዘን በኢትዮጵያ ሲኒማ
የ"አሸንጌ" ፊልም ዳይሬክተር ጳውሎስ ረጋሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ
#ethiopia | የኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ አንዱን ድንቅ ባለሙያውን አጥቷል።
በፊልም ዳይሬክተርነቱ፣ በሙዚቃ ቀማሪነቱና በፖስት ፕሮዳክሽን (Post-production) ሊቅነቱ የሚታወቀው ጳውሎስ ረጋሳ ዛሬ፣ ቅዳሜ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ጳውሎስ በተለይ "አሸንጌ" የተሰኘውን ድንቅ ፊልም ለታዳሚ በማቅረብ የሚታወስ ባለሙያ ነው።
ለብዙ የዘርፉ ባለሙያዎች የሲኒማ ጥበብ መምህር፣ በተግሳጽና በምክር ያሳደገ ታላቅ ወንድም እንዲሁም ነገሩ ሁሉ ፊት ለፊት የሆነ እውነተኛ ባለሙያ ነበር።
ከዳይሬክተርነት ባለፈ በሙዚቃ ቅንብርና በፊልም ቴክኒክ ሥራዎች ላይ የነበረው ተሰጥኦ ለኢትዮጵያ ሲኒማ ዕድገት ትልቅ አሻራ ጥሎ አልፏል።
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጆቹና ለመላው የኪነጥበብ ቤተሰብ መጽናናትን እንመኛለን።
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ፦
መቼ እንደሚከናወን አስከሬኑ ከሕንድ ሲመጣ የምናሳውቅ ይሆናል።
የጥበብ ሰው ጳውሎስ ረጋሳ ነፍስ ይማር!
#getu #ethiopia #cinema #filmmaking #ashengefilm #paulosregassa #art #tribute #ኢትዮጵያ #ሲኒማ #ጳውሎስረጋሳ #አሸንጌ #ሐዘን #ጌጡተመስገን #getutemesgen

1 year ago
የኢትዮጵያን ሲኒማ ያስመሰገነው
ሲኒማቶግራፈር እና ፕሮዲዪሰር ታምራት መኮንን
(ያሬድ ሹመቴ)
~ ኢትዮጵያዊው "የደሴቷ ጠባቂ" ፊልም የአፍሪካ ብቸኛው እጩ እና አሸናፊ ሆኗል!
~ እንዴት አንድ ፊልም ከ11 ዓመታት በላይ ልፋት ሊጠይቅ ይችላል?
#ethiopia | ታምራት መኮንን ተወልዶ ያደገው በባህርዳር ከተማ ነው። ከልጅነቱ ጀምሮ ለሲኒማ ከነበረው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ በፎቶግራፍ አንሺነት የምስል ነገራ ሙያን ተቀላቀለ።
አዲስ አበባ በገባ በጥቂት ዓመታት ውስጥ ስመ ጥር ሲኒማቶግራፈር እና ዳይሬክተር ኦፎ ፎቶግራፊ በመኾን ከፍተኛ ተወዳጅነትን ማትረፍ በቻሉ ፊልሞች ውስጥ እጁን ማሳረፍ ችሏል።
ለ አብነት ያህልም "አሸንጌ" ፤ "ቀይ ስህተት" እና የበርካታ ተመልካቾችን ቀልብ ለዓመታት መግዛት የቻለው "ስርየት" የተሰኘው ፊልም ከስራዎቹ መሐል ተጠቃሽ ናቸው።
ታምራት መኮንን አሜሪን አገር ኒውዮርክ ከተማ በሚገኘው ኒውዮርክ ፊልም አካዳሚ የሲኒማቶግራፈርነት ትምህርቱን ተከታትሎ በከፍተኛ ውጤት ለመመረቅ በቅቷል።
ለትምህርት በሄደበት አጋጣሚም ከእውቅ ፕሮዲዪሰሮች ጋር ተገናኝቶ እዚያው አሜሪካ ውስጥ ሲኒማቶግራፈር በመኾን ከተወሰኑ ኢንዲፔንደንት ፊልም ሰሪዎች ጋር እና Styles P ከተባለ ከተባለ አሜሪካዊ ዕውቅ ራፐር ጋር የሙዚቃ ቪዲዮ እስከ መስራት ደርሷል።
ታምራት በዓለም አቀፍ መድረክ አገሩን የሚያስጠራ ፊልም ለመስራት አቅዶ ወደ አገሩ በተመለሰ ማግስት የቤተሰቦቹን እና የቅርብ ወዳጆቹን አቅም አሰባስቦ "የደሴቷ ጠባቂ" የተሰኘ ፊልም ፕሮዲዪስ ለማድረግ ተነሳ።
ከ11 ዓመታት በፊት በአገር ውስጥ አቅም ከዚህ ቀደም ባልተደፈረ መልኩ በ5k የጥራት ደረጃ ቀረጻ ለማካሄድ መሳሪያዎችን እና ሙያተኞችን ማሰባሰብ ጀመረ።
የቅርብ ወዳጆቹ ዝነኛዋ ተዋናይት ረቂቅ ተሾመ እና ዝነኛው የፊልም ዳይሬክተር ሰውመኾን ይስማው "የደሴቷ ጠባቂ" የተሰኘውን ፊልም ወጥ ድርሰት ጻፉ። እውቁ አርቲስት ተስፋዬ ወንድማገኝ በፕሮዳክሽን ዲዛይነርነት ቡድኑን ተቀላቀለ። በሰውመኾን ይስማው የዝግጅት መሪነት ታምራትን የተከተሉ ሙያተኞች በጥቂት በጀት ግዙፍ ህልም የያዘውን ፊልም ለማምረት ወደ ባህርዳር አቀኑ።
በደምስ አያሌም ተዋንያን መልማይነት፤ አንተነህ አስረስ ፣ ሚካኤል ሚልዮን ፣ ፍቅረየሱስ ዘውዴ ፣ ሃና ፀጋው ፣ ፍሬሕይወት ገረመው ፣ አቢቹ እና ሌሎችም በርካታ ተወዳጅ እና እውቅ ተዋንያን በታምራት መኮንን ሲኒማቶግራፈርነት እና ፕሮዲዩሰርነት "የደሴቷ ጠባቂ" ፊልም ለመስራት ከዛሬ 11 ዓመት በፊት የባህርዳር ከተማን፣ የዘጌ ደሴትን እና ሰከላን ቤታቸው አድርገው ለወራት ከረሙ።
መቼቱን በአብዮቱ ዘመን ያደረገው "የደሴቷ ጠባቂ" ፊልም በከፍተኛ የጥራት ደረጃ እና ጥበባዊ አቅም ከወራት ትግል በኋላ ቀረጻው ቢጠናቀቅም፤ ሙሉ ፊልሙን በታለመው አቅም አጠናቆ ወደ ተመልካች ለማድረስ ግን ለፍጻሜ የሚያበቃውን በጀት ማግኘት የማይታሰብ ሆነ። ቀሪ የፖስት ፕሮዳክሽን ስራዎችን ከአገር ውጪ ለመጨረስ የሚጠይቀው የበጀት መጠን በአንጻራዊነት በአገር ውስጥ አንድ ፊልም ሰርቶ ለመጨረስ የሚያስፈልግውን ያህል ነበር።
የበጀት ምንጮችን ሲያፈላልግ የቆየው ፕሮዲውሰሩ ታምራት መኮንን፤ ለጊዜውም ቢሆን መፍትሄ ሆኖ ያገኘው በአገር ውስጥ የሚገኙ የንግድ ተቋማትን ማስታወቂያዎች በመስራት ከእነሱ የሚያገኘውን ክፍያ ስራው ላይ ማዋል ነበር።
በዚህም ሰበብ የሃበሻ ቢራ፣ የአዋሽ እና ዳሽን ባንክ፣ የፔፕሲ፣ የኩል ውሃ፣ የአንበሳ ጫማ እና የድል ቀለምን ማስታወቂያዎች ሰርቷል። ታምራት ከእነዚህ ተቋማት ያገኘውን ክፍያ ወደ ሌላ ዘርፍ ከማዋል ይልቅ የፊልሙን ወጪዎች እየደጎመ ለዓመታት መታገልን መረጠ።
በዚህ መሐል ጀርመን አገር ሃምቡርግ ከተማ ውስጥ የሚገኝ በጅምር ላይ ያሉ ፊልሞችን በፌስቲቫሉ ላይ ለሙያተኞች አቅርቦ አሸናፊ ለሚሆን ፊልም የፍጻሜ በጀት ግራንት የሚያደርግ ፌስቲቫል የሚካሄድ መኾኑ ከአንድ ባለሙያ ሰማ።
ይህን ጊዜ ታምራት ተስፈኛ በመኾን ፊልሙን ፌስቲቫሉ ላይ ለማቅረብ የሚያስችል ዝግጅት አድርጎ ቅጂውን እንደያዘ ያልጠበቀውን መርዶ ሰማ። ፊልሙን የማስገቢያ ጊዜ ከአንድ ቀን በፊት አልፎበት ነበር።
በዚህ ጊዜ ይህንን ፌስቲቫል የጠቆመው የ"ልጄስ" ፊልም ደራሲ እና ዳይሬክተር ሰማኝጌታ አይችሉህም የደረሰለት።
ሰማኝጌታ በግሉ ባደረገው ንግግር የፌስቲቫሉን አዘጋጆች ቀኑ ያለፈበት ቢሆን እንኳ የምስሉን ይዘት ተመልክተው እንዲወስኑ አግባባቸው። ፈቃዳቸውንም ሰጡ። የፊልሙ ቅንጭብ ተልኮላቸውም ዐዩት። በፌስቲቫሉ ላይ እንዲቀርብም በይፋ ወሰኑ።
ታምራት መኮንን ለ11 ዓመታት ያህል የታገለበትን ፊልም ይዞ ወደ ሃምቡርግ አቀና።
ቅድመ ልየታውን አልፈው ከመላው ዓለም ከተሰባሰቡ 28 አገራት ጋር "የደሴቷ ጠባቂ" አፍሪካን የወከለ ብቸኛ የኢትዮጵያ ፊልም ሆኖ ቀረበ።
"ሰኞ ዕለት የሌሎች አገራት ሙያተኞች ፊልማቸውን እያቀረቡ በዳኞቹ ፊት ቆመው ፒች (ገለጻዊ ሙግት) ሲያደርጉ የምገባበት ጠፋኝ..." ይላል ታምራት የገጠመውን ጭንቀት ሲያስረዳ።
"... ከኖርዌይ፣ ከብራዚል፣ ከአሜሪካ፣ ከፈረንሳይ፣ ከፔሩ፣ ከግሪክ እና ከሌሎች መሰል አገራት ከፍተኛ ጥበባዊ ደረጃ ያላቸው ፊልሞቻቸውን በዳኞች ፊት እያቀረቡ የእያንዳንዱ አገራት የባህል ሚንስቴር እና የፊልም ፈንድ አድራጊ ተቋማት በስራዎቻቸው እምነት አድሮባቸው ስላደረጉላቸው በጀት ድጋፍ በኩራት ሲናገሩ፦ እኔ ምን መናገር እንዳለብኝ ግራ በመጋባት ፈዝዤ ቀረሁ...
... በዓለም አቀፍ መድረክ የሚቀርቡ ፊልሞች ከፊልም ሰሪው በላይ የሚወክሉት አገራቸውን በመኾኑ 'አገሬ አልወከለችኝም። ያገኘሁትም ምንም ድጋፍ የለም' ብሎ መናገር የሚያመጣው ትርጉሙ ምን እንደሆነ ግራ አጋባኝ...
... በማግስቱ ማክሰኞ ፊልሜን አቅርቤ ከዳኞች የሚቀርቡልኝን ጥያቄዎች ለመመለስ መድረኩ ላይ ስቆም ስለምናገረውን ነገር እርግጠኛ አልነበርኩም። ሆኖም ሃቁን ተናገርኩ። ፊልሙን የሰራሁት በቤተሰቦቼ መጠነኛ እገዛ በጓደኞቼ ከፍተኛ ርብርብ እና ማስታወቂያ እየሰራን ባገኘነው ገንዘብ ብቻ መኾኑን ተናገርኩ።
... ዳኞቹ ፊልማችንን ካዩ እና የኔን ገለጻ ካደመጡ በኋላ "The Father of African Cinema" ተብሎ የሚጠራውን ኦስማን ሲንቤንን በስም እየጠሩ፤ የሰራነውን ፊልም የደረጃ ከፍታ በአቻ ንጽጽሮሽ እያመሰጠሩ አድናቆት እና ምስክርነታቸውን ሲሰጡ፤ የኢትዮጵያ ሲኒማ በአፍሪካ ውክልና ደረጃ ከፍ አድርገው አድናቆታቸውን ሲቸሩ፤ ይሰማኝ የነበረው ስሜት እየሆነ ያለው ነገር ምናባዊ እንጂ ዕውናዊ መኾኑን እስከ መጠራጠር በመድረስ ነበር።" ሲል ታምራት የገጠመውን ድብልቅልቅ ስሜት ያስታውሳል።
"የደሴቷ ጠባቂ" ፊልም በ'ምርጥ ምስል' (Best Picture)፤ በምርጥ አጨዋወት (Best Performance) እና በምርጥ ጭብጥ (Best Theam) የፌስቲቫሉ አሸናፊ ከመኾን ባሻገር የቀረውን የፍጻሜ ስራ ሙሉ ለሙሉ እንዲያጠናቅቅ የሚያስችለውን European Work in Progress GRUVI Award አሸናፊ ሆኖ በድል ተወጥቷል።
በዚህም "የደሴቷ ጠባቂ" ፊልም የ30 ሺህ ዶላር (በግምት 4,345,680.00 አራት ሚልየን ገደማ) የሚያወጣ የፖስት ፕሮዳክሽን ፍጻሜ በጀት ግራንት አሸናፊ መኾን ችሏል።
ታምራት መኮንን "በቃ እዚህ ድረስ ነው የቻልኩት" ብሎ ተስፋ ሳይቆርጥ ለዓመታት ከጓደኞቹ ጋር የለፋበት ስራ "ስንነሳ ያሰብነው ዓለም አቀፍ የጥራት ደረጃውን ካልጠበቀ አላወጣውም!" በማለት ዛሬ ላይ ደርሶ ከእነ "ጤዛ"፤ "Lumb" ፤ እና "አትሌቱ" ፊልሞች በኋላ በታላላቅ ዓለም አቀፍ መድረኮች አገራችንን ዳግሞ የሚወክል ግዙፍ ስራ ይዞ መቅረብ የሚችልበት የተስፋ ብርሐን ወለል ብሎ ተከፍቶለታል።
በመጨረሻ የምትለው ነገር ካለህ ብዬ ጥያቄ አቅርቤለት ነበር፦
"ይሄ ፊልም ለዚህ ስኬት የበቃው፤ ይሄ ቀን እንደሚመጣ በባዶ ሜዳ በታያቸው ፊልሙ ላይ በተሳተፉ ባለራዕይ ጓደኞቼ እና መላው የፊልም ቡድን አባላት ምክንያት ነውና እንኳንም ትልቁን ራዕይ አመናችሁበት! እንኳንም ደስ ያላችሁ በልልኝ" ብሎኛል።
እኔም "የፊልም ሥራ የሚጠይቀውን ቀና ትብብር ላልነፈጉ ቅኖች፤ በድንቅ ትወናቸው ዘውትር ለሚያስደንቁን ከያንያን የአገር ልጆች፤ በድርሰት በዝግጅት እና በሁሉም የሙያ ዘርፍ ተሳትፈው ታሪክ ለሚሰሩ ብርቱ እጆች፤ እንዲሁም በግል ጥረታቸው የአገርን ክብር ዘውትር ለሚያስጠብቁ ጠቢባን ምስጋናም ደስታም ይሁን!!" ብዬ ልቋጨው።
#europeanworkinprogressgruviaward
Tamirat Mekonen
Sewmehon Yismaw Sendekie
Rekik Teshome
Tesfaye Wondmagegn
Anteneh Asres
Michael Million
Dereje Woldemariam
Yared Shumete - ያሬድ ሹመቴ

Comments