1 month ago
ዕንቁ ሴቶች በልዩ የእውቅና ሽልማት ተመሰገኑ
#ethiopia | በተለያዩ የሙያና የሥራ ዘርፎች ስኬታማ በመሆን፣ ለሌሎች ሴቶች አርአያ የሆኑ ሴቶች “ዕንቁ ሴት – ንቁ ሴት” በሚል መርሃ ግብር ዕውቅና ተበርክቶላቸዋል።
ሽልማቱ በጳጉሜ 1 2018 ዓ.ም. በዮድ አቢሲኒያ የባህል ምግብ አዳራሽ፣ ፒያሳ ቴዎድሮስ አደባባይ የተካሄደ ሲሆን፣ የተለያዩ ታዋቂ እንግዶችና የሙያ ተወካዮች ታድመዋል።
🏆 በዕለቱ ዕውቅና ካገኙት መካከል፦
- አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን
- ወይዘሮ ምህረት ጎሳዬ
- የቻለ ማሞ
- መካነ ሰላም መሐመድ
- ቲና ተረፈ
- መስከረም አሰግድ
- ሰናይት በዙ
- ፍሬህይወት ታምሩ
- ፅላት ገዝሙ
- ገነት ከበደ (አቢሲያኒያ)
በመርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ባህልና ኪነ-ጥበብ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ዶ/ር አዲሱ ሻንቆ፣ ዶ/ር ወዳጄነህ ማህረነ እና ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል።
የሽልማቱ የበላይ ጠባቂ ሲስተር ዘቢደር ዘውዴ ሲሆኑ፣ መርሃ ግብሩን ዕንቁ ኤቨንትስ እና ሳሜሎስ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን በጋራ አዘጋጅተውታል።
የሽልማቱ መሥራችና ሀሳብ አመንጪ አቶ ሳሙኤል ገረመው፣ “ሴቶችን ወደፊት ማምጣት አገርን ከፍ ማድረግ ነው” በማለት ተቋማትና ግለሰቦች የሽልማቱን ዓላማ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
ከዚህ ቀደም ለ8 ጊዜ በተካሄደው የ**“ዕንቁ ሴት – ንቁ ሴት”** የእውቅና መርሃ ግብር እስካሁን ድረስ 55 ሴቶች ዕውቅና ማግኘታቸው ተገልጿል።
ዝግጅቱ የተለያዩ ተቋማት፣ የሚዲያ አካላትና ግለሰቦች ባደረጉት አስተዋጽኦ በስኬት ተጠናቋል።
✨ ዕንቁ ሴት – ንቁ ሴት፤ ሴቶችን ማበረታታት፣ ሀገርን ማሳደግ!
እዝራ እጅጉ
#ዕንቁሴት #ንቁሴት #የሴቶችሽልማት #womenempowerment #ethiopia #getutemesgen

Comments