3 months ago
"የ10 ደቂቃ ዋጋ"
።።።።።።።።
አንድ ትንሽ ልጅ የአባቱን አይን እያየ፦
"አባዬ... በአንድ ሰዓት ስንት ብር ታገኛለህ?"
አባቱም በስራ የደከመ ሰውነቱን ለማሳረፍ ወደ ሶፋ ጠጋ እያለ "ለምን ትጠይቀኛለህ?" አለው።
ልጁ በቀስታ፣ "እባክህ ንገረኝ..." አለ።
"500 ብር።"
ልጁ እንደገና ጠየቀ፦
"250 ብር ልታበድረኝ ትችላለህ?"
አባቱ ተናደደ። "መጫወቻ ልትገዛ ከሆነ አኹን ቀጥ ብለህ ወደ ክፍልህ ሂድ!"
ልጁ ዝም ብሎ ገባ።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ አባቱ ተረጋጋ። ወደ ክፍሉ ገብቶ 250 ብሩን ሰጠው።
ልጁም ከትራሱ ስር ያለውን ገንዘብ አወጣ። ሁሉንም ቆጠረ።
አባቱም "ምን እያደረክ ነው?" አለው።
ነገር ግን ልጁ ፈገግ ብሎ እንዲህ አለ፦
"አባዬ... አሁን 500 ብር ሞልቶኛል። ነገ ከእኔ ጋር አንድ ሰዓት ታሳልፋለህ?" አለው።
🕰 Quality Time ውድ ስጦታዎችን አይፈልግም። የወላጅን መገኘት ብቻ ይፈልጋል። በዋናነት አጭር የደቂቃዎች ቆይታ አስር ደቂቃ ሊኾን ይችላል ግን ደግሞ ተከታታይነት የሚፈልግ ሲኾን ሃሳብን ከሚበትን ስክሪን መራቅን ይጠይቃል። በልጆች ሁለንተናዊ እድገት ላይ ተአምራዊ ለውጥ የማምጣት አቅም አለው።
ሰዎች ብዙ ጊዜ የሚያስታውሱት የገዛህላቸውን ነገር ሳይሆን፣ ከእነሱ ጋር ያሳለፍከውን ጊዜ ነው።
💡 ስለዚህ ዛሬ ለልጆቻችን በመገኘት አይረሴ ትዝታዎች ይኑሩን መልዕክቴ ነው።
✍️ ብርሃኑ በላቸው አሰፋ
የክቡር ልጆች ደራሲ ( የ2025 ሕንጸት ተሸላሚ መጽሐፍ)
https://t.me/childdevtnetw...

6 months ago
ልቡ በአምላኩ የታመነ
በዲ/ን ዳንኤል ክብረት
📌ላለፉት ስምንት ዓመታት የማውቃቸው የዐቢይ ስምንት ገንዘቦች እነዚህ ናቸው
1. ቁጭት፡- የኢትዮጵያን ታሪኳን ያነበበ፤ ቅርሶቿን የጎበኘ፤ተራሮቿን የወጣ፤ ዋሻዎቿን የመረመረ፤ የመስጊዶቿንና የአብያተ ክርስቲያናቷን ውስጥ የሚያውቅ፤ በዚህ የተነሣም የኢትዮጵያ ኋላ ቀርነት፣ ድህነትና ተዋርዶ የሚቆጨው፡፡ ስለሚቆጨውም ኢትዮጵያን ወደ ትክክለኛ ቦታዋ ለማድረስ የሚለፋ፡፡
2. እልህ፡- የኢትዮጵያ ድህነትና ኋላ ቀርነት እንደሚቆጨው መሪ፤ ንጋቷን ሳያይ፣ ታሪኳን ሳይቀይር፣ ገናንነቷን ሳይመልስ “ለዓይኖቹ ዕንቅልፍ፣ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት” የሌለው፡፡ ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ጋር እልህ የተጋባ፡፡ ቃል የገባለትን፣ ያመነበትንና ለኢትዮጵያ ይጠቅማል ያለውን - ቀን ለፍቶ፣ ሌት ተንከራትቶ ሳያሳካ በቃኝ የማይል፡፡ የትም፣ መቼም፣ በምንም ሁኔታ ከዓላማው የማይዛነፍ፡፡ ከኋላው ያለውን እየተወ ከፊቱ ያለውን ለመያዝ ያለ ማቋረጥ የሚዘረጋ፡፡
3. ልቡ በአምላኩ የታመነ፡- የአንበሳ ግሣት፣ የሌት ወፍ ጩኸት፣ የእባቡ ፉጨት፣ የዕንቁራሪቱ ማሽካካት ምንም የማይመስለው፡፡ ሁሉም ከአምላኩ በታች መሆኑን የሚያምን፡፡ በባሕሩ ላይ ሲራመድ፣ ማዕበሉን እንዳይፈራ ዓይኑን ከፈጣሪው ላይ ያልነቀለ፡፡ ሁሉን የያዘውን የያዘ፤ ማንም የማያሸንፈውን የተጠጋ፤ የማይለወጠውን የተማመነ፤ ዋጋን ለሠሪ፣ ድልን ለፈጣሪ የሚሰጥ፡፡
4. ትጋት፡- ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ጋር በገባው እልህ የተነሣ ትጋት እግሩ፣ ልፋት ባቡሩ የሆነ፡፡ ቀን እንደ ሠራዊት፣ ሌሊት እንደ መላእክት ሲለፋ የምታየው፡፡ ፕሮጀክትን እንደ ልጁ፣ ሥራን እንደ ወዳጁ የሚያይ፡፡ ሕዝበ አዳም እንደ ቤተልሔም ሰዎች ሲተኛ፣ እሱ እንደ እረኞቹ ወደ ፕሮጀክቶቹ ሌት የሚገሠግሥ፡፡
5. ፍቅር፡- በትጋት የሚያገለግላትን፣ ከድህነቷና ከኋላ ቀርነቷ ጋር እልህ የተጋባባትን፣ የስሟንና የታሪኳን ያህል ባለመሠልጠኗ የሚቆጭላትን ኢትዮጵያን ከልቡ የሚወዳት፡፡ ፍቅሩን በዜማ፣ መንሰፍሰፉን በቁዘማ የማይግልጥ፡፡ ከዚያ ይልቅ - ፍቅሩን በመሥዋዕትነት፣ መንሰፍሰፉን በትጋት የሚገልጥላት፡፡ ልጅ ሆኖ የተዋጋላት፤ መሪ ሆኖ ግንባር የወረደላት፤ የኢትዮጵያ ፍቅር እንደ ሞት የበተረታበት፡፡
6. ሁሌ አዲስ፡- የሚወዳትን ሀገር ዕለት ዕለት አዲስ የሚያደርጋት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን በዓመት ሳይሆን በዕለት የሚለካ፡፡ ለኢትዮጵያ - ትናንት ምን አለፈ? ዛሬ ምን ተሰለፈ? ነገ ምን ተነጠፈዠ፣ የሚል፡፡ የመቶ ዓመታትን ዝግመት በወራት ፍጥነት የሚያካክስ፡፡ ኢትዮጵያን እንደ እናቱ የሚያይ፤ በዚህ የተነሣ የፈሰሰ ሊያቀና፣ የተሰበረ ሊያጸና፣ ትናንትን ሊያድስ፣ ነገን ሊቀይስ የሚተጋ፡፡
7. ፈጠራ፡- ፍጥነት ቁርሱ፣ ፈጠራ ትራሱ፡፡ በፍቅር እንደመር፣ በይቅርታ እንሻገር፤ ከቢሮ እስከ ሀገር፤ አረንጓዴ ዐሻራ፤ ገበታ ለሸገር፤ ገበታ ለሀገር፤ ገበታ ለትውልድ፤ የሌማት ትሩፋት፤ ጽዱና አረንጓዴ ሀገር፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ 5 ሚልዮን ኮደርስ፣ የኮሪደር ልማት፣ ኢትዮጵያ ታምርት፣ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ወዘተ.፤ ስምንት ዓመትን እንደ ስምንት መቶ ዓመት የሠራበት፡፡
8. የማንም/ የሁሉም፡- አወላለዱ፣ አስተዳደጉ፣ የትዳር ሕይወቱ፣ የእምነት ጉዞው፣ የባህል ሥሪቱ፣ የአገልግሎት መንገዱ - የሁሉ የሆነ፡፡ በዚህም የተነሣ የማንም የግል ንብረት ያልሆነ፡፡ ከሁሉም ያለው፡፡ ለሁሉም የሚሰጠው ያለው፡፡ የኢትዮጵያ ለመሆን የተሠራ፡፡ በአንድ ሳጥን ሊቆልፉት የማይቻል፣ አማካይ ለመሆን የታደለ፡፡
"አማን አማን እብለከ፤ ከመ ዘነአምር ንነግር፤ ወበዘርኢነ ሰማዕተ ንከውን -
እውነት እውነት እልሃለሁ። የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን" እንዲል መጽሐፉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

9 months ago
ትራስ የዋጠው ጩኸት፡ "ሚሚ"
ከጋብቻ በፊት ጾታዊ ግንኙነት አልፈጽምም" በማለቷ በትራስ ታፍና የተገደለችው የዳባዋ ወጣት!!
ጥቅምት 5 ቀን። በዳባ ወረዳ የሐና ገዳ ቀበሌ ፀሐይ ሳትወድቅ ጨልማለች። ሚሚ ነጋ (ያች የ21 ዓመቷ ኮረዳ) ነጭ ቀሚሷን ለብሳ ከመስተዋት ፊት ስትቆም፣ ነፍሷ እንደ ልብሷ የነጣ ነበር። የምትወደው ኢዶሳ "ነይ ቡና አፍይልኝ" ሲላት፣ ፍቅር እንጂ ሞት እቤት ውስጥ ይጠብቀኛል ብላ አላሰበችም።
ወደ ቤቱ ስትገባ የቡናው ሽታ ሳይሆን፣ የአየር መከፈት ሽታ ነበር የቀደማት። "ሚሚ" አላት ድምፁን ቀነስ አድርጎ። ያ ድምፅ ግን የፍቅር ሳይሆን የአውሬ ጥሪ ነበር። ኢዶሳ የሚሚን ቅዱስ አቋም ያውቀዋል። "ከጋብቻ በፊት ክብሬን አሳልፌ አልሰጥም" የምትለውን ቃሏን ሊሰብር ቆርጦ ተነሳ።
"እባክህ ኢዶሳ... እንዲህ አንሁን" አለች ሚሚ። ድምጿ እየተንቀጠቀጠ፣ አይኖቿ በእንባ እየራሱ ለመነችው። የ21 ዓመት ህልሟ፣ የቤተሰቧ ኩራት፣ ለነገ ያኖረችው ክብሯ በጠባብ ክፍል ውስጥ ሊረክስ ሲል ተማጸነች። እሱ ግን ፍቅርን ሳይሆን ኃይልን መረጠ። የሚሚ "አይሆንም!" የሚል ጩኸት በቤቱ ግድግዳዎች ውስጥ አስተጋባ።
የመጨረሻው ትግል ተጀመረ። ሚሚ ክብሯን ለማዳን በደካማ እጆቿ ስትታገል፣ ኢዶሳ ግን የክፋት ጋኔን ተቆጣጥሮታል። ለመጮህ አፏን ስትከፍት፣ ሁልጊዜ ጭንቅላቷን የምታሳርፍበት፣ ሰላማዊ እንቅልፍ የምትተኛበት ትራስ አፏ ላይ ተጫነ።
ያን ጊዜ ዓለም ዝም አለች። አየር ለማግኘት የምታደርገው መፍጨርጨር እየቀነሰ መጣ። በትራሱ ውስጥ የተቀበረው ጩኸቷ እግዚአብሔር ዘንድ ደረሰ። የሚሚ ነፍስ ከሥጋዋ ስትለይ፣ አይኖቿ ትኩር ብለው የሚያዩት የሚወዳትን ሰው ሳይሆን፣ ገዳይዋን ነበር። ትንፋሿ ሲቆረጥ የኢዶሳ ጭካኔ አላበቃም፤ የረከሰው ስሜቱን በረዶ በሆነው አስክሬኗ ላይ አረካ።
የምሰሶው ምስጢር
ሌሊቱ ቀጠለ። ኢዶሳ ድርጊቱን ለመሸሸግ የሟቿን አስክሬን አንስቶ ምሰሶ ላይ ሰቀለው። "ራሷን አጠፋች" ለማለት። ያ ምሰሶ ሚሚ ለቤት ውስጥ ሥራ የምትደገፍበት እንጂ፣ የሞት መድረክ ይሆናል ብሎ ማን ጠረጠረ?
ነገር ግን ደም አይደርቅም። ፍትህ በዘገየች ቁጥር የሚሚ ደም ከምድር ላይ ይጮኻል። ፖሊስና ሐኪሞች እውነቱን አወጡት። ትራሱ የገደላት፣ ምሰሶው የተሰቀለችበት እንጂ የሞተችበት እንዳልሆነ ተረጋገጠ።
ዛሬ በዳባ ወረዳ ሰማዩ ሲመሽ የሚሚ ሳቅ አይሰማም። የቀረው ትዝታዋ እና በፍትህ አደባባይ የተወሰነው የ25 ዓመት እስራት ነው። ኢዶሳ በብረት አልጋ ላይ ሆኖ ጸጸት ይቆጥረ ይሆናል፤ ሚሚ ግን ነጭ ልብሷ እንደለበሰች፣ ክብሯን እንደጠበቀች ወደማይመለስበት ዓለም ሄዳለች

10 months ago
የመጽሐፍ ምረቃ ግብዣ !
"#በሳይንት #ሰማይ #ስር " የተሰኘ #በአቶ #ሰፊዓለም #ለበን #ትራሱ የህይወት ጉዞ ፣ ውጣ ውረድ ፣ ስኬትና ፈተና ፣ ከገጠር (#ተድባበ #ማርያም ) አስከ በሀገሪቱ ባሉ ታላላቅ የፋይናንስ ተቋማት ( ብሔራዊ ባንክ ፣ ልማት ባንክ ፣ አቢሲኒያ ባንክና አሀዱ ባንክ ወዘተ ) የነበረን ሰፊ የህይወት ጉዞንና ተሞክሮን በተዋበ ቋንቋና በአስደናቂ ገጠመኞች የተሞላን ታሪክ ጋዜጠኛና ደራሲ ወሰን ደበበ ባመረ መልኩ አዘጋጅቶታል። ይህ የባለብዙ ትምህርትና ልምድ ባለቤት የህይወት ተሞክሮን የያዘ መጽሐፍ ነው።
ቅዳሜ ታኅሳሥ 4 ቀን 2018 ዓ.ም. አራት ኪሎ በሚገኘው የንብ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ሲኒሚ አዳራሽ ከቀኑ 10፡ 00 ሰአት
ጀምሮ ይመረቃል።
በዕለቱ በመጻሕፉ ላይ ሐሳብ የሚያቀርቡ ፦
# መ/ር ዳንኤል ሰይፈሚካኤል
# ሰርጸ ፍሬ ስብሐት
# አገኘሁ አዳነ
ከመጽሐፉ ላይ ንባብ የሚያቀርቡ ፦ ኮሜድያን ደረጄ ኃይሌ
አርቲስት ሱራፌል ተካ
አርቲስት ሸዊት ከበደ
አርቲስት ይገረም ደጀኔ
ገጣምያን ፦ ገጣሚት ምልዕልቲ ኪሮስ
ገጣሚ ደምሰው መርሻ
ሙዚቃ ፦ ባህላዊ የሙዚቃ ባንድ
እንዲህ ድምቅ ባለሁኔታ መጻሕፉ በዕለቱ ይመረቃል በዕለቱ ተገኙ መልዕክቱን ለመጻሕፍፍት ወዳጆች አድርሱልን🙏
#ማስታወሻ የመጻሕፉ ሽያጭ ባለታሪኩ ለተማረባቸው ት/ቤቶች አጋዥ መጻሕፍት መግዣ ይውላል።

Sponsored by
Surafel
Comments