ትራስ የዋጠው ጩኸት፡ "ሚሚ"
ከጋብቻ በፊት ጾታዊ ግንኙነት አልፈጽምም" በማለቷ በትራስ ታፍና የተገደለችው የዳባዋ ወጣት!!
ጥቅምት 5 ቀን። በዳባ ወረዳ የሐና ገዳ ቀበሌ ፀሐይ ሳትወድቅ ጨልማለች። ሚሚ ነጋ (ያች የ21 ዓመቷ ኮረዳ) ነጭ ቀሚሷን ለብሳ ከመስተዋት ፊት ስትቆም፣ ነፍሷ እንደ ልብሷ የነጣ ነበር። የምትወደው ኢዶሳ "ነይ ቡና አፍይልኝ" ሲላት፣ ፍቅር እንጂ ሞት እቤት ውስጥ ይጠብቀኛል ብላ አላሰበችም።
ወደ ቤቱ ስትገባ የቡናው ሽታ ሳይሆን፣ የአየር መከፈት ሽታ ነበር የቀደማት። "ሚሚ" አላት ድምፁን ቀነስ አድርጎ። ያ ድምፅ ግን የፍቅር ሳይሆን የአውሬ ጥሪ ነበር። ኢዶሳ የሚሚን ቅዱስ አቋም ያውቀዋል። "ከጋብቻ በፊት ክብሬን አሳልፌ አልሰጥም" የምትለውን ቃሏን ሊሰብር ቆርጦ ተነሳ።
"እባክህ ኢዶሳ... እንዲህ አንሁን" አለች ሚሚ። ድምጿ እየተንቀጠቀጠ፣ አይኖቿ በእንባ እየራሱ ለመነችው። የ21 ዓመት ህልሟ፣ የቤተሰቧ ኩራት፣ ለነገ ያኖረችው ክብሯ በጠባብ ክፍል ውስጥ ሊረክስ ሲል ተማጸነች። እሱ ግን ፍቅርን ሳይሆን ኃይልን መረጠ። የሚሚ "አይሆንም!" የሚል ጩኸት በቤቱ ግድግዳዎች ውስጥ አስተጋባ።
የመጨረሻው ትግል ተጀመረ። ሚሚ ክብሯን ለማዳን በደካማ እጆቿ ስትታገል፣ ኢዶሳ ግን የክፋት ጋኔን ተቆጣጥሮታል። ለመጮህ አፏን ስትከፍት፣ ሁልጊዜ ጭንቅላቷን የምታሳርፍበት፣ ሰላማዊ እንቅልፍ የምትተኛበት ትራስ አፏ ላይ ተጫነ።
ያን ጊዜ ዓለም ዝም አለች። አየር ለማግኘት የምታደርገው መፍጨርጨር እየቀነሰ መጣ። በትራሱ ውስጥ የተቀበረው ጩኸቷ እግዚአብሔር ዘንድ ደረሰ። የሚሚ ነፍስ ከሥጋዋ ስትለይ፣ አይኖቿ ትኩር ብለው የሚያዩት የሚወዳትን ሰው ሳይሆን፣ ገዳይዋን ነበር። ትንፋሿ ሲቆረጥ የኢዶሳ ጭካኔ አላበቃም፤ የረከሰው ስሜቱን በረዶ በሆነው አስክሬኗ ላይ አረካ።
የምሰሶው ምስጢር
ሌሊቱ ቀጠለ። ኢዶሳ ድርጊቱን ለመሸሸግ የሟቿን አስክሬን አንስቶ ምሰሶ ላይ ሰቀለው። "ራሷን አጠፋች" ለማለት። ያ ምሰሶ ሚሚ ለቤት ውስጥ ሥራ የምትደገፍበት እንጂ፣ የሞት መድረክ ይሆናል ብሎ ማን ጠረጠረ?
ነገር ግን ደም አይደርቅም። ፍትህ በዘገየች ቁጥር የሚሚ ደም ከምድር ላይ ይጮኻል። ፖሊስና ሐኪሞች እውነቱን አወጡት። ትራሱ የገደላት፣ ምሰሶው የተሰቀለችበት እንጂ የሞተችበት እንዳልሆነ ተረጋገጠ።
ዛሬ በዳባ ወረዳ ሰማዩ ሲመሽ የሚሚ ሳቅ አይሰማም። የቀረው ትዝታዋ እና በፍትህ አደባባይ የተወሰነው የ25 ዓመት እስራት ነው። ኢዶሳ በብረት አልጋ ላይ ሆኖ ጸጸት ይቆጥረ ይሆናል፤ ሚሚ ግን ነጭ ልብሷ እንደለበሰች፣ ክብሯን እንደጠበቀች ወደማይመለስበት ዓለም ሄዳለች

9 months ago