ልቡ በአምላኩ የታመነ
በዲ/ን ዳንኤል ክብረት
📌ላለፉት ስምንት ዓመታት የማውቃቸው የዐቢይ ስምንት ገንዘቦች እነዚህ ናቸው
1. ቁጭት፡- የኢትዮጵያን ታሪኳን ያነበበ፤ ቅርሶቿን የጎበኘ፤ተራሮቿን የወጣ፤ ዋሻዎቿን የመረመረ፤ የመስጊዶቿንና የአብያተ ክርስቲያናቷን ውስጥ የሚያውቅ፤ በዚህ የተነሣም የኢትዮጵያ ኋላ ቀርነት፣ ድህነትና ተዋርዶ የሚቆጨው፡፡ ስለሚቆጨውም ኢትዮጵያን ወደ ትክክለኛ ቦታዋ ለማድረስ የሚለፋ፡፡
2. እልህ፡- የኢትዮጵያ ድህነትና ኋላ ቀርነት እንደሚቆጨው መሪ፤ ንጋቷን ሳያይ፣ ታሪኳን ሳይቀይር፣ ገናንነቷን ሳይመልስ “ለዓይኖቹ ዕንቅልፍ፣ ለሽፋሽፍቶቹ ዕረፍት” የሌለው፡፡ ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ጋር እልህ የተጋባ፡፡ ቃል የገባለትን፣ ያመነበትንና ለኢትዮጵያ ይጠቅማል ያለውን - ቀን ለፍቶ፣ ሌት ተንከራትቶ ሳያሳካ በቃኝ የማይል፡፡ የትም፣ መቼም፣ በምንም ሁኔታ ከዓላማው የማይዛነፍ፡፡ ከኋላው ያለውን እየተወ ከፊቱ ያለውን ለመያዝ ያለ ማቋረጥ የሚዘረጋ፡፡
3. ልቡ በአምላኩ የታመነ፡- የአንበሳ ግሣት፣ የሌት ወፍ ጩኸት፣ የእባቡ ፉጨት፣ የዕንቁራሪቱ ማሽካካት ምንም የማይመስለው፡፡ ሁሉም ከአምላኩ በታች መሆኑን የሚያምን፡፡ በባሕሩ ላይ ሲራመድ፣ ማዕበሉን እንዳይፈራ ዓይኑን ከፈጣሪው ላይ ያልነቀለ፡፡ ሁሉን የያዘውን የያዘ፤ ማንም የማያሸንፈውን የተጠጋ፤ የማይለወጠውን የተማመነ፤ ዋጋን ለሠሪ፣ ድልን ለፈጣሪ የሚሰጥ፡፡
4. ትጋት፡- ከድህነትና ከኋላ ቀርነት ጋር በገባው እልህ የተነሣ ትጋት እግሩ፣ ልፋት ባቡሩ የሆነ፡፡ ቀን እንደ ሠራዊት፣ ሌሊት እንደ መላእክት ሲለፋ የምታየው፡፡ ፕሮጀክትን እንደ ልጁ፣ ሥራን እንደ ወዳጁ የሚያይ፡፡ ሕዝበ አዳም እንደ ቤተልሔም ሰዎች ሲተኛ፣ እሱ እንደ እረኞቹ ወደ ፕሮጀክቶቹ ሌት የሚገሠግሥ፡፡
5. ፍቅር፡- በትጋት የሚያገለግላትን፣ ከድህነቷና ከኋላ ቀርነቷ ጋር እልህ የተጋባባትን፣ የስሟንና የታሪኳን ያህል ባለመሠልጠኗ የሚቆጭላትን ኢትዮጵያን ከልቡ የሚወዳት፡፡ ፍቅሩን በዜማ፣ መንሰፍሰፉን በቁዘማ የማይግልጥ፡፡ ከዚያ ይልቅ - ፍቅሩን በመሥዋዕትነት፣ መንሰፍሰፉን በትጋት የሚገልጥላት፡፡ ልጅ ሆኖ የተዋጋላት፤ መሪ ሆኖ ግንባር የወረደላት፤ የኢትዮጵያ ፍቅር እንደ ሞት የበተረታበት፡፡
6. ሁሌ አዲስ፡- የሚወዳትን ሀገር ዕለት ዕለት አዲስ የሚያደርጋት፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን በዓመት ሳይሆን በዕለት የሚለካ፡፡ ለኢትዮጵያ - ትናንት ምን አለፈ? ዛሬ ምን ተሰለፈ? ነገ ምን ተነጠፈዠ፣ የሚል፡፡ የመቶ ዓመታትን ዝግመት በወራት ፍጥነት የሚያካክስ፡፡ ኢትዮጵያን እንደ እናቱ የሚያይ፤ በዚህ የተነሣ የፈሰሰ ሊያቀና፣ የተሰበረ ሊያጸና፣ ትናንትን ሊያድስ፣ ነገን ሊቀይስ የሚተጋ፡፡
7. ፈጠራ፡- ፍጥነት ቁርሱ፣ ፈጠራ ትራሱ፡፡ በፍቅር እንደመር፣ በይቅርታ እንሻገር፤ ከቢሮ እስከ ሀገር፤ አረንጓዴ ዐሻራ፤ ገበታ ለሸገር፤ ገበታ ለሀገር፤ ገበታ ለትውልድ፤ የሌማት ትሩፋት፤ ጽዱና አረንጓዴ ሀገር፤ ዲጂታል ኢትዮጵያ፣ የምግብ ሉዓላዊነት፣ 5 ሚልዮን ኮደርስ፣ የኮሪደር ልማት፣ ኢትዮጵያ ታምርት፣ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም፣ ወዘተ.፤ ስምንት ዓመትን እንደ ስምንት መቶ ዓመት የሠራበት፡፡
8. የማንም/ የሁሉም፡- አወላለዱ፣ አስተዳደጉ፣ የትዳር ሕይወቱ፣ የእምነት ጉዞው፣ የባህል ሥሪቱ፣ የአገልግሎት መንገዱ - የሁሉ የሆነ፡፡ በዚህም የተነሣ የማንም የግል ንብረት ያልሆነ፡፡ ከሁሉም ያለው፡፡ ለሁሉም የሚሰጠው ያለው፡፡ የኢትዮጵያ ለመሆን የተሠራ፡፡ በአንድ ሳጥን ሊቆልፉት የማይቻል፣ አማካይ ለመሆን የታደለ፡፡
"አማን አማን እብለከ፤ ከመ ዘነአምር ንነግር፤ ወበዘርኢነ ሰማዕተ ንከውን -
እውነት እውነት እልሃለሁ። የምናውቀውን እንናገራለን፤ ያየነውንም እንመሰክራለን" እንዲል መጽሐፉ።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

6 months ago