7 months ago
''ደምን በገንዘብ በሚሸጡ የጤና ተቋማት ላይ ጥብቅ እርምጃ ይወሰዳል'' የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት
#ethiopia | የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ከበጎ ፈቃደኞች በነጻ የተሰበሰበውን ደም ለታካሚዎች በገንዘብ በሚሸጡ የመንግስትም ሆነ የግል የጤና ተቋማት ላይ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል።
የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አምሳሉ ታዬ እንደገለጹት፤ ደም የሚሰበሰበው የሰው ልጅን ህይወት ለማዳን ሲሆን፣ ማንኛውም የጤና ተቋም ለታካሚዎች በነጻ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
ሆኖም አንዳንድ ተቋማት ‘የአገልግሎት ክፍያ’ በሚል ስም ከታካሚዎች ገንዘብ እንደሚቀበሉ የሚደርሱ ጥቆማዎች እንዳሉ አመልክተዋል። ይህን ብልሹ አሰራር ለመግታት ተቋሙ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ አስታውቋል።
ተቋሙ ከጤና ተቋማቱ ጋር በገባው የመግባቢያ ሰነድ መሰረት ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ስርአት እየዘረጋ መሆኑንና በቀጣይም የደም አገልግሎትን የሚመለከት ህግ በማውጣት የቁጥጥር ስራውን ለማጠናከር እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እንደገለፁት፤ አንድ ዩኒት ደም ለህክምና ዝግጁ ለማድረግ ከተሰበሰበ በኋላ እንደ ኤች.አይ.ቪ፣ ሄፓታይተስ እና ሲፊሊስ ካሉ በሽታዎች ነጻ መሆኑን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ ምርመራዎች እንዲሁም ደሙን ወደ ቀይ የደም ሴል፣ ፕሌትሌት እና ፕላዝማ ለመለየት የሚሰሩ ስራዎች ከፍተኛ ወጪ ይጠይቃሉ።
ለነዚህ ስራዎች የሚጠይቁት የቴክኖሎጂና የኬሚካል ግብአቶች በሙሉ በውጭ ምንዛሬ የሚገዙ በመሆናቸው በአማካይ እስከ 46 ዶላር ወጪ ይደረግበታል።
አቶ አምሳሉ አያይዘውም የሀገሪቱ የደም አቅርቦት ከፍላጎቱ በአማካይ በግማሽ እንደሚያንስ ገልፀዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiofm #getutemesgen #getu #ጌጡ #ኢትዮጵያ #ደምባንክ #ጤና #ህይወት #በጎፈቃደኝነት #ደምልገሳ #ቁጥጥር #እርምጃ

Comments