23 days ago
የአባቶች ምርቃት፦ ከልብ የመነጨ የደስታ እንባና ምስጋና!
ዓመት አልፏል…
ወጥተናል… ወርደናል…
ነግደናል… አትርፈናል…
ተምረናል… ሠርተናል…
ብዙ ነገር አድርገናል…
ግን… ለነፍሳችንስ?
እኛ አዲሱን ዓመት በአዲስ ተስፋ፣ በአዲስ ሕልምና በአዲስ ጉልበት ልንቀበል ስንዘጋጅ፣ በገዳማት፣ በረሃማ አካባቢዎችና በገጠር አብያተ ክርስቲያናት የሚኖሩ አባቶች፣ መነኮሳትና መነኮሳያት ምን ይጠብቃሉ?
ምናልባት… የእርስዎን ትንሽ ልግስና ብቻ።
አንድ ጧፍ…
እጣን…
ዘቢብ…
ዕጣን ማቅረቢያ ወይም ሌላ የአምልኮ አገልግሎት ቁሳቁስ…
እንኳን መርፌና ክር ቢሆን…
ለእነሱ ትልቅ ተስፋ ሊሆን ይችላል።
ማኅበረ ጽዮን — 53 ዓመታት የአገልግሎት ጉዞ
ማኅበረ ጽዮን ለ53 ዓመታት በታማኝነት ያገለገለውን ተልዕኮ በመቀጠል፣ የጳጉሜን ወራትንና የመስቀል በዓልን አስመልክቶ ልዩ የዲጂታል ገቢ ማሰባሰቢያ ዘመቻ ጀምሯል።
እግዚአብሔር ቢፈቅድ፣ ዘንድሮም በገዳማትና በረሃማ አካባቢዎች የሚገኙ አባቶችን፣ መነኮሳትን፣ መነኮሳያትን እና የእመቤታችንን እንግዶች ለመደገፍ ይሠራል።
አዲሱን ዓመት በአዲስ ልብ እንቀበል።
የምንሰጠው ምንም ያህል ትንሽ ቢሆን፣ ለሌላ ሰው ትልቅ ተስፋ ሊሆን ይችላል።
መልካም ሥራ ከተሠራ በኋላ የለውም።
ለመለገስ
አቢሲኒያ ባንክ: 2121 / 1365417
ሕብረት ባንክ: 1481111630915017
አሐዱ ባንክ: 0008364120301
ዛሬ የምንሰጠው ትንሽ ነገር፣ ነገ የአንድ አባት የደስታ እንባ ሊሆን ይችላል።
እንለግስ፤ እንደግፍ፤ በረከትን እንካፈል!
#ማኅበረጽዮን #የበጎአድራጎትጥሪ #ምርቃት #በጎሥራ #share #ethiopia
1 month ago
ይህን ቪዲዮ በአጋጣሚ አላዩትም…
በገዳማት፣ በገጠር አብያተ ክርስቲያናትና በአብነት ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ከ3,500 በላይ ነዳያን፣ አባቶችና እናቶች የእርስዎን የድጋፍ እጅ ይጠብቃሉ።
ለ53 ዓመታት በታማኝነት ያገለገለው ማኅበረ ጽዮን በዚህ የበዓል ወቅት ያካሄደውን የበጎ አድራጎት ዘመቻ ለመደገፍ የበኩልዎን ይወጡ።
የድጋፍ አካውንቶች
አቢሲኒያ ባንክ
1365417 / 2121
ሕብረት ባንክ
1481111630915017
አሐዱ ባንክ
0008364120301
እርስዎ የሚያደርጉት Like እና Share ሌላ ሰው የሚዘረጋው የድጋፍ እጅ ሊሆን ይችላል።
Like ያድርጉ፣ Share ያድርጉ፣ መልዕክቱን ያድርሱ!
“ወርኃ ጳጉሜንን በበጎ ሥራ ሸኝተን፤ አዲሱን ዓመት በበረከት እንቀበል!”
#ማኅበረጽዮን #የበጎአድራጎትጥሪ #ጳጉሜን #በጎሥራ #share #ethiopia
Comments