21 days ago
"ዜጎችን በሙያ በማብቃት ከጥገኝነት ለማውጣት እየሰራን ነው!" ወይዘሮ ሀናን ሙሐመድ
#ethiopia | ባቡል ኸይር የበጎ አድራጎት ድርጅት ተረጂነትን በክህሎት የመተካት ራዕዩን ለማሳካት ለሰባተኛ ጊዜ ያሰለጠናቸውን ወጣቶች ዛሬ አስመርቋል፡፡
በልዩ ልዩ የሙያ መስኮች ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 80 ሰልጣኞች የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደመቀ ሁኔታ የምረቃ ስነ ስርዓታቸውን አካሂደዋል፡፡
የድርጅቱ መስራችና ሥራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሀናን ሙሀመድ በመርሃ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ ከስድስት ዓመታት በፊት በ16 ሴቶች ጥረት በምግብ ድጋፍ ስራ መጀመሩን አስታውሰው፤ ዛሬ ላይ ዜጎችን በክህሎት አብቅቶ ወደ አምራችነት የሚያሸጋግርበት ደረጃ ላይ መድረሱ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ተመራቂዎቹም ያገኙትን እውቀት በመጠቀም ራሳቸውን እንዲለውጡና ለሀገራቸው የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዕለቱ ከተመረቁት መካከል 52ቱ በልብስ ስፌት፣ 21ዱ በመሰረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና እንዲሁም 7ቱ በቋንቋ ትምህርት የሰለጠኑ ናቸው፡፡
ሰልጣኞቹ ወደ ስራው ዓለም በቀላሉ እንዲገቡ ለማገዝ እንደ ውጤታቸው የልብስ ስፌት ማሽኖችና የገንዘብ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል፡፡
ባቡል ኸይር እስካሁን ከ500 በላይ ዜጎችን ያስመረቀ ሲሆን፤ በቀጣይም የራሱን የጋርመንት ፋብሪካ በማቋቋም ሰልጣኞቹን በቋሚነት ቀጥሮ ለማሰራት እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡
በምረቃው ላይ የተገኙት የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ እና የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ የስራ ኃላፊዎች በበኩላቸው፤ ድርጅቱ ችግረኞችን በዘላቂነት ለመደገፍና ወደ ስራ ለማስገባት እያከናወነ ያለው ተግባር የሚደነቅና ተጠናክሮ ሊቀጥል የሚገባው መሆኑን ገልጸዋል፡፡
#ባቡልኸይር #ምረቃ #ሙያዊስልጠና #በጎአድራጎት #ኢትዮጵያ #አዲስአበባ #ክህሎት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa