1 month ago
የቅዱስ ላሊበላ የትርጓሜ ትምህርት ቤት ጉዞ
ክፍል ፫
#ethiopia | በባለፈው ክፍላችን — በደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የአዲስ ኪዳን ትርጓሜና ነገረ ድኅነት በህንፃዎቹ አሰራርና በመልከአ ምድራዊ አደረጃጀቱ እንዴት በቀጥታ ይገለጥ እንደነበር፣ የብሉይ እና የአዲስ ኪዳን ትስስር፣ እንዲሁም ከወቅቱ የግብፅ ጳጳስ ጋር ተያይዞ የተከሰተውን ታሪካዊ አጋጣሚ ተመልክተናል።
በአሁኑ ክፍላችን ደግሞ የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ ታሪክና የትርጓሜ ትምህርት ቤት በሂደት እንዴት ሊደክም እና ሊቋረጥ እንደቻለ፣ የታሪክ አጠናቃሪዎች ክፍተት ምን እንደነበረ፣ እንዲሁም ከዘመናት መቋረጥ በኋላ ትምህርት ቤቱ እንደገና እንዴት ሊያንሰራራ እንደቻለ የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የአራቱ ጉባኤያት መጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርት ቤት መምህር ሊቀ ሊቃውንት ሳሙኤል አስናቀ ከሰጡት ማብራሪያ ጋር አያይዘን እንመለከታለን።
የታሪክ ድርሳናት እንደሚጠቁሙት በሀገራችን በነበሩ ፈታኝ የታሪክ አጋጣሚዎችና በተለይም በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አካባቢ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከፍተኛ የሆነ የሥርዓትና የትምህርት መዋቅራዊ መደናቀፍ ገጥሟት ነበር።
ሊቀ ሊቃውንት ሳሙኤል አስናቀ እንደሚያስረዱት፤ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኋላ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከሃይማኖቱ መሠረታዊ እውቀትና ከነገረ መለኮት ምስጢር ጀምሮ የምታስተምረውን ያንን ጥልቅ ትምህርት ማስተማር አቁማ ቆይታለች። የቀደመው ታላቅ የጉባኤ ሥርዓት ደክሞ፣ ቤተ ክርስቲያኒቱ እንዳትዘጋና አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ ብቻ በማሰብ የዜማና የጸሎት ሥርዓቱ ላይ ትኩረት ተደርጎ እንዲቀጥል የተደረገበት የታሪክ አጋጣሚ ነበረ።
በደብረ ሮሃም ቢሆን በሂደት ከትርጓሜና ከሊቃውንት አንጻር የሚመጥን ተቋማዊ ትምህርት ቤት ሳይዘረጋ በመቆየቱ ምክንያት፣ ትምህርቱ እስከ መቋረጥ ደረጃ ደርሶ ነበረ። እንዳንድ አብያተ ክርስቲያናት እንኳ ቀዳሽ ካህን አጥተው የተዘጉበት ጊዜ እንደነበረ ታሪክ ያሳያል። ኋላ ላይ በቦታው በነበሩ አስተዳዳሪዎች በተለይም እንደ አባ ብርሃነ ሥላሴ ባሉ አባቶች ጥረት በቦታው የተወለዱ ልጆች ሄደው የዜማውንና የድጓውን ትምህርት ተምረው እንዲመጡ በማድረግ ታላቅ እንክብካቤ ከተደረገ በኋላ አገልግሎቱ ሊቀጥል ችሏል።
ይሁን እንጂ የታሪክ አጠናቃሪዎችና የጸሐፊያን ክፍተት ትምህርት ቤቱ በሂደት እንዲሸፈንና ታሪኩም እንዲደበዝዝ ካደረጉ ዋና ዋና ምክንያቶች አንዱ ነበረ። ሊቀ ሊቃውንት ሳሙኤል አስናቀ እንደሚገልጹት፤ ቅዱስ ላሊበላ ለአገርና ለቤተ ክርስቲያን ያደረገው አስተዋጽኦ፣ በወቅቱ ሶሪያ ድረስ አራት ጳጳሳትን እስከ መሾም የደረሰበት ታላቅ መንፈሳዊ ተጽዕኖና በደብረ ሮሃ የነበረው ከፍተኛ እንቅስቃሴ በግልጽ ተጽፎ ወይም ተመዝግቦ ባለመያዙ ምክንያት እውነተኛው ታሪክ ሳይገለጥ ቆይቷል።
በቅርብ ዘመናት ትምህርት ቤቱን እንደገና ለመተከል በተደረጉ ሙከራዎችም ቢሆን መሠረታዊ የታሰበ ተቋማዊ መዋቅርና እንክብካቤ ይጎድለው ነበረ። ሊቀ ሊቃውንት ሳሙኤል እንደሚናገሩት፤ ትምህርት ቤቱ ሲጀመር በጠቅላይ ቤተ ክህነት ደረጃ ለአንድ ተማሪ 70 ብር እየተከፈለ በጣም በጥቂት ተማሪዎች ነበረ የተጀመረው። ትምህርት ቤቱ ተቋማዊ ማህተም፣ ራሱን የቻለ ህግና የሂሳብ ደብተር፣ እንዲሁም የተደራጀ ጽሕፈት ቤት ሳይኖረው ለ24 ዓመታት ያህል በመቆየቱ ተማሪዎች በቂ ምግብና ማረፊያ አጥተው ይፈተኑ ነበረ።
ተማሪዎች እዚያው ይገኙ በነበሩት መጋዘኖችና ተገቢ ባልሆኑ ቦታዎች እየተኙ፣ በታላቅ የመከራና የችግር ጉዞ ውስጥ አልፈዋል። መምህርና ደቀ መዛሙርቱ በዕለት ተዕለት ኑሮአቸው ስለሚበሉትና ስለሚያድሩበት ነገር እንዲጨነቁ መደረጉ ደግሞ ትምህርት ቤቱ በሚፈለገው ልክ ፍሬያማ እንዳይሆን አድርጎት ቆይቷል።
በኋላም በ2015 ዓ.ም አካባቢ በመምህር ሊቀ ሊቃውንት ልብሰ ማርያም አራቱ ጉባኤ እንደገና እንዲከፈት ተደርጎ የነበረ ቢሆንም፣ በተከሰቱት የእንክብካቤና የትኩረት ማጣት ችግሮች ምክንያት ከስድስት ወራት ቆይታ በኋላ መምህሩ በመውጣታቸው ትምህርት ቤቱ እንደገና ተዘጋ፤ ደቀ መዛሙርቱም ተበተኑ።
ከዚህ ሁሉ ዘመናት መቋረጥና መደናቀፍ በኋላ ግን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በሊቃውንቱና በምዕመናን ጥረት ትምህርት ቤቱ እንደገና የሚያንሰራራበት አዲስ ምዕራፍ ተከፈተ። በ2016 ዓ.ም ነሐሴ ፍልሰታ አካባቢ ወደ ቦታው የገቡት ሊቀ ሊቃውንት ሳሙኤል አስናቀ፣ በ2017 ዓ.ም መስከረም መጨረሻ አካባቢ ወንበር ዘርግተው የአራቱ ጉባኤያት መጻሕፍት ትርጓሜ ትምህርቱን በይፋ አስጀምረዋል።
ሲጀምሩ የነበሩት የህንፃ፣ የስንቅ፣ የማረፊያና የመጻሕፍት እጥረት እጅግ ፈታኝ ነበሩ። ነገር ግን በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መመሪያ፣ በአካባቢው ምዕመናንና ታላላቅ ገዳማት ድጋፍ ትምህርት ቤቱ እንደገና እንዲደራጅ ተደረገ። ለምሳሌ ከተከዜ ምዕራፈ ቅዱሳን አቡነ ሀዋሪያ ክርስቶስ ኪዳነምህረት አንድነት ገዳም ሁለት መነኮሳትን ለመማር ሲልክ የትምህርት ክፍሉንና ቤቱን ለመሥራት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን አምጥቶ ድጋፍ አድርጓል፤ ሌሎች አባቶችና ምዕመናንም እንዲሁ አብረው ቆመዋል።
ዛሬ የደብረ ሮሃ ቅዱስ ላሊበላ የትርጓሜ ትምህርት ቤት ከ20 ወደ 60 በሚጠጉ ቋሚ ደቀ መዛሙርት አድጓል። ተማሪዎቹም ከተለያዩ ሀገራችን ክፍሎች ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከጉራጌ፣ ከጎንደር፣ ከሸዋና ከጎጃም የመጡ ናቸው። ትምህርት ቤቱም የቆየውን ባህላዊ አሰራር ከዘመናዊ አደረጃጀት ጋር በማጣመር የትምህርት፣ የስልጠና፣ የኮምፒውተር፣ የህዝብ ግንኙነትና የልማት ክፍሎችን አቋቁሟል።
በተለይም ደቀ መዛሙርቱ ትርጓሜውን በቃል ከመያዝ ባለፈ በኮምፒውተር እንዲጽፉ፣ ጥናታዊ ጽሑፎችን በማዘጋጀት በጉባኤው ፊት አቅርበው እንዲተቹ፣ እንዲሁም ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን (ላፕቶፖችና ፕሪንተሮችን) በመጠቀም እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ ተደርጓል። ይህም ተማሪዎች የትምህርቱን ምስጢርና አረዳድ በጥበብ እንዲጨብጡ አስችሏቸዋል።
የዚህ አዲስ ማንሰራራት ውጤት ደግሞ በበዓላት ወቅት መታየት ጀምሯል። ከተለያዩ ቋንቋዎች የመጡ ደቀ መዛሙርት የግዕዝንና የአማርኛን ትርጓሜ በሚገባ አጥንተው፣ በቅዱስ ላሊበላ በሚገኙ በ10 ቤተ መቅደሶችና በአካባቢው በሚገኙ ጥንታዊ አብያተ ክርስቲያናት እንደ ገነተ ማርያም፣ ነአክቶ ለአብ፣ አሸተን ማርያም ና ይምርሃነ ክርስቶስና ባሉት ታላላቅ መድረኮች ወንጌልንና የሕማማት ትርጓሜን ፣ ውዳሴ ማርያም ቅዳሴ ማርያም ትርጓሜን በብቃት መተርጎም ጀምረዋል። ይህ ስኬት ደብረ ሮሃ እንደ ቀደመ ታሪኳ የጥበብና የወንጌል ትርጓሜ ማዕከልነቷን እንደገና እየመለሰች መሆኗን የሚያበስር ህያው ምስክር ነው።
በቀጣዩ ክፍል (ክፍል ፬ እና የመጨረሻው)፦
የደብረ ሮሃ የትርጓሜ ትምህርት ቤት የወደፊት ራእይና የረጅም ጊዜ ግብ ምንድን ነው?
ትምህርት ቤቱ ለአገራችንና ለዓለም አቀፉ መንፈሳዊ ማህበረሰብ የሚያበረክተው ዘላቂ አስተዋጽኦ፤

3 months ago
ቅዱስ ዑራኤል ከክፉ ነገር ሁሉ ይከልለን፤ምልጃው እና ረድኤቱም አይለየን🙏
ለተፈቀደላቸው ሁሉ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ይገልጣል🙏
ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33፥7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል” በማለት እንደተናገረ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩት ሰዎች በጨነቃቸው ጊዜ በመካከላቸው እየተገኘ ያጽናናቸዋል። ምሥጢር ይገልጥላቸዋል፤ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቃቸዋል። ዑራኤል ማለት “ብርሃነ እግዚአብሔር” ማለት ነው። ዑራኤል በብርሃናት ላይ ሁሉ የተሾመ ነው፡፡ በመጽሐፈ ሔኖክ 6፥2 “ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ዑራኤል በመብረቅና በነጎድጓድ የተሾመ ነው” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ከሊቃነ መላእክት አንዱ መሆኑንና ፍርሃት ረዓድ ላለባቸው ረዳታቸው እንደሆነ የመላእክትን ነገር የተናገረ ሄኖክ ነግሮናል፡፡ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ገላጭ ነው።
ምሥጢር ማናገር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆንም የተሠወረውን መግለጥ፣ በአዲስ ቋንቋ ማናገር ለመላእክት የተሰጠ ጸጋቸው መሆኑም ግልጽ ነው። የተወደደ ሥራ ለሚሠሩና እንዲያውቁ ለተፈቀደላቸው ሁሉ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ይገልጣል፡፡ በመጽሐፈ ዕዝራ ሱትኤል 13፥38 እንደተጻፈው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ዕዝራ ሱቱዔልን “አፍህን ክፈት፤ እኔም የማጠጣህን ጠጣ” ብሎ ሐምሌ 22 አእምሮና ማስተዋልን ገልጦለታል። ለሄኖክም ምሥጢረ ሰማይንና ዕውቀትን የገለጠለት እርሱ ነው፡፡ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ልቡናውን ያበራለት ይህ መልአክ እንደሆነ ገዳሙ ባሳተመው ገድሉ ላይ ተጽፏል። በዚህ አገልግሎቱም ሊቃውንቱ “ከሣቴ ምሥጢር” ወይም “ምስጢርን የሚገልጽ” ይሉታል። አፋቸውን ከፍተው የምስጋና ቃል የሚናገሩ ሁሉ ክብርና ጥበቃን ከመላእክት ይቀበላሉ፡፡
ዕዝራ ለረጅም ወራት እግዚአብሔርን ደጅ ጸንቶ ነበር። የነገሩትን የማይረሳ እግዚአብሔር መልአኩን ላከለት፤ የሰማዩን ምሥጢርም ዐወቀ። ይህ መልአክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ በመካከላቸው ሁኖ መንገድ ይመራቸው እንደነበር በድርሳነ ዑራኤል ተገልጿል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ ደሙን በፈቃዱ ሲያፈስም በጽዋዕ የተቀበለው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል መሆኑን በዕለተ ዓርብ በሚነበበው ግብረ ሕማማት ተጽፏል። በሊቀ መላእክትነት የተሾመበት በዓል ጥር 22፣ ከጌታችን የፈሰሰውን ደም በጽዋዕ የተቀበለበት መጋቢት 27 ቀን ይከበራል። ገዳማውያን ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሩታል፣ እርሱም ይራዳቸዋል፤ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444

6 months ago
የጸሎተ ሐሙስ በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ተከበረ
#ethiopia | የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የሕጽበተ እግርና የጸሎተ ሐሙስ በዓልን በፒያሳ በሚገኘው የልደታ ማርያም ካቴድራል በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች አክብራ ውላለች።
በዚህ ታላቅ መንፈሳዊ መርሐ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ተገኝተው የሕጽበተ እግር ሥርዓቱን መርተዋል።
ብፁዕነታቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀ መዛሙርቱ እግር በማጠብ ያሳየውን የትሕትና እና የአገልግሎት ምሳሌነት በማሰብ የምእመናንን እግር አጥበዋል።
በዕለቱ በተከናወነው የቅዳሴ ጸሎትና ልዩ ልዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ላይ በርካታ ምእመናን የተገኙ ሲሆን፣ የክርስቶስን ሕማማትና የመጨረሻውን የእራት ግብዣ የሚያዘክሩ ጸሎቶችም በጋራ ቀርበዋል።
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ ለምእመናኑ ባስተላለፉት መልእክት የጸሎተ ሐሙስን መንፈሳዊ ትርጉምና የእርስ በእርስ መዋደድን አስፈላጊነት አጽንኦት ሰጥተው አብራርተዋል።
ጌትነት ተመስገን
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
📷 EBC

ጸሎተ ሐሙስ
የትሕትናና የአዲስ ኪዳን ብስራት
ዛሬ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ "ጸሎተ ሐሙስ" ወይም "ሕጽበተ እግር" ተብሎ የሚታሰበው ታላቅ ዕለት ነው። ይህ ቀን ስድስት የተለያዩ መጠሪያዎችና ጥልቅ ትርጉሞች አሉት፦
ጸሎተ ሐሙስ
ጌታ በጌቴሴማኒ የአትክልት ስፍራ የጸለየበት በመሆኑ።
ሕጽበተ እግር
የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ትሕትናን ያስተማረበት።
ምሴተ ሐሙስ
የጌታ እራት ወይም ቅዱስ ቁርባን የተመሰረተበት።
የነጻነት ሐሙስ
የሰው ልጅ ከኃጢአት ባርነት ነጻ መውጣቱ የታወጀበት።
የአዲስ ኪዳን ሐሙስ
የጥላው (የብሉይ ኪዳን) አልፎ የእውነቱ (የአዲስ ኪዳን) መሥዋዕት የተጀመረበት።
የአይሁድ ፋሲካ
አይሁድ የመሻገሪያ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ዕለት።
"እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፣ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል።" (ዮሐ 13:14)
#getu #holythursday #maundythursday #humility #ethiopianorthodox #passionweek #lastsupper #newcovenant #ሕማማት #ጸሎተሐሙስ #ሕጽበተእግር #ትሕትና #ጌጡተመስገን #getutemesgen

ሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ - የጥያቄና የትምህርት ቀን 🙏
ጌታችን አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ በዕለተ ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠው ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና ዕለተ ማክሰኞ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ አንድም በዚህ ዕለት ጌታችን በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ ዕለቱ “የትምህርት ቀን” ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር፣ ሲጠይቅ መሰንበት እንደሚገባው ይህ መጽሐፋዊ ሥርዓት ይነግረናል፡፡ በዕለተ ሰኞ የነጋዴዎችን ንብረት መገልበጥና ማባረሩን መነሻ በማድረግ “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ?” ሲሉ ጠይቀውታል፡፡ ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራት፣ ድንቅ ድንቅ ሥራዎችና ትምህርቱ ህዝቡ እንዲከተለው ስላደረገ የካህናት አለቆች በቅናት ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ሊያጋጩት የቀየሱት ስልት ነው፡፡
ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነውና ጌታችን በራሴ ሥልጣን ነው ቢላቸው ጸረ መንግሥት ነው በማለት ለሮማ መንግሥት ያሳጡት ነበር፡፡ ጌታችን ግን ለጥያቄያቸው ቀጥተኛ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ “የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው? ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር?” በማለት በጥያቄ መልሶላቸዋል፡፡ እነርሱም “ከሰማይ ነው” ቢሉት “ለምን አላመናችሁበትም?” እንዳይላቸው ሰጉ፡፡ “ከሰው ነው” ቢሉት ደግሞ ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ መምህር ይፈሩት፣ እንደ አባት ያከብሩት ነበርና እንዳይጣሏቸው ፈሩ፤ እናም “ከወዴት እንደሆነ አናውቅም” የሚል የተንኮል ምላሽ ሰጡት፡፡ እርሱም “እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም” አላቸው፡፡ በልቡናቸው የሚያደርጋቸውን ተግባራት ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንደሚያደርግ ቢያውቁም በክፋትና በጥርጥሬ ስለተሞሉ ነበር የጠየቁት፡፡
በማቴዎስ ወንጌል 21÷28፣ 25÷46፣ በማርቆስ ወንጌል 12÷12፣ 13÷37፤ በሉቃስ ወንጌል 20÷9፣ 21÷38፣ የሚገኙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ስለማክሰኞ ዕለት የሚነገሩ ትምህርቶችን ይዘዋል፡፡ ዳግመኛም በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ የትምህርት ቀን ይባላል፡፡ ይኸውም ከሃይማኖት የራቁትን፣ ከፍቅረ እግዚአብሔር የተለዩትን አስተምሮ ማቅረብ፣ መክሮ መመለስ እንደሚገባን ሲገልጽልን ነው፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ፣ ከዋዛ ፈዛዛ ተጠብቆ የጌታችንን ውለታ፣ ሕማሙን፣ ግረፋትና ስቅለቱን፣ ሞቱንና መከራውን እያሰበ በስግደት ይህን ሳምንት ሊያሳልፈው ይገባል፡፡ ገዳማውያን ይህን ፍቅሩን እያሰቡ በጾምና በጸሎት ይኖራሉ፤ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957

Sponsored by
Surafel
6 months ago
በበለስ አንጻር ኃጢአትን ረገማት🙏
በትንቢተ ኢሳይያስ 53÷4-12 “ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፡፡ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጠረ፡፡ እርሱ ግን ግፍን አላደረገም፤ ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም፡፡” ተብሎ እንደ ተጻፈ፡፡ ሰሙነ ሕማማት፣ ሕማምና ሞት የማይገባው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞት ለራሱ በማድረግ ለእኛ ቤዛ መሆኑ የሚነገርበት ነው፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለው የእኛን ሕማም መኾኑን በመዘከር፤ ከማንኛውም የሥጋ ሥራ በመታቀብ ዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር ሰሙነ ሕማማትን ልናከብር ይገባል፡፡ የሰሙነ ሕማማት ሰኞ የበለስ ቀን ይባላል፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆሣዕና ማግሥት ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አከናውኗል፤ አንደኛ ከቅጠል በስተቀር ፍሬ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፡፡ ሁለተኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡
ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ “በማግሥቱ ተራበ” ይላል፡፡ ነገር ግን በኢሳ. 46÷25 “እግዚአብሔር ለዘለዓለም አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ጌታችንም በመዋዕለ ስጋዌው ሲያስተምር “የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፤ ሥራውንም እንፈጽም ዘንድ ነው፤” ሲል ተናግሯል፡፡ ታዲያ ጌታችን ለምን ተራበ? ሰማያውያን መላእክት እንዳይራቡ አድርጎ የፈጠረ፤ እስራኤልን ገበሬ በማያርስበት፣ ዘር በሌለበት፣ ዝናብ በማይጥልበት ምድረ በዳ የመገበ፤ በአምስት አንጀራና በሁለት ዓሣ ከአምስት ሺሕ የሚበልጡ ሰዎችን የመገበ ጌታ “ተራበ” ተብሎ ሲነገር እጅግ ይደንቃል፡፡ በእርግጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው በመሆኑ አልተራበም አንልም፡፡ የጌታችን ረኃብ የድህነት፣ የማጣት አይደለም፡፡ የክርስቶስ ረኃቡ የበለስ ፍሬ ሳይሆን የሃይማኖትና የመልካም ሥነ ምግባርን ፍሬ ሽቶ ማጣቱን ለማጠየቅ የተነገረ ነው።
በለስስ ቤተ እስራኤል ናቸው እንዲል፡፡ ጌታችን የፈለገውን ጽድቅ ከእነርሱ ባለማግኘቱ ጉባኤ አይሁድን ረግሟል፡፡ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “በበለስ አንጻር ኃጢአትን ረገማት” ብሏል፡፡ እስራኤልም በአንድ ወገን የተጠበቀባቸውን ፍሬ ባለማፍራታቸው ተረግመዋል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “አሕዛብ በእግዚአብሔር ቸርነት አበባ ሰበሰቡ፤ በአይሁድ ዘንድ ግን እሾኹ ተረፈ፡፡ ይኸውም የሃይማኖት ጉድለት ነው፤” በማለት እስራኤል ከፍቅር ይልቅ እርግማን እንዳገኛቸው፤ አሕዛብ ደግሞ የቃሉን ትምህርት ሰምተው የእጁን ተአምራት አይተው ያመኑበትን የእግዚአብሔር የጸጋ ልጁ ለመኾን መብቃታቸውን ይመሰክራል፡፡ እሾኽ የእርግማን፤ አበባ የእግዚአብሔር ጸጋ ልጅነት ምሳሌ ነው፡፡ ዛሬ ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይሆን? ፍሬ ወይስ ቅጠል? በቅዱሳን ጸሎት በገዳማት በረከት እንታጠር፡፡ ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና።
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
በትንቢተ ኢሳይያስ 53÷4-12 “ደዌያችንን ተቀበለ፤ ሕማማችንንም ተሸከመ፡፡ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጠረ፡፡ እርሱ ግን ግፍን አላደረገም፤ ተንኮልም በአፉ አልተገኘበትም፡፡” ተብሎ እንደ ተጻፈ፡፡ ሰሙነ ሕማማት፣ ሕማምና ሞት የማይገባው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእኛን ሕማምና ሞት ለራሱ በማድረግ ለእኛ ቤዛ መሆኑ የሚነገርበት ነው፡፡ ምእመናን ክርስቶስ የተቀበለው የእኛን ሕማም መኾኑን በመዘከር፤ ከማንኛውም የሥጋ ሥራ በመታቀብ ዋዛ ፈዛዛ ባለመነጋገር ሰሙነ ሕማማትን ልናከብር ይገባል፡፡ የሰሙነ ሕማማት ሰኞ የበለስ ቀን ይባላል፡፡ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሆሣዕና ማግሥት ከቢታንያ ወደ ኢየሩሳሌም ሲገባ ሁለት ነገሮችን አከናውኗል፤ አንደኛ ከቅጠል በስተቀር ፍሬ ያልተገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፡፡ ሁለተኛ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡
ቅዱስ ማቴዎስ በወንጌሉ “በማግሥቱ ተራበ” ይላል፡፡ ነገር ግን በኢሳ. 46÷25 “እግዚአብሔር ለዘለዓለም አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ጌታችንም በመዋዕለ ስጋዌው ሲያስተምር “የእኔስ መብል የላከኝን የአባቴን ፈቃድ አደርግ ዘንድ፤ ሥራውንም እንፈጽም ዘንድ ነው፤” ሲል ተናግሯል፡፡ ታዲያ ጌታችን ለምን ተራበ? ሰማያውያን መላእክት እንዳይራቡ አድርጎ የፈጠረ፤ እስራኤልን ገበሬ በማያርስበት፣ ዘር በሌለበት፣ ዝናብ በማይጥልበት ምድረ በዳ የመገበ፤ በአምስት አንጀራና በሁለት ዓሣ ከአምስት ሺሕ የሚበልጡ ሰዎችን የመገበ ጌታ “ተራበ” ተብሎ ሲነገር እጅግ ይደንቃል፡፡ በእርግጥ ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው በመሆኑ አልተራበም አንልም፡፡ የጌታችን ረኃብ የድህነት፣ የማጣት አይደለም፡፡ የክርስቶስ ረኃቡ የበለስ ፍሬ ሳይሆን የሃይማኖትና የመልካም ሥነ ምግባርን ፍሬ ሽቶ ማጣቱን ለማጠየቅ የተነገረ ነው።
በለስስ ቤተ እስራኤል ናቸው እንዲል፡፡ ጌታችን የፈለገውን ጽድቅ ከእነርሱ ባለማግኘቱ ጉባኤ አይሁድን ረግሟል፡፡ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “በበለስ አንጻር ኃጢአትን ረገማት” ብሏል፡፡ እስራኤልም በአንድ ወገን የተጠበቀባቸውን ፍሬ ባለማፍራታቸው ተረግመዋል፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ “አሕዛብ በእግዚአብሔር ቸርነት አበባ ሰበሰቡ፤ በአይሁድ ዘንድ ግን እሾኹ ተረፈ፡፡ ይኸውም የሃይማኖት ጉድለት ነው፤” በማለት እስራኤል ከፍቅር ይልቅ እርግማን እንዳገኛቸው፤ አሕዛብ ደግሞ የቃሉን ትምህርት ሰምተው የእጁን ተአምራት አይተው ያመኑበትን የእግዚአብሔር የጸጋ ልጁ ለመኾን መብቃታቸውን ይመሰክራል፡፡ እሾኽ የእርግማን፤ አበባ የእግዚአብሔር ጸጋ ልጅነት ምሳሌ ነው፡፡ ዛሬ ጌታችን ወደ መቅደስ ሕይወታችን ቢመጣ ምን ያገኝ ይሆን? ፍሬ ወይስ ቅጠል? በቅዱሳን ጸሎት በገዳማት በረከት እንታጠር፡፡ ገዳማውያንን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና።
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957
6 months ago
ለተፈቀደላቸው ሁሉ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ይገልጣል🙏
ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33፥7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል” በማለት እንደተናገረ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩት ሰዎች በጨነቃቸው ጊዜ በመካከላቸው እየተገኘ ያጽናናቸዋል። ምሥጢር ይገልጥላቸዋል፤ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቃቸዋል። ዑራኤል ማለት “ብርሃነ እግዚአብሔር” ማለት ነው። ዑራኤል በብርሃናት ላይ ሁሉ የተሾመ ነው፡፡ በመጽሐፈ ሔኖክ 6፥2 “ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ዑራኤል በመብረቅና በነጎድጓድ የተሾመ ነው” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ከሊቃነ መላእክት አንዱ መሆኑንና ፍርሃት ረዓድ ላለባቸው ረዳታቸው እንደሆነ የመላእክትን ነገር የተናገረ ሄኖክ ነግሮናል፡፡ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ገላጭ ነው።
ምሥጢር ማናገር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆንም የተሠወረውን መግለጥ፣ በአዲስ ቋንቋ ማናገር ለመላእክት የተሰጠ ጸጋቸው መሆኑም ግልጽ ነው። የተወደደ ሥራ ለሚሠሩና እንዲያውቁ ለተፈቀደላቸው ሁሉ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ይገልጣል፡፡ በመጽሐፈ ዕዝራ ሱትኤል 13፥38 እንደተጻፈው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ዕዝራ ሱቱዔልን “አፍህን ክፈት፤ እኔም የማጠጣህን ጠጣ” ብሎ ሐምሌ 22 አእምሮና ማስተዋልን ገልጦለታል። ለሄኖክም ምሥጢረ ሰማይንና ዕውቀትን የገለጠለት እርሱ ነው፡፡ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ልቡናውን ያበራለት ይህ መልአክ እንደሆነ ገዳሙ ባሳተመው ገድሉ ላይ ተጽፏል። በዚህ አገልግሎቱም ሊቃውንቱ “ከሣቴ ምሥጢር” ወይም “ምስጢርን የሚገልጽ” ይሉታል። አፋቸውን ከፍተው የምስጋና ቃል የሚናገሩ ሁሉ ክብርና ጥበቃን ከመላእክት ይቀበላሉ፡፡
ዕዝራ ለረጅም ወራት እግዚአብሔርን ደጅ ጸንቶ ነበር። የነገሩትን የማይረሳ እግዚአብሔር መልአኩን ላከለት፤ የሰማዩን ምሥጢርም ዐወቀ። ይህ መልአክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ በመካከላቸው ሁኖ መንገድ ይመራቸው እንደነበር በድርሳነ ዑራኤል ተገልጿል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ ደሙን በፈቃዱ ሲያፈስም በጽዋዕ የተቀበለው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል መሆኑን በዕለተ ዓርብ በሚነበበው ግብረ ሕማማት ተጽፏል። በሊቀ መላእክትነት የተሾመበት በዓል ጥር 22፣ ከጌታችን የፈሰሰውን ደም በጽዋዕ የተቀበለበት መጋቢት 27 ቀን ይከበራል። ገዳማውያን ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሩታል፣ እርሱም ይራዳቸዋል፤ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
ነቢዩ ቅዱስ ዳዊት በመዝሙር 33፥7 “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሠፍራል” በማለት እንደተናገረ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ዑራኤል እግዚአብሔርን የሚፈሩና የሚያከብሩት ሰዎች በጨነቃቸው ጊዜ በመካከላቸው እየተገኘ ያጽናናቸዋል። ምሥጢር ይገልጥላቸዋል፤ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይጠብቃቸዋል። ዑራኤል ማለት “ብርሃነ እግዚአብሔር” ማለት ነው። ዑራኤል በብርሃናት ላይ ሁሉ የተሾመ ነው፡፡ በመጽሐፈ ሔኖክ 6፥2 “ከቅዱሳን መላእክት አንዱ ዑራኤል በመብረቅና በነጎድጓድ የተሾመ ነው” ተብሎ ተጽፏል፡፡ ከሊቃነ መላእክት አንዱ መሆኑንና ፍርሃት ረዓድ ላለባቸው ረዳታቸው እንደሆነ የመላእክትን ነገር የተናገረ ሄኖክ ነግሮናል፡፡ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ገላጭ ነው።
ምሥጢር ማናገር የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ቢሆንም የተሠወረውን መግለጥ፣ በአዲስ ቋንቋ ማናገር ለመላእክት የተሰጠ ጸጋቸው መሆኑም ግልጽ ነው። የተወደደ ሥራ ለሚሠሩና እንዲያውቁ ለተፈቀደላቸው ሁሉ ቅዱስ ዑራኤል ምሥጢር ይገልጣል፡፡ በመጽሐፈ ዕዝራ ሱትኤል 13፥38 እንደተጻፈው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል ዕዝራ ሱቱዔልን “አፍህን ክፈት፤ እኔም የማጠጣህን ጠጣ” ብሎ ሐምሌ 22 አእምሮና ማስተዋልን ገልጦለታል። ለሄኖክም ምሥጢረ ሰማይንና ዕውቀትን የገለጠለት እርሱ ነው፡፡ ለአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ልቡናውን ያበራለት ይህ መልአክ እንደሆነ ገዳሙ ባሳተመው ገድሉ ላይ ተጽፏል። በዚህ አገልግሎቱም ሊቃውንቱ “ከሣቴ ምሥጢር” ወይም “ምስጢርን የሚገልጽ” ይሉታል። አፋቸውን ከፍተው የምስጋና ቃል የሚናገሩ ሁሉ ክብርና ጥበቃን ከመላእክት ይቀበላሉ፡፡
ዕዝራ ለረጅም ወራት እግዚአብሔርን ደጅ ጸንቶ ነበር። የነገሩትን የማይረሳ እግዚአብሔር መልአኩን ላከለት፤ የሰማዩን ምሥጢርም ዐወቀ። ይህ መልአክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ ግብጽ በተሰደደች ጊዜ በመካከላቸው ሁኖ መንገድ ይመራቸው እንደነበር በድርሳነ ዑራኤል ተገልጿል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ አደባባይ ደሙን በፈቃዱ ሲያፈስም በጽዋዕ የተቀበለው መልአኩ ቅዱስ ዑራኤል መሆኑን በዕለተ ዓርብ በሚነበበው ግብረ ሕማማት ተጽፏል። በሊቀ መላእክትነት የተሾመበት በዓል ጥር 22፣ ከጌታችን የፈሰሰውን ደም በጽዋዕ የተቀበለበት መጋቢት 27 ቀን ይከበራል። ገዳማውያን ዘወትር በጸሎታቸው ይጠሩታል፣ እርሱም ይራዳቸዋል፤ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና ከበረከታቸው እንካፈል፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
8 months ago
🩸 የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መንፈሳዊ ጉዞ፡ ዐቢይ ጾም ከሰማያት መውረድ እስከ ቀራንዮ ደም
👉ከአንድ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኝ ለፊደል ፖስት የተላከ
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ፣ ዐቢይ ጾም ዝም ብሎ የምግብ ለውጥ የሚደረግበት ወቅት አይደለም። ይህ ጾም የሰው ልጅ በኃጢአት ምክንያት ከፈጣሪው ተለይቶ በነበረበት የጨለማ ዘመን፣ አምላክ የሰውን ልጅ ፍለጋ ያደረገውን የፍቅር ጉዞ የምናስብበት የታሪክ መዝገብ ነው።
ከገነት የተሰደደውን አዳም እንባ ለማበስ፣ የአለማት ጌታ ዙፋኑን ትቶ በምድር የተንከራተተበት፣ የተራበበትና በመጨረሻም ደሙን ያፈሰሰበት ምስጢር በዚህ ጾም ውስጥ ተቀብሯል።
፩. ዘወረደ፡ ፍቅር አምላክን ከዙፋኑ አወረደው
ጉዞው የሚጀምረው "ዘወረደ" በሚለው ሳምንት ነው። ትርጉሙ "የወረደ" ማለት ነው። የሰማይና የምድር ጌታ፣ መላእክት በፊቱ የሚንቀጠቀጡለት አምላክ፣ አዳምን ፍለጋ ወደ ምድር ወረደ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ ይህንን ሲገልጽ፣ አምላክ ክብሩን እንደ መጋረጃ ገፎ፣ ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሶ መምጣቱን ይነግረናል። የነፍሳችንን ስደት ሊያቆም እርሱ ስደተኛ ሆነ። አምላክ ለእኔ ሲል ተራ ሰው ሆኖ በበረት ተኛ!
፪. ቅድስት፡ የነፍስ መታጠቢያ
ሁለተኛው ሳምንት "ቅድስት" ነው። ጌታችን በገዳመ ቆሮንቶስ 40 ቀንና 40 ሌሊት የጾመውን ጾም እናስባለን። ዲያብሎስ በረቂቅ ተንኮሉ ቀረበው። አዳምን በምግብ ጥቂት ፍሬ ጥሎት ነበር፤ ጌታችን ግን በታላቅ ጾም ድል አደረገው። ጌታችን ስለ እኛ ተራበ፤ ስለ እኛ ተጠማ። እኛ ግን ዛሬም በሥጋ ፍላጎት ተሸንፈን ለፈጣሪያችን ጀርባችንን ሰጥተናል። ይህ ሳምንት "ጌታ ሆይ እንደ ቸርነትህ ማረኝ" ብለን የምንጮኽበት የቅድስና ወቅት ነው።
፫. ምኵራብ፡ የፈረሰውን መቅደስ አዳሽ
በሦስተኛው ሳምንት ጌታችን ወደ ምኵራብ (መቅደስ) ገባ። ቤቱ የንግድ ቦታ ሆኖ አገኘው። እየገፈተረ አስወጣቸው "ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል" ብሎ አስወጣቸው። ዛሬም ጌታችን ወደ እኛ ልብ መቅደስ ሲመጣ፣ ልባችን በቂም፣ በበቀልና በስግብግብነት ተሞልቶ ያገኘዋል። በመገፍተር ሳይሆን በፍቅሩ ሊገሥጸን ይሻል።
፬. መጻጒዕ፡ የብቸኞች መጠጊያ
ለ38 ዓመታት በአልጋ ላይ ተኝቶ "የሚረዳኝ ሰው የለኝም" እያለ ሲያለቅስ የነበረውን መጻጒዕን እናስባለን። ዓለም ሁሉ ስትረሳው፣ አምላክ ግን አልረሳውም። ዛሬም በሕመም የምትማቅቁ፣ በብቸኝነት የምትቆስሉ ነፍሳት ሆይ—አምላካችሁ አልረሳችሁም። "አልጋህን ተሸክመህ ሂድ" የሚለው ቃል ዛሬም ለደከመች ነፍሳችን ተስፋ ነው።
፭. ደብረ ዘይት፡ የተስፋ ብርሃን
የጾሙ እኩሌታ ላይ ስንደርስ ስለ ዳግም ምጽአቱ እናስባለን። ጌታችን በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሆኖ ዓለም እንደምታልፍና እርሱ በክብር እንደሚመጣ ነገረን። ይህ ሳምንት የአዳምን ልጆች ናፍቆት ይጭራል። አማኞች በመልካም ሥራ እንዲጸኑና ልባቸውን እንዲያዘጋጁ የሚያሳስብ የንቃት ወቅት ነው።
፮. ገብር ኄር፦ ታማኝ አገልጋይ በመሆን በመክሊት (በጸጋ) ስለ ማትረፍ የሚማርበት።
፯. ኒቆዲሞስ፦ ስለ ዳግም ልደት (ጥምቀት) እና ስለ እውነት ፈላጊነት የሚነገርበት።
፰. ሆሣዕና፦ ጌታችን በታላቅ ምስጋና ወደ ኢየሩሳሌም የገባበትና የሕማማት መጀመሪያ።
🕯️ ሰሙነ ሕማማት፡ የአምላክ ስቃይ ጥልቀት
ከሆሣዕና ማግስት ጀምሮ የምንገባበት ሳምንት ሰሙነ ሕማማት ይባላል። እዚህ ጋር ነው እንባ የሚፈሰው። እዚህ ጋር ነው የአምላክ ፍቅር ጥግ የሚታየው። ይህ ሳምንት "ሳምንተ ተገሥጾ" ይባላል።
ሰኞ (አንጽሖተ መቅደስ)
ጌታችን ከቢታንያ ሲመጣ ተራበ። ፍሬ የሌላትን በለስ ረገማት። በለስ የአዳም ምሳሌ ናት—በቅጠል (በተስፋ) የተሸፈነች ግን ፍሬ (ምግባር) የሌላት። "ከዛሬ ጀምሮ ለዘላለም ፍሬ አይገኝብሽ" ሲላት፣ እኛም በሕይወታችን ፍሬ እንዳይጠፋብን እያለቀስን እንድንጸልይ ያስተምረናል። በዚያው ዕለት በመቅደስ ይሸጡ የነበሩትን ገልብጧል።
ማክሰኞ (የጥያቄ ቀን)
ጌታችን በመቅደስ ሲያስተምር የአይሁድ ካህናትና ጻፎች መጡ። "እነዚህን በምን ሥልጣን ታደርጋለህ?" ብለው ጠየቁት። ሊያጠምዱት ፈለጉ። ጌታችን ግን በጥበቡ መለሰላቸው። ስለ ዓለም ፍጻሜም በሰፊው አስተማረ። ይህ ቀን "የጥያቄ ቀን" ይባላል፤ እኛም በሕሊናችን ብዙ ጥያቄዎችን ይዘን ወደ ጌታ የምንቀርብበት ቀን ነው።
ረቡዕ (የምክር ቀን / ምክረ አይሁድ)
ይህ ቀን እጅግ የሚያሳዝን ነው። ይሁዳ ጌታውን ለመሸጥ ከአይሁድ ጋር የተማከረበት ቀን ነው። "ምን ትሰጡኛላችሁ? እኔ አሳልፌ እሰጣችኋለሁ" አለ። ለሦስት ዓመታት አብሮት የበላ፣ ተአምራቱን ያየ ደቀ መዝሙር፣ ጌታውን በሰላሳ ብር ሸጠው። ጌታችን ግን ይህን ሁሉ እያወቀ ይሁዳን ይወደው ነበር። "ይሁዳ ሆይ በመሳም አሳልፈህ ትሰጠኛለህን?" የሚለው ድምፅ ዛሬም የከዳነውን ጌታ ስናስብ ልብ ይሰብራል።
ጸሎተ ሐሙስ (የምስጢር ሐሙስ)
ጌታችን የደቀ መዛሙርቱን እግር አጠበ። የዓለማት ንጉሥ ሆኖ ሳለ፣ የባሪያውን እግር ሲያጥብ እስቲ በዓይነ ሕሊናችሁ ተመልከቱት። ከዚያም "ይህ ሥጋዬ ነው... ይህ ደሜ ነው" ብሎ ምስጢረ ቁርባንን ሰጠን። በዚያች ሌሊት ወደ ጌቴሴማኒ ሄዶ ጸለየ። ጭንቀቱ በረታ፤ "ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ አዘነች" አለ። ላቡ እንደ ደም ጠብታ ወደ ምድር ፈሰሰ። ጌታችን ስለ እኛ ፍዳ ተጨነቀ።
🩸 ስቅለተ ዓርብ፡ የቀራንዮው ታላቅ ስቃይ
ይህ ቀን በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ አስለቃሹ ቀን ነው። ፈጣሪ በፍጥረቱ እጅ የተገረፈበት ቀን!
ፍርዱ፦ ጌታን በፍርድ አደባባይ አቆሙት። ፊቱን ተተፋበት—ያ መላእክት ሊያዩት የሚመኙትን ቅዱስ ፊት! በጅራፍ ተገረፈ። ጅራፉ አጥንት ድረስ የሚሰነጥቅ ነበር። ሰውነቱ እንደ ታረሰ መሬት ተተለተለ። ደሙ እንደ ጎርፍ ፈሰሰ።
የእሾህ አክሊል፦ የእሾህ አክሊል ሰርተው በራሱ ላይ ደፉበት። በዘንግ መቱት፤ እሾሁ ወደ አእምሮው ሰረጸ።
መንገደ ቀራንዮ፦ ያንን ከባድ መስቀል ተሸክሞ ወደ ቀራንዮ እንዲወጣ ተገደደ። ደክሞት ሲወድቅ በጅራፍ ይገረፋል፤ ሲነሣ ይገፋታል። በመንገድ ላይ እናቱ ድንግል ማርያም አየችው። ልጇ ሲሰቃይ፣ ልብሷ በደሙ ሲጨማለቅ ስታይ "ልጄ ሆይ ምን አደረጉህ?" እያለች አለቀሰች። ያ የእናትና የልጅ መገናኘት ዓለትን የሚያቀልጥ ነበር።
ስቅለቱ፦ በቀራንዮ መስቀል ላይ ዘረጉት። እጆቹንና እግሮቹን በትላልቅ ሚስማሮች ወጉት። መዶሻው ሲመታ ድምፁ በሰማይና በምድር ተሰማ። በመስቀል ላይ ሆኖ ሳለ "ተጠማሁ" አለ። የውኃ ምንጭ የሆነው አምላክ፣ ስለ እኛ ሲል ተጠማ። "አባት ሆይ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ብሎ ለገዳዮቹ ጸለየ።
በመጨረሻም "ተፈጸመ" ብሎ ነፍሱን ሰጠ። ያኔ ፀሐይ ጨለመች፣ ጨረቃ ደም መሰለች፣ ምድር በታላቅ ድንጋጤ ተናወጠች። የቤተ መቅደስ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ተቀደደ። ፈጣሪ ለፍጥረቱ ሲል ሞተ!
🎐 ቀዳም ስዑር እና ትንሣኤ
ቅዳሜ ጌታ በመቃብር ዋለ። መቃብሩ ታተመ። ነገር ግን ሞት ሊይዘው አልቻለም። እሁድ መንፈቅ ሌሊት፣ መቃብሩን ከፍቶ ተነሣ! ሞትን ድል አደረገው! አዳምን ከሲኦል አውጥቶ ወደ ቀደመ ክብሩ መለሰው። የዐቢይ ጾም ለቅሶ በደስታ፣ በረከቱ በትንሣኤ ብርሃን ተተካ።
ማጠቃለያ፦
ይህ የ55 ቀናት ጉዞ፣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማኞች የአምላክን ፍቅር የሚረዱበት ነው። ይህ ታሪክ ዛሬም በልባችን ውስጥ ሊነገር ይገባል።
አምላካችን እግዚአብሔር ጾሙን የበረከትና የፈውስ ያድርግልን። ትንሣኤውን ለማየት ያብቃን።

11 months ago
ገድላቸው የተከበረ አባት፣ በትሩፋት የተጋ፣ የመልካም ነገሮች ኹሉ አባት፣ ይላቸዋል፡፡
የተውለዱት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ በሮም ሉፊ በሚባል አውራጃ የካቲት 16 ነው፡፡ በሃገራችን በኢትዮጵያ በስማቸው የታነጹ 3ት ታላላቅና ጥንታዊ ገዳማት ያሏቸው፡፡ በሊቀ ሰማዕታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ዘመን የነበሩና ሰማዕትነት የተቀበሉ፣ ከማዕድ በኋላ ስብሐት ተብሎ ስማቸው ተጠርቶ መጉረስ ሙታንን እንደሚያስምር ቃል ኪዳን የተሰጣቸው አባት ናቸው አባ ቡላ ወይም አቡነ አቢብ፡፡ ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ሲኸን፤ አቢብ ደግሞ የብዙዎች አባት፣ የመልካም ሥራ ኹሉ ባለቤት ማለት ነው፡፡
ወላጆቻቸው እጅግ ጽኑዕ ክርስቲያኖች ሲሆኑ ልጅ አልነበራቸውም፡፡ በዘመነ ሰማዕታት ክርስቲያኖችን ሲያሳድድ ከነበረው ከመክስምያኖስ ሸሽተው በበረሃ ሳሉ በመልአክ ብሥራት ተወልደዋል፡፡
ሲጸነሱም ወላጆቻቸው የእግዚአብሔር መልአክ በሮማይስጥ ቋንቋ “ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ በጽዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ያከበረው” የሚል የብርሃን ጽሑፍ በዛፍ ላይ ሲጽፍ ዐይተዋል:: በዘመነ ሰማዕታት በመወለዱ ለአንድ ዓመት ሳይጠመቅ ቆይተው እመቤታችን ለሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ወደ በረሃ ወርዶ እንዲያጠምቀው አዘዝችው፤ ሊያጠምቀው ሲል ሕፃኑ ተነስቶ እጆቹንም ዘርግቶ "አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡ የሕፃኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው፡፡ እነርሱም በዛፉ ላይ የተገለጸውን ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ::
ወላጆቹ ገና በ10 ዓመቱ ተከታትለው ስላረፉ ጎረቤቶች አሳድገውታል፡፡ ሃገረ ገዢው ለጣዖት ስገዱ ብሎ አዋጅ ባስነገረ ጊዜ በሕፃን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ፡፡ ሃገረ ገዢውም ተበሳጭቶ ስፍር ቁጥር የሌለው መከራና ስቃይ አበዛበት፡፡ ይሁንና ኀይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና ከሞቶ አስነሳው፡፡
ቅዱስ ቡላ ወደ ሌላ ከሃዲ መኰንን ዘንድ ሄዶ ስለአምልኮ ጣዖቱ ገሠጸው፡፡ ያም ከሃዲ መኰንን ብዙ ካሠቃየው በኋላ ሚያዝያ 18 ቀን ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ለ2ኛ ጊዜ ከሰማይ ወርዶ ቅዱስ ቡላን ከሞት አስነሣው፡፡ ወደ አንድ ገዳምም ወስዶ በምንኩስና እንዲኖር መታዘዙን ነገረው፡፡ አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዘወትር ዐርብ የጌታችን የመድኀኔ ዓለምን ሕማማት እያሰበ ራሱን ስጋውን በተለያየ መከራ እየጎዳ ኖሯል፡፡
ምንም ነገር ሳይቀምስ፤ መዝሙረ ዳዊትን እየጸለየ ለ42 ዓመታት ጹሟል፡፡ በአንዲት ቀንም ከረጅም ዛፍ ላይ በተወረወረ ጊዜ ሰይጣን በረታበትና ገደለው፡፡ ነገር ግን ጌታችን ተገልጦለት ከሞት አስነሣውና “ከእንግዲህ ስምህ ቡላ አይሁን አቢብ ተባል እንጂ የብዙዎች አባት ትሆናለህ” አለው፡፡ አቡነ አቢብ ታላቁ አባ ዕብሎይን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: የካቲት 22 ሲያርፍ ገዳሙ በመላእክት ተሞላ:: ሰው ቢረሳ ቢረሳ ምግቡን አይረሳምና “ስለ አቡነ አቢብ” ስለ አባ ቡላ ብሎ በሚመገብ ጊዜ ያሰበውን ማርልኝ ብለው የለመኑትን ልመና አምላካችን ተቀብሎላቸው ዛሬም በዚህ በቃል ኪዳናቸው የሚያስምሩ ሆነዋል፡፡ ገዳማውያን በተጋድሏቸው ድንቅ ቃል ኪዳን ይቀበላሉ፡፡ ገዳማቸውን ስንደግፍ በዓታቸውን ስናጸና ከበረከታቸው እንሳተፋለን፡፡

1 year ago
በሊቀ ሰማዕታት በቅዱስ ጊዮርጊስ ዘመን የነበሩና ሰማዕትነት የተቀበሉ፣ ከማዕድ በኋላ ስብሐት ተብሎ ስማቸው ተጠርቶ መጉረስ ሙታንን እንደሚያስምር ቃል ኪዳን የተሰጣቸው አባት ናቸው አባ ቡላ ወይም አቡነ አቢብ፡፡
በሃገራችን በኢትዮጵያ በስማቸው የታነጹ 3ት ታላላቅና ጥንታዊ ገዳማት አሏቸው፡፡ ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ ማለት ሲኸን፤ አቢብ ደግሞ የብዙዎች አባት፣ የመልካም ሥራ ኹሉ ባለቤት ማለት ነው፡፡ ገድላቸው የተከበረ አባት፣ በትሩፋት የተጋ፣ የመልካም ነገሮች ኹሉ አባት፣ ይላቸዋል፡፡ የተውለዱት በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ በሮም ሉፊ በሚባል አውራጃ የካቲት 16 ነው፡፡ ወላጆቻቸው እጅግ ጽኑዕ ክርስቲያኖች ሲሆኑ ልጅ አልነበራቸውም፡፡ በዘመነ ሰማዕታት ከመክስምያኖስ ሸሽተው በበረሃ ሳሉ በመልአክ ብሥራት ተወልደዋል፡፡
ሲጸነሱም ወላጆቻቸው የእግዚአብሔር መልአክ በሮማይስጥ ቋንቋ “ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ በጽዮንም አድሮ የሚኖር የያዕቆብ ፈጣሪ ያከበረው” የሚል የብርሃን ጽሑፍ በዛፍ ላይ ሲጽፍ ዐይተዋል:: ሕጻኑ ቡላ በዘመነ ሰማዕታት በመወለዱ ለአንድ ዓመት ሳይጠመቅ ቆይቶ እመቤታችን ለሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ወደ በረሃ ወርዶ እንዲያጠምቀው አዘዝችው፤ ሊያጠምቀው ሲል ሕፃኑ ተነስቶ እጆቹንም ዘርግቶ "አሐዱ አብ ቅዱስ፣ አሐዱ ወልድ ቅዱስ፣ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው፡፡ የሕፃኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው፡፡ እነርሱም በዛፉ ላይ የተገለጸውን ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ:: ወላጆቹ ገና በ10 ዓመቱ ተከታትለው ስላረፉ ጎረቤቶች አሳድገውታል፡፡
ሃገረ ገዢው ለጣዖት ስገዱ ብሎ አዋጅ ባስነገረ ጊዜ በሕፃን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ፡፡ ሃገረ ገዢውም ተበሳጭቶ ስፍር ቁጥር የሌለው መከራና ስቃይ አበዛበት፡፡ ይሁንና ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና ከሞቶ አስነሳው፡፡ ቅዱስ ቡላ ወደ ሌላ ከሃዲ መኰንን ዘንድ ሄዶ ስለአምልኮ ጣዖቱ ገሠጸው፡፡ ያም ከሃዲ መኰንን ብዙ ካሠቃየው በኋላ ሚያዝያ 18 ቀን ራሱን በሰይፍ አስቆረጠው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም ለ2ኛ ጊዜ ከሰማይ ወርዶ ቅዱስ ቡላን ከሞት አስነሣው፡፡ ወደ አንድ ገዳምም ወስዶ በምንኩስና እንዲኖር መታዘዙን ነገረው፡፡ አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዘወትር ዐርብ የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን፣ የመድኀኔ ዓለምን ሕማማት እያሰበ ስጋውን በተለያየ መከራ እየጎዳ ኖሯል፡፡ ምንም ነገር ሳይቀምስ፤ መዝሙረ ዳዊትን እየጸለየ ለ42 ዓመታት ጹሟል፡፡
በአንዲት ቀንም ከረጅም ዛፍ ላይ ቁልቁል በተወረወረ ጊዜ ሰ ይጣን በረታበትና ገደለው፡፡ ነገር ግን ጌታችን ተገልጦለት ከሞት አስነሣውና “ከእንግዲህ ስምህ ቡላ አይሁን አቢብ ተባል እንጂ የብዙዎች አባት ትሆናለህ” አለው፡፡ አቡነ አቢብ ታላቁ አባ ዕብሎይን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: ከዚህ ዓለም ድካም ሲያርፍም ገዳሙ በመላእክት ተሞላ:: ሰው ቢረሳ ቢረሳ ምግቡን አይረሳምና “በእንተ አቡነ አቢብ” ስለ አባ ቡላ ብሎ በሚመገብ ጊዜ ያሰበውን ማርልኝ ብለው የለመኑትን ልመና አምላካችን ተቀብሎላቸው ዛሬም በዚህ በቃል ኪዳናቸው የሚያስምሩ ሆነዋል፡፡
ገዳማውያን ዓለምን ትተዋልና ቃል ኪዳናቸው ምሕረትን ያስገኛል፡፡ ገዳማቸውን እደግፍ በዓታቸውን እናጽና።

በአንዲት ቀንም ከረጅም ዛፍ ላይ ቁልቁል በተወረወረ ጊዜ ሰይጣን በረታበትና ገደለው፡፡ ነገር ግን ጌታችን ተገልጦለት ከሞት አስነሣውና “ከእንግዲህ ስምህ ቡላ አይሁን አቢብ ተባል እንጂ የብዙዎች አባት ትሆናለህ” አለው፡፡ አቡነ አቢብ ታላቁ አባ ዕብሎይን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት ይነጋገር ነበር በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: ከዚህ ዓለም ድካም ሲያርፍም ገዳሙ በመላእክት ተሞላ:: ሰው ቢረሳ ቢረሳ ምግቡን አይረሳምና “በእንተ አቡነ አቢብ” ስለ አባ ቡላ ብሎ በሚመገብ ጊዜ ያሰበውን ማርልኝ ብለው የለመኑትን ልመና አምላካችን ተቀብሎላቸው ዛሬም በዚህ በቃል ኪዳናቸው የሚያስምሩ ሆነዋል፡፡

Comments