4 days ago
የሉሲዎቹ ድንቅ ድል! ኢትዮጵያ ሩዋንዳን 1–0 አሸነፈች
#ethiopia | ለ2028 የሎስ አንጀለስ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ውድድር በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም የተጫወተው የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን — ሉሲዎቹ — ከሜዳቸው ውጪ የሩዋንዳ አቻቸውን 1–0 በማሸነፍ ጠቃሚ ድል አስመዝግበዋል።
በጠንካራ ፉክክር የታጀበው ጨዋታ ብቸኛዋ ግብ በመጀመሪያው አጋማሽ ጭማሪ ደቂቃ፣ በ45+3ኛው ደቂቃ ላይ ተቆጥራለች። ግቧንም የሩዋንዳዋ ተጫዋች ኡዛዬሴንጋ ሊድያ በራሷ መረብ ላይ በማስቆጠር ሉሲዎቹን ወደ መሪነት አሸጋግራለች።
የዛሬው ከሜዳ ውጪ የተገኘው 1–0 ድል ሉሲዎቹን ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር ለማለፍ ጥሩ ዕድል የፈጠረላቸው ሲሆን፣ የመልስ ጨዋታው በጥቅምት 3 ቀን በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል።
ሉሲዎቹ የጀመሩትን ድል በመልሱ ጨዋታ ያስጠብቁ!
#ኢትዮጵያ #ሉሲዎቹ #እግርኳስ #ኦሊምፒክማጣሪያ #ኢትዮጵያከሩዋንዳ #ethiopia #lucy #football

RESPECT ❤️
በዕውነቱ ይነዝራል እስኪ የነዘረውውው ☹️
@Bisrat_Sport_433et
@Bisrat_Sport_433et የኩሩ ህዝቦች መኖሪያ የህብሬ ብሔር ቡቃያ የሰላም ተምሳሌት አርማ የቀለሞች ህብር ኢትዮጵያ በደም አሻራሽ አትሞ ህዝቦች ለሴጡን አደራ ለሕገ መንግስታችን ክብር ታጥቀን ቆሜናል በጋራ 🎵🎵🎵🎵🎵🎵 ሉሲዎቹ ከድሉ በኋላ በስታዲየም በመገኘት ቡድናችንን ሲያበረታቱ ከነበሩት የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አባላት ጋር በጋራ ደስታቸውን አጣጥመዋል። @Bisrat_Sport_433et …

ሉሲዎቹ ወሳኝ ድል አሳክተዋል !
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር ያደረገውን የኦሎምፒክ ማጣሪያ ጨዋታ 1ለ0 አሸንፏል።
ሉሲዎቹን አሸናፊ ያደረገች ብቸኛ ግብ ኡዛዬሴንጋ ሊዲያ በራሷ መረብ ላይ አስቆጥራለች።
የሁለቱ ብሔራዊ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ጥቅምት 3/2019 ዓ.ም ድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል።
ኢትዮጵያ ጨዋታውን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈች በቀጣይ የቦትስዋና እና ታንዛኒያን አሸናፊ ትገጥማለች።
@tikvahethsport kidusyoftahe

9 days ago
ሉሲዎቹ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፉ !
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሼልስ ጋር ያደረገውን ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታ 10ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸነፈ።
በጨዋታው ዳግማዊት ሰለሞን ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች።
ቀሪዎቹን የሉሲዎቹ ግቦች እሙሽ ዳንኤል 2x ፣ ቤተልሔም መንተሎ ፣ ቱሪስት ለማ ፣ ቤተልሄም በቀለ ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ እና አሻንታ ማሪ (ራሷ ላይ) አስቆጥረዋል።
ብሔራዊ ቡድኑ ከሲሼልስ ያደረጋቸውን ሁለት የወዳጅነት ጨዋታዎች 26ለ0 ማሸነፍ ችሏል።
ሉሲዎቹ በቀጣይ የ 2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣርያ ጨዋታቸውን ከሩዋንዳ ጋር ያደርጋሉ።
@tikvahethsport kidusyoftahe Photo

Sponsored by
Surafel
12 days ago
ሉሲዎቹ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፉ !
ከፊቱ የ 2028 ኦሎምፒክ ማጣሪያ ጨዋታ ያለበት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የአቋም መለኪያ ጨዋታ አድርጓል።
ከ ሲሼልስ አቻቸው ጋር ጨዋታቸውን ያደረጉት ሉሲዎቹ 16ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፈዋል።
ለሉሲዎቹ የማሸነፊያ ግቦችን :-
- አረጋሽ ካልሳ 2x
- እሙሽ ዳንኤል 2x
- ንግስት በቀለ 2x
- ታሪኳ ዴቢሶ 2x
- ቤቴልሄም መንተሎ 2x
- ምህረት አየለ
- ቱሪስት ለማ
- ሚለን ጋይም
- ማህሌት ምትኩ
- እፀገነት ግርማ
- ዳግማዊት ሰለሞን ማስቆጠር ችለዋል።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሼልስ ጋር ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታውን የፊታችን ቅዳሜ ያደርጋል።
ሉሲዎቹ የ 2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣርያ ጨዋታቸውን ከሩዋንዳ ጋር ያደርጋሉ።

17 days ago
ሉሲዎቹ
ተጋጣሚያቸውን አውቀዋል ! የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለ ሎስ አንጀለስ ኦሎምፒክ ለማለፍ ለሚያደርገው የማጣርያ ውድድር ተጋጣሚዎቹን አውቋል። ብሔራዊ ቡድኑ በሁለተኛው ዙር የማጣርያ ጨዋታ የ ሩዋንዳ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥም ይሆናል። ሉሲዎቹ ይህንን ጨዋታ በደርሶ መልስ ውጤት ከረቱ በሶስተኛው ዙር ማጣርያ ከቦትስዋና እና ታንዛኒያ አሸናፊ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል። የሁለተኛ ዙር…
6 months ago
የሉሲዎቹ ግስጋሴ
ኢትዮጵያ ኮስታሪካን ረታ ወደ ግማሽ ፍፃሜ አለፈች
#ethiopia | በቱርክ አዘጋጅነት እየተካሄደ በሚገኘው የ"UEFA Friendship Cup" የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ድንቅ ድል አስመዝግቧል።
ሉሲዎቹ ኮስታሪካን 1 ለ 0 በመርታት በስድስት ነጥብ ወደ ግማሽ ፍፃሜው መሸጋገራቸውን አረጋግጠዋል።
የጨዋታው ድምቀቶች፦
የማሸነፊያዋ ግብ፦ ህዳአት ካሡ በ37ኛው ደቂቃ ድንቅ ግብ ከመረብ አሳርፋለች።
የፅናት ድል፦ ምትኬ ብርሃኑ በሰማንያ ሰባተኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ብትወጣም፣ ቡድኑ በቁጥር ብልጫ ሳይበገር ውጤቱን አስከብሮ ወጥቷል።
የአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ ስኬት፦ በመጀመሪያው ጨዋታ ዩራጓይን 3 ለ 0 የረታው ቡድኑ፣ ዛሬም ብቃቱን አስመስክሯል።
ቀጣይ ትልቅ ጨዋታ
ምድባቸውን በድል ያጠናቀቁት ኢትዮጵያ እና ኖርዌይ ሚያዚያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም የምድብ አንደኝነትን ለመያዝ ይፋለማሉ።
ሉሲዎቹ በዓለም መድረክ ኢትዮጵያን እያስጠሩ ነው!
#getu #lucyethiopia #uefafriendshipcup #u18womensfootball #ethiopiavscostarica #challewlemecha #footballethiopia #risingstars #womeninsports #ኢትዮጵያ #ሉሲዎቹ #እግርኳስ #ጌጡተመስገን #getutemesgen

11 months ago
የለምለም- ደም.....የማሊያ ሳይዝ - ያመጣው መዘዝ‼️
➡️ "በቦክስ አፍንጫዬን መታኝ"
➡️ "ልበሰው ብላ ማሊያውን ወረወረችብኝ፥ ተፀፅቻለሁ"
➡️ "በጊዜያዊነት አግደነዋል"
ለምለም አስታጥቄ የሀዋሳ ከተማ የሴቶች ቡድን ተጫዋች ነች፤ በቅርቡ በነበረው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሉሲዎቹ አባል ነበረች፤ የኢትዮጵያ ከ20 አመት በታች ብሄራዊ ቡድንም ተጫዋች ሆናም ሀገሯን ወክላለች፤ ወጣቷ ተከላካይ ለምለም በክለቧ የቡድን መሪ አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባት በተንቀሳቃሽ ምስል ሰኞ እለት መረጃው ተሰራጭቶ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር፤ ጉዳዩ የተከሰተው ግን ከ11 ቀናት በፊት ነው፤ ለመሆኑ ምንድነው የተፈጠረው? ተጫዋቿና ቡድን መሪው ምን አሉ? የአሰልጣኙ ምስክርነትስ? ክለቡ ምን ወሰነ? ሁሉንም አነጋግረን ዝርዝር መረጃ ይዘናል፥ እነሆ፦
🔷 ስለ ግጭቱ፦
★ መቼ፦ ከ11 ቀናት በፊት ቅዳሜ ጥቅምት 22/2018
★ ሰዓት፦ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ
★ የት፦ አዲስ አበባ ብሌን ፕላዛ
★ ተደብዳቢ፦ ለምለም አስታጥቄ
★ ደብዳቢ፦ ታረቀኝ ወንድሙ
★ መረጃው የወጣው፦ ሰኞ ህዳር 1/2018
🔷 የለምለም ቃል፦
"የማደርገው ቁምጣ ስለጠፋብኝና ክለቡ የሰጠኝ ማሊያ ስለሰፋኝ ቁምጣውን ብቻውን ከማሰራ ብዬ ሌላ ሁለት ማሊያ እንዲሰራልኝ ለክለባችን ቡድን መሪ ደውዬ ጠየኩት፤ ያኔ ብሄራዊ ቡድን ነበርኩ፤ በራሴ ወጪ ማሰራት ስለምችል እሱም እሺ አለኝ፤ ብሩንም አስገባሁለት፤ ከብሄራዊ ቡድን ተመልሼ ሁለት ቀን ልምምድ ሰርቼ ቅዳሜ ጥቅምት 22 ማታ ማሊያውን ልቀበል ወደ እሱ ክፍል ሄድኩ፤ ሰጠኝ፤ ሳየው ሳይዙ ላርጅ ነው፤ ይሄማ እንደባለፈው ላርጅ ነው፥ ሚዲየም ነው ያዘዝኩት እኮ አልኩት፤ ጥሩ ቀን አላሳለፈም መሰለኝ ስሜታዊ ሆነ፤ ተረጋግተን እንድናወራ ላስረዳው ብሞክር 'ውጪ' ብሎ አስወጣኝ፤ ክፍሌ ገብቼ ማሊያውን ስለካው ከበፊቱ የባሰ በጣም ሰፊና ረጅም ነው፤ ከዛ ከጓደኛዬ ጋር ማሊያውን ልንመልስለት ሄድን፤ አንዴ አንኳኳን፤ መልስ የለም፤ ሁለተኛ ስናንኳኳ ከፈተልን
'ታሬ ይሄ አይሆነኝም፤ ይቅርብኝ' ብዬ በሩ አጠገብ ያለ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጬ ስወጣ ማሊያውን አንስቶ ከኋላዬ ወረወረብኝ፤ ማሊያውን ላነሳ ዝቅ ስል ፀጉሬን ይዞ ከታች ወደላይ በቦክስ አፍንጫዬን መታኝ፤ ደማ፤ ፀጉሬን ይዞ አለቅም አለ፤ ጓደኛዬ ልታስለቅቀኝ ሞከረች፤ አልቻለችም፤ መጮህ ጀመረች፤ ከአጠገቡ ክፍል የነበረችው በረኛችን ጩኸቱን ሰምታ ወጣችና ታግላ ፀጉሬን አስለቅቃ አተረፈችኝ፤ ሌሎች ተጫዋቾችም መጡ፤ እሱ ክፍሉ ገባና ዘግቶ ተቀመጠ፤ ሶስቱ አምበሎች፣ ወጌሻችን እንዲሁም ዋናና ምክትትል አሰልጣኞቹ ወደ ሆስፒታል ወሰዱኝ፤ ህክምና ተደረገልኝ፤ ለክፉ አይሰጥም ብለው ማስታገሻ ሰጡኝና ተመለስኩ፤ ይህ ባይፈጠር ደስ ይለኝ ነበር፤ እኔ ከማንም ጋር ተጣልቼ አላውቅም፤ በመነጋገር መፍታት እንችል ነበር፤ ያ ቀን በሌላ ነገር ተናዶ ነበር መሰለኝ ስሜታዊ ሆኖ ያንን ጥቃት ፈፀመብኝ"
🔷 የቡድን መሪው የአቶ ታረቀኝ ወንድሙ ቃል፦
"ታምሩ ከመጀመሪያው ልንገርህ፤ እኛ ሀዋሳ ዝግጅት ላይ ነበርን፤ ለምለም ለብሄራዊ ቡድን ተመርጣ ሄዳ ነበር፤ ደውላ ማሊያ እንደጠፋባትና እንዳሰራላት ጠየቀችኝ፤ እኔም እሺ አልኳት፤ ገንዘብ ላከችልኝ፤ ኦሜጋ ጋርመንት ሁለቱንም ማሊያ በሚዲየም ሳይዝ እንዲሰሩላት አዘዝኩላት፤ ተሰራላት፤ ማሊያውን ስቀበል ግን ሳይዙን አላየሁም ነበር፤ ቦርሳ ውስጥ ከትቼ አዲስ አበባ ይዤላት ሄድኩ፤ ክስተቱ የተፈጠረ ቀን ላይ ማሊያውን ስጠኝ ብላ ደወለችልኝ፤ እኔ ባንክ ስለነበርኩ ስመለስ አልኳት፤ ማታ ላይ በማግስቱ ጨዋታ ስለነበረብን ለቅድመ ጨዋታ ተሰበሰብን፤ እኔ ከቡድን መሪነት ባለፈ የቀድሞ ግብ ጠባቂ ስለነበርኩ የቡድኑ የበረኞች አሰልጣኝ ነኝ፤ ሁለት ስራ ነው ደርቤ የምሰራው፤ ስለ በረኞቹ እየተወያየን እያለን አሁንም ማሊያውን ስትለኝ ሰጥቻት ልመለስ ብዬ ስብሰባውን ሳልጨርስ ወደ ክፍሌ ሄድኩ፤ ማሊያውን ሰጠኋት፤ ይዛ ሄደች፤ ጃኬት ደርቤ ልወጣ ስል ተመልሳ መጣችና በሩን በሀይል ደበደበች፤ ምን ተፈጠረ ብዬ ደንግጬ ስከፍት 'ምንድነው ያመጣህልኝ? እኔ ያዘዝኩት ሚዲየም ነው' አለችኝ፤ እኔ ሳይዙን አላየሁትም፥ አሁን ምን ማድረግ እችላለሁ ስላት 'እንዴት እንዴት ነው የምትናገረው' አለችኝ፤ ይዘሽ ሂጂና ከአሰልጣኝሽ ጋር ተነጋገሪ ብዬ አስወጣኋትና በር ዘጋሁ፤ በጣም ደክሞኝ ስለነበር ስብሰባውንም አልሄድም ብዬ አልጋ ላይ እያለሁ ከአምስት ደቂቃ በኋላ የዶርሟን ልጅ አስከትላ መጣች፤ በሀይል በሩን ደበደበች፤ ድምፅዋን ስለሰማሁ ዝም አልኩ፤ አሁንም አንኳኳች፤ ዝም አልኩ፤ በሶስተኛው ከፈትኩ፤ መጀመሪያ ማሊያውን እላዬ ላይ ወረወረች፤ ልበሰው አለችኝ፤ በጣም ስሜታዊ ስለሆንኩ በጥፊ መታኋት፤ ነሰራት፤ ጩኸት ተፈጠረ፤ ሰው ተሰበሰበ፤ ምክትል አሰልጣኟ ቪዲዮ መቅረፅ ጀመረች፤ ቪዲዮውን ለቦርድ አመራሮች ላከች፤ ወዲያው ከሆቴል እንድወጣ ተወሰነ፤ ወጣሁ፤ ሰኞ እለት ወደ ሀዋሳ ተመለስኩ"
🔷 የአሰልጣኝ መልካሙ ታፈረ ምስክርነት
"ቅዳሜ ጥቅምት 22 ምሽት በማግስቱ ላለብን ጨዋታ በሆቴሉ 14ኛ ፎቅ ቴራስ ላይ እየተወያየን ነበር፤ ምሽት ሁለት ሰዓት አካባቢ አንዲት ተጫዋች መጣችና ችግር ተፈጥሯል አለችን፤ ወደ ዘጠነኛ ፎቅ ስንወርድ ለምለም ከአፍንጫዋ ደም እየፈሰሰ እያለቀሰች ደረስን፤ ስንጠይቅ በማሊያ ሳይዝ ምክንያት መጋጨታቸውን ነገሩን፤ ሀላፊነት ስላለብን ለክለቡ ሀላፊዎች ሪፖርት አደረግን፤ ለምለምንም ወደ ለገሀር አጠቃላይ ሆስፒታል ወሰድናት፤ ህክምና ተደርጎላት ለሊት ሰባት ሰዓት አካባቢ ተመለስን፤ እሷንም ተጫዋቾቹንም አረጋጋን፤ በማግስቱ ከአዲስ አበባ ከተማ ጋር ተጫውተን አሸነፍን፤ ለምለም ለጨዋታው በቂ የስነ ልቦና ጥንካሬ ላይ ስላልነበረች ተጠባባቂ ወንበር ላይ ተቀምጣ አሳልፋለች፤ ክለቡም ቡድን መሪው የእሁዱን ጨዋታ እንዳይመራና ከሆቴል እንዲወጣ ወደ ሀዋሳ ሄዶ ሪፖርት እንዲያደርግ ወሰነ፤ ለፌዴሬሽኑም በስነ ምግባር ጥሰት ምክንያት እንደተነሳ አሳወቀ፤ ለቀጣይ ጨዋታዎችም ሌላ የቡድን መሪ ተተካ፤ ከ10 ቀን በኋላ ደግሞ ይህ ቪዲዮ ወጣ፤ መፈፀም የሌለበት ተግባር ነው የተፈፀመው፤ በዚህ ደረጃ ሴት ልጅ ላይ እጁን መሰንዘር አልነበረበትም፤ እኔም የሴት ልጅ አባት ነኝ፤ በተፈጠረው ሁላችንም አዝነናል"
🔷 ከድብደባ እስከ ኮከብ ተጫዋችነት
ሀዋሳ ከተማ ከአዲስ አበባ አቻው ጋር ሲጫወት ያልተጫወተችው ለምለም በቀጣዩ ጨዋታ ቡድኗ ሀዋሳ ከተማ ድሬደዋ ከተማን 2-0 ሲረታ የመጀመሪያ አሰላለፍ ውስጥ ገባች፤ መጫወት ብቻ ሳይሆን የእለቱ ኮከብ ተጫዋች ተብላ ተሸለመች፤ ቤተሰቦቿም ሆኑ ስፖርት አፍቃሪው ሰኞ ቪዲዮው እስከተለቀቀበት ጊዜ ድረስ የለምለምን ኮከብ ተጫዋችነት እንጂ መደብደቧን፥ አስር አስቸጋሪ ቀናትን ማሳለፏን አያውቅም ነበር፤ ቪዲዮው ሲለቀቅ ግን ቤተሰቧም ከህዝቡ እኩል ሰማ "ቤተሰቦቼ እንዲሰሙ አልፈለኩም ነበር፤ ክለቡ ጉዳዩን ስለያዘው በስክነት እንዲሄድ ነበር ፍላጎቴ፤ በሶሻል ሚዲያ ከተለቀቀ በኋላ ቤተሰቤ አወቀ፤ በተለይ እናቴ ተረበሸች፤ ለእናቴም ለወንድሞቼም በህግ መያዙን ነግሬ አረጋጋኋቸሁ፤ የክለቡ አመራሮችም ከኔ ጎን እንደሆኑና መብቴን እንደሚያስከብሩ አረጋግጠውልኛል" ትላለች
🔷 የቡድን መሪው ፀፀትና ይቅርታ
" በቀጣዩ ጨዋታ የጨዋታው ኮከብ ከሆነች በኋላ የፅሁፍ መልዕክት ላኩላት፤ 'የሰራሁት ነገር በጣም ፀፅቶኛል፤ እኔም የሴት ልጅ አባት ነኝ፤ አንቺ ላይ እንዲህ አደርጋለሁ ብዬ አንድም ቀን አስቤ አላውቅም፤ ላንቺ ያለኝን ቦታ አንቺም ታውቂያለሽ፤ ጥሩ ልጅ ነሽ፤ እኔንም በደንብ ታውቂኛለሽ፤ ይቅር በይኝ፥ ይቅርታ፤ የጨዋታው ኮከብ ስለተባልሽም እንኳን እግዚአብሔር ረዳሽ፤ በርቺ' አልኳት እሷም ይቅርታውን እንድተቀበለች መለሰችልኝ፤ ከ10 ቀናት በኋላ ቪዲዮው ወጣ፤ ከቤተሰቤ ጋርም ግጭት ውስጥ ገባን፤ ባለቤቴም ስሜታዊ ሆነች፤ የልጅ አባት ነኝ፤ የስምንት ወር ህፃን ልጅ አለን፤ ክለቡም ቀጥቶኝ ቤቴ ነው ያለሁት፤ ይህ ሁሉ ተደራርቦብኝ ዝም ብዬ ነበር፤ ታምሩ ላንተ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ቃለምልልስ የሰጠሁት፤ ቪዲዮው አሁን ለምን እንዲለቀቅ እንደተፈለገ አልገባኝም፤ እኔን ለማጥቃት ካልሆነ ችግሩን በይቅርታ ፈተነዋል፤ በድጋሚ ለምለምን፣ የክለቤን አባላትና ሀላፊዎችን እንዲሁም የኢትዮጵያ ህዝብን በሙሉ ይቅርታ እጠይቃለሁ፤ የቀን ጎዶሎ አጋጥሞኝ ነው ያንን ስህተት የሰራሁት፤ አሁንም የትኛውንም ቅጣት ለመቀበል ዝግጁ ነኝ
🔷 የክለቡ እርምጃና መግለጫዎች
ሀዋሳ ከተማ የቡድን መሪው አቶ ታረቀኝ ወንድሙን በጊዜያዊነት ከስራው አግዶታል፤ የቡድን መሪው ግን ደብዳቤ እንዳልደረሰውና የክለቡን የመጨረሻ ውሳኔ ቤቱ ሆኖ እየጠበቀ እንደሆነ ነግሮናል
የኢትዮጵያ የሴት እግርኳስ ተጫዋቾች ማህበር ድርጊቱን አውግዞ ቡድን መሪው ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድና በህግ እንዲጠየቅ መግለጫ አውጥቷል፤ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ደግሞ ሀዋሳ ከተማ ስለ ጉዳዩ አስቸኳይ ማብራሪያ እንዲሰጠው ጠይቋል
የማሊያ ሳይዝ የደም መዘዝ አስከትሏል፤ ለምለም 'ማሊያውን ጠረጴዛ ላይ ነው ያስቀመጥኩት ከዛ አንስቶ ወረወረብኝ' ትላለች፤ ቡድን መሪው ታረቀኝ ደግሞ 'ልበሰው ብላ ወረወረችብኝ' ይላል፤ ምንም ሆነ ምንም ግን መጨረሻው አካላዊ ጥቃት መሆን አልነበረበትም፤ ጥቃት ማድረስ የስሜት ውጤት ሊሆን አይገባውም!
★ ለዚህ ዘገባ የተባበሩንን በሙሉ ከልብ እናመሰግናለን፤ በሴት እግርኳስ ተጫዋቾች አካላዊና ፆታዊ ጥቃቶች ዙሪያ ብዙ ችግሮች ይሰማሉ፤ ማስረጃዎችን እየሰበሰብን እንቀጥላለን፤ መረጃም እንቀበላለን
በጋዜጣና ታምሩ ዓለሙ

Comments