Logo
FIDEL POST NEWS
ትናንት በለንደን የፍልስጤም እርምጃን ለመደገፍ በተደረገ ሰልፍ ላይ ፖሊስ ከ400 በላይ ሰዎችን ማሰሩ ተነገረ

የፍልስጤም እርምጃ ቡድን በጁላይ መጀመሪያ ላይ “አሸባሪ” ቡድን ነው ተብሎ ከታወጀና ከታገደ በኋላ፣ ይህንን በመቃወም እና ድጋፋቸውን ለመግለጽ ለተሰበሰቡ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ፖሊስ በለንደን ባደረገው ሰልፍ ከ400 በላይ የሚሆኑትን ማሰሩ ማዋሉ ትችትን አስከትሏል።

የህግ አስከባሪ አካላት ከመጀመሪያው አንስቶ በግልጽ እና በይፋ ለቡድኑ ድጋፍ የሚሰጥ ማንኛውም ሰው በቁጥጥር ስር እንደሚውል አስጠንቅቀው ነበር፤።

ምክንያታቸው ደግሞ ቡድኑ በ በአየር ኃይል ማዕከል ላይ አውዳሚ ድርጊቶችን በመፈጸሙ ታግዷል በሚል ነው።

በርካታ የእንግሊዝ መገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አደጋውን በመጋፈጥ ትናንት እኩለ ቀን ላይ በብሪታንያ ፓርላማ ፊት ለፊት ተሰብስበው “ዘር ማጥፋትን እቃወማለሁ። የፍልስጤምን እርምጃ እደግፋለሁ” የሚል መፈክር የያዙ በራሪ ወረቀቶችን ይዘው ነበር።
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.