Logo
SeledaPost
#wollouniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል።

የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ነባር የቅድመ ምረቃ እና የድኅረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም የመግቢያ ጊዜ መስከረም 08 እና 09/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት በየምትማሩበት ግቢ (ደሴ ግቢ፣ ኮምቦልቻ ግቢ እና ልዕለ ህክምና ግቢ) ሪፖርት ማድረግ እንዳለባችሁ ተገልጿል።

በ2018 ዓ.ም አዲስ ለምትመደቡ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ተምራችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ጥሪ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።

Seledadotio
Seledadotio
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.