የባህል ጥበባትና ስፖርት ሚዲያ ፎረም ምስረታ እየተከናወነ ነው
#ethiopia | የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የተደራጀ መረጃ ለማቅረብና ለሀገራዊ ጥቅም በሚውሉ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመሥራት ያለመ የሚዲያ ፎረም ምስረታ በቢሾፍቱ ከተማ እያከናወነ ይገኛል።
የባህል፣ ጥበባትና ስፖርት ሚኒስትር ክብርት ሸዊት ሻንካ በሚዲያ ፎረም ምስረታ ማስጀመሪያ መድረክ ላይ እንደገለጹት፣ የሚዲያ ፎረሙ የተቋቋመበት ዋና ዓላማ ሚኒስቴሩ በባህል ጥበባትና በስፖርት ዘርፍ የሚያከናውናቸውን ተግባራት ለህዝብ ተደራሽ በሆነ መንገድ ለማድረስ መሆኑን ገልጸዋል።
አክለውም፣ ሚኒስቴሩ በስፖርት፣ በኪነጥበብ እና በባህላዊ እሴቶች ላይ የሚሰሩ ስራዎች ለህዝብ የሚደርሱት በበመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት በመሆኑ፣ ፎረሙ ለመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች የተደራጀና ትክክለኛ መረጃ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል።
ይህ ደግሞ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያ ስነምግባር ላይ ተመስርተው ለህዝብ መረጃ እንዲያደርሱና ሀገራዊ ጥቅሞችን በሚያጎሉ ጉዳዮች ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ያስችላቸዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የብዝሃ ባህል፣ ማንነትና ቋንቋ ያላት ሀገር መሆኗን ገልጸው፣ የህዝቦችን የጋራ አብሮነትና አንድነት በሚያጎሉ፣ እንዲሁም ድንቅ የሆኑ ባህላዊ እሴቶችን ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ የጋዜጠኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ሚኒስቴሯ አብራርተዋል።
ሚኒስቴሩም ከወረዳ እስከ ብሄራዊ ደረጃ ባሉ የኪነጥበብ ውድድሮች ተሰጥኦ ያላቸውን ወጣቶች በማውጣትና በማበረታታት የሀገር ገፅታ ግንባታ ላይ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

1 year ago