Logo
SeledaPost
የእስራኤል ድንገተኛ ጥቃት‼️

የየመን የሐውቲዎች መሪ አላ ሐውቲ ትናንት ምሽት 10 ከፍተኛ ባለሥልጣኖችን ሰብስቦ ንግግር እያደረገ በሚገኝበት ሰዓት የእራኤል አየር ኃይል በምሽግ ደርማሽ እና መሬት ሰርጓጅ ቦንብ ከባድ ጥቃት ሰንዝሯል።

የእስራኤል አየር ኃይል 2 ሺህ ማይል አይር ላይ ነዳጅ እየሞላ ሐውቲው መሪ አላ ሐውቲን ንግግር እያደረገና ባለሥልጣኖችን ስብሰባ እንደተቀመጡ ነው ጥቃት የተፈፀመው።

የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስቴር ባለሥልጣኖች በቀጥታ የሐውቲዎችን ስብሰባ ቀደም ብሎ ሞሳድ በተከለው ካሜራ ስብሰባ ያዩ ነበር ከዚያም ጠቅላዩ የአየር ኃይሉ በቀጥታ ወደ የመን እየበረረ መድረሱን ይመለኩቱ እንደነበር ተሰምቷል።

አየር ኃይሉ ከላይ ልክ እንደ ዝናብ በለቀቀው ምሽግ አፍራሽና መሬት ደርማሽ ቦንብ በሐውውቲዎች ላይ ሲለቅ ጠቅላይ ሚ/ር ቤናሚር ናታናሁን ይመለከቱ ነበር ተብሏል ::

በጥቃቱ ሁሉም የሀውቲ መሪዎች እንደተገደሉ በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች እየተገለፀ ቢሆንም ከእስራኤል ማረጋገጫ አልተሰጠም።

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ጥቃቱ የሀውቲ መሪዎችን ያነጣጠረ መሆኑን ጠቁመው የሀውቲ መሪዎች ስለመገደላቸው መረጃ እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል።

ሀውቲ በበኩሉ መሪዎቼ አልተገደሉም እስራኤል እንደተለመደው በንፁሃን ላይ ነው ጉዳት ያደረሰችው ሲል ማስተባበያ ሰጥቷል።

Seledadotio
Seledadotio
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.