Logo
Getu Temesgen
ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ጌቱ ሥራዎቹን ከአንጋፋ ፀሐፍት ጋር በማጣመር "መባያ " The Golden Mean በሚል ያስመርቃል።

#ethiopia | ቅዳሜ ነሐሴ 24 ቀን2017 ዓ.ም ከረፋዱ 3:30 ሰዓት ጀምሮ በብሔራዊ ቤተመዛግብትና ቤተመጻህፍት /ወመዘክር / ሕሩይ አዳራሽ ጥሪ የተደረገላቸው አርቲስቶችና ታዋቂ ግለሰቦች ፣የኪነጥበብና የማርኬቲንግ ባለሙያዎች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት ያስመርቃል።

መባያ The Golden Mean መጽሐፍ በይዘትና ቅርፁ የተለየ ሲሆን፣ኪነጥበባዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ፍልስፍናዊና ቢዝነስ ነክ ርዕሰ ጉዳዮች የተካተቱበት ነው።

በዓይነታቸው ዝንቅ የሆኑ በአቀራረባቸውም ደ የተመጠኑ ለመባያነት መብቃት የቻሉ ሐሳብና ጉዳዮች በአንድ የተሰነቁበት መጽሐፍ በማሰናዳት ለተደራሲያን አበርክቷል ።

ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ጌቱ ከዛሬ 15 አመታት በፊት የሕትመት ሚዲያን በመቀላቀል በኔሽን፣አውራምባ ታይምስ ፣በቁም ነገርና ቃልኪዳን መፅሔት ላይ የተለያዩ መጣጥፎችን በመፃፍ ይታወቃል።

በተለያዩ የኪነጥበብ መድረኮች ከሚያቀርባቸው ስራዎች በተጨማሪ በ2002 አ/ም "ሰይጣን አስቶኘ "በሚል የመጀመሪያውን የግጥም መድብል መጽሐፍ ለአንባቢያን አብርክቷል።

በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት 98.1 በፕሮግራም ክፍል ጋዜጠኛነት ለ5 አመታት ካገለገለ በኋላ፣ሙሌ ሚክስ መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን በሚል ባቋቋመው የራሱ ድርጅት አማካይነት የብራንዲንግና ፕሮቶኮል የሬድዮ ፕሮግራም ፎርማት " አቤት" የተሰኘ የሬዲዮ ሾ በማዘጋጀት ከ120 በላይ ድርጅትና ተቋማትን መለያ ብራንድና ፕሮፋይል (Branding & profile )በመሥራት አስተዋውቋል። ከዚህ በተጨማሪም Abet Podcast ሚል ፖድካስት ገፅ በማቋቋም እየሠራም ይገኛል።

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.