የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወደ ጅምላ ብድር አቅርቦት ለመሸጋገር ማቀዱ ተገለጸ !!
#ethiopia | የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አሁን የሚከተለውን የችርቻሮ ብድር (ለግለሰቦችና ድርጅቶች ቀጥተኛ ብድር) አሰራር በመቀየር፣ ወደ ጅምላ ብድር አቅርቦት ለመሸጋገር ማቀዱ ተገለጸ።
ይህ አዲስ የቢዝነስ ሞዴል በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ በዴሊዮት በተባለ ዓለም አቀፍ አማካሪ ድርጅት የተጠና ሲሆን፣ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።
በአዲሱ አሰራር መሰረት፣ ባንኩ ብድርን በቀጥታ ለግለሰቦች እና ለነጠላ ድርጅቶች ከማቅረብ ይልቅ፣ የረጅም እና የመካከለኛ ጊዜ ብድሮችን ለንግድ ባንኮችና ለማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ያቀርባል። እነዚህ ተቋማት ደግሞ በልማት ባንክ መስፈርት መሰረት በተመረጡ ዘርፎች ለሚንቀሳቀሱ አልሚዎች ብድሩን ያበድራሉ።
ሪፖርተር እንደዘገበዉ ይህ የቢዝነስ ሞዴል የልማት ባንክን የመንግስት ፖሊሲ ባንክነት ከማጠናከሩም በላይ፣ የመንግስት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የልማት ዘርፎች ላይ ሀብት በማሰባሰብ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።
በተያያዘ ዜና፣ ባንኩ በ2017 የሂሳብ ዓመት ከብድር መልስ 24 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ ከፍተኛ ብልጫ ማሳየቱ ተዘግቧል።
#kgethiopia

1 year ago