የሎጎ ነገር
#ethiopia | በአሜሪካ ከ600 በላይ ሬስቶራንቶች ያሉት ክራከር ባሬል ሎጎ የመቀየር እቅዱን ሰረዘ።
ፕሬዝደንት ትራምፕን ጨምሮ የበርካታ ደንበኞች ወቀሳን ያተረፈው የክራከር ባሬል አዲስ ሎጎ በተዋወቀ በጥቂት ቀናት ከስራ ውጭ ሆኗል።
ኩባንያው ምሽት ላይ በኤክስ ገፁ አዲሱን ሎጎ በደንበኞች ፍላጎት እንደተወ አስታውቋል።
ፕሬዝደንት ትራምፕም ውሳኔውን አሞግሰዋል።
ኩባንያው ለሪብራንዲንግ 700 ሚሊየን ዶላር መድቦ ሲሰራ ነበር።
ወደ 50 አመት የሚጠጋው የሬስቶራንቱ ሎጎ የእንጨት በርሜል የተደገፈ ሰውን ከፅሁፍ በተጨማሪ ያካተተ ነበር።
ሆኖም ስራ ላይ ሊውል የነበረው አዲስ ሎጎ የኩባንያውን ፅሁፍ ብቻ የያዘ ቀለል ያለ ምልክት ነበር።
የተለያዩ ዘገባዎች እንደጠቀሱት አተርፍ ተብሎ የተጀመረ የሎጎ ቅያሬ ያስከተለው ተቃውሞ ኩባንያው በገበያ ዋጋው እንዲቀንስ እንዲሁም የገንዘብ ኪሳራ ጭምር እንዲያስተናግድ እንዳደረገው ገልፀዋል።
#kgethiopia

1 year ago