የቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዜና ዕረፍት
ነሐሴ 21 ቀን 1967 ዓ.ም
መስከረም 2 ቀን 1967 ዓ.ም ወታደራዊው የደርግ ሥርዓት ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴን ከስልጣናቸው አወረደ ፤የንጉሱ መውረድም በብሔራዊ ራዲዮንና ቴሌቭዥን አማካይነት ዜናው ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ ሆነ ።
ይህ ከሆነ ከ 11 ወራት በሁዋላ በነሀሴ 21 ቀን 1967ዓ.ም የኢትዮጵያ ራዲዮ ለአርባ አመታት ኢትዮጵያን በንጉሰ ነገሥትነት የመሩት ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ማረፋቸውን ይፋ አደረገ፤የጃንሆይ ዜና ዕረፍት ብዙዎችን አስደነገጠ ፤በወቅቱ የንጉሱ አሟሟት ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን የአለምን ማህበረሰብ ጭምር አነጋገረ ። ወታደራዊው መንግስት ባወጣው መግለጫ ንጉሰ ነገስቱ ተፈጥሮዋዊ ሞት ነው የሞቱት ቢልም ንጉሰ ነገስቱ መገደላቸውን የሚያመለክቱ መረጃዎች እየጎሉ መጡ ፤በወቅቱ የጤናቸውን ሁኔታ እስር ቤት ድረስ በእየለቱ እየሄዱ ይከታተሉ የነበሩት እውቁ ኢትዮጵያዊው የህክምና ሰው ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ንጉሱ ፍጹም ጤነኛ እንደነበሩና ለሞት የሚያደርስ የጤና እክል አልነበራቸውም ሲሉ ገልጸው ነበር ።
ጃንሆይ በእስር ላይ በነበሩበት ወራት በስደት የነበረው ልጃቸው ልዑል አስፋ ወሰን ኃይለስላሴ "አባቴ እጅግ ጤነኛ ነበር ፤ለሞት የሚያደርሰው ምክንያት የለም ፤አባቴ ተገድሏል ይህም በአለም አቀፋ ቀይ መስቀልና በገለልተኛ ዶክተሮች የአሟሟቱ ሁኔታ ይጣራልኝ ሲል መንግስትን ጠይቋል ፤ ወታደራዊው መንግስት ግን ይህንን ከንጉሳውያን ቤተሰቦች የተነሳውን ጥያቄ አልተቀበለውም አስከሬናቸውንም ሊሰጥ ፈቃደኛ አልነበረም ።
*************)*************************
የጃንሆይ አስከሬን የተገኛው ከ 1983 ዓ.ም የመንግስት ለውጥን ተከትሎ ከተካሄደው የአመታት ፍለጋ በሁዋላ በምኒሊክ ቤተመንግስት በደርግ ፅ/ቤት ህንጻ ስር ነው ።
**************************************************
የቀብር ሥነስርዓታቸውም እጅግ ደማቅ በሆነ ሥነስርዓት በቅድስ ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።
Via: እዮብ ዘለቀ

1 year ago