ዝክረ ~ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ
የአንጋፋው የአደባባይ ምሁር የመታሰቢያ ፕሮግራም በድምቀት ተካሄደ
ይትባረክ ዋለልኝ
#ethiopia | የአንጋፋው ምሁር ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በህይወት የተለየበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የዶ/ር ደረጄጀ ዘለቀ የቅርብ ጓደኞች ያዘጋጁት "ዝክረ "ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ " የመታሰቢያ ፕሮግራም ትላንት ነሐሴ 17 ቀን 2017 ዓ.ም በአማራጭ የማረፊያ ስፍራ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተካሂዷል።
አዳራሹ በታዳሚያን ሞልቶ የነበረው "ዝክረ "ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ " የመታሰቢያ ፕሮግራም የህሊና ፀሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን የዶ/ር ደረጀ ዘለቀን የተለያዩ የህይወት ገፅታዎች የሚያሳዬ ፕሮግራሞች በስነፁሑፍና በኳይር የሙዚቃዎች በታጀበዉ ቀርበዋል::
ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በአደባባይ ምሁርነቱ በማሕበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮችን በማንሳትና የትችት ዓይኑ በስሜት ያልተዳከመ ፣ በብሶትና በእውነት ላይ የተመሠረተ ማንነቱን ለራሱን ሳይሆን ለሀገርና ለሕዝብ ጥቅምና ክብር ያበረከተውን አስተዋጸኦ በተመለከተ የፊልም ባለሙያዉ ዳዊት ተስፋዬ ፣ ሠዓሊና ገጣሚ ቸርነት ወ/ገብርኤል ፣ ሰለሞን ሹምዬ ዲስኩር አቅርበዋል::
እንዲሁም ሠዓሊና ገጣሚ ቸርነት ወ/ገብርኤል አሪፍ ግጥም
ያቀረበ ሲሆን ሳውንድ የኳይር ቡድን ደግሞ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በህይወት በነበረበት ጊዜ የሚወዳቸውን የዘማሪ ሐና ተክሌን መዝሙሮች እና የድምፃዊ ጥላሁን ገሰሰ ሙዚቃዎች አቅርበዋል::
በዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ተማሪው ና ተመካሪው የነበረውና አሁን በቴላቪቭ ዩንቨርስቲ የዶክትሬት ተማሪ የሆነው አቶ ደጀን አማን ብዙዎቻችን የማናውቀውን የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የአካዲያሚያዊ ስብእናው በዝርዝር ያሳየ ግሩም የጥናት ፁሑፍ አቅርቦአል::
አቶ ደጀን አማን በዚህ ፅሑፋቸው ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በሕግ ሙያው መስክ በመምህርነቱ በጥናትና ምርምሩ ዘርፍ ስላበረከትው አስተዋፅኦ በሐገር ውስጥና በዓለማቀፍ ጆርናሎች ላይ ስላሳተማቸው የጥናት ፁሑፎች እንዲሁም ታላላቅ የውጭ ሐገር የህግ ምሁራን ስለ ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የሰጡትን ምስክርነት አካቶ ምርጥ የጥናት ፁሑፍ አቅርቦአል::
በዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ የዶ/ር ደረጀ ዘለቀን የህይወት ታሪክ እና በማሕበራዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ በጥናትና ምርምሩ ዘርፍ የሰራቸውን ተግባራት በዝርዝር የሚያሳይ እንዲሁም በርካታ ታላላቅ ሰዎች ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ የሰጡትን ምስክርነት እና አስተያየት የያዘ መፅሔት ታትሞ ለታዳሚው ተሰጥቷል::
በተጨማሪም የዶ/ር ደረጀ ዘለቀን ብዙ መልኮች የሚያሳይ ቤተሰቦቹ: አብሮ አደግ ጓደኞቹ የቅርብ ጓደኞቹእና የስራ ባልደረቦቹ የተሳተፉበት ዶክመንተሪ ፊልም በዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ ለዕይታ በቅቷል::
እንዲሁም ዶ/ር ደረጀ ዘለቀ በህይወት በነበረበት ወቅት እናትዋን በህይወት ላጣችው ልጅ በድምፁ ቀርፆ የላከላትን እጅግ አስገራሚ የማፅናኛ መልእክት ሰለሞን ሹምዬ ከምስል ጋር አዋህዶ በትላንቱ ፕሮግራም ላይ አቅርቦልናል::
በተጨማሪም የፕሮግራሙ ድምቀት የነበረው የደረጀ አድናቂ በሆነው በሰዓሊ ግርማዊ ዓለማየሁ የተሰራው የዶ/ር ደረጀ ዘለቀ ፓርትሬት የጥበብ ስራ ነው:: ይህፓርትሬት በኮላዥ የሥዕል ስራ የተሰራ ሲሆን የደረጅ መለያዎች ከሆኑ ሃሳቦች ጋር ተዋህዶ የተሰራ ምርጥ የጥበብ ስራ ነው::
ትላንት የተካሄደው "ዝክረ "ዶ/ር ደረጄ ዘለቀ " የመታሰቢያ ፕሮግራም የዶ/ር ደረጀ ዘለቀን ብዙ የህይወት መልኮች ያሳየ ብቻ ሳይሆን ዶ/ር ደረጀ ዘለቀን በስነጽሑፍ: በፊልም: በሥዕል እና በሙዚቃ የተገለፀበት ፕሮግራም ነበር::
በመጨረሻም በዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ በቤተ ጉራጌ ተገንብቶ በዶ/ር ደረጄ ዘለቀ ዘለቀ ስም ለተሰየመው የመታሰቢያ ቤተመጽሀፍት የመጽሐፍ ልገሳ ተከናውኗል::
በዚህ የመታሰቢያ ፕሮግራም ላይ የዶ/ር ደረጄ ቤተሰቦቹ የአ.አ.ዩ መምህራንና የስራ ባልደረቦቹ የፈረንሳይ ለጋሲዬን አብሮ እደግ የሰፈር ጓደኞቹ በርካታ አድናቂዋቹ ተገኝተዋል::

1 year ago