Logo
FIDEL POST NEWS
ትራምፕ የአሜሪካ የመከላከያ ኢንተለጀንስ ኤጀንሲ ኃላፊን ከስልጣናቸው አነሱ

አሶሺየትድ ፕሬስ ከሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት ማጣራት ተከትሎ፣ የመከላከያ ኢንተለጀንስ ኤጀንሲ ኃላፊ የሆኑት ሌተናል ጀነራል ጄፍሪ ክሩዝ ትናንት ከስራ መባረራቸውን ዘግቧል።

ይሁን እንጂ የክሩዝ መባረር ምክንያት አልታወቀም።በዚያው ቀን የመባረር ዘመቻው በክሩዝ እንዳላበቃም ታውቋል።

ስሙ እንዳይገለጽ የፈለገ አንድ የአሜሪካ ባለስልጣን እንደተናገሩት፣ የባህር ኃይል ሪዘርቭ እና የባህር ኃይል ልዩ ጦርነት አዛዥ ኃላፊም ከስልጣናቸው ተነስተዋል።

ሦስቱም ባለስልጣናት የመባረራቸው ምክንያት እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ክሩዝ ከስልጣናቸው የተነሱት በቅርቡ ለሚዲያ የወጣው የተቋማቸው የመጀመሪያ ሪፖርት ነው።

ሪፖርቱ እንደዘገበው በአሜሪካ አየር ኃይል በሶስት የኢራን የኑክሌር ተቋማት ላይ ሰኔ 15 የተደረገው የአየር ጥቃት የቴህራንን ፕሮግራም የገታው ለጥቂት ወራት ብቻ ሲሆን፣ ትራምፕ ግን ሙሉ በሙሉ እንዲወድም ይፈልጉ ነበር።

ትራምፕ በሪፖርቱ መውጣት በጣም ተናደዋል። ዋይት ሃውስ ሪፖርቱን ሙሉ በሙሉ ሀሰተኛ ዜና ብሎታል። እንዲሁም የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዘገባውን ያወጡትን የሲኤንኤን እና የኒውዮርክ ታይምስን ጨምሮ ሌሎች የመገናኛ ብዙሃንን፣ ሀሰተኛ ዜና በማሰራጨት ክፉኛ ተችተዋል።

የአሜሪካ ሴኔት ኢንተለጀንስ ኮሚቴ ምክትል ሊቀመንበር ሴናተር ማርክ ዋርነር፣ ሌላ ከፍተኛ የብሄራዊ ደህንነት ባለስልጣን ማባረር፣ የትራምፕ አስተዳደር የስለላ መረጃን እንደ ብሄራዊ ደህንነት መሳሪያ ሳይሆን ለታማኝነት ማረጋገጫ መጠቀሙን እንደሚያሳይ ተናግረዋል።
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.