አንድ ኮሎምቢያዊ ገበሬ በእርሻው ላይ ሲሰራ 600 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ተቀብሮ አገኘ
ገንዘቡ የሟቹ አደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪ የነበረው ፓብሎ ኤስኮባር ሊሆን ይችላል ተብሏል።
የኮሎምቢያ ሚዲያን ዋቢ በማድረግ ማርካ የተባለ የየቀን ጋዜጣ ድረ-ገፅ ከቀናቶች በፊት እንደዘገበው አንቲዮኪያ በተባለ ቦታ የተገኘው ገንዘብ ማንነቱ እንዳይገለጽ የፈለገው ገበሬ፣ የእርሻ ቦታውን ሲያሰፋ ከመሬት አንድ ሜትር በላይ ጥልቀት ላይ የተቀበሩ በርካታ የዛገ የብረት በርሜሎች አገኝቷል።
በርሜሎቹ በመቶዎች የሚቆጠሩ በጥቅል የታሰሩ በዋነኝነት የአሜሪካ ዶላር የባንክ ኖቶች የያዙ ሲሆን፣ እነዚህም በጥሩ ሁኔታ ተጠብቀው ተገኝተዋል።
የኮሎምቢያ ባለስልጣናት ግኝቱ እንደተነገረ ወዲያውኑ ገብተው የገንዘቡን ትክክለኛ ምንጭ ለመወሰን ምርመራ ጀመሩ። የመጀመሪያው ግምት እንደሚያሳየው፣ ገንዘቡ የ1980ዎቹ እና 1990ዎቹ የሜደሊን ካርቴል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በቀላሉ ህጋዊ ማድረግ ወይም ማንቀሳቀስ ስላልተቻለ ለማከማቸት ይጠቀሙባቸው ከነበሩት መደበቂያዎች አንዱ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
ይህ የፓብሎ ኤስኮባር ገንዘብ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘበት አይደለም። ዝናው በከፍተኛ ደረጃ በነበረበት ጊዜ፣ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪው ራሱ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ በእርሻ ቦታዎችና በጫካ ውስጥ ደብቆ ነበር። ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ በ1993 ከሞተ በኋላ ተረስተው ነበር።
ይህ ግኝት ስለ አፈ ታሪካዊው "ፓብሎ ኤስኮባር ሀብቶች" ፍላጎትን እንደገና አነሳስቷል፣ ነገር ግን የገበሬውን እና የቤተሰቡን ደህንነት በተመለከተም ስጋትን ፈጥሯል።
የጉስታቮ ፔድሮ መንግስት አሁን ገንዘቡን መውረስ ወይም ለገበሬው ሽልማት መስጠት እንዳለበት እያጤነ ነው።
Seledadotio

1 year ago