በኢትዮጵያ ከሁለት የማይበልጡ የግመል ወተት ላኪዎች ብቻ በመኖራቸው ምርቱ ወደ ተወሰኑ የዓለም ሀገራት እየቀረበ ይገኛል ተባለ
ኢትዮጵያ በ2017 በጀት ዓመት ለውጪ ገበያ ካቀረበችዉ 7መቶ 42 ቶን የግመል ወተት 60 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘቷን የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዮት አስታውቋል።በኢንስቲትዮቱ የማህበራዊ ኢኮኖሚክስና እሴት ሰንሰለት አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ሳህሉ ሙሉ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የግመል ወተትን ወደ ተወሰኑ ሀገራት ብቻ እየላከች ትገኛለች።
በአሁኑ ወቅት በባህላዊ መንገድ ይልቅ ምርቱ ተቀነባብሮ ወደ ውጪ ገበያ የሚላክበት ሁኔታ መኖሩን የገለፁት ዶክተር ሳህሉ በምስራቁ የኢትዮጵያ ክፍል ምርቱ ለመዳረሻ ገበያ ይቀርባል።ኢትዮጵያ በዋናነት ምርቱን ወደ ሶማሊያ፣ኳታር እና ሰሜን አሜሪካ ለሽያጭ እንደምታቀርብ የተነገረ ሲሆን አሁን ላይ ከሁለት በማይበልጡ የግመል ወተት ላኪዎች ምርቱ ለሽያጭ እየቀረበ ይገኛል።
የግመል ወተት እንደ ሶማሌ እና አፋር ካሉ የኢትዮጵያ ክፍሎች ወደ መዳረሻ ገበያዎች ይላካል፡፡ ምርቱን ለሽያጭ የሚያቀርቡ በርካታ ላኪዎች ባለመኖራቸው በአብዛኛው ለሀገር ውስጥ ገበያ ለማዋል ተገደዋል፡፡ በቀጣይ ከዘርፋ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ምርቱ በተገቢው መንገድ እሴት ተጨምሮበት ለውጪ ገበያ እንዲቀርብ የሚያስችሉ የድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ ተብሏል።
Seledadotio

1 year ago