Logo
FIDEL POST NEWS
ፑቲን በአደባባይ ላይ ብዙም የማይጠቀሙበትን እንግሊዘኛ ቋንቋን ትናንት በትንሽ ቃላት ሲናገሩ ተሰምተዋል

ቭላድሚር ፑቲን ከትራምፕ ጋር ትናንት ከነበረው ስብሰባው በኋላ በተረጋጋ መንፈስ ውስጥ የነበሩ ቢሆንም፣ ጋዜጠኞች ለፕሬዚዳንቶቹ የሰጧቸውን ጥያቄዎች ሳይመልሱ የጋዜጣዊ መግለጫውን አጠናቀዋል።

በመቀጠልም ፑቲን ቀጣዩ ስብሰባ የሩሲያ ዋና ከተማ በሆነችው ሞስኮ እንዲካሄድ ሐሳብ አቀረቡ። ይህንንም በአደባባይ ብዙም በማይጠቀሙበት በእንግሊዘኛ ቋንቋ ተናገሩ።

“Next time in Moscow,ቀጣዩ ስብሰባ ሞስኮ ውስጥ ይሁን” ሲሉም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል።

ትራምፕ ሐሳቡን ለመመርመር ፈቃደኛ መሆናቸውን ቢናገሩም፣ ሐሳቡን በአዎንታዊም ይሁን በአሉታዊ መልኩ ስለመመልከታቸው ምንም ፍንጭ አልሰጡም።
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.