Logo
Getu Temesgen
ዛሬ ለመልዕክት መለዋወጫነት የምንጠቀመው ቴሌግራም በይፋ ለህዝብ የተገለጠበት ዕለት ነው
#ethiopia | በፓቨል ዱሮቭ እና ወንድሙ የበለፀገው ቴሌግራም በዚህች ቀን ከ12 ዓመት በፊት ለIOS ተጠቃሚዎች ይፋ ከሆነ በኋላ ነበር ከወራት በኋላ በጥቅምት ወር ለአንድሮይድ ተጠቃሚዎች ይፋ የሆነው።

በብዙዎች የተወደደው ቴሌግራም በጊዜ ሂደት ተጠቃሚዎቹን የሚያስደስቱ ለውጦችንም ሲያደርግ ሰንብቷል።

ምን ለውጦች ነበሩ ?

በመስከረም 2014 ቴሌግራም እስከ 1.5 ጂቢ መጠን ያላቸውን ፋይሎች እንዲላኩ ማድረግ ያስቻለ ሲሆን በዚሁ ወር ነበር ለኮምፒዩተር የሚሆነውን መተግበሪያውንም ይፋ ያደረገው።

በመጋቢት ወር 2014 የድምፅ መልዕክትን ያስተዋወቀው ቴሌግራም በተጨማሪ እንደ ጀርመንኛ እና ጣልያንኛ ያሉ ቋንቋዎችንም ወደ መተግበሪያው ጨምሯል።

በጥቅምት ወር 2014 ቴሌግራም አሁን ላይ የምንጠቀማቸውን 'User names' ያስጀመረበት ወቅት ሲሆን ይህም ለሰዎች ስልክ ቁጥራችንን ሳንሰጥ በቀላሉ እንድንገናኝ አስችሏል።

በሚያዝያ 2015 ደግሞ ደህንነቱን ለማሻሻል የ'Two step Verification' ሲያስተዋውቅ በዛው አመት 2015 ላይ ቦቶች ይፋ ሆኑ።

በመስከረም 2015 ደግሞ ቴሌግራም ሰዎች ቻናሎችን ከፍተው ለሰዎች በአንድ ጊዜ መረጃ እንዲሰጡ ያስቻለ ለውጥን አደረገ።

በግንቦት 2017 የቪዲዮ መልዕክትን መላላክን የፈቀደው ቴሌግራም በ2018 200 ሚሊየን ንቁ ወርሃዊ ተጠቃሚዎችንም ማፍራት ቻለ።

በ 2019 የኮሮና ቫይረስን መከሰት ተከትሎ የጤና ተቋማት ቻናሎችን መክፈት ሲጀምሩ ቴሌግራም ትክክለኛ መረጃ ከትክክለኛው ቦታ መሆኑን ለማረጋገጥ ለቻናሎቹ ዕውቅና መስጠትን ጀምሮ ነበር።

በ2020 400 ሚሊየን ተጠቃሚዎችን የደረሰው ቴሌግራም በዛው አመት በ2020 ሰባተኛ አመቱን በማስመልከት የቪዲዮ የስልክ ልውውጥን አስጀመረ።

በ2022 700 ሚሊየን ተጠቃሚዎችን ያፈራው ቴሌግራም በአይነቱ ልዩ የሆነውን የቴሌግራም ፕሪሚየም አገልግሎቱን አስጀመረ።

በመጋቢት ወር 2024 የቴሌግራም ቻናል ባለቤቶች በቻናላቸው ማስታወቂያ ማስተላለፍ የሚችሉበትን እና 50 በመቶ ገቢ መጋራት የሚችሉበትን የማስታወቂያ ስርዓት ይፋ አደረገ።

በአሁኑ ጊዜ ከ1 ቢሊየን በላይ ወርሃዊ ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት ቴሌግራም ሰዎች የቻናል ባለቤቶችን መሸለም የሚችሉበትን መንገድ በመፍጠር ፈጠራን እንዲደግፉ አድርጓል።

ቴሌግራም የራሱን ብሎክቼይን በመጀመርም የክሪፕቶ ከረንሲ እንዲያድግ የራሱን ሚና ሲወጣ የራሱን የቴሌግራም የክሪፕቶ ማስቀመጫ ዋሌትም በመፍጠር የክሪፕቶከረንሲ ዝውውሮችን ቀላል አድርጓል።

የተጠቃሚዎችን መረጃ አሳልፎ ከመስጠት አንፃር ፈቃደኝነቱን ባለማሳየቱ በሃገራት ፓቨል ዱሮቭ በተደጋጋሚ የሚከሰስ ሲሆን ተጠቃሚዎች ግን ይህንን የዱሮቭን አቋም በበጎነት ይመለከቱታል።

እነሆ ዛሬ ለመልዕክት መለዋወጫነት የምንጠቀምበት ቴሌግራም ይፋ ከሆነ ዛሬ 12 ዓመት ሞልቶታል።
#tm #telegram

1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.