የኤሌክትሪክ ሽያጭ ዋጋ ማስተካከያ ለቀጣይ 3 አመታት ይቀጥላል ተባለ
የኤሌክትሪክ ሽያጭ ዋጋ ማስተካከያ በእቅዱ መሰረት ለቀጣይ ሶስት አመታት እንደሚቀጥል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አስታዉቋል ፡፡
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደተናገሩት ተቋሙ ከአስር ዓመታት በላይ የታሪፍ ማሻሽያ ሳያደርግ በከፍተኛ ብድር የኃይል ተደራሽነትን የሚያሳድጉ የኃይል መሰረተ ልማት ስራዎችን ሲያከናውን ቆይቷል ብለዋል ፡፡
ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ይህንን ያሉት ነሐሴ 1/2017 ዓ.ም በተቋሙ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ላይ ነው።
በዚህም ተቋሙ የህልውና አደጋ ውስጥ በመግባቱ በመንግሥት በኩል የሀገር ውስጥ ዕዳ ጫና ስረዛ እንደተደረገለት አስታውሰዋል፡፡
በተጨማሪም ተቋሙ የፋይናንስ ቁመናውን ለማሻሻል፣ የኃይል ሽፋንን ለማሳደግ እና የኦፕሬሽንና የፕሮጀክት ወጪዎችን ለመሸፈን በጥናት ላይ ተመስርቶ የታሪፍ ማሻሻያ መተግበሩን ዋና ስራ አስፈፃሚዉ ተናግረዋል፡፡
የታሪፍ ማሻሽያው በየሩብ ዓመቱ ተከፋፍሎ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን ኢንጂነር አሸብር አንስተዋል ፡፡
የታሪፍ ማሻሻያው ከጎረቤት ሀገራት አንፃር ሲታይ አሁንም እጅግ ዝቅተኛና የተቋሙን ወጪ መሸፈን የማይችል መሆኑን ገልፀዋል፡፡
Ethio Fm

1 year ago